• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ለዋዜማ ሬዲዮ – የህዳሴውን ግድብ ዜናችሁን ላስተካክልላችሁ

February 6, 2020 01:19 am by Editor 2 Comments

የውሃ ሃብት ባለሙያ ነኝ፤ የግድቡ ጉዳይ ቀጥታ ከሙያዬ ጋር ባይገናኝም እንደዜጋ ሁኔታውን በቅርብ እከታተላለሁ፤ ፖለቲካንም እንዲሁ። የዋዜማን ሰዎች ዋዜማ ሳትሆኑ ነው የማውቃችሁ፤ ካገር ከመውጣታችሁ በፊት ማለቴ ነው። የማውቃችሁም በግል ሳይሆን እንደማንኛውም የሚዲያ ተጠቃሚ ነው፤ ስለዚህ እናንተ አታውቁኝም። አሁንም ዋዜማን እከታተላለሁ። ከዳያስፖራ ከሚመነጩት የዜና ዘገባዎችና መረጃዎች የእናንተ በተሻለ መጠን ተዓማኒነትና ሥርዓት የያዘ ነው ብዬ ስለማምን አነባችኋለሁ።

“ኢትዮጵያን ቋሚ ባለዕዳ የሚያደርገው የህዳሴ ግድብ ስምምነት ላይ መንግስት የመፈረም ፍላጎት እያሳየ ነው” በሚል ርዕስ ያወጣችሁትን ዘገባ አንብቤዋለሁ። ዘገባው እንደሚለው ለረጅም ጊዜ የተጠበቀውን ሰነድ ስምምነት እንድትፈርም ኢትዮጵያ ግፊት እየተደረገባት እንደሆነ፤ ይህም “ኢትዮጵያን ቋሚ የውሀ ባለ እዳ የሚያደርግ መሆኑን”፤ ረቂቅ ሰነዱ እጃችሁ እንደገባ፤ ፕሬዚዳንት ትራምፕ ጠ/ሚ/ር ዐቢይ ላይ ተጽዕኖ እያደረጉባቸው እንደሆነ፣ ኢትዮጵያ ካልፈረመች ከአሜሪካ የምታገኘው ድጋፍ መስተጓጎል እንደሚገጥመው ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ “በገደምዳሜ መጠቆማቸው” በእናንት በኩል ግምት እንዳለ፣ ወዘተ የሚያትት ነው።

ዜናው መረጃ የሚያስተላለፍ መሆን ሲገባው ግምት፣ መላምት፣ ጠማማነትና ምኞትን የሚገልጽ ሆኖ አግኝቼዋለሁ። ከዚህ ይልቅ ግን የዘነጋው አንድ ትልቅ እውነታ አለ – ጠ/ሚ/ር ዐቢይ ስምምነቱ እንዳይፈረም መመሪያ ስለመስጠታቸው ነው።

ሰኞ ዕለት ጠ/ሚ/ር ዐቢይ በተወካዮች ም/ቤት በኩል ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ባስተላለፉት መልዕክት ላይ “የህዳሴ ግድብ ስምምነት ፊርማ እንዲዘገይ አመራር ሰጥቻለሁ” ብለዋል። ዶ/ር ዐቢይ ረቂቁን ተመለከቱ፣ የትራምፕን፣ የዓለም ባንክ ፕሬዚዳንት እና የአሜሪካውን የገንዘብ ሚ/ር አነጋገሩ፤ ፍላጎታቸው ምን እንደሆነ በስልክ ንግግራቸው ተረዱ፤ ረቂቁ እንዳይፈረም ትዕዛዝ ሰጡ። እንዲያውም በውጭ አገር ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች የሚሰጣቸው የሙያ ምክር ጠቃሚ መሆኑን በመጥቀስ ምስጋና ሁሉ አቅርበው ነበር። ይህ ሊያስመሰግናቸውና እናንተም ባወጣችሁት ጽሁፍ መግለጽ የሚገባችሁ ነበር። የኢትዮጵያን ጥቅም አሳልፈን አንሰጥም ነው ያሉት!

የውሃ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትራችን ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺም ረቡዕ ዕለት ለሚዲያ ሰዎች ሲናገሩ “በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ በሚደረገው ስምምነት የኢትዮጵያን በወንዙ የመጠቀም መብት በዘላቂነት በማያስጠብቅ ሁኔታ አንድም ቃል ከተካተተ ኢትዮጵያ” አትፈርምም ነው ያሉት። ይህንንም ጨምረዋል፤ “የግድቡ የውኃ ሙሌትና አለቃቀቅን በሚመለከት ውይይት የተደረገ ሲሆን፥ በተለይም ድርቅ በሚከሰትበት ወቅት የሦስቱን ሀገራት ጥቅም በሚያስጠብቅ መልኩ ተካሂዷል” ነው ያሉት። መቼም ዐቢይን ባታምኗቸው ዶ/ር ስለሺን የምትጠራጠሯቸው አይመስለኝም።

ይህ ሁሉ እውነታ እያለ ኢትዮጵያን ባለዕዳ የሚያደርግ ስምምነት ሊፈረም ነው ብሎ መናገሩ የሚዲያችሁን ተዓማኒነት ትልቅ ጥያቄ ላይ ጥሎታል፤ በተለይ ለእኔ። ሌሎቹንም ዘገባዎቻችሁን በጥንቃቄና በዓይነቁራኛ እንዳነብ ያስገደደኝ ሆኗል። በተለይ እናንተ ከለውጡ ጋር በተያያዘ በአገር በቀል መፍትሔ ፍለጋ ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ እያደረጋችሁ ያላችሁ በዚህ መልኩ ይህንን ዘገባ ማውጣታችሁ “ውይ እንደነ እንትና ዋዜማም …” አስብሎኛል። ልድገመውና – ረቂቁ አልተፈረምም፤ እንዳይፈረም ዶ/ር ዐቢይ ትዕዛዝ ሰጥተዋል። እንደ መሪ ይህ ትክክለኛና ተጠቃሽ ተግባር ነው።

እናንተ በዘገባችሁ ሌላው ያከላችሁት ነገር ኢትዮጵያ ተጽዕኖ እየተደረገባት ነው፤ እነ ዶ/ር ዐቢይም ሊፈርሙ እየተዘጋጁ ነው የሚል ነው። ለዚህም ያቀረባችሁት መላምት ኢትዮጵያ ካልፈረመች አሜሪካ የምትሰጠውን ዕርዳታ መያዣ አድርጋባታለች የሚል ነው። ሌላውና ውሃ የማይቋጥረው መላምታችሁ ትራምፕ ለፍልስጤምና እስራኤል ያቀረቡት የሰላም ሃሳብ “በመላው የዓረቡ አለም ተቀባይነት ባለማግኘቱ” ግብጽ የአረቡ ዓለም ተጽዕኖ ፈጣሪ በመሆኗ ይህንን ሰነድ አረቡ ዓለም እንዲቀበል ካግባባች “(ለ)ውለታዋ የህዳሴ ግድብ እንደ እጅ መንሻ” እንደቀረበላት ነው።

ይህንን በጣም የወረደ አመክንዮ ሆኖ አግኝቼዋለሁ። ሲጀመር የትራምፕን የሰላም ዕቅድ “መላው የዓረቡ አለም” አልተቃወመውም። ሳዑዲ አረቢያ፣ አረብ ኤሜሬትስ፣ ግብጽ፣ ኳታርና ሞሮኮ ከአዎንታዊ አስተያየት እስከ ጥንቃቄ የተሞላበት ድጋፍ ሰጥተዋል። በተለይ ሳዑዲ አረቢያ ከመቼውም በተለየ መልኩ እስራኤልን በመደገፍ መቆሟ አነጋጋሪ ጉዳይ ሆኗል።

ሌላውና ዋንኛው ነጥብ በዚህ የፍልስጤም ተወካይ ወይም መሃሙድ አባስ በሌሎበት ትራምፕና የእስራኤሉ ጠ/ሚ/ር ኔታንያሁ ብቻቸውን ይፋ ያደረጉት “ፕላን” ፍልስጤምን ታሳቢ ያላደረገ የፖለቲካ ቁማር ነው። ኔታኒያሁ ከሙስና እና ማጭበርበር ጋር በተያያዘ ትልቅ ክስ ተመሥርቶባቸው ግራ ገብቷቸዋል። ወር ባነሰ ጊዜ ውስጥ ደግሞ አገር አቀፍ ምርጫ ይጠብቃቸዋል። ለሕዝባቸው “የሚሸጡት” የምርጫ ሸቀጥ ያስፈልጋቸዋል። ለዚህም ደግሞ እስራኤልን በጭፍን ከሚደግፍ ፕላን የተሻለ አይኖርም።  

ትራምፕ በዩክሬይን ጉዳይ ከፍተኛ ቅሌት ገጥሟቸው የውጭ ጉዳይ አመራር ላይ ዜሮ ናቸው የሚለው ቁጥር የጨመረበት ወቅት ላይ ናቸው። እጅግ ውስብስብ የሆነውን የፍልስጤምና እስራኤል ጉዳይ ለመፍታት ከመድፈር አልፎ የሰላም ዕቅድ ይዘው ብቅ ማለታቸው የውጭ ጉዳይ ፖለቲካ ላይ በሳል ናቸው ከማስባል ባለፈ ለዚህ ዓመቱ (የፈረንጆች) የአሜሪካ ምርጫ ጥሩ ደጋፊ እንዲያስገኝላቸው ታልሞ የተሠራ ነው። እሳቸውም የራሳቸውን ዕቅድ “የክፍለዘመኑ ስምምነት” በማለት የጠሩት ያለምክንያት አይደለም።

ሌላው ቢቢሲ እንደዘገበው ይህ ዕቅድ ለትራምፕ የዚህ ዓመት ምርጫ ትልቅ ድጋፍ የሚያሰጣቸው ነው፤ በተለይ በ2016ቱ ምርጫ በጭፍን ለደገፏቸው የኢቫንጀሊካል (ወንጌላውያን) ክርስቲያኖች። እነዚህ ኢቫንጀሊካሎች ለእስራኤል ጭፍን ድጋፍ ያላቸው ከመሆን በተጨማሪ ለትራምፕ ምርጫ ትልቅ የገንዘብ ድጋፍ አድራጊዎችም ናቸው። ያለፈውን ዓይነት ድጋፍ በዚህኛው የምርጫ ዘመቻ ለማግኘት ይህንን መሰሉ የመካከለኛው ምስራቅ ዕቅድ ማውጣት ወሳኝ ነው። በዚህ ላይ የትራምፕ ምክትል ማይክ ፔንስና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ማይክ ፖምፔዎ ተጠቃሽ ኢቫንጀሊካል ናቸው።

ይህ የፖለቲካ ጥቅም ከማስገኘት ያላለፈ ምኞት ያለውንና ፍልስጤምን ያላሳተፈ ዕቅድ የተቃወሙትን አረብ አገራት ለማሳመን ከግብጽ ይልቅ ባልተለመደ ሁኔታ ለእስራኤል ልዩ ድጋፍ እያደረገች ያለችውና ዕቅዱን የደገፈችው ሳዑዲ አረቢያ የተሻለችና ዋንኛ ተመራጭ ነች።

ለማንኛውም እናንተ እጃችን ገብቷል ያላችሁትን ረቂቅ፥ የስምምነት ሰነድ ሆኖ እንዳይፈረም ጠ/ሚ/ር ዐቢይ መመሪያ ሰጥተውበታል። ይህ መጠቀስ የሚገባው ትልቅ ሥራ ነው። ዕቅዱን የተቃወሙትን የአረብ አገራት ለማሳመን ግብጽ የተሻለች ነች፤ ይህንንም ካደረገች የአባይን ግድብ ስምምነት እሷን እንዲጠቅም ተደርጎ እንዲወሰን ይደረጋል የሚለውም የዓለምን በተለይም የአሜሪካንና የመካከለኛው ምስራቅ ፖለቲካ ያላገናዘበ ስንኩል “ትንታኔ” ነው።

ዋዜማዎች እንደ አንዳንድ ስም አይጠሬ ጭፍን ሚዲያ እንዳትሆኑ ተጠንቀቁ። ውሃ ሲወስድ እያሳሳቀ ነው።

ባለሙያው ነኝ       


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው።

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Left Column, Opinions Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Comments

  1. Segel says

    February 6, 2020 06:20 pm at 6:20 pm

    (ፕሬዚዳንት ትራምፕ ጠ/ሚ/ር ዐቢይ ላይ ተጽዕኖ እያደረጉባቸው እንደሆነ፣ ኢትዮጵያ ካልፈረመች ከአሜሪካ የምታገኘው ድጋፍ መስተጓጎል እንደሚገጥመው ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ “በገደምዳሜ”…) Hahaha ?
    Quid pro quo

    Reply
  2. ተፈራ says

    February 8, 2020 12:40 am at 12:40 am

    ከዚህ ከላይ ከተቀመጠው መቃወሚያ በሁዋላ የዋዜማ አቋም ወይም ምላሽ ምን እንደሆነ ባልረዳም የሁሉንም ወገን ሃሳብ ሳነብ የታየኝና የገባኝ አንድ ጉዳይ ቢኖር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባገዱት ወይም ፊርማ እንዳይፈረም ካዘዙ በራሱ የዜናው አስፈላጊነት በዜና ደረጃ መሆን ያለበት አይመስለኝም። ምክንያቱም ዋዜማ አገኘሁት ያለው ሰነድ ነው ፊርማ እንዳይኖርበት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያስቆሙት። ስለዚህ ባደባባይ፣ ህዝብ እየሰማ፣ ዲፕሎማቶችና የውጭ አገር ሚዲያዎች እየቀዱት፣ ግብጾች እየሰሙ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ” እንዳትፈርሙ” ካሉ ሌላ ተከላካይ ጠበቃ የሚያሻቸው አይሆንም።
    እንደ መሪ አቋም ወስደዋል። እንደ መሪ የወሰዱትን አቋም ለፓርላማና ለህዝብ ገልጠዋል። እንደ መሪ ቃል የገቡትን የኢትዮጵያን ጥቅም ማስጠበቅቃቸውን አረጋግጠዋል። ታዲያ እኝህ ሰው በዚህ ጉዳይ ላይ መመሪያ ሰጡ፣ ቃላቸውን ጠበቁ፣ መመሪያ ሰጡ በሚል ቃላቸውና ተጋባራቸው ተጠቅሶ ዜናው መሰራት ሲገባው እሳቸው የተቃወሙትንና መመሪያ በመስጠት ያስቆሙትን የድርድር ሃሳብ አስመልክቶ እንዴት ሰይፍ ይመዘዝባቸዋል?
    ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ አገራቸውን ለማገልገል ትልቅ ክፍያና ኑሮ ጥለው ወደ አገራቸው የገቡ ድንቅ ባለሙያ፣ አገር ወዳድና ባለ መልካም ተሞክሮ መሆናቸውን የሚያውቋቸው ይመሰክራሉ። እሳቸውና ቲማቸው ይህንኑ በተደጋጋሚ ያረጋግጣሉ። እናም እኚህንም ሰው .…

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጃዋርና በቀለ መታሠራቸው ተሰማ June 30, 2020 09:17 am
  • አገራዊ መድረክ ውጪ ድብቅ ውይይትን አንቀበልም June 17, 2020 06:57 am
  • ዴክሳሜታሶን! የኮሮና መድሀኒት June 17, 2020 06:49 am
  • የሰኔ 14ቱ ቀለበታዊ የፀሃይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ! June 17, 2020 06:38 am
  • የግብፅ የአባይን ውሃ ብቻዬን ልጠቀም ግትር አቋም ድርድር እንቅፋት ሆኗል June 10, 2020 07:15 am
  • የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!? April 12, 2020 02:48 am
  • በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሚጠቀሙበት የኤርትራ ስደተኛ ካምፕ ሊዘጋ ነው March 18, 2020 08:37 pm
  • እየተፈረካከሰ ያለው አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ March 18, 2020 08:09 pm
  • ኮሮና አዲስ ጉድ መዘዘ – ከቻይና በፊት በአሜሪካ ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎችን ቀጥፏል March 16, 2020 11:41 pm
  • የኮንዶሚኒየም ቤቶች በደላሎችና በመመሪያ ሰጪዎች ኔትዎርክ እየተቸበቸበ ነው! ታከለ የት ናቸው? March 9, 2020 10:18 am
  • ኤርሚያስ ለገሠ ከባለአደራ ተባረረ March 9, 2020 08:09 am
  • ድፍድፍ ሲቀል ይንሳፈፋል፤ ምሁር ሲዘቅት ይመራል፥ March 7, 2020 11:24 pm
  • ኢትዮጵያዊ ምን ይመስላል? በምንስ ይመሰላል? March 7, 2020 10:29 pm
  • WHY I WROTE “MONEY, BLOOD AND CONSCIENCE” March 4, 2020 11:15 pm
  • አድዋ፤ የጥቁር ሕዝብ ድል! March 2, 2020 11:24 am
  • ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ (አባ ጎራው) March 2, 2020 11:12 am
  • የኦነግ ሁለት መልክና ሦስት ግብሮች – ቃርሚያው ኃይል ቅጥር ነፍሰገዳይ ሆኗል February 25, 2020 11:26 pm
  • በቡራዩ “የጃል ማሮ” ፎቶ ጨረታ አፈናከተ፤ “ቡራዩ ሆኖ ከሃዲን ማሞካሸት አይቻልም” ነዋሪዎች February 17, 2020 09:13 pm
  • “ዲቃላ” የፍረጃ ፖለቲካ በኦሮሚያ የኃይል አሰላለፉን እየቀየረ ነው February 13, 2020 11:58 pm
  • “ከዚህ በኋላ ማናቸውንም በወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን” አንታገስም – ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ February 13, 2020 05:07 pm
  • “እኛ ማንም ተሳዳቢ እንዲመጣብን አንፈልግም” የጅማ ነዋሪ February 13, 2020 09:28 am
  • “ወላጆቻችሁ ሰላማዊ ሰልፍ በሕዝቡ ያስደርጉልን” – አጋቾች February 11, 2020 07:53 pm
  • “ወንጀል የፈጸመም ያስፈጸመም ተይዞ ለህግ ይቀርባል፤ ምርመራም ተጀምሯል” February 11, 2020 06:59 pm
  • ጃዋር ወደ መጨረሻው “የትግል” ስልቱ – አማራን ማበጣበጥ! February 10, 2020 11:54 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule