• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ስቀው ያሳሳቁን፣ በርተው የጠፉ የጥበብ ሰዎች እና ልናሽረው የማንችለው ቁስል!

November 2, 2013 08:35 am by Editor Leave a Comment

ቀልድ ሲነሳ አስቂኝ ሶስቱ ድንቅ ተዋናዮች አለባቸው ተካ፣ ልመንህ ታደሰና አብርሃም አስመላሽ በልዩ ችሎታቸው ለእኔ እና ለብዙዎች ከፍ ያለ ቦታ አላቸው። ነፍሱን ይማረው አለባቸው ተካ ድሃ እንደደገፈ በአሳዛኝ የመኪና አደጋ አለፈ!  ህይወቱን ለጥበብና በፋና ወጊ መልካም ተግባር ተሰልፎ ሲያሳልፍ ተስገብግቦ ሃብት አላካበተምና ለእሱና ለቤተሰቦቹ የረባ ጥሪት ሳይጥል አለፈ  …  መልከ መልካሙ ልመንህ ከምድረ አሜሪካ አዕምሮውን ስቶ ከሞቱት በላይ ካሉት በታች ሆኖ በአዲስ አበባ አውራ ጎዳናዎች ይንከራተታል … የሙያ አጋሮቹ  ከምድረ አሜሪካ ያደረጉት ሁሉ ትብብር ቢሳካ ኖሮ ልመንህ ዛሬ ድኖ እናየው ነበር፣ ግን አልሆነምና በናኘበት ከተማ ራሱን ጥሎ ነሁልሎ ማየቱ ልብ ይሰብራል፣ ያሳዝናል! አንዳንድ ወዳጆቸ ልመንህን ለመደገፍ በግል ከሚደረገው ጥረት ባለፈ በተቀናጀ መልኩ እርዳታ እንደማይደረግለት አጫውተውኛል፣ ለዚህም ምክንያቱ የህምሙ ክፋት እንደሆነ የገለጹልኝ ሃገር ቤት ያሉ የሙያ አጋሮቹም ቢሆንም ለከፋው ህመም መላ ማጣታቸውን ይናገራሉ  … ብቻ ልመንህም እንዲህ ሆኗል … አዕምሮውን የሳተ በየጎዳናው ተንከራታች … ክፉ ጊዜ ….

አዱ ገነት ተወልዶ አድጎ ለዛ ያለውን የሃገር ቤት የገጠር ቃና ንግግርን በግ ለመሸጥ ወደ አዲስ አበባ ከሚመጡ ከበግ ነጋዴዎች ተለማምዶ ሲናገረው ገጠር  ተወልደው ያደጉትን ያስንቅ ነበር፣ ከገጠር መጥተው የገጠሩን አነጋገር ወደ ከተምኛው ለመቀየር ሲደነባበሩ አዲስ አበቤው የተገላበቢጦሽ የእነሱን የአነጋገር ዘይቤ ተክኖና ተውቦ አገር ምድሩን በፈጠራው ሲያስቀው ድንቅ ችሎታ ነበረው። አብርሃም አስመላሽ … በአንድ ወቅት ከአብርሃም ጋር ተገናኘተን ከቀልድ ያለፈ የጨዋታውን ለዛ ኮምኮሜዋለሁ!  መልካም ሰብዕናም እንደ ነበረው ወዳጆቸና ወዳጆቹ አጫውተውኛል!  አብርሃም አስመላሽ …aberaham asmelash

አብርሃም ወደ ጀርመን ሃገር ሄዶ ህክምና እንዲያገኝ ትልቁን ድርሻ ለተወጡት የሙያ አጋሮቹ ላደረጉት ትብብር አድናቂዎቹ ምስጋናችን ከፍ ያለ ነው … ዛሬ አንድ መረጃ ደረሰኝና ከምስጋናው  አልፌ ብዙውን አውጥቸ አወረድኩ … አብርሃም የመሞቱን መሪር መርዶ ከሰማን እያለፈ ባለው ሳምንት ውስጥ  ጥቅምት 21 በእለተ ማርያም 2013 ዓም ነው!   ከዚያች ቀን ወዲህ  የአብርሃምን ሬሳውን ወደ ሃገር ቤት ለመውሰድ የገንዘብ ድጋፍ እርዳታ መጠየቁን   ሰምቻለሁ … እናም የጥበብ ሰዎች መጨረሻ አሳሰበኝ! … ወገን ለወገን ነውና የአብርሃም ሬሳ የሚወዳት ሃገሩ አፈር ትቀምስ ዘንድ ሁላችንም የእርዳታ እጃችን ብንዘረጋ መልካም ነው በሚል በሳውዲ ነዋሪ አሳሳቢ ከሆነው የምህረት አዋጅ ማለቅ ስጋት ወጣ ብየ ይህችን ማስታወሻ ሞነጫጨርኩ …

ከአብርሃም ሳልወጣ ቀጠልኩ. ..  ከሬሳው ማመላለሻው እርዳታ በኋላስ? ብየ ለራሴ አልጎመጎምኩ … እሱም እንደ ኮሜዲ አለባቸው ከወደ ኋላ ጥሏቸው የሄዱ ቤተሰቦች እንዳሉት ሰምቻለሁ … እናም የእነሱም መጻኤ እጣ ፋንታ በእኛው ካልተደገፈ መላ አይኖረውም … በሚል ጀምሬ ምናል የኪነ ጥበብ ሰዎች እና ታዋቂ ግለሰቦች እንዲህ እያለፉ ስላሉ ብርቅየ የሃገራችን ልጆችን እና ቤተሰቦችን ቢታደጓቸው? ቢያንስ ለኪነ ጥበብ አፍቃሪ አድናቂዎቻቸውን በተነሳሽነት በማሰባሰብ የድጋፍ እርዳታ ቢያሰባስቡላቸው ስል ማሰቤ አልቀረም! ቅድሚያ ድጋፉ ከሙያ አጋሮች ቢጀምር አልኩና ራሴን ያዝ አደረግኩት … ብዙ ከእርዳታ ጋር የተገናኙ ጉዳዮች ታወሱኝ!

የእርዳታ ነገር ሲነሳ በርካታ የከሸፉ ሙከራዎችን አይረሱኝም፣ አለም ደቻሳ ሊባኖስ በኢትዮጵያ ቆንስል በር በአንድ አረብ “ጀብራሬ” እየተጎተተች ባየናት በጥቂት ቀናት ልዩነት ራሷን ገደለች አሉን … ከወራት በኋላ ጥላቸው የሔደቻቸውን ልጆች ለመርዳት በተጠራው አለም አቀፍ አርዳታ ለተጠራው እርዳታ የተገኘው ምላሽ አያኮራም! እዚህ ሳውዲ በርካቶች ለከፋ ችግር ሲዳረጉ በግል የሚደረጉትም ሆነ በማህበራዊ ገጾች ለሚጠራ እርዳታ የሚሰጠው ምላሽ ያሸማቅቃል … ያን ሰሞን ለአመታተ በብዕራቸው አገር ያስደመሙ ሁለት ኩሩ የስነ ጽሁፍ ሰዎች በየተራ መታመማቸውን በሰማን … የጋዜጠኛ ጸሃፍት ባልደረቦዎቻችን መታመም ካንገበገባቸው ወንድሞች እርዳታ ይሰበስቡ ከነበሩት መካከል አንዱ ወዳጀ  እንደ ጨው የተበተንን የዚያች ሃገር  ጋዜጠኞች ዘንድ እርዳታና ድጋፍ አገኝ ብሎ ከአውሮፖ አሜሪካ በመላላክ ሲባትል ያተረፈው ድካም ብቻ ሳይሆን የሰውን ጭካኔ መሆኑን አጫውቶኛል። ይህንን አሳዛኝ ገጠመኝ ያጫወተኝ ወዳጀ መጨካከናችን አስታውሶ ያቀበለኝ መረጃ ተስፋ ባያስቆርጠኝ ሳያሳዝነኝ አልቀረም! ብቻ ጊዜው ተበላሽቶ ጨካኞችን እያወገዝን ጨቋኞች መሆናችን ዘልቆ ቢያደማም ተስፋ መቁረጥ ከቶ አይገባም …

አዎ ካለፈው ልንማር ከቻልን ዛሬ በመልካም ነገር ማስቀጠል እንችላለን! ዛሬ የብርቅየውን ኮሜዲ የአብርሃም አስመላሽን ነፍስ ይማር ስንል በስሙ ለተጠየቅነው እርዳታ እጃችን እንዘርጋ ዘንድ ግድ ይለናል!  አስተባባሪዎችም ግልጽ የሆነ እርዳታ ማሰባሰብ አድርጉ፣ የስልክ የባንክ አድራሻና ሌላም ተገቢ መረጃዎችን ስጡ! አበው “ሃምሳ ሎሚ ለአንድ ሰው ሸክሙ፣ ለሃምሳ ሰው ጌጡ ነው!” እንደሚሉት ነውና የቻለ እንዳቅሙ ይርዳ … ይህ መሰሉ እርዳታ ወገንተኛነታችን እና ሰብዕናችን እናሳይበት እንደሁ ማለት እንጅ ሰው ሰጥቶ፣ ደግፎ አያጠግብም … ሰጥቶ እና ደግፎ የሚያጠግብ አንድ ፈጣሪ አምላክ ብቻ ነው … የቻልን እንለግስ …አንድየ ሁሉንም ያያል ለሰጭ ይስጠዋል እናም እንረዳዳ! ስቀው ያሳሳቁን፣ በርተው የጠፉ የጥበብ ሰዎች እና መጨረሻቸው እንዲህ ሲሆን ማየቱ ቢያምም ከታደግናቸው ልናሽረው የምንችለው ቁስል እንዳለ አንዘንጋ  ስል የማለዳ ወጌን ቋጨሁ!

ለቤተሰቦች መጽናናትን እመኛለሁ … የሟችን ነፍስህን ይማር !

ነቢዩ ሲራክ

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጃዋርና በቀለ መታሠራቸው ተሰማ June 30, 2020 09:17 am
  • አገራዊ መድረክ ውጪ ድብቅ ውይይትን አንቀበልም June 17, 2020 06:57 am
  • ዴክሳሜታሶን! የኮሮና መድሀኒት June 17, 2020 06:49 am
  • የሰኔ 14ቱ ቀለበታዊ የፀሃይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ! June 17, 2020 06:38 am
  • የግብፅ የአባይን ውሃ ብቻዬን ልጠቀም ግትር አቋም ድርድር እንቅፋት ሆኗል June 10, 2020 07:15 am
  • የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!? April 12, 2020 02:48 am
  • በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሚጠቀሙበት የኤርትራ ስደተኛ ካምፕ ሊዘጋ ነው March 18, 2020 08:37 pm
  • እየተፈረካከሰ ያለው አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ March 18, 2020 08:09 pm
  • ኮሮና አዲስ ጉድ መዘዘ – ከቻይና በፊት በአሜሪካ ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎችን ቀጥፏል March 16, 2020 11:41 pm
  • የኮንዶሚኒየም ቤቶች በደላሎችና በመመሪያ ሰጪዎች ኔትዎርክ እየተቸበቸበ ነው! ታከለ የት ናቸው? March 9, 2020 10:18 am
  • ኤርሚያስ ለገሠ ከባለአደራ ተባረረ March 9, 2020 08:09 am
  • ድፍድፍ ሲቀል ይንሳፈፋል፤ ምሁር ሲዘቅት ይመራል፥ March 7, 2020 11:24 pm
  • ኢትዮጵያዊ ምን ይመስላል? በምንስ ይመሰላል? March 7, 2020 10:29 pm
  • WHY I WROTE “MONEY, BLOOD AND CONSCIENCE” March 4, 2020 11:15 pm
  • አድዋ፤ የጥቁር ሕዝብ ድል! March 2, 2020 11:24 am
  • ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ (አባ ጎራው) March 2, 2020 11:12 am
  • የኦነግ ሁለት መልክና ሦስት ግብሮች – ቃርሚያው ኃይል ቅጥር ነፍሰገዳይ ሆኗል February 25, 2020 11:26 pm
  • በቡራዩ “የጃል ማሮ” ፎቶ ጨረታ አፈናከተ፤ “ቡራዩ ሆኖ ከሃዲን ማሞካሸት አይቻልም” ነዋሪዎች February 17, 2020 09:13 pm
  • “ዲቃላ” የፍረጃ ፖለቲካ በኦሮሚያ የኃይል አሰላለፉን እየቀየረ ነው February 13, 2020 11:58 pm
  • “ከዚህ በኋላ ማናቸውንም በወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን” አንታገስም – ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ February 13, 2020 05:07 pm
  • “እኛ ማንም ተሳዳቢ እንዲመጣብን አንፈልግም” የጅማ ነዋሪ February 13, 2020 09:28 am
  • “ወላጆቻችሁ ሰላማዊ ሰልፍ በሕዝቡ ያስደርጉልን” – አጋቾች February 11, 2020 07:53 pm
  • “ወንጀል የፈጸመም ያስፈጸመም ተይዞ ለህግ ይቀርባል፤ ምርመራም ተጀምሯል” February 11, 2020 06:59 pm
  • ጃዋር ወደ መጨረሻው “የትግል” ስልቱ – አማራን ማበጣበጥ! February 10, 2020 11:54 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule