በዚህ ሳምንት መጀመሪያ አካባቢ ከጅማ ዞንና ከከተማዋ የተውጣጡ የተለያዩ የማህበረሰብ አካላት የተሳተፉበትና በህዝቦች አብሮነት እሴት ላይ ትኩረቱን አድርጎ በተዘጋጀው መድረክ ላይ ተሳታፊዎች ምን አሉ? የህዝቡን አብሮ የመኖር እሴት የሚሸረሽሩ ተግባራት ተነቅፈዋል። የኦሮሞ ህዝብ በሰላም የመኖር እሴትና አኩሪ ባህል እንዳለው ተብራርቷል። በመሰዳደብ፣ ጥላቻና ነቀፋ ላይ ያተኮሩ ተግባራትን ሊወገዙ እንደሚገባቸው ሀሳብ ተሰጥቷል። ህዝቡን እንወክላለን የሚሉ አካላት እየተፈፀሙ ያሉ የህዝቡን አብሮነት እሴት የሚሸረሽሩ ተግባራት ተወግዘዋል። የተወሰኑ የውይይት ተሳታፊዎች ሀሳብ፦ "ከየትኛውም ብሄርም ይሁን ሃይማኖትም ይሁን ክልል ተንኮል የሚያስብ ሰው የትም አይደርስም። በመሳደብ የሚመጣ ለውጥ የለም።" "አዋቂና ለኦሮሞ ተስፋ ናቸው ከምንላቸው ሰዎች … [Read more...] about “እኛ ማንም ተሳዳቢ እንዲመጣብን አንፈልግም” የጅማ ነዋሪ
“ወላጆቻችሁ ሰላማዊ ሰልፍ በሕዝቡ ያስደርጉልን” – አጋቾች
የሙያው ባለቤቶችና ተመራማሪዎች ታጋቾችን ማስለቀቅ ራሱን የቻለ ታላቅ ጥበብና ስልት ይጠይቃል ይላሉ። የአጋቾችን ስነልቡና ለመስረቅ፣ ለማለስለስ፣ ወዘተ አደራዳሪዎች ፈጽሞ ሊታሰቡ የማይችሉ የሚባሉ ዘዴዎችን ሲጠቀሙ ይስተዋላሉ። የአጋቾቹን ፍቅረኛ ወይም እናት ወይም ሌላ ተወዳጅ የቤተሰብ አባል ወደ ዕገታው ቦታ በማምጣት በድምጽ ማጉያ የተማጽንዖ ቃል እንዲናገሩ ይደረጋሉ። የሃይማኖት መሪዎች፣ ሽማግሌዎች፣ ሌሎች ተጽዕኖና አመኔታ ሊጣልባቸው የሚችሉ ሰዎች በዚህ እንዲሳተፉ ይደረጋል። ይህንና ሌሎች መሰል ተግባራትን በመጠቀም የታገቱት ያለ አንዳች ችግር በነጻ እንዲወጡ ሙከራ ይደረጋል። በዚህም ምክንያት ረጅም ጊዜ የሚወስድ ዕገታ በሰላም የመጠናቀቅ ዕድሉ በጣም ከፍተኛ ነው ይባላል። ማፈን፣ ማገት፣ ሰዎችን ያለፈቃዳቸው በቁጥጥር ሥር ማዋል፣ ወዘተ ያልተለመደ ተግባር … [Read more...] about “ወላጆቻችሁ ሰላማዊ ሰልፍ በሕዝቡ ያስደርጉልን” – አጋቾች
“ወንጀል የፈጸመም ያስፈጸመም ተይዞ ለህግ ይቀርባል፤ ምርመራም ተጀምሯል”
የዚህች ሃገር ችግር የሴራ ፓለቲካ ነው። ጀዋር ሞሃመድ ዛሬ (ሰኞ) ለማየት የሚሰቀጥጥ አንድ ቪዲዮ ለጠፈ። በጣም አንጀት የሚበላ ጥቁርም ሆነ ነጭ ኦሮሞም ሆነ አማራ፤ የሰውን ልጅ እንደዛ በጭካኔ ማሰቃየት ከባድ የሰብዓዊነት ጥሰት ነው። የህግ ተጠያቂነት ደግሞ ግድ ነው፤ ግን ደግሞ ማነው ይህን ወንጀል የፈጸመው? ዋናው ነገር ይህንን ወንጀል የፈጸመውን እና ያስፈጸመውን ለይቶ ለህግ ማቅረብ ነው። ቪዲዮው ልጁ ግፍ ሲፈጸምበት እንጂ ግፍ የፈጸሙትን አያሳይም ለምን ወንጀለኞችን መደበቅ አስፈለገ? ታስቦበት ስለተፈጸመ ነው። በሴራ ከመዘፈቅ ይልቅ ወንጀሉን የፈጸሙትን በማጋለጥ ለህግ የበላይነት መተባበር ነበር። ግን ያንን ትተው ግፍ የተፈጸመበትን በማሳየት ህዝብን ማበሳጨት ነበር የተፈለገ። ወንጀሉን የፈጸመውን በመደበቅ አማራ ኦሮሞን አሰቃየ ማለት የፖለቲካ ሴራ ነው። ነገሩ … [Read more...] about “ወንጀል የፈጸመም ያስፈጸመም ተይዞ ለህግ ይቀርባል፤ ምርመራም ተጀምሯል”
ጃዋር ወደ መጨረሻው “የትግል” ስልቱ – አማራን ማበጣበጥ!
“ወንጀል የፈጸመም ያስፈጸመም ተይዞ ለህግ ይቀርባል” ታዬ “ዲቃላ” በጃዋር ስሌት ዋስትና የሌላቸው ኦሮሞዎች “በዐቢይ ላይ ቁርዓን ይዤ ጅማ እዘምታለሁ” ጃዋር ጃዋር በሁለት ጠርዝ ወደ መጨረሻው ምዕራፍ እየበረረ መሆኑንን የሚያሳዩ ምልክቶች እየታዩ ናቸው። በገሃድ እንደታየው ቤተመንግሥት ለመግባት የተጫኑለትን ስሞች በሙሉ አራግፎ ፖለቲከኛ ሆኗል። ወደ ሥልጣን በሚያደርገው ጉዞ ዋንኛው ዓላማ የተደረገው አማራን ማበጣበጥ ነው። ለዚህም ምኞቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጅማና በመላው ኦሮሚያ እንዲጠሉ ቁርዓን ይዞ ዘመቻ እንደሚያደርግ ይፋ አድርጓል። በተመሳሳይ ደግሞ በጃዋር ጉዳይ መለሳለስ አሳይቷል እየተባለ የሚተቸው መንግሥት የተከማቸውን ፋይል ሊገልጥ ጫፍ መዳረሱን የሚያሳዩ ፍንጮችም ገሃድ እየወጡ ነው። በሌላ በኩል “ዲቃላ” በሚል ጃዋር የሚጠራቸው ኦሮሞዎች ዋስትናቸውን … [Read more...] about ጃዋር ወደ መጨረሻው “የትግል” ስልቱ – አማራን ማበጣበጥ!
“ህወሓት ስለ ብልፅግና ፓርቲ ህጋዊነት አይመለከተውም!” ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ
https://www.youtube.com/watch?v=NIvQXi8NwPo&feature=youtu.be&fbclid=IwAR13D7r_vtAWnyoTUm8e_yaHBwF_-QBrSVp7wJhB0-ezVQNHVrUZFPXecR8 … [Read more...] about “ህወሓት ስለ ብልፅግና ፓርቲ ህጋዊነት አይመለከተውም!” ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ
ለዋዜማ ሬዲዮ – የህዳሴውን ግድብ ዜናችሁን ላስተካክልላችሁ
የውሃ ሃብት ባለሙያ ነኝ፤ የግድቡ ጉዳይ ቀጥታ ከሙያዬ ጋር ባይገናኝም እንደዜጋ ሁኔታውን በቅርብ እከታተላለሁ፤ ፖለቲካንም እንዲሁ። የዋዜማን ሰዎች ዋዜማ ሳትሆኑ ነው የማውቃችሁ፤ ካገር ከመውጣታችሁ በፊት ማለቴ ነው። የማውቃችሁም በግል ሳይሆን እንደማንኛውም የሚዲያ ተጠቃሚ ነው፤ ስለዚህ እናንተ አታውቁኝም። አሁንም ዋዜማን እከታተላለሁ። ከዳያስፖራ ከሚመነጩት የዜና ዘገባዎችና መረጃዎች የእናንተ በተሻለ መጠን ተዓማኒነትና ሥርዓት የያዘ ነው ብዬ ስለማምን አነባችኋለሁ። “ኢትዮጵያን ቋሚ ባለዕዳ የሚያደርገው የህዳሴ ግድብ ስምምነት ላይ መንግስት የመፈረም ፍላጎት እያሳየ ነው” በሚል ርዕስ ያወጣችሁትን ዘገባ አንብቤዋለሁ። ዘገባው እንደሚለው ለረጅም ጊዜ የተጠበቀውን ሰነድ ስምምነት እንድትፈርም ኢትዮጵያ ግፊት እየተደረገባት እንደሆነ፤ ይህም “ኢትዮጵያን ቋሚ የውሀ ባለ እዳ … [Read more...] about ለዋዜማ ሬዲዮ – የህዳሴውን ግድብ ዜናችሁን ላስተካክልላችሁ
ካድሬውና ገጣሚው
ሁለትም ናቸው። በግብ ግን የሚለያቸው የለም። ያን ጊዜ በአካል ላይተዋወቁ ይችሉ ይሆናል። በመንፈስ ግን የአንድ እናት ልጆች ናቸው። ትላንት ገጽ ለገጽ ሳይገናኙ፡ በስምም ሳይተዋወቁ በአንድ ካምፕ ለአንድ ሰፈር ሲጫወቱ ነበር። በመሃል መንገዳቸው ተለያየና በየፊናቸው ህይወትን ቀጠሉ። አንደኛው የህወሀት ቃለቀባይ ስጋጃ አንጣፊ ሆኖ ተከሰተ። ሌላኛው በኪነጥበብና መዝናኛ መድረኮች የጭቃ ውስጥ እሾህ ባህርይ ተላብሶ ብቅ አለ። ነገ እንደሚገናኙ ላያውቁ ይችሉ ይሆናል። አንድ ቀን የመንፈስ ጥምረታቸውን በአካል ተገናኝተው የሚያጠናክሩበት ጊዜ እንደሚኖር ሀገር ቤት ሳሉ ላያውቁት ይችሉም ይሆናል። የባህርይ አምላክ፡ በመንፈስ ያጣመራቸው ጌታ ፍቃድ ሆኖ ግን ሳያውቁት በባህር ማዶ ተገናኙ። በአካልም በመንፈስም ተቀራረቡ። በየግል በልባቸው የተከመረውን የጥላቻና የእኩይ መንፈስ በጋራ … [Read more...] about ካድሬውና ገጣሚው
“የህዳሴ ግድብ ስምምነት ፊርማ እንዲዘገይ አመራር ሰጥቻለሁ” ጠ/ሚ/ር ዐቢይ
ኢትዮጵያን ለማፈራረስ የተገዙ ሌት ከቀን እየደከሙ ነው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕን ጨምሮ ከአደራዳሪዎቹ ጋር በስልክ ከተነጋገሩ በኋላ የህዳሴ ግድብ ስምምነት ፊርማ እንዲዘገይ አመራር መስጠታቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ተናገሩ። ዐቢይ ከትራምፕ ጋር በስልክ መነጋገራቸው ይፋ ከሆነ በኋላ ራሳቸውን ተንታኝ ያደረጉ ወገኖች የስምምነት ፊርማው እንዲፈረም በተደራዳሪዎች ላይ ጫና እንደፈጠሩ በመግለጽ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ሲያጠልሹዋቸው ከርመው ነበር። ዶ/ር ዐቢይ ሰኞ በተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ባደረጉት ጥያቄና መልስ እንደገለጹት የህዳሴውን ግድብ አስመልክቶ የኢትዮጵያን ጥቅም አሳልፎ መስጠትን በተመለከተ የሚደረግ አንድም ዓይነት ስምምነት እንደማይኖር አረጋግጠዋል። ከፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ ከአሜሪካው የገንዘብ ሚኒስትር ስቴፈን ሙኑሺን እና ከዓለም ባንኩ ፕሬዚዳንት … [Read more...] about “የህዳሴ ግድብ ስምምነት ፊርማ እንዲዘገይ አመራር ሰጥቻለሁ” ጠ/ሚ/ር ዐቢይ
ኦፌኮ መጋጨት ጀመረ – ጃዋር በጸሃፊው በኩል የተሳሳተ መረጃ አሰራጨ
ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና እያወቁ ሕግን በመጣስ የወሰኑት ውሳኔ ወደ ሌላ ቀውስ ሊያመራ እንደሚችል ስጋት የገባቸው ወገኖች የተማጽንዖ ጥሪ አቀረቡ። ኦፌኮ ስህተቱን ከማረም ይልቅ እርስ በርስ የሚጣረስ መረጃ ማሰራጨቱ በፓርቲው ውስጥ መለያየት እየፈጠረ መሆኑና ጃዋር ደጋፊዎቹን በጅምላ ወደ አመጽ ለመምራት ዝግጅት እያደረገ መሆኑ ታወቀ። ጸሃፊው ያሰራጩት የተሳሳተ መረጃ በጃዋር መመሪያ ነው። ስጋቱ የተነሳው ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ቀነ ገደብ አስቀምጦ ለኦፌኮ በድጋሚ የላከው የጃዋር ዜግነት ጉዳይን የሚመለከተውን ደብዳቤ ተከትሎ አዲስ “አስተምህሮት” መጀመሩ ነው። ለዚሁ የሕግ ይከበር ጥያቄ ቅድሚያ መልስ የሰጡት ሊቀመንበሩ ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ነበሩ። በምላሻቸው “(ጃዋር) መልኩም ሲታይ ኢትዮጵያዊ ይመስላል” በማለት ስላቅ አዘል መላምት ካስቀመጡ በኋላ ጃዋር መልስ እንዲሰጥበት ደብዳቤው … [Read more...] about ኦፌኮ መጋጨት ጀመረ – ጃዋር በጸሃፊው በኩል የተሳሳተ መረጃ አሰራጨ
ከደምቢዶሎ ከጠፉት 17 ተማሪዎች
° 14’ቱ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች መሆናቸው ° 2 ተማሪዎች በግቢው ውስጥ መኖራቸው ° 2 ተማሪዎች ጎንደር እና ጎጃም ቤተሰቦቻቸው ጋር መመለሳቸው ° 10 ተማሪዎች በፍለጋ ላይ መሆናቸው የተቀሩት ስማቸው እየተጠቀሱ ያሉት ተማሪዎች ግን የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች አይደሉም ተብሏል፡፡ በወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል እና በአቶ ንጉሱ ጥላሁን የተመራ የልዑካን ቡድን ከደምቢዶሎ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ጋር በስፍራው ውይይት እያካሄደ ነው፡፡ በስፍራው የሚገነኘው የኢቢሲ ሪፖርተር የመንግስት ቃል አቀባዩን አቶ ንጉሱ ጥላሁንን እና የዩኒቨርሲቲውን ፕሬዝዳንት አነጋግሯቸዋል፡፡ አቶ ንጉሱ ከዚህ ቀደም ሌሎች 21 ሰዎች ታግተው መለቀቃቸውን በድጋሚ ለኢቢሲ ተናግረዋል፡፡ ከተለያዩ የመንግስት ባለስልጣናት እየተሰጡ ያሉ የተዛቡ መረጃዎችንም በሂደት እያጠራን እንሄዳለን ብለዋል፡፡ … [Read more...] about ከደምቢዶሎ ከጠፉት 17 ተማሪዎች










