• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

አሸባሪው ህወሓት በሕገወጥ የጦር መሣሪያ ዝውውር በሕግ መታገድ፤ መሪዎቹም በኃላፊነት መጠየቅ አለባቸው

December 8, 2019 04:54 pm by Editor Leave a Comment

ራሱን የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሓት/ትህነግ) በማለት የሚጠራውና በኢትዮጵያ እጅግ አስከፊ የሚባልና ትውልድን ያወደመ ርዕዮት በመከተል አገር ያፈረሰው የወንበዴዎች ጥርቅም፤ እስካሁንም በዓለምአቀፍ የአሸባሪዎች የመረጃ ቋት በአሸባሪነት ተመዝግቦ የሚገኝ ድርጅት መሆኑ ይታወቃል። አባላቱና ደጋፊዎችም በዚሁ ሁኔታ የሚታዩ መሆናቸውን ብዙዎች የሚስማሙበት ነው።

በአገራችን ባለፉት ሁለት ዓመታት ያህል በእጅጉ ተንሰራፍቶ ከሚገኙት ሦስት ሕገወጥ ሥራዎች መካከል አንዱ ሕገወጥ የጦር መሣሪያ ዝውውር ነው። ሌሎቹ ሁለቱ ደግሞ ሕገወጥ የገንዘብ ዝውውርና ሐሰተኛ የዜና ዘገባዎች ናቸው። በሦስቱም ውስጥ አሸባሪው ህወሓት እጁ እንዳለበት በርካታ ጠቋሚ መረጃዎች አሉ።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ድብቅ ምሥጢራትን በማውጣት የሚታወቀው ethio wiki leaks “ህወሓት እና የጦር መሳሪያ ዝውውር ኮሪደሮቹ” በሚል ርዕስ ባወጣው አጭር የመረጃ ዘገባ ላይ ህወሓት ህገወጥ የጦር መሣሪያ የሚያዘዋውርበት መስመሮችን አቅርቧል፤ ለዚህም ድርጊቱ ለኢትዮጵ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካ ቀንድም ስጋት በመሆኑ በኢጋድ እንዲሁም በዓለምአቀፉ ፍርድቤት በኃላፊነት እንዲጠየቅ ይገባል ብሏል።

የፌዴራሉ መንግሥት በዚህ ጉዳይ ላይ ከባለሞያዎች ጋር በመነጋገር ተግባራዊ ቢያደርግ ብዙዎች የሚደግፉት ሃሳብ እንደሆነ ይገመታል።  

“ህወሓት እና የጦር መሳሪያ ዝውውር ኮሪደሮቹ”

ባለፉት ሃያ ወራት በፖለቲካና የሽብር ተግባሮቹ ተግቶ ሲንቀሳቀስ የነበረው ህወሓት የጦር መሳሪያ ክምችትን ጨምሮ በዝውውር ላይ ተሳትፎ እያደረገ ይገኛል።

የጦር መሳሪያዎቹ የነፍስ ወከፍና የቡድን ተብለው በሁለት ሊከፈሉ ይችላል። ጦር መሳሪያዎቹ በሱዳን በኩል ባለው መስመር እንዲገቡ የሚያደርግ ሲሆን÷ የጦር መሳሪያዎቹ መነሻ ከቱርክና ከሰሜን አፍሪቃ ሀገራት እንደሆነ መረጃዎች ያመለክታሉ ።

የጦር መሳሪያ መተላለፊያ ኮሪደሮቹ፤

ከሱዳን ሱፍ ውሃና ወዲ ኢሎ አድርጎ ሉግዲ ሁመራ የሚያስገባው መስመር የጦር መሳሪያ ዝውውር የሚካሄድበት ዋና ኮሪደር ነው።

የወልቃይት ምድር የሆነችው ሉግዲ በምዕራባዊ የትግራይ ዞን ስር የምትገኝ የድንበር ከተማ ናት።

ከሱዳን የድንበር አካባቢዎች (በዋናነት ወዲ ኢሎ እና ሱፍ ውሃ) በኩል ተሻግሮ የሚገባ በርካታ የጦር መሳሪያ የሚከማችባትና የሚሰራጭባት ማዕከል ነች።

በምስሉ ላይ በቀይ የተመለከተችው ቦታ ‘ሉግዲ’ ትሰኛች

ሉግዲ ይህ ነው የሚባል የፌዴራሉ የፀጥታና ደህንነት (መከላከያ፣ ፌዴራል ፖሊስ) መዋቅር የሌለባት ነፃ ቀጣና ስትሆን፤ በሉግዲ በኩል የሚገባው የጦር መሳሪያ በሁመራ በኩል በሁለት አቅጣጫ ይሰራጫል።

በሽሬ በኩል ወደ መሀል ትግራይ የሚገባው አንደኛው መስመር ሲሆን፤ ከሁመራ ወደ ጎንደርና መሀል አገር የሚሰራጭበት ደግሞ ሁለተኛው መስመር ነው። ወደትግራይ የሚሄደው የክምችቱ አካል ሲሆን÷ በጎንደር በተለያዬ አቅጣጫ ወደመሀል አገር የሚላከው ደግሞ የሽብርና የንግዱ አካል ነው ።

ሉግዲ ላይ ያለው የጦር መሳሪያ ዝውውር የሶሪያዋን ምዕራብ ‘አሊፖ’፣ የሊቢያዋን ‘ቤንጋዚ’፣ የየመኗን ‘ታአዝ’ እና ‘አርሃብ’ ከተማ የሚመስል ነው። ልዮነቱ እነዚህ ከተሞች የእርስ በርስ ጦርነት የሚካሄድባቸው የጦር ቀጣና መሆናቸው ሲሆን፤ ሉግዲ ደግሞ ጎረቤቶቹን በሽብር እያመሰ ራሱን ለነፃ ሀገር ምስረታ እያዘጋጀ ባለው ድርጅት [ህወሓት] ስር ያለች  የጦር መሳሪያ ማስገቢያ ኮሪደር  ማዕከል መሆኗ ብቻ ነው።

በትንሿ የድንበር ከተማ ሉግዲ በኩል ህወሓት ምን እየሰራ እንዳለ ማዕከላዊው መንግሥት ያውቃል ። ዝምታው ይሄን ያህል ተራዛሚ የሆነበት ምክንያት ለማናችንም ግልፅ አይደለም‼

የአገሪቱ ዳር ድንበር በመከላከያ ሰራዊት እንደሚጠበቅ በአዋጅ የተደነገገ ጉዳይ ሆኖ እያለ ÷ ቀጣናው ላይ ጥበቃው የላላ መሆኑ÷ በአካባቢው የህወሓት ጦር በእጥፍ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ በቂ መረጃዎች አሉ ።

የማዕከላዊው መንግሥት የትኩረት አቅጣጫ በኤርትራ ‘ሱከቱር’ እና በሱዳን ‘ሐምዳይት’ በኩል ብቻ መሆኑ÷ ህወሓት በሉግዲ በኩል የራሱን የጦር መሳሪያ ዝውውር ኮሪደር ከፍቷል።

የጦር መሳሪያ ዝውውር ውስጥ እጁን የዘፈቀው ይሄ አውሬ ድርጅት ኢትዮጵያን የደም ኩሬ ለማድረግ ተግቶ እየሰራ ነው።

በማዕከላዊው መንግሥት ስር ያሉት÷ የፀጥታና ደህንነት ተቋማት ባለፈው አንድ ዓመት ብቻ በጦር መሳሪያ ዝውውርና ሕገወጥ ትጥቅ በሚል 40,000 የጦር መሳሪያ መወረሱን ትላንት አንድ official ሪፖርት ላይ ያገኘሁት መረጃ ያመለክታል።

ለሽብር ቡድኖች እገዛ በማድረጉ÷ ሽብርንም በማበረታታቱ ከማዕከላዊው መንግሥት በኀይል የተወገደው ታሊባን ቶራቦራን የሙጥኝ ብሎ አያሌ የሽብር ጥፋቶችን እንዳደረሰ ይታወቃል። ዛሬም ወደ መንግሥትነት ለመመለስ ባለፈበት የ18 ዓመት የሽብር ተልዕኮው ላይ ይገኛል።

ታሊባን ለሽብር ተግባራቱ የፋይናንስ እና የሎጀስቲክስ ፍላጎቶቹን እያሟላ ያለው ድራግን ጨምሮ የጦር መሳሪያ ንግድና ሌሎች የኮንትሮባንድ ስራዎችን በመስራት ነው።

አሁን ህወሓት ከታሊባን የተለየ ተግባር እያከናወነ አይደለም። የጦር መሳሪያ ዝውውሩ አንድም የፋይናንስ አቅሙን ይጨምርለታል ። ሁለትም በጎረቤትና በመሀል አገር ኢንሰርጀንሲን ጨምሮ ሌሎች የሽብር ተግባራት እንዲበራከቱ ለማድረግ እየተጠቀመበት ይገኛል።

ህወሓት የአፍሪቃ ቀንድ የሠላምና ደኀንነት ስጋት ነው

ማዕከላዊው መንግሥት ከኢጋድ እና የአፍርቃ ሕብረት ጋር በመመካከር በሕግ እንዲታገድ ብሎም መሪዎቹ በICC እንዲጠይቁ በጋራ ተቀናጅተው ሊሰሩ ይገባል

ጊዜው በረዘመ ቁጥር ቀጣናው ወደ አስከፊ ትርምስ ውስጥ መግባቱ አይቀሬ ነው

ጎልጉል፤ የድረገጽ ጋዜጣ

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Politics, Social Tagged With: Full Width Top, illegal weapon, Middle Column, tplf

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጃዋርና በቀለ መታሠራቸው ተሰማ June 30, 2020 09:17 am
  • አገራዊ መድረክ ውጪ ድብቅ ውይይትን አንቀበልም June 17, 2020 06:57 am
  • ዴክሳሜታሶን! የኮሮና መድሀኒት June 17, 2020 06:49 am
  • የሰኔ 14ቱ ቀለበታዊ የፀሃይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ! June 17, 2020 06:38 am
  • የግብፅ የአባይን ውሃ ብቻዬን ልጠቀም ግትር አቋም ድርድር እንቅፋት ሆኗል June 10, 2020 07:15 am
  • የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!? April 12, 2020 02:48 am
  • በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሚጠቀሙበት የኤርትራ ስደተኛ ካምፕ ሊዘጋ ነው March 18, 2020 08:37 pm
  • እየተፈረካከሰ ያለው አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ March 18, 2020 08:09 pm
  • ኮሮና አዲስ ጉድ መዘዘ – ከቻይና በፊት በአሜሪካ ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎችን ቀጥፏል March 16, 2020 11:41 pm
  • የኮንዶሚኒየም ቤቶች በደላሎችና በመመሪያ ሰጪዎች ኔትዎርክ እየተቸበቸበ ነው! ታከለ የት ናቸው? March 9, 2020 10:18 am
  • ኤርሚያስ ለገሠ ከባለአደራ ተባረረ March 9, 2020 08:09 am
  • ድፍድፍ ሲቀል ይንሳፈፋል፤ ምሁር ሲዘቅት ይመራል፥ March 7, 2020 11:24 pm
  • ኢትዮጵያዊ ምን ይመስላል? በምንስ ይመሰላል? March 7, 2020 10:29 pm
  • WHY I WROTE “MONEY, BLOOD AND CONSCIENCE” March 4, 2020 11:15 pm
  • አድዋ፤ የጥቁር ሕዝብ ድል! March 2, 2020 11:24 am
  • ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ (አባ ጎራው) March 2, 2020 11:12 am
  • የኦነግ ሁለት መልክና ሦስት ግብሮች – ቃርሚያው ኃይል ቅጥር ነፍሰገዳይ ሆኗል February 25, 2020 11:26 pm
  • በቡራዩ “የጃል ማሮ” ፎቶ ጨረታ አፈናከተ፤ “ቡራዩ ሆኖ ከሃዲን ማሞካሸት አይቻልም” ነዋሪዎች February 17, 2020 09:13 pm
  • “ዲቃላ” የፍረጃ ፖለቲካ በኦሮሚያ የኃይል አሰላለፉን እየቀየረ ነው February 13, 2020 11:58 pm
  • “ከዚህ በኋላ ማናቸውንም በወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን” አንታገስም – ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ February 13, 2020 05:07 pm
  • “እኛ ማንም ተሳዳቢ እንዲመጣብን አንፈልግም” የጅማ ነዋሪ February 13, 2020 09:28 am
  • “ወላጆቻችሁ ሰላማዊ ሰልፍ በሕዝቡ ያስደርጉልን” – አጋቾች February 11, 2020 07:53 pm
  • “ወንጀል የፈጸመም ያስፈጸመም ተይዞ ለህግ ይቀርባል፤ ምርመራም ተጀምሯል” February 11, 2020 06:59 pm
  • ጃዋር ወደ መጨረሻው “የትግል” ስልቱ – አማራን ማበጣበጥ! February 10, 2020 11:54 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule