ኢትዮጵያ ግራ በሚያጋባና ሊተነበይ በማይችል የፖለቲካ ቀውስ ውስጥ መገኘቷን ያመኑ የህወሃት ሰዎች መካካል የእርቅ ሃሳብ ላይ ለማተኮር እቅድ እንዲያዝ ሃሳብ ማንሳታቸው ተሰማ። ኢህአዴግ የቀድሞው የአፈና ገመዱ መንተቡን የሚያሳዩ ምልክቶች መታየታቸውና አለመተማመን መንገሱ ተጠቆመ። ለጎልጉል መረጃ በመስጠት የሚታወቁ የኢህአዴግ ከፍተኛ አመራርና ዲፕሎማት እንዳሉት ህወሃት ውስጥ "እርቅ አስፈላጊ ነው" በሚል እቅድ እንዲያዝና እንዲሰራበት ሃሳብ ቀርቧል። በድርጅቱ ውስጥ በተፈጠረ አለመተማመን ሳቢያ ስጋት የገባቸው የህወሃት ሰዎች የእርቅ ሃሳብ እንዲሰራበት ያቀረቡት ሃሳብ ግን በመደበኛ ስብሰባ አይደለም። በህወሃትና ህወሃት በሚያዛቸው አቻ ፓርቲዎች መካከል ያለው የመከባበርና የመገዛት ስሜት ከመለስ ሞት በኋላ መበላሸቱ፣ በኢህአዴግም ሆነ በህወሃት ደረጃ የተፈጠረው ልዩነትና በሙስና ስም … [Read more...] about በህወሃት ውስጥ የዕርቅ ሃሳብ መነሳቱ ተሰማ
“ኧረ እኔስ ጨነቀኝ”
ሰውየው ያገባት ሚስቱ ቤተሰቦቿ ሃብታሞች ነበሩ። እሱ ደግሞ መናጢ የሚባል ደሃ ነበር። አንድ ቀን የማይቀረው ሞት የሚስቱን አባት ነጠቀና ቀብር ወጡ። አስከሬን እየተከተሉ ሲያለቅሱ ባል ሚስቱ ጎን ሆኖ ልክ እንደሷ "አባቴ አባቴ" በማለት ያለቅስ ጀመር። ሚስትም " የት የወለደህን ነው አባቴ የምትለው" በማለት አፍታ ወስዳ ባሏን ገሰጸችው። ባል ለቅሶውን ቀየረና "አባቷ፣ አባቷ …” በማለት ያስነካው ጀመር። ይህን ጊዜ ሚስት አሁንም ለቅሶዋን ቆም አድርጋ "የበላኸው ጨማ፣ የጠጣኸው ጠጅ አያንቅህም? አባቷ አባቷ የምትለው" አለችው። ባልም ደንግጦ ላፍታ ዝም በማለት ካሰበ በኋላ "አረ እኔስ ጨነቀኝ፣ አረ እኔስ ጨነቀኝ … ” በማለት እያለቀሰ የባለቤቱን አባት ሸኘ። ይህ አጠር ተደርጎ የቀረበ የቀድሞ ምሳሌ ነው። ኢትዮጵያውያን አገራቸውን ይወዳሉ። አገራቸውን በልጅ፣ በሚስት፣ በእናት፣ … [Read more...] about “ኧረ እኔስ ጨነቀኝ”
የመረጃ መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ (ኢንሳ) በከፍተኛ ሥልጣንና ጉልበት በድጋሚ ሊቋቋም ነው
ባለፉት በርካታ ዓመታት በሥራ ላይ የሚገኘውን የመረጃ መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ ከፍተኛ ኃላፊነትና ጉልበት የሚሰጥና በድጋሚ እንዲቋቋም የሚያደርግ ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማ ቀረበ፡፡ በፓርላማው ቋሚ ኮሚቴዎች ተጨማሪ ውይይት እየተደረገበት የሚገኘው ይህ ረቂቅ አዋጅ፣ በቀጣዮቹ ጥቂት ሳምንታት ይፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ረቂቅ አዋጁ ከፀደቀ በኋላ ኤጀንሲው በድጋሚ የሚዋቀር ሲሆን የአገሪቱ የፋይናንስ ተቋማትን፣ ብሔራዊ የኤሌክትሪክ ኃይል መረብን፣ በግንባታ ላይ የሚገኘውን አገራዊ የባቡር ትራንስፖርት መረብን፣ ወታደራዊ የኮምፒዩተር ሥርዓትንና ሌሎች ኮምፒዩተራይዝድ የሆኑ መሠረተ ልማቶችን በኮምፒዩተር አማካይነት ከሚቃጡ ጥቃቶች የመጠበቅ ኃላፊነት ይኖረዋል፡፡ የረቂቅ አዋጁ አባሪ ሰነድ ሆኖ የቀረበው ማብራሪያ እንደሚያስረዳው፣ በአገሪቱ በሚታየው የኢኮኖሚ ዕድገት ሳቢያ በርካታ የአገሪቱ … [Read more...] about የመረጃ መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ (ኢንሳ) በከፍተኛ ሥልጣንና ጉልበት በድጋሚ ሊቋቋም ነው
በሚዩኒክ ጀርመን የወያኔ የአባይ ግድብ ቦንድ ሽያጭ ተስተጓጎለ
እ.ኤ.አ. ቅዳሜ ኖቬምበር 02, 2013 ዓ.ም. በጀርመን ሚዩኒክ ከተማ ወያኔ ሊያደርግ ያሰበው የአባይ ግድብ ቦንድ ሽያጭ ከተለያዩ የጀርመን ከተሞች በተሰበሰቡ ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ ሊከሽፍ ችሏል። ከዚህ በፊት በጀርመን ፍራንክፈርት ጨምሮ በተለያዩ የአውሮፓና ሰሜን አሜሪካ ከተሞች እክል የገጠመው የወያኔ የቦንድ ሽያጭ ኮሚቴ አካሄዱን በመቀየር የቦንድ ሽያጩ ይጀመራል ተብሎ ከታሰበበት ጊዜ ሶስት ሰዓት ያህል በማዘግየት ለተቃውሞ የመጡትን ሰዎች ተስፋ ለማስቆረጥ ያደረገው ሙከራ ሳይሳካ ከመቅረቱም በላይ በወቅቱ በነበረው ቅዝቃዜና ብርድ ሳይበገሩ የፕሮግራሙን መጀመር በትዕግስት በቅርብ ርቀት የተከታተሉት እነዚህ ተቃዋሚዎች የመግቢያ ትኬት ሽያጭ ሲጀመር በአንድ ጊዜ ቁጥራቸው ከሶስት መቶ በላይ የሚሆኑ የኦነግ አባላት፣የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር አባላት፣የኢህአፓ … [Read more...] about በሚዩኒክ ጀርመን የወያኔ የአባይ ግድብ ቦንድ ሽያጭ ተስተጓጎለ
ስቀው ያሳሳቁን፣ በርተው የጠፉ የጥበብ ሰዎች እና ልናሽረው የማንችለው ቁስል!
ቀልድ ሲነሳ አስቂኝ ሶስቱ ድንቅ ተዋናዮች አለባቸው ተካ፣ ልመንህ ታደሰና አብርሃም አስመላሽ በልዩ ችሎታቸው ለእኔ እና ለብዙዎች ከፍ ያለ ቦታ አላቸው። ነፍሱን ይማረው አለባቸው ተካ ድሃ እንደደገፈ በአሳዛኝ የመኪና አደጋ አለፈ! ህይወቱን ለጥበብና በፋና ወጊ መልካም ተግባር ተሰልፎ ሲያሳልፍ ተስገብግቦ ሃብት አላካበተምና ለእሱና ለቤተሰቦቹ የረባ ጥሪት ሳይጥል አለፈ ... መልከ መልካሙ ልመንህ ከምድረ አሜሪካ አዕምሮውን ስቶ ከሞቱት በላይ ካሉት በታች ሆኖ በአዲስ አበባ አውራ ጎዳናዎች ይንከራተታል ... የሙያ አጋሮቹ ከምድረ አሜሪካ ያደረጉት ሁሉ ትብብር ቢሳካ ኖሮ ልመንህ ዛሬ ድኖ እናየው ነበር፣ ግን አልሆነምና በናኘበት ከተማ ራሱን ጥሎ ነሁልሎ ማየቱ ልብ ይሰብራል፣ ያሳዝናል! አንዳንድ ወዳጆቸ ልመንህን ለመደገፍ በግል ከሚደረገው ጥረት ባለፈ በተቀናጀ መልኩ እርዳታ … [Read more...] about ስቀው ያሳሳቁን፣ በርተው የጠፉ የጥበብ ሰዎች እና ልናሽረው የማንችለው ቁስል!
እኔና አንቺ…፪
መቼም እኔና አንቺን ሲፈጥረን ጉዳችሁ አይለቅ ያለን ነን የኛ ብለን ክብር ሰጥተን ያመነው ሰው ደ’ሞ ከዳን። ይሄን ሰማሁ ይሄውልሽ አንቺም ሰሚው አይቅርብሽ እንደው ቢገርመኝ እንጂ ነገሩ፥ይሄማ ምኑ ይወራል የኛ ያሉት ሲከዳ፥ቃሉ ለአፍ ይመራል ብቻ ምን ይደረግ? ”ውሻ በቀደደው…” ይባል የል የሱስ መክደት ምን ይደንቃል? እንደው ግን ለነገሩ፤ እየገደሉ እያያቸው በደም ተጨማልቆ እጃቸው ከነሱ ጋር አብሮ እየደለቀ ከበሮ የተለጠፈው ውስጣቸው ምን አግኝቶ ምን አጥቶ ነው? በምኑስ ላይ ምን ሊጨምር? መች አነሰው? ንዋይ ክብር በይ ተይው ግድ የለም፤ መቼም-እኔና አንቺን ሲፈጥረን ጉዳችሁ አይለቅ ያለን ነን። እንግዲህ ካልሰማሽም ስሚ፤ ከሰማሽም-ቻልአድርጊው እኛን ያልከዳን ማን አለ? የበደለን … [Read more...] about እኔና አንቺ…፪
No Easy Way to Democratize Ethiopia?
When I read Tagel Getahun’s article - Ethiopia: No Easy Way to Democratize Ethiopia, on one of the Ethiopian websites, I was shocked. Then I went to find out the original source of the article. Alas! – it was the All Africa. Taking it seriously, I figured this is not written by any lawyer ( Tagel Getahun Is a Lawyer. He Can Be Contacted At Tagelgbekele@yahoo.com ) or any one individual but by TPLF leaders, the governing body of the country. It is carefully planned, written, rewritten, reviewed, … [Read more...] about No Easy Way to Democratize Ethiopia?
እረፍት የሚነሳው ህምም
እረፍት አደርግ ብየ ከማህበራዊ መገናኛ መድረኩ ገለል ባልኩባቸው እንደ ብርሃን ፍጥነት በሚወረወሩት ባለፉት ጥቂት ቀናት ከበርካታ ወዳጆቸ በርካታ መልዕክቶች ይደርሱኛል። ብዙው መልዕክት ደግሞ የሚያጠነጥነው በጅዳ እና በአካባቢው በተፈናቃይ የኮንትራት ሰራተኞች አሰቃቂ ስቃይ ላይ ያተኮራል ... ለነገሩ የአብዛኞቹ መልዕክቶች ብቻ ሳይሆኑ ከመልዕክቶች ጋር የሚላኩልኝ መረጃዎች እረፍት የሚነሱ ናቸው! ... አዎ ተንቀሳቃሽ ምስል ጭምር በመረጃነት የታጨቀባቸውን የመልዕክት መረጃ ጭብጦች እውነታ ለማረጋገጥ ወደ ጅዳ ቆንስል አመራሁ ... መኪናየን አቁሜ ትንሽ እንደ ተራመድኩ እያለ ከፊት ለፊቴ አንዲት ልጅ እግር ኢትዮጵያዊ ብቻዋን እያወራች ስታልፍ ስመለከት በመደናገጥ ሰላምታ አቅረብኩላት፣ መልስ ሳትሰጠኝ አለፈች! ደነገጥኩና ባለሁበት ቆሜ በአይኔ ተከተልኳት ... በፈጣን እርምጃ … [Read more...] about እረፍት የሚነሳው ህምም
ኢትዮጵያን እንደገና ማነጽ
መግቢያ የዛሬው የመወያያ ሃሳብ ኢትዮጵያን እንደገና ለማነጽ ኣዲስ የማህበራዊ ፖለቲካ መዋቅር በማስተዋወቅ ላይ ያተኮረ ነው። ይህ መዋቅር ኢትዮጵያን ወደ ኣዲስ ኪዳን የሚጋብዝ ነው። ኢትዮጵያ የገጠማት የከፋ ችግር በኣብዛኛው ከታችኛው የማህበራዊ ፖለቲካ (socio politics) መዋቅር ጋር የተገናኘ በመሆኑ በዚህ ላይ ኣማራጭ ሃሳብ ማምጣት በተለይ ይህ የኣሁኑ ትውልድ የሚጠበቅበት ይመስላል። ያለፉትን ችግሮች ኣስር ጊዜ እያወጣን ብናወርዳቸው ድካም ብቻ ይሆንብናልና። በተለምዶ ያ ትውልድ እያልን የምንጠራው ቀዳሚው ትውልድ ኣንድ የሆነ ሼል ሰብሮ የወጣ ነበር። ያ ትውልድ ለዘመናት የነበረውን ዘውዳዊ ኣገዛዝ ደፍሮ የጠየቀ፣ የፍትህና የእኩልነትን ጥያቄዎች ኣንግቦ ግንባሩን ለጥይት የሰጠ በመሆኑ ታሪክ ሁልጊዜም ያ ትውልድ....እያለ ሲያስታውሰው እንዲሁ ይኖራል። ያ ትውልድ የሆነ … [Read more...] about ኢትዮጵያን እንደገና ማነጽ
ትግላችን ከእንግዲህ ወዴት? እንዴት?
ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ፡፡ … [Read more...] about ትግላችን ከእንግዲህ ወዴት? እንዴት?










