• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

በህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ ባለሥልጣናት “ተዘርፈናል” – የሳውዲ ባለሃብቶች!

November 26, 2015 12:16 am by Editor Leave a Comment

የሳውዲ ባለሃብቶች እነሱ “የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት” ያሏቸው አንዳንድ የህወሃት/ኢህአዴግ ሹሞች መሬታቸውንና መሣሪያዎቻቸውን የዘረፏቸው መሆኑን በማስታወቅ ክስ አሰሙ፡፡

ህዳር 15 ቀን 2008 ዓም በወጣው ታዋቂው የሳውዲ ጋዜጣ አረብ ኒውስ በኢትዮጵያ ባለው አገዛዝ አንዳንድ ባለሥልጣኖች መሬታቸውን እየተቀሙ በደልና ዘረፋ እየተፈጸመባቸው መሆኑን በአፍሪካ የሳውዲ ባለሃብቶችን ቡድን የሚመሩት ሞሀመድ አልሸህሪ የተባሉ ባለሃብት ለአረብ ኒውስ አስታውቀዋል። እኒሁ ባለሃብቶችን መርተው ወደ አፍሪካና ወደ ኢትዮጵያ ከአመታት በፊት ወደ የዘለቁት ባለሃብት አንዳንድ የአገዛዙ ኃላፊዎች በኢንቨስትመንት ፈቃድ ወደ ሀገሪቱ ያስገቡትን ንብረቶች ለመውረስ በእርሳቸውና በጓደኞቻቸው ላይ የወንጀል ክስ እንደተመሰረተባቸው ማስታወቃቸውን አረብ ኒውስ ዘግቧል። ቅሬታ አቅራቢው ሳውዲ ባለሃብት ሞሃመድ አልሸህሪ ለአረብ ኒውስ ጋዜጣ እንዳስታወቁት ሙስናው የከፋ እየሆነ መምጣቱን በመጠቆም ሳውዲ ባለሃብቶች በማመሳሰል (forgery) ወንጀል ሳይቀር ተወንጅለው ለስራ ያስገቧቸውን እቃዎች መመለስ እንዳልቻሉ አስረድተዋል።

ከስድስት አመት በፊት ጀምሮ በእርሻ ስራ ላይ ተሰማርተው የነበሩ ሳውዲ ባለሃብቶች በአገዛዙ የተገባላቸው ቃል በተግባር ባለመፈጸሙ 50% ያህሉ ባለሃብቶች ከኢትዮጵያ ለቀው መውጣታቸውን እኒሁ ቅሬታ አቅራቢ ሳውዲ ባለሃብት ተናግረዋል። በደረሰባቸው በደል ተማረው ሀገሪቱን ለቀዋል ስላሏቸው ባለሃብቶች ሲያስረዱም የቻሉት ሸጠው መውጣታቸውን አልደበቁም። መሸጥ ያልቻሉት እቃቸውን ትተው የወጡት ግን ተመልሰው እቃቸውን ቢጠይቁ “በማናውቀው ወንጀል እንያዛለን!” በሚል ስጋት ባለሃብቶች ኢትዮጵያ ላይ ወረታቸውን በትነው መቅረታቸውን ሞሃመድ አልሸህሪ ለአረብ ኒውስ አስታውቀዋል።

ከዚህ ቀደም ተሰምቶ የማይታወቀውን የሳውዲ ባለሃብቶች ቅሬታና ብሶት ለታዋቂው የሳውዲ ጋዜጣ ለአረብ ኒውስ በአደባባይ ያጋለጡት ባለሃብቱ ሞሃመድ አልሻህሪ ቅሬታቸውን ለሁለቱም ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ቢያቀርቡም እስካሁን ምንም አይነት ምልሽ እንዳላገኙ ጠቁመዋል!

ይህ በእንዲህ እንዳለ የዜናውን ማስፈንጠሪያ በፌስቡኬ ላይ እንደለጠፍኩ “እንዴት ይህን ያልተጨበጠ መረጃ ሊንክ Link ይዘህ ትለጥፋለህ?” በማለት የጅዳ ቆንስል ዲፕሎማት ቆንስል ሸሪፍ በስልክ ቅሬታቸውን ግልጸውልኛል። ለሚሊዮኖች በአለም ዙሪያ የተሰራጨውን መረጃ ማስተላለፌን በአግራሞት የተመለከቱትና በጅዳ ቆንስል የኢኮኖሚ ሃላፊ አቶ ሸሪፍ ኼሪ በዜናው ዙሪያ ዘርዘር ባለ መልኩ አነጋግረውኛል። እኔም ያቀረብኩት መረጃ ከአረብ ኒውስ ማግኘቴን ደግሜ በማስረዳት ማስተባበያ ማቅረብ እንጂ የወጣውን መረጃ አታሰራጩ፣ አለያም አትለጥፉ ማለት እንደሚከብድ አሳውቄቸዋለሁ!

ቆንስል ሸሪፍ በመጨረሻም “አረብ ኒውስ ጋዜጣ ዛሬ ያወጣው መረጃ የተዛባ በመሆኑ አስፈላጊው ሁሉ እርምጃ ይወሰዳል” በማለት “ፍጹም መሰረተ ቢስ ነው!” ላሉት የተሰራጨ መረጃ ምላሽ ለመስጠት በሪያድ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በኩል አስፈላጊ ዝግጅት በመደረግ ላይ መሆኑን ገልጸውልኛል!

ቸር ያሰማን!

ነቢዩ ሲራክ
ህዳር 15 ቀን 2008 ዓ.ም.

(የዜናው ርዕስና አንዳንድ ክፍሎች በጎልጉል የኤዲቶሪያል ፖሊሲ መሠረት ታርመዋል፡፡ ፎቶ፡ የባለሃብቶቹ ሳይሆን ለማሳያነት የቀረበ)

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: News, Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጃዋርና በቀለ መታሠራቸው ተሰማ June 30, 2020 09:17 am
  • አገራዊ መድረክ ውጪ ድብቅ ውይይትን አንቀበልም June 17, 2020 06:57 am
  • ዴክሳሜታሶን! የኮሮና መድሀኒት June 17, 2020 06:49 am
  • የሰኔ 14ቱ ቀለበታዊ የፀሃይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ! June 17, 2020 06:38 am
  • የግብፅ የአባይን ውሃ ብቻዬን ልጠቀም ግትር አቋም ድርድር እንቅፋት ሆኗል June 10, 2020 07:15 am
  • የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!? April 12, 2020 02:48 am
  • በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሚጠቀሙበት የኤርትራ ስደተኛ ካምፕ ሊዘጋ ነው March 18, 2020 08:37 pm
  • እየተፈረካከሰ ያለው አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ March 18, 2020 08:09 pm
  • ኮሮና አዲስ ጉድ መዘዘ – ከቻይና በፊት በአሜሪካ ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎችን ቀጥፏል March 16, 2020 11:41 pm
  • የኮንዶሚኒየም ቤቶች በደላሎችና በመመሪያ ሰጪዎች ኔትዎርክ እየተቸበቸበ ነው! ታከለ የት ናቸው? March 9, 2020 10:18 am
  • ኤርሚያስ ለገሠ ከባለአደራ ተባረረ March 9, 2020 08:09 am
  • ድፍድፍ ሲቀል ይንሳፈፋል፤ ምሁር ሲዘቅት ይመራል፥ March 7, 2020 11:24 pm
  • ኢትዮጵያዊ ምን ይመስላል? በምንስ ይመሰላል? March 7, 2020 10:29 pm
  • WHY I WROTE “MONEY, BLOOD AND CONSCIENCE” March 4, 2020 11:15 pm
  • አድዋ፤ የጥቁር ሕዝብ ድል! March 2, 2020 11:24 am
  • ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ (አባ ጎራው) March 2, 2020 11:12 am
  • የኦነግ ሁለት መልክና ሦስት ግብሮች – ቃርሚያው ኃይል ቅጥር ነፍሰገዳይ ሆኗል February 25, 2020 11:26 pm
  • በቡራዩ “የጃል ማሮ” ፎቶ ጨረታ አፈናከተ፤ “ቡራዩ ሆኖ ከሃዲን ማሞካሸት አይቻልም” ነዋሪዎች February 17, 2020 09:13 pm
  • “ዲቃላ” የፍረጃ ፖለቲካ በኦሮሚያ የኃይል አሰላለፉን እየቀየረ ነው February 13, 2020 11:58 pm
  • “ከዚህ በኋላ ማናቸውንም በወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን” አንታገስም – ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ February 13, 2020 05:07 pm
  • “እኛ ማንም ተሳዳቢ እንዲመጣብን አንፈልግም” የጅማ ነዋሪ February 13, 2020 09:28 am
  • “ወላጆቻችሁ ሰላማዊ ሰልፍ በሕዝቡ ያስደርጉልን” – አጋቾች February 11, 2020 07:53 pm
  • “ወንጀል የፈጸመም ያስፈጸመም ተይዞ ለህግ ይቀርባል፤ ምርመራም ተጀምሯል” February 11, 2020 06:59 pm
  • ጃዋር ወደ መጨረሻው “የትግል” ስልቱ – አማራን ማበጣበጥ! February 10, 2020 11:54 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule