ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብና የኢትዮጵያ ወዳጆች አገራችንን ለአለፉት 27 ዓመታት ያሻውን በማድረግ በከፍተኛ አፈናና የጉልበት አገዛዝ ሲገዛ የነበረው ህወሃትና በሌሎች አክራሪ ብሄረተኞች ትብብርና ቅንጅት የታየውን የለውጥ ተስፋና እየተካሄዱ ያሉ ለውጦችን ለማደናቀፍ በከፍተኛ ሁኔታ እንቅስቃሴ ላይ ይገኛሉ። ህወሃት በገዥነት ዘመኑ ከኢትዮጵያ ሕዝብ የዘረፈውን ሀብት በመጠቀም የተለያዩ ቡድኖችን በገንዘብ በመደለል ከትግራይ ውጭ ያለውን የአገራችንን ክፍል ከማተራመስ በላይ ወደ ማፍረስ እየተንቀሳቀሱ መሆኑን በየቀኑ የአገራችንን ፖለቲካ ከሚዳስሱ ባለሙያወች በበቂ ሁኔታ ከተረዳን ቆይተናል። በዚህም ምክንያት አገራችንን ከተጋረጠባት ሴረኛ አደጋ ለመታደግ ከዚህ ቀደም በአሜሪካና አውሮፓ የምንገኝ በቁጥር 31 የምንሆን በሶፍት ዌርና ኢንፎርሜሽን ኮሚንኬሽን ሙያወች የተሰማራን … [Read more...] about 31 Ethical Hackers ያወጡት መግለጫ
“አልቃሻው ሚኒስትር ደኤታ” ኤርምያስ ለገሠ
በሕይወት በነበረበት ጊዜ ኢትዮጵያን ጠርንፎ የነበረውን ኢህአዴግን እንዲያገለግሉ የሚመለመሉ በርካታ ወዶገብ ጥቅመኞች ነበሩ። በአንድ ወቅት ተስፈኛ ካድሬዎችን ለመመልመል ሲኒየሮቹ ካድሬዎች በሄዱበት ክፍለከተማ ከተሰበሰቡት መካከል አንዱ ኤርሚያስ ለገሰ ነበር። በወቅቱ አብሮት የነበረ የቅርብ ወዳጄ እንደሚለው ከሆነ “ደርግን ገረሰስን” የሚሉት ተጋዳላዮች በወቅቱ ደረሰብን በማለት ከመድረኩ ሲያወሩ ኤርሚያስ ከሥር ሆኖ በአራት መዓዘን ያለቅስ ነበር። አገር ለመገንጠል የተነሱት የወንበዴዎች ክምችት “ቁርጠኝነታቸው፣ በቦምብ ላይ መረማመዳቸው፣ አንዱ ለሌላው ልሙት ማለቱ፣…” ነበር ኤርሚያስን ተንሰቅስቆ ያስለቀሰው፤ ይህንኑ ቃል በሌላ ጊዜ ደግሞታል። ይህንን እንስፍስፍ እጩ ካድሬ ማንነት የጠየቁ መልማዮች ወዲያውኑ በብርሃን ፍጥነት ኤርሚያስን ከክፍለከተማ አስፈነጠሩትና መድረሻውን አሁን … [Read more...] about “አልቃሻው ሚኒስትር ደኤታ” ኤርምያስ ለገሠ
አሸባሪው ህወሓት በሕገወጥ የጦር መሣሪያ ዝውውር በሕግ መታገድ፤ መሪዎቹም በኃላፊነት መጠየቅ አለባቸው
ራሱን የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሓት/ትህነግ) በማለት የሚጠራውና በኢትዮጵያ እጅግ አስከፊ የሚባልና ትውልድን ያወደመ ርዕዮት በመከተል አገር ያፈረሰው የወንበዴዎች ጥርቅም፤ እስካሁንም በዓለምአቀፍ የአሸባሪዎች የመረጃ ቋት በአሸባሪነት ተመዝግቦ የሚገኝ ድርጅት መሆኑ ይታወቃል። አባላቱና ደጋፊዎችም በዚሁ ሁኔታ የሚታዩ መሆናቸውን ብዙዎች የሚስማሙበት ነው። በአገራችን ባለፉት ሁለት ዓመታት ያህል በእጅጉ ተንሰራፍቶ ከሚገኙት ሦስት ሕገወጥ ሥራዎች መካከል አንዱ ሕገወጥ የጦር መሣሪያ ዝውውር ነው። ሌሎቹ ሁለቱ ደግሞ ሕገወጥ የገንዘብ ዝውውርና ሐሰተኛ የዜና ዘገባዎች ናቸው። በሦስቱም ውስጥ አሸባሪው ህወሓት እጁ እንዳለበት በርካታ ጠቋሚ መረጃዎች አሉ። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ድብቅ ምሥጢራትን በማውጣት የሚታወቀው ethio wiki leaks “ህወሓት እና የጦር መሳሪያ … [Read more...] about አሸባሪው ህወሓት በሕገወጥ የጦር መሣሪያ ዝውውር በሕግ መታገድ፤ መሪዎቹም በኃላፊነት መጠየቅ አለባቸው
48 ሰዓት ሳይሞላ በአቶ ዳውድ የሚመራው “ኅብረት” ወደ ዘጠኝ ወረደ
አርብ ዕለት በአቶ ዳውድ ኢብሣ የሚመራ “የአስር ድርጅቶች” ኅብረት ፈጸሙ መባሉ ብዙም ሳይቆይ ስምምነቱን ከፈረሙት መካከል አንዱ ነው የተባለለት የአገው አገር አቀፍ ሸንጎ በስምምነቱ ላይ እንደሌለበት አስታውቋል። ሸንጎው ባወጣው መረጃ መሠረት ሸንጎው ውኅደት ማድረጉን አስመልክቶ ደጋፊዎቻቸው ጥያቄ ያቀረቡ መሆኑን በመጥቀስ የሰጠው ምላሽ “በዚህ ዙሪያ ከብሔራዊ ሥራ አስፈጻሚ ጀምሮ እስከ ዞንና ወረዳ ውይይት” ያልተደረገበት መሆኑን በመጥቀስ በኅብረት ስምምነቱ ላይሸንጎው እንዳልተገኘ ገልጾዋል። በተመሳሳይ ዜና ህወሓት “የፌዴራሊስት” ጉባዔ በማለት በመቀሌ ጠርቶት በነበረ ስብሰባ ላይ ከደብረጽዮን በስተቀኝ አንድ ወንበር ቀጥሎ ተቀምጦ የሚታየው በፊት ለፊቱ “የአገው ተወካይ” የሚል ቢሆንም ስብሰባው ከመጀመሩ በፊት የአገው ማኅበረሰብ ተሰብስቦ ተወካይ እንደማይልክ መግለጫ … [Read more...] about 48 ሰዓት ሳይሞላ በአቶ ዳውድ የሚመራው “ኅብረት” ወደ ዘጠኝ ወረደ
የመከላከያ ሚኒስትር ለማ መገርሳ መልቀቂያ አላቀረቡም!!
ዜናው የውሸት ነው ለሥራ ወደ አሜሪካ ያቀኑት የመከላከያ ሚኒስትር ለማ መገርሳ የሥልጣን መልቀቂያ ማስገባታቸውን ጠቅሶ ፋኑኤል ክንፉ ፈንታሌ በሚባለው የግል የዩቲዩብ ገጹ በድምጽ ያሰራጨው ዜና ከእውነት የራቀ መሆኑ ተጠቆመ። “የፈንታሌ ሚዲያ ምንጮች" እንደነገሩት ያስታወቀው ፋኑኤል ክንፉ ዜናው እውነት እንደሆነ አድርጎ ለማሳየት የተጠቀመው አቶ ለማ ለቪኦኤ የሰጡትን ቃለ ምልልስ ነው። ለአቶ ለማም ሆነ በኦሮሚያ ጉዳይ እጅግ ቅርብ የሆኑ የሚዲያ ውጤቶች ለጊዜው ምንም ያላሉበትን ጉዳይ ፋኑኤል ምንጮቹን ጠቅሶ ይህንን አነጋጋሪ ዜና ትናትን ሌሊት (በአዲስ አበባ አቆጣጠር) ላይ መለጠፉ አነጋጋሪ ሆኗል። ዛሬ ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የመከላከያ ሚኒስትርን ጠቅሶ እንዳለው ከሆነ የአቶ ለማ የስልጣን መልቀቅ ጥያቄ የሚታወቅ አይደለም። … [Read more...] about የመከላከያ ሚኒስትር ለማ መገርሳ መልቀቂያ አላቀረቡም!!
የጃዋር “ቄሮ”፣ ባልደረቦቹና ባለሥልጣናት በአሸባሪነት እንዲፈረጁ ተመድ የቀረበለትን ክስና ማስረጃ ተቀበለ
“ግድያ ከተፈጸመ በኋላ አስከሬኖችን ለመቀጣጫ ተጠቅመዋል” አሉ ፕሮፌሰር ጌታቸው። ሲያስረዱም “ገድለው የሰውነትን ክፍል በመበጣጠስ ሜዳ ላይ ጥለዋል። ይህ የሆነው አንተም እንዲህ ትሆናለህ፣ ለቀህ ጥፋ፣ ሂድ፣ የሚል የመቀጣጫ ማሳያ ለመጠቀም ሲባል ነው። ይህንን ያዩ፣ የፈሩ ቤተክርስቲያን ተሸሸጉ፣ ጫካ ውስጥ ተጠለሉ። ወደ ማይታወቅ ቦታ አመለጡ”። ይህ የተባለው ትግሉን አጠናቆ ወደ ቤቱ የገባውና አደረጃጀት የሌለው መስዋዕትነት የከፈለውን ቄሮ ሳይሆን በጃዋር መሃመድ የሚመራ፣ ከፍተኛ ገንዘብ የሚያዘዋውር፣ የተደራጀ፣ ትዕዛዝ አመንጪ ያለው፣ አዛዥና የዕዝ ሠንሠለት ያለው፣ የማዘዣ ኮማንድ የተበጀለት … የጥፋት ኃይል በአሸባሪነት እንዲፈረጅ ጥያቄ በቀረበበት ወቅት ነው። በማስረጃ ተደግፎ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ክስ የቀረበበት ይህ ኃይል በአሸባሪነት … [Read more...] about የጃዋር “ቄሮ”፣ ባልደረቦቹና ባለሥልጣናት በአሸባሪነት እንዲፈረጁ ተመድ የቀረበለትን ክስና ማስረጃ ተቀበለ
ጃዋር ዕቁብ በልቶ ከጨዋታው ወጣ – “አበደን” ተተገበረ
በተለያየ የቅጽል ማዕረግ የሚሞሸረው ጃዋር መሐመድ “ስለቀጣዩ የፖለቲካ ሂደትና አዲስ ስትራቴጂ” ለመነጋገር አዲስ አበባን ሲለቅ በምርጫ እንደሚሳተፍ ለሚከተሉት ሁሉ መልዕክት አስተላልፎ ነበር። ይህንኑ ተከትሎ “ጠቅላይ ሚኒስትር” በሚል ደጋፊዎቹንና እየለመነ አበል የሚሰጣቸው የሚዲያ ባለሟሎቹ ሲያስተጋቡ ቆይተዋል። አዲስ ፓርቲ ያቋቁም ወይም ካሉት ፓርቲዎች ጋር የመቀላቀል ሃሳብ እንዳለው ለጊዜው እንዳልወሰነ፣ ነገር ግን ወደ ምርጫ የመግባቱ ጉዳይ ያለቀለት እንደሆነ ጃዋር ያስታወቀው ከምርጫው በፊት የድምጽ ስሌትን በማስላት እንደሆነ በይፋ አስታውቆም ነበር። በአሜሪካ የተለያዩ ግዛቶች፣ በካናዳ፣ በኖርዌይ፣ ስዊድን፣ ጀርመንና እንግሊዝ የቅስቀሳ ዘመቻውንና የገንዘብ ማሰባሰብ ተግባሩን ካከናወነ በኋላ ለጀርመን ድምጽ በሰጠው ቃለ ምልልስ ወደ ምርጫ ለመግባት አለመወሰኑን … [Read more...] about ጃዋር ዕቁብ በልቶ ከጨዋታው ወጣ – “አበደን” ተተገበረ
ኢትዮጵያ በ2032
የምንፈልጋት ኢትዮጵያ በ2032 በሚል ርእስ ሀገር አቀፍ የውይይት መድረክ በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ይገኛል። ሀገር አቀፍ የውይይት መድረኩን በፎረም ኦፍ ፌዴሬሽን እና ዴስትኒ ኢትዮጵያ ኢኒሼቲቭ ናቸው በጋራ ያዘጋጁት። በመድረኩ ላይም የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚልን ጨምሮ የክልል ርእሳነ መስተዳድሮች እና ምክትል ርእሳነ መስተዳድሮች፣ የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል። በተጨማሪም የበርካታ ሀገር አቀፍ እና ክልላዊ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች እና ተወካዮችም በመድረኩ ላይ ተሳትፈዋል። መድረኩ የሀገሪቱን የፖለቲካ ፓርቲዎች እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላትን በማቀራረብ የወደፊት የሀገሪቱ እጣ ፈንታ ላይ ለመወያየት በማለም የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል። የመድረኩ ተሳታፊ የሆኑ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮችም፤ በመድረኩ ደስተኛ መሆናቸውን … [Read more...] about ኢትዮጵያ በ2032
ኦብነግ፤ ከህወሓቶች ጋር መቀመጥ በሕዝብ ደም መቀለድ ነው!
በቀን 10/03/2012 ዓ.ም ተፅፎ በቁጥር 07642/2019 ወጪ የተደረገው አስገራሚ ደብዳቤ ይድረስ “ለህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ፣ መቀሌ” በማለት ይጀምራል። ጉዳዩ፡- “ስለተጠራንበት ስብሰባ ይመለከታል” በማለት ይቀጥላል። የዚህን ደብዳቤ ትርጉምና ፋይዳ በቅጡ ለመረዳት የተፃፈበትን አውድ በአጭሩ መዳሰስ ያስፈልጋል። በደብዳቤው ላይ ፊርማቸውን አኑረው የላኩት የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ-አውጪ ግንባር (ኦብነግ) ዋና ሊቀመንበር አቶ አብዲርሃማን መሃመድ ናቸው። ከላይ እንደተገለፀው ዋና ጉዳዩ ሰሞኑን በመቀሌ ከተማ እየተካሄደ ባለው ስብሰባ ላይ እንዲገኙ ከህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ ለቀረበላቸው ጥሪ የተሰጠ ምላሽ ነው። ህወሓት በመቀሌው ስብሰባ ላይ እንዲገኙ ጥሪ ያቀረበላቸው በሥልጣን ዘመኑ በአሸባሪነት የፈረጃቸው የኦብነግ አመራሮች ናቸው። እንግዲህ በአካባቢው ያለውን የተፈጥሮ … [Read more...] about ኦብነግ፤ ከህወሓቶች ጋር መቀመጥ በሕዝብ ደም መቀለድ ነው!
“አበሉን ክፈሉና መልሱት”፤ የህወሓት የመቀሌ ስብሰባ ቅሌት
የአገው ማኅበረሰብ ተወካይ አልላከም የህወሓት መሪዎች ኢትዮጵያን እናድን በሚል ማምታቻ ቃል ኢትዮጵያን ለማፍረስ ፌደራሊስት ኃይሎች ያሏቸውንና ጫሚሶወችን ጋብዘዋል። ከእነኚህ ተጋባዥ ሰዎች አብዛኛዎቹ 1) የሚከፈላቸውን አበል እንጂ የህወሃት ያረጀና ያፈጀ አብዮታዊ ዲሞክራሲ ሀሳብ ምን እንደሆነ አያውቁም2) በኢትዮጵያ ፖሊቲካም ሆነ ኢኮኖሚ ተፅእኖ ፈጣሪዎች ያልነበሩ ናቸው3) የህወሃት ስሪቶች እንደ መሆናቸው መጠን ወደፊትም ተጽእኖ መፍጠር ቀርቶ ቤተሰባቸውን ሊያሳምኑ አይችሉም4) እስከካሁን ባለው መረጃ ኦብነግ፣ ኦነግ፣ ሲአንና በፕሮፌሰር መረራ የሚመራው ኦፌኮ ግብዣውን ተቀብለው አልሄዱም። በአጠቃላይ ህወሃት እያደረገ ያለው አልሞትኩም፣ አልበሰበስኩም ትግል የትግራይን በጀት በአበል ስም መበተን፣ መስጠትና መቀበል ካልሆነ በቀር የሚያመጣው አንድ ውጤት የለም። … [Read more...] about “አበሉን ክፈሉና መልሱት”፤ የህወሓት የመቀሌ ስብሰባ ቅሌት










