እንደ ዶክተር ጌታቸው በጋሻው አባባል ጤንነታቸው ከታወኩት ውስጥ ልደባለቅ እንጂ ከምዬ ኢትዮጵያ አንፃር ዛሬም ወያኔና ሻቢያ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጾች ናቸው። እብድ ልባል እንጂ ሁለቱም የኢትዮጵያ ሕዝብና ሀገር ላይ የተጫወቱና እየተጫወቱ ያሉ ናቸው። ወያኔን ቤተመንግስት ደጃፍ ድረስ ሸኝቶ የመቶ ዓመት የቤት ሥራ የሰጠን ሻቢያ ገና “77 ዓመት ይቀረዋል”። ኢትዮጵያዊነት ብሔራዊ ስሜት ከቶም እንዳያንሰራራ የሻቢያን የቤት ሥራ እያከናወነ ያለው ወያኔ ቢንገዳገድ ቀሪውን የሚቀጥል እየተዘጋጀልንና እየተደገሰልን ነው። አዎ ሻቢያን በኤርትራ፣ ወያኔን በኢትዮጵያ ለሥልጣን ያበቃቸው ከጋለባቸው ጋር እየተጋለቡ፣ ዛሬ ያሉትን ነገ እየካዱ፣ ትላንት የጣሉትን ዛሬ እያነሱ፣ ዛሬ ያቀፉትን ነገ እያረዱ፣ ሀገር ኢትዮጵያን እንዳሻቸው ሊጋልቡ፤ ሊታመን ከሚገባው በላይና ያለ ይሉኝታ እየተገለባበጡ … [Read more...] about ዝናብ አይፈሬ ታጋዮች
“አልመች አለው ጎኔ!”
ጥበብ የማህበረሰቡ ሁለንተናዊ ስሜት የሚገለጽባቸው ቀዳሚው እያዝናና የሚያስተምር ዘርፍ ቢሆንም አሁን አሁን ግን ያ እየሆነ አይታይም። የማፍር፣ የምኮራባቸው ጥበበኞች ጉዳይ አሁን አሁን ያሳስበኝ ይዟል ... እናም የጎልማሳው አቀንቃኝ የጃኪ "አልመች አለው ጎኔ!" ጣዕመ ዜማ ውስጥ ስሜቴን ቢነካካው፣ የማፍር የምኮራባቸው፣ ጥበበኞች ... ብየ ጀመርኩት! የጥበብ ሰዎች በግል እንደ ተራ ዜጋ የፈቀዱትን ፖለቲካ አቋም የመያዝ መብታቸውን የማከብር ቢሆንም ታዋቂነታቸውን ተጠቅመው ከእውነተኛ የህዝብ መብት ጥያቄና ስሜት ሳይሆን ለሆዳቸው ሲያድሩ ማስተዋል ስሜትን ይጎዳል። በተለይም ደግሞ የጥበብ ሰዎች ለሆዳቸው አድረው ከገዥ አንባገነኖች ጋር ወግነው የህዝብ ድምጽ ሳይሆን የፖለቲካ ፖርቲዎች ቱልቱላ ሲሆኑ ማየት ያማል። ያለመታደል ሆኖ በእኛ ኢትዮጵያ ከጥቂት የጥበብ ሰዎች በስተቀር … [Read more...] about “አልመች አለው ጎኔ!”
እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲፬
የጎልጉል ወዳጅ ወለላዬ "እኚህ ሰው ማናቸው?" በሚል ርዕስ ግሩም ዝግጅት ሲያቀርቡ መቆየታቸው ይታወሳል። ይህንን ዝግጅት በጥያቄና በግጥም መልክ የሚያቀርቡት እንደመሆኑ ምላሹም በግጥም እንዲሆን አንባቢያንን እርሳቸውም እኛም እናደፋፍራለን። ወለላዬ ከተለያዩ የግልና መሰል የህይወት ውጣውረዶች በኋላ አሁን ዝግጅታቸውን እንደገና ጀምረዋል። ጎልጉልም በደስታ እንኳን ደህና መጡ ይላቸዋል። የመጨረሻው "እኚህ ሰው ማናቸው?" ፲፫ኛው ነበር የዚያን መልስ ከአዲሱ ጥያቄ ጋር አቅርበናል። ወዳጃችን ወለላዬ በድጋሚ እንኳን ደህና መጡ ምስጋናችን ይድረስዎ። ከዚህ በፊት ኮሎኔል ታምራት ይገዙን አቅርቤ መልስ ሳልሰጥ አቋርጨ ነበር። አሁን ከመልሱ ጋር አዲስ ልኪያለሁ መልስ ይዘን የቀረብነው ምስላቸውን በፊት ይባሉ ነበረ ኮሎኔል ታምራት ኮሎኔል ታምራት ታምራት … [Read more...] about እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲፬
እውነቱ ይውጣ!
ሴቶችን በወንዶች ፊት፣ ወንዶችን በሴቶች ፊት ልብስ እያስወለቁ የአካላቸውን ክፍሎች ሁሉ ለማየት የሚያስችል እንቅስቃሴ አንዲሠሩ ማስገደድ በሽተኞችን ያስደስታል፤ የምርመራ ዘዴ ግን አይደለም፤ ውርደት እንዲሰማቸው ከሆነ በወራዶች ሰዎች ፊት የምን መዋረድ አለ? ወራዶች እነሱ ደረጃ ላይ ከእነሱ ጋር ያስተካክላሉ አንጂ አያዋርዱም፤ በሌላ አነጋገር ወራዶች አያዋርዱም፤ ወራዶቹ ደንቆሮዎችም ሆነው ነው እንጂ ልብስ የሚያስወልቁ እነሱ ብቻ አይደሉም፤ ሀኪሞችም ልብስ አስወልቀው፣ አጋድመው በጣታቸውም ሆነ በመሣሪያ የፈለጉትን የአካል ክፍል አንደፈለጉ ያደርጉታል፤ ወራዶቹና ደንቆሮዎቹ ከሚያደርጉት የሀኪሞቹ የሚለየው ሀኪሞቹ ሰዎችን ለማዳን ሲሉ ነው፤ ወራዶቹና ደንቆሮዎቹ ግን የራሳቸውን ሱስ ለማርካት፣ የራሳቸውን ህመም ለማስታገስ ነው፤ ወራዶቹንና ደንቆሮዎቹን ከመለዮአቸው አራቁቻቸዋለሁ! ከነውር … [Read more...] about እውነቱ ይውጣ!
ከጩኸት ወደ ተግባር የሚነገድበት የስደት ማእበል ትውልድ ከየት መጣ?
የውጭ ጠላቶቻችንና የውስጥ ገዢዎቻችን በአንድ ድምጽ የሚሰሩ መሆናቸውን በተደጋጋሚ አይተናል። በጥቃቅን ልዩነቶች ላይ ማተኮሩን እንተወው፤ አስጠቅቶናል፤ አሳፍሮናል፤ አድክሞናል። በገፍ ለሚሰደደውና ለሚዋረደው ብዙ ሚሊየን ወጣት ትውልድ እንደምናስብ አምናለሁ። እምነት፤ ጩኸት፤ ፀሎት አስፈላጊ ቢሆኑም አንገት ቆራጭ ሽብርተኞችን አይከላከሉም። አፋኝ፤ አግላይና ራሱን አገልጋይ የሆነ የመንግሥት ስርዓትን አይለውጡም። ሁለቱንም አብሮና ተባብሮ ለመለወጥ ይቻላል የሚል እምነት አለኝ [ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ]። … [Read more...] about ከጩኸት ወደ ተግባር የሚነገድበት የስደት ማእበል ትውልድ ከየት መጣ?
አሜሪካ አይሲስን ለምን ፈጠረችው?
ግብጽ የሃያ አንድ ክርስቲያን ዜጎችዋን በአይሲስ መታረድ ዜና እንደሰማች ዝም ብላ አልተቀመጠችም ነበር። ብሄራዊ የሃዘን ቀንም አላወጀችም። እንዲህ ነበር የሆነው። ከመቅጽበት ተዋጊ አውሮፕላኖችዋን አስነስታ ወደ ሊቢያ ላከቻቸው። የአይሲስ አራጆች የተከማቹበትን ደርና የተሰኘ ስፍራ እያከታተለች በቦምብ ቀጠቀጠችው። ብዙ አራጆች በድብደባው አለቁ። እንደ ግብጽ አጀማመር ቢሆን የሊብያው አይሲስ ክንፍ ድሮ-ድሮ ከምድረ-ገጽ ይጠፋ ነበር። ግና አልሆነም። አሜሪካ ጣልቃ ገባች። ግብጽ የአሜሪካን "ጸረ-ሽብር" ዘመቻ በማገዝዋ ምስጋና ማግኘት ሲገባት በተቃራኒው ተወገዘች። ከጥቂት ድብደባ በኋላ ፔንታጎን ግብጽን አስጠነቀቀ[0]። የኦባማ አተዳደርም ደብደባው በአፋጣኝ እንዲቆም ቀጭን መልእክት ላከ። ይህ ድርጊት ከዚህ ቀደም ስለ አይሲስ አፈጣጠር ኤድዋርድ ስኖደን[1] የለቀቀው ምስጢራዊ መረጃ ጋር … [Read more...] about አሜሪካ አይሲስን ለምን ፈጠረችው?
“መንግሥት የሌለው እዚህ ብቻ ነው!”
ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ስሞኑን በአሸባሪው አይሲስ የተወሰደውን አሰቃቂ ተግባር በማውገዝ በአገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ላይ ያወጣው መግለጫ እንዲህ ይነበባል:- የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ መግለጫ ባለፈው እሁድ አይሲስ ባሰራጨው ቪዲዮ ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖች በሁለት የተለያዩ ቦታዎች ሲገደሉ ተመልክተናል። ስለ ቪዲዮው ብዙ ማለት ቢቻልም ወገኖቻችን ከአገራቸው ወጥተው ወደ ተሻለ ኑሮ ፍለጋ መንከራተታቸው ለዚህ ዓይነቱ አሰቃቂ ሞት ዳርጓቸዋል። ከአገራቸው የወጡት እየኖሩ ከመሞት ለመትረፍ ቢሆንም በስደት ደግሞ እጅግ መራራውን የሞት ጽዋ ጠጥተዋል። ይህ የወገኖቻችን ዕልቂት በዓለማችን ላይ በሚገኝ በምንም ዓይነት ቋንቋ፣ አገላለጽ፣ አጻጻፍ፣ እንባ፣ ወዘተ ሊገለጽ የማይችል ነው። ረዳት አልባ ሆነው የተመለከትነው ትዕይንታቸውም በውስጣችን ለዘመናት የማይሽር ቁስል ይዞ … [Read more...] about “መንግሥት የሌለው እዚህ ብቻ ነው!”
አልሸባብ አይሲስን ሊቀላቀል ነው
በሶማሊያ የሽብር ተግባራትን በመፈጸም የሚታወቀው አልሸባብ ደመኛና አረመኔውን አይሲስን ሊቀላለቀል መሆኑ ተሰማ፡፡ አገራችንን በተጨማሪ የሽብር ስጋት ውስጥ እነደሚጥላት ተገምቷል፡፡ የሶማሊያን ስፊ ግዛት የሚቆጣጠረው አልሸባብ የማእከላዊ ስልጣኑን ካጣ ወዲህ በደረሰበት ወታደራዊ ኪሳራ የአለም አቀፍ አሸባሪው አልቃይዳ ክንፍ በመሆን እያካሄደ ባለው የደፈጣ ውጊያ ሶማሊያ ሰላምና መረጋጋት ርቋት በንጹሃን ደም የታጠበች መንግስት አልባ ጦር ሜዳ ከሆነች ከሁለት ዓስርት አመታት በላይ አስቆጥራለች። ሟቹ አቶ መለስ የቆሰቆሱት የሶማሊያ ችግር እስካሁን አልበረደም፤ የኢትዮጵያን ጦር ጨምሮ ከተለያዩ አፍሪካ ሃገራት የተውጣጡ ወታደሮች የሶማሊያን ሰላምና ጸጥታ ለማስከበር እያደረጉ ያለው ጥረት መና ቀርቶ የእሳቱ ወላፈን ድንበር ተሻግሮ ለዜጎቻቸው ጦስ እስከ መሆን ርቆ የሄደበት አጋጣሚ የሰላም … [Read more...] about አልሸባብ አይሲስን ሊቀላቀል ነው
“ከሞቱት ያልሞትነው!”
'' ….. የለቅሶና የብዙ ዋይታ ድምፅ በራማ ተሰማ፤ ራሔል ስለ ልጆችዋ አለቀሰች፤ ልጆችዋ ስለሞቱባት መጽናናት እምቢ አለች።…." /ማቴዎስ 2፡18/ ኮንፊሽየስ ወደ ጫካ በመሄድ ግዜውን ማሳለፍ ይወድ ነበር ይባላል። ከዕለታት እንድ ቀን እንደተለመደው ወደ አንድ፤ ከአካባቢው 'ርቆ ወደሚገኝ ጫካ አመራ። ከሰዓታት ጉዞ በኋላ ጥቅጥቅ ባል ጫካ ውስጥ እንደደረሰ ለማርፍ ሲሞክር የገጠመው፤ የተለመደው የወፎች ዝማሬና የአበባወችና የዛፎች ውብ ማዕዛ ሳይሆን እጅግ አሳዛኝ ፣ የለቅሶና የሲቃ ድምጽ ነበር። ኮንፊሽየስ የሰማውን ማመን እያቃተው ወደዚያው አመራ፤ ወደ ድምጹ እየተጠጋ ሲሄድ፤ አንዲት ሴት ሳሩን እየነጨች መሬቱን እየቧጨረች የ ''ኤሎሄ'' ዋይታ ታስተጋባለች። ራሱን ለመቆጣጠር እየሞከረ ቀስ እያለ ተጠጋት። ሊያጽናናትም ሞከረ። ግን የምትጽናና ሴት ሁና አላገኛትም። ይሁን እንጂ በዚህ … [Read more...] about “ከሞቱት ያልሞትነው!”
ሽብርን በማሸበር!!
* ሕዝብ ዋስትናና መተማመን አጥቷል ረቡዕ ዕለት ኢህአዴግ በጠራው ሰልፍ ዜጎች ስሜታቸውን ሲያንጸባርቁ የተሰጣቸው ምላሽ ሽብርን በአሸባሪነት አመጣጥኖ የመመለስ አይነት እንደሆነ ተጠቆመ፡፡ የሰላማዊ ሰልፉ አጠቃላይ ገጽታና የሕዝብ ስሜት በአገሪቱ የዋስትና ማጣት ስሜት እየገዘፈ መሄዱን የሚያሳይ ሆኗል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ ሊታረድ ነው፤ በሰሜን አሜሪካ የሥራ ጉብኝት እያደረጉ ባሉት ይልቃል ላይ እዚያው እንዲቀሩ ተጽዕኖ ይደረጋል ተብሏል፡፡ በአይሲስ የታረዱትና የተረሸኑትን “ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን እያጣራሁ ነኝ” ሲል የነበረው ኢህአዴግ እንዴት እንዳጣራ ለሕዝብ ባያሳውቅም ወዲያው ሕዝባዊ ለመሆን በመመኘት በአገሪቷ ላይ የሐዘን ቀን ከማወጅ በተጨማሪ ሕዝቡ ሰላማዊ ሰልፍ እንዲወጣ ጥሪ አድርጎ ነበር፡፡ አንድ የጎልጉል አስተያየት ሰጪ “ሕዝቡ ለ24 ዓመታት በሐዘን ላይ ነው ሦስት ቀንማ … [Read more...] about ሽብርን በማሸበር!!









