በኢትዮጵያ ያለው የጸጥታና ደኅንነት ሁኔታ አስተማማኝ ሁኔታ ላይ አለመሆኑ ተነገረ፡፡ የዕርዳታ ድርጅት ሠራተኞች ወደ መስክ የሚያደርጉት የሥራ ጉብኝት ተከለከለ፤ የፕሮጀክት ሥራዎች ሊደናቀፉ እንደሚችሉ ተገምቷል፡፡ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ያለው የጸጥታ ሁኔታ አስቸጋሪ ደረጃ ላይ በመድረሱ ኢህአዴግ የዕርዳታ ድርጅት ሠራተኞችን ወደተወሰኑ የአገሪቱ ክፍሎች እንዳይንቀሳቀሱ ማስጠንቀቂያ የሰጣቸው መሆኑን መረጃው የደረሳቸው ለጎልጉል አስታውቀዋል፡፡ በሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ በተለይ የአማራ ክልልና በምዕራብ ደግሞ የጋምቤላ ክልል አካባቢ ያለው ውጥረት እጅግ እያየለ በመምጣቱ በቦታዎቹ ላይ የሚንቀሳቀሱ የዕርዳታ ድርጅት ሠራተኞች ሊደርስባቸው ስለሚችል ጉዳት ተጠያቂ እንደማይሆን ኢህአዴግ በሰጠው ማሳሰቢያ አስታውቋል፡፡ ማስጠንቀቂያ ከተሰጣቸው የዕርዳታ ድርጅቶች መካከል የካቶሊክ ዕርዳታ … [Read more...] about በኢትዮጵያ የጸጥታ ሁኔታ አላስተማመነም
News
መለስ ሳይጠየቁ ሾለኩ
* “የሟቾች ቁጥር እስከ መቶ ሊደርስ ይችላል” ነዋሪዎች * “የሞቱት 14 ሰዎች ናቸው” ኢህአዴግ ሰሞኑን በጋምቤላ በደረሰው የእርስበርስ ፍልሚያ እስከመቶ የሚጠጉ መሞታቸውን የክልሉ ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡ ኢህአዴግ በበኩሉ የሞቱት 14 ብቻ ናቸው ይላል፡፡ ዘረኝነትንና ጠባብ ጎሰኝነትን ለኢትዮጵያ እንደ “ገጸ በረከት” ያመጡት መለስ በየቦታው የጫሩት እሣት ለፍርድ ሳያቀርባቸው ሾልከዋል፡፡ እሣቱ ግን አሁንም እየነደደ ነው፡፡ ጎልጉል ከአካባቢው ነዋሪዎችና ጉዳዩን በቅርብ ሲከታተሉ ባገኘው መረጃ መሠረት በግጭቱ የሞቱት እስከ መቶ እንደሚደርስ ይነገራል፡፡ ግጭቱ ከመነሻው በቀላሉ የተነሣ ቢሆንም ወዲያውኑ ወደከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱ ሥር የሰደደ ፖለቲካዊ ምክንያት እንዳለው ነዋሪዎች ይናገራሉ፡፡ ይህንኑ ዜና ኢሳት ሲዘግብ የሟቾቹ ቁጥር ከመቶ እንደሚያልፍ ምንጮቹን ጥቅሶ … [Read more...] about መለስ ሳይጠየቁ ሾለኩ
የመለስ “ሌጋሲ” – የድርብ አኻዝ ዕድገት ውጤት
ሥልጣን የያዙ ሰሞን ሞት የቀደማቸው መለስ ሲጠየቁ የኢትዮጵያን ሕዝብ በቀን ሦስት ጊዜ እመግባለሁ ወይም ሲመገብ አያለሁ የሚል የውሸት ተስፋ ሰጥተው ነበር፡፡ “የቀማኛ ኢኮኖሚ አቀንቃኝ” የነበሩት መለስ ለሥልጣናቸው ማራዘሚያ ጥቂቶችን በሃብት እንዲወጠሩ ሲያደርጉ የተቀረውን ኢትዮጵያዊ በቀን ሶስቴ ቀርቶ በሶስት ቀን አንዴ የማይመገብ አድርገውት ተሰናብተዋል፡፡ “ሌጋሲያቸውን እንጠብቃለን፤ እናስጠብቃለን” የሚሉት ያሁኖቹ ዘራፊዎችና ተላላኪዎች አገር በሁለት አኃዝ አድጋለች፤ ኢኮኖሚው ዓለምን እያስደነቀ ነው፤ ህዳሴ ነው፤ ውዳሴ ነው፤ … በማለት በቁማቸው ይዋሻሉ፤ የጥቅም ተካፋዮቻቸውም ይህንኑ ይዘው በየቀኑ ሲያናፉ ይውላሉ፡፡ ህወሃት ስለዘረጋው የዘራፊ፤ የቀማኛ፤ የሌባ፤ ኢኮኖሚ ብዙ ሊባልበት ይቻላል፡፡ ሌብነቱን ደግሞ መለስ ራሳቸው መስክረው ነው የሞቱት፡፡ “ያስቸገረን የመንግሥት … [Read more...] about የመለስ “ሌጋሲ” – የድርብ አኻዝ ዕድገት ውጤት
“ስህተትን ማመን አዲሱ የኢሕአዴግ አካሄድ ነው” – መረራ ጉዲና
"መንግሥት ስህተቱን ካመነ ኦሮምያ ውስጥ ለተፈፀሙ ወንጀሎች ተጠያቂ የሆኑ አጥፊዎች በገለልተኛ አካል ተለይተው ይቀጡ” ሲሉ የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ጠይቀዋል። “ስህተትን ማመን አዲሱ የኢሕአዴግ አካሄድ ነው” ሲሉም ተችተዋል። “ቀደም ሲል የመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣን በኦሮምያ ክልል ለተፈጠረው ችግር ዋናው መንስዔ የመልካም አስተዳደር እጦት ነው” ማለታቸው ይታወቃል። የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ መለስካቸው አምሃ በጉዳዩ ላይ ዝርዝር አለው፡፡ እዚህ ላይ ያዳምጡ። (ምንጭ: VOA) … [Read more...] about “ስህተትን ማመን አዲሱ የኢሕአዴግ አካሄድ ነው” – መረራ ጉዲና
የአውሮጳ ፓርላማ ኢህአዴግን “ልክ ሊያስገባ”?!
* ውሳኔው “ማዕቀብና የዕርዳታ ቅነሳ አያስከትልም” አና ጎሜዝ * የቴድሮስ አድሃኖም “ዲፕሎማሲያዊ ልመና” አልሰራም የአውሮጳ ፓርላማ ሐሙስ ዕለት ባለ 19 ነጥብ ውሳኔ ህወሃት/ኢህአዴግ በሚገዛት ኢትዮጵያ ላይ አስተላልፏል፡፡ ጉዳዩ ኢህአዴግ “ልክ ሊገባ ይሆን” የሚል አመለካከት ጭሯል፡፡ ረቂቁ ለውይይት እንዳይቀርብ የቻሉትን ያህል የጣሩት ቴድሮስ አድሃኖም “ዲፕሎማሲያቸው” አልሠራም፡፡ ውሳኔው “ማዕቀብና የዕርዳታ ቅነሳ አያስከትልም” በማለት አና ጎሜዝ ተናገሩ፡፡ ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ ውሳኔው “ውስጡ በብረት የተወጠረ የቦክስ ጓንቲ ነው” ብለውታል፡፡ የአውሮጳ ፓርላማ ሐሙስ ዕለት የኢትዮጵያን ጉዳይ በተመለከተ የቀረበለትን ረቂቅ ውይይትና ክርክር ካካሄደ በኋላ በከፍተኛ አብላጫ ድምጽ ያለ አንዳች ማሻሻያና ለውጥ እንዳለ አጽድቆታል፡፡ ጉዳዩን ከሥሩ ሲከታተሉና ለኅብረቱ … [Read more...] about የአውሮጳ ፓርላማ ኢህአዴግን “ልክ ሊያስገባ”?!
አዛን “መታገስ የማይቻል ጩኸት” እያስከተለ ነው – ኔታኒያሁ
የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቢኒያም ኔታኒያሁ አዛን “መታገስ የማይቻል ጩኸት” እየሆነ መጥቷል በማለት ተናገሩ፡፡ ጉዳዩ ያስቆጣቸው የሙስሊም መሪዎች ንግግሩ በሃይማኖታችን ላይ ማዕቀብ ለመጣል የተቃጣ ነው ብለውታል፡፡ ባለፈው አርብ በእስራኤል ሸንጎ የሊኩድ ፓርቲ አባላት በተገኙበት ኔታኒያሁ ባደረጉት ንግግር በእስራኤል የሚገኙ የአረብ ከተሞች ለአገሪቷ ሕግ መገዛት አለባቸው ብለዋል፡፡ ይህንንም በማድረግ ለአገሪቷና ለማኅበረሰቡ ግዴታቸውን መወጣት አለባቸው በማለት አስታውቀዋል፡፡ “በአብዛኛዎቹ የአረብ ከተሞች ሕግ አይከበርም፤ ይህም አዛን እና ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት ተጠቃሽ ናቸው” በማለት ቢኒያም ኔታኒያሁ የተናገሩ ሲሆን ከዚህ አኳያ ከበርካታ መስጊዶች የሚሰማው አዛን “መታገስ የማይቻል ጩኸት እያስከተለ” ስለሆነ መንግሥታቸው ሕግ ሊያወጣ መወሰኑን አስታውቀዋል፡፡ አዛን … [Read more...] about አዛን “መታገስ የማይቻል ጩኸት” እያስከተለ ነው – ኔታኒያሁ
የትግራይ ነጋዴዎችን ለመጥቀም አዲስ የበርበሬ አዋጅ በጎጃም
ኢትዮጵያን በነጻ አውጪ ስም እየገዛ ያለው የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሃት) በተለይ በምዕራብ ጎጃም አካባቢ የደነገገው አዲስ የበርበሬ አዋጅ ችግር እያስከተለ መሆኑን የጎልጉል እማኝ ዘጋቢ (ireporter) በላኩልን መረጃ አስታውቀዋል፡፡ እንደ እማኝ ዘጋቢው ከሆነ አዋጁ የወጣው በ2002ዓም ሲሆን በሥራ ላይ መዋል የጀመረው በዚህ ዓመት እንደሆነ ያስረዳሉ፡፡ ይህ በበርበሬ ላይ ብቻ የተደነገገው አዋጅ ዋና ምክንያቱን በውል ለማወቅ የሚያዳግት ቢሆንም እንደ እማኝ ዘጋቢው አስተያየት በርበሬው ወደ ትግራይና አዲስ አበባ የሚላክ በመሆኑ በተለይ የትግራይ ነጋዴዎችን በከፍተኛ ሁኔታ ለመጥቀም ታስቦ እንደሆነ ከሚሰጡት ግምቶች የላቀው መሆኑን ያስረዳሉ፡፡ እማኝ ዘጋቢያችን የላኩልን መረጃ እንዲህ ይነበባል፡- “በአማራ ክልል በምዕራብ ጎጃም ዞን በቡሬ በፍኖተ ሰላም በሺንዲ … [Read more...] about የትግራይ ነጋዴዎችን ለመጥቀም አዲስ የበርበሬ አዋጅ በጎጃም
በኦሮሚያ ከተሞች የሚካሄድ ተቃዉሞ ቀጥሏል
ከተጀመረ ወራትን ያስቆጠረውና ከሁለት መቶ በላይ ሰዎች በጭካኔ ለመገደላቸው መረጃ የሚቀርብበት ሕዝባዊ ንቅናቄ አሁንም በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች ቀጥሎዋል። ኢህአዴግ በአፈቀላጤዎቹ አማካኝነት "ሰልፍ የወጣ የለም፣ ከተማችን ሰላም ነው፣ የተገደለ የለም፣ . . ." በማለት የማስተባበያ ሙከራው በራሱ ሹሞች ሲጨናገፍ በተደጋጋሚ ይስተዋላል። በሌላ በኩል በፌዴራልና በአግአዚ መራር ሰቆቃ እየደረሰበት ያለው ሕዝብ "ባርነት በቃን፣ ግድያው ይቁም፣ የታሰሩት ይፈቱ፣ . . ." የሚሉ መፈክሮችን እያነገበ ሰላማዊ ተቃውሞውን ቀጥሎዋል። የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ ባለፉት ሦስት ቀናት የተከሰተውን ያቀረበው ዘገባ ከዚህ በታች ይገኛል። ባለፈው ሐምሌ ወር ከአምቦ ወደ አዲስ አበባ ተወስዶ ታስሮ እንደነበርና ታሞ ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ህክምና ላይ ሳለ ህይወቱ እንዳለፈ የተነገረው ተማሪ አብደታ … [Read more...] about በኦሮሚያ ከተሞች የሚካሄድ ተቃዉሞ ቀጥሏል
በልማት ስም የሚካሄዱ እርምጃዎች ይቁሙ
ተቃዋሚው ሕብረት የኢትዮጵያ ፌድራላዊ አንድነት መድረክ፤ በአገሪቱ እየታየ ያለውን ቀውስና ሌሎች ነባር ችግሮች አስመልክቶ አሳስበውኛል፤ ባላቸው ጉዳዮች ዙሪያ በትላንትናው ዕለት ለጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ ግልጽ ደብዳቤ ጽፏል። “የሕዝቦቻችንን ጥቅሞች ማዕከል ያላደረጉና ሕዝብን ያላሳተፉ በልማት ስም የሚካሄዱ እርምጃዎች በአስቸኳይ እንዲቆሙና የሃገሪቱ ሕገ መንግስታዊ ድንጋጌዎች እንዲጠበቁ እንጠይቃለን።” መድረክ። መድረክ መፍትሔ ያላቸውን ባለ አምስት ነጥብ ደብዳቤ መነሻነት የድርጅቱ ሊቀ መንበር ከአሜሪካ ድምጽ ጋር ያደረጉትን ቃለ ምልልስ ከዚህ ያድምጡ። … [Read more...] about በልማት ስም የሚካሄዱ እርምጃዎች ይቁሙ
ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የደረሰው ጥቃት
የጎልጉል እማኝ ዘጋቢ (ireporter) የሆኑ በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የደረሰውን ጥቃት ከፎቶ ጋር አያይዘው ልከውልናል፡፡ ዘጋቢው እንዳሉት ከሆነ እዚያው ተማሪ ሲሆኑ የደረሰውን ሁኔታ በዚህ መልኩ ይገልጹታል፡- “ከትላንት ወዲያ (ማክሰኞ) ማታ ካፌ ተማሪዎች ተቃውሞ ሊያሰሙ ሲሞክሩ ፌዴራሎች በዱላ ጀመሩ፤ ከዚያም ዶርም ገባን፤ ሁላችንንም ዶርም እየገቡ በሩን እየሰበሩ እያወጡን አዳሩን ሲደበድቡን አደሩ፤ እስካሁን የሆነ ብሎክ መግባትም አይቻልም፤ የሞተ ሰው አለ እየተባለ ነው፤ እዚያም መግባት አይቻልም፤ ሌላ ብሎክ ደግሞ እሣት ተያይዞ ነበር፤ ማታ እሣት አደጋ መጥቶ አጠፋው … ወዴት እንሂድ? ወደ አገራችን እንዳንሄድ መንገድ ተዘግቷል፤ ኬላ በሙሉ (ተዘግቷል)፤ ወደ ጊቢም እንዴት እንግባ? ያገኙትን ነው የሚቀጠቅጡት፤ … ” በማለት በዚያ የደረሰውን ጥቃት እንድናሰማላቸው ከፎቶዎች ጋር … [Read more...] about ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የደረሰው ጥቃት










