የሃዘኑ ድባብ ከመብራቱ መቆራረጥ ጋር ተዳምሮ ጨለማውን አብሶታል። የአሁኑ መብራት መቋረጥ ግን ከወትሮ ፈረቃ ለየት ያለ ነው። ሆን ተብሎ የተደረገ ይመስላል። ከጥቂት ስፍራ በስተቀር ሁሉም ቦታ በአንዴ እንዲጠፋ ነው የተደረገው። ከሬድዋን ሁሴን እና ከሃይለማርያም የቴሌቭሽን ዲስኩር በኋላ ሃገሩ ሁሉ ጨለማ እንዲሆን አደረጉ። ይህንን ለማድረግም በቂ ምክንያት ነበራቸው። ሃዘን ያልወጣለት ህዝብ አደባባይ ወጥቶ በአረመኔ ወታደሮች ሲቀጠቀት በማህበራዊ ድረ-ገጽ እንዲታይ አልተፈለገም። ህዝቡ እርስበርስ መረጃ እንዲለዋወጥ መፍቀዱም አደጋ አለው። ስልኩም ጠፋ! ለጥቂት ጉልበተኞች ግን ይህ መብራት ከቶውንም አይጠፋም። ግዜው እስኪደርስ፣ የሚመኩበት ጉልበታቸው እስኪፈታ ድረስ ይበራል። እስከዚያው ብዙሃኑ በጨለማ ይኖራሉ። የአቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ንግግር ግን ከቴድሮስ አድሃኖም ጋር ትንሽ … [Read more...] about የሃዘኑ ድባብ በዱላ ታጅቦ. . .
CREW Condemns the Massacre of Innocent Ethiopians by Extremists
Center for the Rights of Ethiopian women (CREW) strongly condemns the brutal murder of Ethiopian Christians in Libya and the recent xenophobic attacks of Ethiopians and other African migrants in South Africa. Thirty Ethiopians were brutally murdered by ISIS in Libya. Half of them were beheaded at a Libyan shoreline and the other half were shot dead in southern Libya, hundred miles from the shores. The released video showing the mass brutal killing refers to victims as those “belonging to … [Read more...] about CREW Condemns the Massacre of Innocent Ethiopians by Extremists
ቀላጤ ሬድዋን – ፖሊሶቹ “ኢትዮጵያውያን መሆናቸው” ይጣራልን!
አፈቀላጤ ሬድዋን “ጥቂት” በማለት የጠሯቸው ነገር ግን በዓለምአቀፍ ሚዲያ በብዙ ሺህ ተብሎ የተዘገበው የተቃውሞ ትዕይንት ከቪዲዮ ምስሎች ላይ ያውጣጣነው ፎቶ በዚህ መልኩ አቅርበነዋል፡፡ ቀላጤ ሬድዋን 7ፖሊሶች መደብደባቸውን ሲናገሩ ፖሊሶቹ ስላሸበሩት ሕዝብ ግን ምንም አለማለታቸው “እንዳያስገመግማቸው” ያስፈራል፡፡ ከ“ምርጫው” በኋላ የሚመጣውን የፈሩ ይመስላል ቀላጤ ሬድዋን ኅያዋንን ብቻ ሳይሆን ሰማዕታትንም ዜግነት በመንፈግ ትጋታቸውን ጨምረዋል፡፡ ስለዚህ ደብዳቢ ፖሊሶቹ “ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን ያጣሩልን” እንላለን፡፡ ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን … [Read more...] about ቀላጤ ሬድዋን – ፖሊሶቹ “ኢትዮጵያውያን መሆናቸው” ይጣራልን!
“እኛን ያዳኑን ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ናቸው”
አይሲስ በሊቢያ ተጨማሪ ኢትዮጵያውያንን መያዙን ከአይሲስ ያመለጠው ኢትዮጵያዊ ለቪኦኤ ገለጸ፡፡ እርሱንና ሌሎችን በአይሲስ እንዳይወሰዱ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ማስጣላቸውን ተናገረ፡፡ ይኸው ስሙ እንዳይገለጽ የጠየቀው ወገን እንደተናገረው እኛን ከአይሲሲ ያዳኑን ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ናቸው፤ በሀገራችን በፍቅር ነው የኖርነው ክርስቲያኖቹን ለይታችሁ አትወስዱም በማለት ሙስሊሞቹ እንደተከራከሩላቸው፤ እንደጮሁላቸው አስረድቷል፡፡ በዚህም ምክንያት እርሱና ሌሎች ላሁኑ ከመሞት ተርፈዋል፤ ከዚህ ወዲህ የሚሆነውን ግን ለመናገር እንደማይችልና ሁሉንም “እግዚአብሔር ነው የሚያውቀው” በማለት በእምነት እየጠበቁ መሆናቸውን ከተሰወረበት ቦታ ለአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ ጋዜጠኛ ተናግሯል፡፡ ይኸው ከአይሲስ ያመለጠው ኢትዮጵያዊ ከዚህ በፊት ቤንጋዚ ላይ ከሌላ የትግራይ ተወላጅ ጋር ተይዘው በኤሌክትሪክ … [Read more...] about “እኛን ያዳኑን ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ናቸው”
ከሰማያዊና ከአንድነት ሰሜን አሜሪካ የድጋፍ ድርጅቶች ማህበራት የተሠጠ መግለጫ
በዚህ ባሣለፍነው ሣምንት በኢትዮጵያውያን ላይ በሊቢያና ደቡብ አፍሪካ የደረሰው እጅግ በጣም ዘግናኝ ጭካኔ የጅምላ ግድያ ማለትም በሊቢያ ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖችን ወደ ዕስልምና እንዲቀየሩ ጠይቀዋቸው እምቢ ስላሏቸው ብቻ ግማሾቹን በቢላዋ አንገታቸውን አርደዋቸዋል፡፡ ግማሾቹን ደግሞ በጥይት እራሣቸውን በመምታት ሠላሳ(30) ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖችን በግፍ አይስል (ISIL) ተብሎ በሚጠራው የእስላማዊ አሸባሪ ቡድን ተሰውተዋል፡፡ በደቡብ አፍሪካም እንዲሁ ኢትዮጵያውያን ሰደተኞች ላይ ቤንዚን በማርከፍከፍ ከተሽከርካሪ ጐማ ጋር በማሰር ሦስት ኢትዮጵያውያን በእሣት ተቃጥለው እንዲሞቱ ተደርጓል፡፡ በደቡብ አፍሪካ ኢትዮጵያውን ስደተኞችን በእሣት ያቃጠሉት የደቡብ አፍሪካ ጥቁር ዜጐች ናቸው፡፡ በሁለቱም አገሮች የደረሰው አሠቃቂው የኢትዮጵያውያን ጅምላ ሞት ምከንያት ስር መሠረቱ ቁጥጥር ያጣው … [Read more...] about ከሰማያዊና ከአንድነት ሰሜን አሜሪካ የድጋፍ ድርጅቶች ማህበራት የተሠጠ መግለጫ
“ሕገወጦቹ!”
አይሲስ አሰቃቂ ግድያ የፈጸመባቸው ወገኖቻችን ቤተሰቦች መርዶ ሰምተው ሃዘን ተቀምጠው ባሉበት ወቅት ኢህአዴግና “የፌስቡክ የልማት አርበኛ ሚኒስትሮቹ” “ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን እያጣራን፤ እስካሁን አላረጋገጥንም” እያሉ ያላግጡ ነበር፡፡ አዲስ አድማስ እንዲህ ይላል፡- “በአዲስ አበባ የኢያሱ ይኩኖአምላክ እና የባልቻ በለጠ ቤተሰቦች ድንገተኛ መርዶ የደረሳቸው እሁድ እለት ነው። በሰላሳዎቹ ዕድሜ ላይ የነበሩት ኢያሱና ባልቻ በአንድ ሰፈር ውስጥ ያደጉ ጎረቤታሞች ናቸው - በቀድሞው ወረዳ 21 ቀበሌ 25፤ በአሁኑ ወረዳ 10። የሟቾቹ ቤተሰቦች መኖሪያ ቤት አጠገብ ለአጠገብ ስለሆነ ለቅሶውም አንድ ላይ ነው፡፡ “ኢያሱና ባልቻ የዛሬ ሁለት ወር ገደማ ወደ ሊቢያ የሄዱት አንድ ላይ እንደሆነ የገለፀልን የኢያሱ ወንድም፤ የሊቢያውን የግድያ ወሬ የሰማው እሁድ ዕለት ነው - ስልክ ተደውሎ። … [Read more...] about “ሕገወጦቹ!”
“ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን ለማረጋገጥ እንሞክራለን”
እንደ ሚዲያ ወይም እንደ ጋዜጠኛ ሳይሆን እንደ ሰብዓዊ ፍጡር ይህን እንጽፋለን፡፡ እንደ ክርስቲያን ወይም እንደ ሙስሊም ሳይሆን እንደ አንድ ሰው ይህን እንናገራለን፡፡ ሰብዓዊነት ከሙያ በላይ ነው፡፡ ሰብዓዊነት ከሃይማኖት በላይ ነው፡፡ ሰብዓዊነት ከዘር በላይ ነው፡፡ ሰብዓዊነት ከምን ዓይነት መጠሪያ በላይ ነው፡፡ በሊቢያ የሚገኘው የአይሲስ ተወካይ ቡድን 30 ኢትዮጵያውያንን አረደ፤ በጥይት ረሸነ፡፡ የዓለም ዜና ማሰራጫዎች ዘገባውን አቀረቡ፤ ኢትዮጵያውያን መታረዳቸውን አወጁ፤ ዓለም ቪዲዮውን ተመለከተው፤ ዜናውን አነበበው፡፡ እኛም በሃዘንና በእንባ አንብበነዋል፤ ተመልክተነዋል፤ (ፎቶም ሆነ ቪዲዮውን እዚህ ላይ አንለጥፍም)፡፡ ኋይት ሃውስ እንኳን መግለጫ ሰጠ፤ ድርጊቱን ኮነነ፤ ከሰብዓዊነት በታች፤ ዘግናኝ፣ ፍጹም አረመኔያዊ፣ ጨካኝና ስሜት አልባ በማለት አወገዘው፡፡ ኢትዮጵያውያኑ … [Read more...] about “ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን ለማረጋገጥ እንሞክራለን”
“በሃይማኖት ማስገደድ የለም!”
የፌስቡክ ወዳጃችን Abubeker Siraj ከዚህ በታች ያለውን ጽሁፍ ከመልዕክት ጋር ልከውልናል፤ ሁሉንም እንዳለ አቅርበነዋል፡፡ ለፌስቡክ ወዳጃችን Abubeker Siraj ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ ሰላም እና በረከት ቅኑን መንገድ በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን ጎልግሎች ሆይ! እኔ አንድ አንባቢያቹ ነኝ ከአዲስ አበባ። ፅሁፎቻቹን አነባለው አደንቃለው። ከምንም በላይ አገር ወዳድነታችሁ እና ሚዛናዊነታችሁን ሳላደንቅ አላልፍም። ዛሬ አንዲት ጉዳይ ላወራቹ ፈልጌ ነበር። እሱም አሁን ከዚህ በታች ያለው ሊንክ ላይ የሚገኘው የወንድሜ ኢብኑ ሙነወር (Ibnu Munewor) ፅሁፍ የሚያጠነጥነው ሰሞኑን አይ ኤስ አይ ኤስ በፈፀመው ዘግናኝ ኢ ሰብአዊ ተግባር ላይ ሲሆን በጥቅሉ እኛ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ከዚህ አፀያፊ እና ዘግናኝ ተግባር ፍፁም የፀዳን መሆናችንን እና ከክርስቲያን ወገኖቻችን … [Read more...] about “በሃይማኖት ማስገደድ የለም!”
መፍትሔው የአማራ ተራድኦና የዕርቅ ድርጅት አይደለም
ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ! … [Read more...] about መፍትሔው የአማራ ተራድኦና የዕርቅ ድርጅት አይደለም
ጨለማው ሳምንት
ወጣት እየሩሳሌም አስፋው እንደወትሮው ቴሌቭዥን ከፍታ እየተመለከተች ነው። ብርቱካንማ ቱታ የለበሱና፣ እጆቻቸው የፍጢኝ የታሰሩ ወጣቶች በአሸባሪዎች ታጅበው ሲጓዙ ያሳያል ቴሌቭዥኑ። ለእርድ ከተሰለፉት ወገኖች ፊት ለፊት ላይ ያለው የእየሩሳሌም ወንድም ነበር። ሌላኛው ወንድሟም ከበስተኋላ ተሰልፏል። እያሱ ይኩኑዓምላክ እና ባልቻ በለጠ፤ ሁለቱም በዚያች ቅጽበት ክቡር ነብሳቸውን በግፈኞች ተነጠቁ። ከሁሉም የከፋ የሚያደርገው ደግሞ ወዳጅ ዘመዶች የነዚህን ወገኖች አስከሬን አግኝተው ለመቅበር እድል እንኳን ባለማግኘታቸው ነው። የሁሉንም ልብ የሚሰብር ክስተት! "ወንድሞቼ ያልፍልኛል ብለው ከቤት እንደወጡ እዚያው በበረሃ ቀሩ።" ትላለች እየሩሳሌም። እትብታቸው የተቀበረባትን ሃገር ለቀው ሲወጡ ጣሊያን ለመግባት ነበር ዕቅዳቸው። አውሮፓን አልመው ቀዬአቸውን ለቅቀው የወጡ እነዚህ ወጣቶች … [Read more...] about ጨለማው ሳምንት










