ለዚህ ሃሳብ ማብራሪያ የሰጡት የህወሓት ሊቀ መንበርና የትግራይ ክልል መንግሥት ምክትል ርዕስ መስተዳድር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር) ውይይቱ የተናጠል ሳይሆን ሁሉንም አካላት ማካተት እንዳለበት መናገራቸውን ጠቅሷል። "የውውይት መድረክ መፈጠር ካለበት፣ ሁሉም የኢትዮጵያ ፖለቲካ ድርጅቶች፣ ብሔር ብሔረሰቦችን የሚወክሉ ፌደራሊስት ኃይሎች የሚሳተፉበት አገራዊ መድረክ መዘጋጀት አለበት እንጂ ከህወሓት/ትግራይ መንግሥት ጋር በድብቅ የሚደረግ ውይይት አንቀበልም፤ ትርጉምም አያመጣም" ማለታቸውን ቢሮው ገልጿል። ምክትል ርዕሰ መስተዳደሩ "ውይይቱ በመጨረሻ ሰዓት የተጀመረ ቢሆንም መሞከሩ ግን ጥሩ ነው" ያሉ ሲሆን ጨምረውም "የአገሪቱን ችግር ለመፍታት የሚንቀሳቀስ አካል ችግሩ የተፈጠረው ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን በማፍረስ በአገሪቱ አምባገናናዊ ሥርዓት ለመገንባት እየተሯሯጠ በሚገኘው … [Read more...] about አገራዊ መድረክ ውጪ ድብቅ ውይይትን አንቀበልም
Right Column
በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሚጠቀሙበት የኤርትራ ስደተኛ ካምፕ ሊዘጋ ነው
በትግራይ የሚገኘውና 18 ሺሕ ገደማ ኤርትራውያን የሚኖሩበት ሕንፃፅ የስደተኞች መጠለያ ሊዘጋ መሆኑን ስደተኞች ለዶይቼ ቬለ ተናገሩ። በመጠለያው የሚኖሩ በአስር ቀናት ሕንፃጽ መጠለያን እንዲለቁ በኢትዮጵያ ስደተኞች እና ከስደት ተመላሾች ጉዳይ አስተዳደር ባለፈው ሐሙስ ትዕዛዝ እንደተሰጣቸው ለዶይቼ ቬለ አስረድተዋል። በኢትዮጵያ ከሚገኙ ስድስት ኤርትራውያን ስደተኞች ከሚያስተናግዱ መጠለያ ጣብያዎች መካከል አንዱ የሆነው በትግራይ ክልል ሽረ ከተማ አቅራቢያ የሚገኘው ሕንፃፅ የስደተኞች መጠለያ ካምፕ ከሰባት ዓመት በፊት ተቋቁሞ 18 ሺህ ገደማ ኤርትራውያን ስደተኞች እያስተናገደ የሚገኝ ማእከል ነው። በስደተኞች መጠልያ ጣብያው ሕንፃፅ የሚኖሩ ኤርትራውያን እንደሚሉት ባለፈው ዕለተ ሐሙስ ነበር የሚኖሩበት መጠልያ እንደሚዘጋና በአስር ቀናት ውስጥ ቦታ እንዲቀይሩ የተነገራቸው። … [Read more...] about በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሚጠቀሙበት የኤርትራ ስደተኛ ካምፕ ሊዘጋ ነው
ኢትዮጵያዊ ምን ይመስላል? በምንስ ይመሰላል?
የዛሬ ሃምሳ ዓመት ገደማ መሰለኝ የያኔው ወጣት የዩኒቬርሲቲ ተማሪው ኢብሳ ጉተማ “ኢትዮጵያዊው ማን ነው?” በሚል ርዕስ አንድ ጽሁፍ አቅርቦ ለውጥ ፈላጊውን የዩኒቬርሲቲውን ማህበረሰብ ጥም ለማርካት የሞከረው። አብዛኛው የዩኒቨርሲቲው ተማሪ የፊውዳል ሥርዓቱ አገሪቷን ወደፊት እንዳትራመድ ጠፍንጎ የያዛት መሆኑን የተረዱና ሥርዓቱ ካልተለወጠ የሕዝቦቿ አብሮነት ውሎ አድሮ መሸረሸሩ አይቀሬ መሆኑን ተገንዝበው ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን ለማናበብ መላ ይመቱ ነበርና የዚህ ንቁ ተማሪ ግጥም ጊዜውን ጠብቆ የመጣ ነበር። በዚሁ ጊዜ ነበር ከተማሪው እንቅስቃሴ መሪዎች አንዱ የነበረው ዋለልኝ መኮንን የብሄር ጥያቄን አስመልክቶ ታሪካዊውን ጽሁፍ ያቀረበው። አንዳንዶች ያኔም ሆነ ዛሬ እነዚህን ጽሁፎችን አስመልክቶ ሁለቱን ንቁ የተማሪው ማህበረሰብ አባላትን አገሪቷን ለመበታተን ሆን ብለው … [Read more...] about ኢትዮጵያዊ ምን ይመስላል? በምንስ ይመሰላል?
“ዲቃላ” የፍረጃ ፖለቲካ በኦሮሚያ የኃይል አሰላለፉን እየቀየረ ነው
በኦሮሚያ ክልል አዲስ የተነሳው የፍረጃ ፖለቲካ የኃይል አሰላለፉን እንደቀየረና በርካታ የክልሉን ተወላጆች እያሳሰበ መሆኑ ተገለጸ። አካሄዱ ወደ ዘር ማጽዳት ለሚደረገው ድብቅ ጉዞ አመላክች ተደርጎ ሊወሰድ እንደሚችል አስተያየት እየተሰጠ ነው። ሲጀመር “ዲቃላ” የሚለው ፍረጃ በድንገት የተሰነዘረው የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይን ስም በማንሳት ነው ቢባልም አቶ በቀለ ገርባ ቀደም ብለው ለዚህ አካሄድ ፍንጭ መስጠታቸውን ስጋት የገባቸው ለጎልጉል እንደመነሻ ያነሱታል። “ከሌሎች ብሔረሰቦች ጋር አትጋቡ፣ አትነግዱ” ሲሉ ዲስኩር ያደረጉት አቶ በቀለ ገርባ ይህ ንግግራቸው በወቀቱ ከፍተኛ ተቃውሞ አስነስቶባቸው እንደነበር ያወሱት እነዚህ ክፍሎች፣ ይህንኑ መርዘኛ ቅስቀሳ ለማስተባበል ጃዋር መሐመድ የሚመራቸው ሚዲያዎች በዘመቻ መልክ መትጋታቸውን ያክላሉ። በወቅቱ በፕሮፓጋንዳ ብዛት ነገሩ … [Read more...] about “ዲቃላ” የፍረጃ ፖለቲካ በኦሮሚያ የኃይል አሰላለፉን እየቀየረ ነው
“ከዚህ በኋላ ማናቸውንም በወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን” አንታገስም – ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ
“በየቦታው የሚፈጠሩ የወንጀል ድርጊቶች ዋነኛ ችግር የፖለቲካ አመራሮች እጅ” አለበት ጠቅላይ አቃቤ ሕግ በኢትዮጵያ የሕግ የበላይነትን ለማስከበር የተወሰዱ እና ሊወሰዱ ይገባቸዋል ስላላቸው እርምጃዎች የካቲት 5፣ 2012 መግለጫ አውጥቷል። በየቦታው የሚፈጠሩ የወንጀል ድርጊቶች ዋነኛ ችግር የፖለቲካ አመራሮች እጅ እንዳለበት የገለጸው መግለጫ ለሀገሪቱ ደህንነትና ለህዝቡ ህልውና ሲባል ከዚህ በኋላ ማናቸውንም በወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን እንደማይታገስ አቋም መያዙን ይፋ አድርጓል። የመግለጫው ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፦ ከኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የተሰጠ መግለጫ የሕግ የበላይነትን ማስከበር ለድርድር የሚቀርብ ጉዳይ አይደለም የኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የፍትህ ስርዓቱን የማጠናከርና የህግ የበላይነትን የማክበርና የማስከበር ተግባሩን … [Read more...] about “ከዚህ በኋላ ማናቸውንም በወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን” አንታገስም – ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ
“ወላጆቻችሁ ሰላማዊ ሰልፍ በሕዝቡ ያስደርጉልን” – አጋቾች
የሙያው ባለቤቶችና ተመራማሪዎች ታጋቾችን ማስለቀቅ ራሱን የቻለ ታላቅ ጥበብና ስልት ይጠይቃል ይላሉ። የአጋቾችን ስነልቡና ለመስረቅ፣ ለማለስለስ፣ ወዘተ አደራዳሪዎች ፈጽሞ ሊታሰቡ የማይችሉ የሚባሉ ዘዴዎችን ሲጠቀሙ ይስተዋላሉ። የአጋቾቹን ፍቅረኛ ወይም እናት ወይም ሌላ ተወዳጅ የቤተሰብ አባል ወደ ዕገታው ቦታ በማምጣት በድምጽ ማጉያ የተማጽንዖ ቃል እንዲናገሩ ይደረጋሉ። የሃይማኖት መሪዎች፣ ሽማግሌዎች፣ ሌሎች ተጽዕኖና አመኔታ ሊጣልባቸው የሚችሉ ሰዎች በዚህ እንዲሳተፉ ይደረጋል። ይህንና ሌሎች መሰል ተግባራትን በመጠቀም የታገቱት ያለ አንዳች ችግር በነጻ እንዲወጡ ሙከራ ይደረጋል። በዚህም ምክንያት ረጅም ጊዜ የሚወስድ ዕገታ በሰላም የመጠናቀቅ ዕድሉ በጣም ከፍተኛ ነው ይባላል። ማፈን፣ ማገት፣ ሰዎችን ያለፈቃዳቸው በቁጥጥር ሥር ማዋል፣ ወዘተ ያልተለመደ ተግባር … [Read more...] about “ወላጆቻችሁ ሰላማዊ ሰልፍ በሕዝቡ ያስደርጉልን” – አጋቾች
ጃዋር ወደ መጨረሻው “የትግል” ስልቱ – አማራን ማበጣበጥ!
“ወንጀል የፈጸመም ያስፈጸመም ተይዞ ለህግ ይቀርባል” ታዬ “ዲቃላ” በጃዋር ስሌት ዋስትና የሌላቸው ኦሮሞዎች “በዐቢይ ላይ ቁርዓን ይዤ ጅማ እዘምታለሁ” ጃዋር ጃዋር በሁለት ጠርዝ ወደ መጨረሻው ምዕራፍ እየበረረ መሆኑንን የሚያሳዩ ምልክቶች እየታዩ ናቸው። በገሃድ እንደታየው ቤተመንግሥት ለመግባት የተጫኑለትን ስሞች በሙሉ አራግፎ ፖለቲከኛ ሆኗል። ወደ ሥልጣን በሚያደርገው ጉዞ ዋንኛው ዓላማ የተደረገው አማራን ማበጣበጥ ነው። ለዚህም ምኞቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጅማና በመላው ኦሮሚያ እንዲጠሉ ቁርዓን ይዞ ዘመቻ እንደሚያደርግ ይፋ አድርጓል። በተመሳሳይ ደግሞ በጃዋር ጉዳይ መለሳለስ አሳይቷል እየተባለ የሚተቸው መንግሥት የተከማቸውን ፋይል ሊገልጥ ጫፍ መዳረሱን የሚያሳዩ ፍንጮችም ገሃድ እየወጡ ነው። በሌላ በኩል “ዲቃላ” በሚል ጃዋር የሚጠራቸው ኦሮሞዎች ዋስትናቸውን … [Read more...] about ጃዋር ወደ መጨረሻው “የትግል” ስልቱ – አማራን ማበጣበጥ!
“ህወሓት ስለ ብልፅግና ፓርቲ ህጋዊነት አይመለከተውም!” ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ
https://www.youtube.com/watch?v=NIvQXi8NwPo&feature=youtu.be&fbclid=IwAR13D7r_vtAWnyoTUm8e_yaHBwF_-QBrSVp7wJhB0-ezVQNHVrUZFPXecR8 … [Read more...] about “ህወሓት ስለ ብልፅግና ፓርቲ ህጋዊነት አይመለከተውም!” ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ
ካድሬውና ገጣሚው
ሁለትም ናቸው። በግብ ግን የሚለያቸው የለም። ያን ጊዜ በአካል ላይተዋወቁ ይችሉ ይሆናል። በመንፈስ ግን የአንድ እናት ልጆች ናቸው። ትላንት ገጽ ለገጽ ሳይገናኙ፡ በስምም ሳይተዋወቁ በአንድ ካምፕ ለአንድ ሰፈር ሲጫወቱ ነበር። በመሃል መንገዳቸው ተለያየና በየፊናቸው ህይወትን ቀጠሉ። አንደኛው የህወሀት ቃለቀባይ ስጋጃ አንጣፊ ሆኖ ተከሰተ። ሌላኛው በኪነጥበብና መዝናኛ መድረኮች የጭቃ ውስጥ እሾህ ባህርይ ተላብሶ ብቅ አለ። ነገ እንደሚገናኙ ላያውቁ ይችሉ ይሆናል። አንድ ቀን የመንፈስ ጥምረታቸውን በአካል ተገናኝተው የሚያጠናክሩበት ጊዜ እንደሚኖር ሀገር ቤት ሳሉ ላያውቁት ይችሉም ይሆናል። የባህርይ አምላክ፡ በመንፈስ ያጣመራቸው ጌታ ፍቃድ ሆኖ ግን ሳያውቁት በባህር ማዶ ተገናኙ። በአካልም በመንፈስም ተቀራረቡ። በየግል በልባቸው የተከመረውን የጥላቻና የእኩይ መንፈስ በጋራ … [Read more...] about ካድሬውና ገጣሚው
“የህዳሴ ግድብ ስምምነት ፊርማ እንዲዘገይ አመራር ሰጥቻለሁ” ጠ/ሚ/ር ዐቢይ
ኢትዮጵያን ለማፈራረስ የተገዙ ሌት ከቀን እየደከሙ ነው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕን ጨምሮ ከአደራዳሪዎቹ ጋር በስልክ ከተነጋገሩ በኋላ የህዳሴ ግድብ ስምምነት ፊርማ እንዲዘገይ አመራር መስጠታቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ተናገሩ። ዐቢይ ከትራምፕ ጋር በስልክ መነጋገራቸው ይፋ ከሆነ በኋላ ራሳቸውን ተንታኝ ያደረጉ ወገኖች የስምምነት ፊርማው እንዲፈረም በተደራዳሪዎች ላይ ጫና እንደፈጠሩ በመግለጽ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ሲያጠልሹዋቸው ከርመው ነበር። ዶ/ር ዐቢይ ሰኞ በተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ባደረጉት ጥያቄና መልስ እንደገለጹት የህዳሴውን ግድብ አስመልክቶ የኢትዮጵያን ጥቅም አሳልፎ መስጠትን በተመለከተ የሚደረግ አንድም ዓይነት ስምምነት እንደማይኖር አረጋግጠዋል። ከፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ ከአሜሪካው የገንዘብ ሚኒስትር ስቴፈን ሙኑሺን እና ከዓለም ባንኩ ፕሬዚዳንት … [Read more...] about “የህዳሴ ግድብ ስምምነት ፊርማ እንዲዘገይ አመራር ሰጥቻለሁ” ጠ/ሚ/ር ዐቢይ










