• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ካድሬውና ገጣሚው

February 5, 2020 10:30 am by Editor 1 Comment

ሁለትም ናቸው። በግብ ግን የሚለያቸው የለም። ያን ጊዜ በአካል ላይተዋወቁ ይችሉ ይሆናል። በመንፈስ ግን የአንድ እናት ልጆች ናቸው። ትላንት ገጽ ለገጽ ሳይገናኙ፡ በስምም ሳይተዋወቁ በአንድ ካምፕ ለአንድ ሰፈር ሲጫወቱ ነበር። በመሃል መንገዳቸው ተለያየና በየፊናቸው ህይወትን ቀጠሉ። አንደኛው የህወሀት ቃለቀባይ ስጋጃ አንጣፊ ሆኖ ተከሰተ። ሌላኛው በኪነጥበብና መዝናኛ መድረኮች የጭቃ ውስጥ እሾህ ባህርይ ተላብሶ ብቅ አለ። ነገ እንደሚገናኙ ላያውቁ ይችሉ ይሆናል።

አንድ ቀን የመንፈስ ጥምረታቸውን በአካል ተገናኝተው የሚያጠናክሩበት ጊዜ እንደሚኖር ሀገር ቤት ሳሉ ላያውቁት ይችሉም ይሆናል። የባህርይ አምላክ፡ በመንፈስ ያጣመራቸው ጌታ ፍቃድ ሆኖ ግን ሳያውቁት በባህር ማዶ ተገናኙ። በአካልም በመንፈስም ተቀራረቡ። በየግል በልባቸው የተከመረውን የጥላቻና የእኩይ መንፈስ በጋራ የሚያራግቡበት፡ ትላንት ሳይተዋወቁ ለተሰለፉበት ክፉ ዓላማ ከግብ መድረስ በአንድነት የሚሰሩበት መድረክ ተመቻቸላቸው። ማን ያውቃል? ይህ ይሆን ዘንድ ቀድሞ የታቀደ ቢሆንስ? መጠርጠሩ አይከፋም።

ከሚለያያቸው ይልቅ የሚያመሳስላቸው ነገሮች ብዙ ናቸው። የባህርይ ጥምረታቸው መንታ አስመስሏቸዋል። ሲበዛ ክፉዎች ናቸው። ከሞላው ይልቅ የጎደለው የሚታያቸው፡ ከፍቅር ይልቅ ጥላቻ የሚቀናቸው፡ የሰላሙ መንገድ የሚጎረብጣቸው፡ ለቀውስና ብጥብጥ አእምሮአቸው የሚፈጥንባቸው፡ ህይወትን ከሴራ ትብታብ ውጪ ለማየት ፈጣሪ ያላደላቸው፡ ከብርሃን ይልቅ የጨለማው እድምተኛ መሆንን የመረጡ፡ አንድነት ሲኖር የሚነስራቸው፡ የልዩነት ዜማ ከአንደበታቸው የማይጠፋ በጥቅሉ እኩይ ባህሪያትና መንፈሶች ጓዛቸውን ጠቅልለው በልባቸው ቤት የሰሩባቸው የክፉዎች ሁሉ ክፉ ናቸው። ለራሳቸው ያላቸው ፍቅር የትየለሌ ነው። በራስ ፍቅር ጨርቃቸውን ጥለው ሊያብዱ የደረሱ፡ በጋጠወጥ ባህሪያቸው የሚኮሩ፡ ባልተገራ አንደበታቸው የሚመጻደቁ፡ ገብረገብ በራቀው ማንነታቸው የሚኮፈሱ፡ ሰው ሰው አለመሽተትን የስኬቶች ሁሉ ስኬት አድርገው የሚዘባነኑ የትውልድ እርግማኖች ናቸው። ኤርሚያስ ለገሰና ቴዎድሮስ ጸጋዬ።

ከሰሞኑ እፍ ያለ ፍቅር ውስጥ ናቸው። በአንድ ቂጥ ካልፈሳን ዓይነት ጥምረታቸውን ይዘው ብቅ ብለዋል። በመሃላችን ንፋስ እንኳን አይግባ ሲሉም አንድም ሁለትነታቸውን እያስተዋወቁ ነው። ስለአንድ ዓላማ የተሰለፉ ሁለት ሚዲያዎችን ይቆጣጠራሉ። በአንደኛው የጀመሩትን የጥላቻ ስብከት በሌላኛው ሚዲያ መቋጨት የየዕለት ስራቸው አድርገውታል። የዩቲዩብ ዘመን ነውና ሽቀላው ጦፎላቸዋል። ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ተጎልቶ ለሚጠብቃቸው ግሪሳ የሚሆን የወሬ ቀለብ እያመረቱ በየቀኑ ብቅ ይላሉ። መቆሚያ የሌለው የጥላቻ ስብከታቸው፡ ሉጋም ያጣው የሴራ ትርክታቸው፡ መጨረሻው የማይታወቅ የውሸት ዲስኩራቸው በግሪሳው ተከታያቸው ዘንድ ክብርና ሞገስን አስገኝቶላቸዋል።

ትላንት የተናገሩትን ትተው በአዲስ መስመር አዲስ ታሪክ ሲናገሩ የማይጠይቃቸው መንጋ አላቸው። ዶ/ር አብይና ጃዋር መሀመድ አንድ ናቸው ብለው በተናገሩ ማግስት አንድ አለመሆናቸው ሲረጋገጥ ምነው ዋሻችሁን ብለው የሚይዛችው የለም። ዶ/ር አብይና አቶ ለማ መገርሳ የሚለያቸው ምንም ነገር የለም ሲሉ ከርመው ሁለቱ ሰዎች መንገዳቸው ለየቅል መሆኑ በአደባባይ ሲገለጥ ‘’አሁንስ አበዛችሁት’’ የሚላቸው ወዳጅ ከአጠገባቸው አይገኝም። ውሸታቸውንም፡ ቅጥፈታቸውንም እያላመጠ በሚውጥ ግሪሳ ተከበዋልና ነገም ከዚህ የተወላገደ መስመር የሚመልሳቸው አይኖርም። ፈጣሪ ከሰማይ ወርዶ ካልታረቃቸው በቀር።

እውነት ለመናገር እነዚህን ሁለት የአንድ መንፈስ ልጆች ሁኔታ ሳጤን አስተዳደጋቸው እንዴት ይሆን የሚል ጥያቄ ይጭርብኛል። እንደኛ ተቆንጥጠው አላደጉ ይሆን? ዘወትር ቅዳሜና እሁድ ጠዋት በቴሌቪዥን ስር ቁጭ ብለው የአባባ ተስፋዬን ምክርና ተረት እየሰሙ ልጅነታቸውን አላሳለፉ ይሆን? ታላቅን ማክበር፡ ይሉኝታ፡ ገብረገብነት፡ ጨዋነትና መሰል ኢትዮጵያዊ መገለጫ በሆኑ መልካም ነገሮች ውስጥ ሳያልፉ ይሆን የጎለመሱት? የልጅነት ስነልቦናቸው እንዴት ይሆን? ክፉው ብቻ የሚታያቸው ምክንያቱ ምንድን ነው? ጥላቻን የሚዘምሩት፡ ልዩነትን የሚሰብኩት፡ እንዴት ሆነው ቢያድጉ ነው? አንድ የእግዚያብሄር ፍጡር ከክፋት በቀር እንዴት በጎ ነገር አልታይህ ይለዋል? በኢትዮጵያ ስም እየማሉ በልባቸው የተጠመቀውን ጥላቻ እየረጩ እሰከመቼ ህይወትን ይገፏት ይሆን?

Ermias Nimani


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው።

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Opinions, Right Column Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Comments

  1. gi haile says

    February 8, 2020 06:45 am at 6:45 am

    ስለ እብዶቹ ሁለት ራህይ የሌላቸው ያለኛ ማን የሚሉ ካድሬና ቀባጣሪ የፓለቲካ ሀሁ ቆጣሪዎች ጋር ቦታ ሰጥቶ መፃፍ ጊዜ ማጥፋት ነው። ኤርምያስ ለገሰ ሶስት ምላስ ያለው አዲስ ዘንዶ ሳይሆን ይቀራል ብላችሁ ነው። ሁሉን ሰድቦና ተቃውሞ ካለኔ ኣዋቂ የለም ያለን ትዕቢተኛ ትዕቢቱ አፍርጦ እስኪጥለው ድረስ መመልከት ነው። “ስጋ ቁጠር ቢሉ ጣፊያ አንድ ኣለ እነሱ ናቸው።

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጃዋርና በቀለ መታሠራቸው ተሰማ June 30, 2020 09:17 am
  • አገራዊ መድረክ ውጪ ድብቅ ውይይትን አንቀበልም June 17, 2020 06:57 am
  • ዴክሳሜታሶን! የኮሮና መድሀኒት June 17, 2020 06:49 am
  • የሰኔ 14ቱ ቀለበታዊ የፀሃይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ! June 17, 2020 06:38 am
  • የግብፅ የአባይን ውሃ ብቻዬን ልጠቀም ግትር አቋም ድርድር እንቅፋት ሆኗል June 10, 2020 07:15 am
  • የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!? April 12, 2020 02:48 am
  • በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሚጠቀሙበት የኤርትራ ስደተኛ ካምፕ ሊዘጋ ነው March 18, 2020 08:37 pm
  • እየተፈረካከሰ ያለው አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ March 18, 2020 08:09 pm
  • ኮሮና አዲስ ጉድ መዘዘ – ከቻይና በፊት በአሜሪካ ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎችን ቀጥፏል March 16, 2020 11:41 pm
  • የኮንዶሚኒየም ቤቶች በደላሎችና በመመሪያ ሰጪዎች ኔትዎርክ እየተቸበቸበ ነው! ታከለ የት ናቸው? March 9, 2020 10:18 am
  • ኤርሚያስ ለገሠ ከባለአደራ ተባረረ March 9, 2020 08:09 am
  • ድፍድፍ ሲቀል ይንሳፈፋል፤ ምሁር ሲዘቅት ይመራል፥ March 7, 2020 11:24 pm
  • ኢትዮጵያዊ ምን ይመስላል? በምንስ ይመሰላል? March 7, 2020 10:29 pm
  • WHY I WROTE “MONEY, BLOOD AND CONSCIENCE” March 4, 2020 11:15 pm
  • አድዋ፤ የጥቁር ሕዝብ ድል! March 2, 2020 11:24 am
  • ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ (አባ ጎራው) March 2, 2020 11:12 am
  • የኦነግ ሁለት መልክና ሦስት ግብሮች – ቃርሚያው ኃይል ቅጥር ነፍሰገዳይ ሆኗል February 25, 2020 11:26 pm
  • በቡራዩ “የጃል ማሮ” ፎቶ ጨረታ አፈናከተ፤ “ቡራዩ ሆኖ ከሃዲን ማሞካሸት አይቻልም” ነዋሪዎች February 17, 2020 09:13 pm
  • “ዲቃላ” የፍረጃ ፖለቲካ በኦሮሚያ የኃይል አሰላለፉን እየቀየረ ነው February 13, 2020 11:58 pm
  • “ከዚህ በኋላ ማናቸውንም በወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን” አንታገስም – ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ February 13, 2020 05:07 pm
  • “እኛ ማንም ተሳዳቢ እንዲመጣብን አንፈልግም” የጅማ ነዋሪ February 13, 2020 09:28 am
  • “ወላጆቻችሁ ሰላማዊ ሰልፍ በሕዝቡ ያስደርጉልን” – አጋቾች February 11, 2020 07:53 pm
  • “ወንጀል የፈጸመም ያስፈጸመም ተይዞ ለህግ ይቀርባል፤ ምርመራም ተጀምሯል” February 11, 2020 06:59 pm
  • ጃዋር ወደ መጨረሻው “የትግል” ስልቱ – አማራን ማበጣበጥ! February 10, 2020 11:54 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule