• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

እውነቱ ይውጣ!

May 2, 2015 04:39 am by Editor 1 Comment

ሴቶችን በወንዶች ፊት፣ ወንዶችን በሴቶች ፊት ልብስ እያስወለቁ የአካላቸውን ክፍሎች ሁሉ ለማየት የሚያስችል እንቅስቃሴ አንዲሠሩ ማስገደድ በሽተኞችን ያስደስታል፤ የምርመራ ዘዴ ግን አይደለም፤ ውርደት እንዲሰማቸው ከሆነ በወራዶች ሰዎች ፊት የምን መዋረድ አለ? ወራዶች እነሱ ደረጃ ላይ ከእነሱ ጋር ያስተካክላሉ አንጂ አያዋርዱም፤ በሌላ አነጋገር ወራዶች አያዋርዱም፤ ወራዶቹ ደንቆሮዎችም ሆነው ነው እንጂ ልብስ የሚያስወልቁ እነሱ ብቻ አይደሉም፤ ሀኪሞችም ልብስ አስወልቀው፣ አጋድመው በጣታቸውም ሆነ በመሣሪያ የፈለጉትን የአካል ክፍል አንደፈለጉ ያደርጉታል፤ ወራዶቹና ደንቆሮዎቹ ከሚያደርጉት የሀኪሞቹ የሚለየው ሀኪሞቹ ሰዎችን ለማዳን ሲሉ ነው፤ ወራዶቹና ደንቆሮዎቹ ግን የራሳቸውን ሱስ ለማርካት፣ የራሳቸውን ህመም ለማስታገስ ነው፤ ወራዶቹንና ደንቆሮዎቹን ከመለዮአቸው አራቁቻቸዋለሁ!

ከነውር በቃላት ወደነውር በተግባር፣ ያውም በመሥሪያ ቤት!

ዱሮ ዱሮ ከቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ቲያትር ፊት ለፊት የአንድ ኢጣልያዊ ቡና ቤት ነበር፤ እዚያ ውጭ ተቀምጠን ቡና ስንጠጣ አንዲት ውብ ሴት ወደጸጉር መሥሪያው ቤት ስትመጣ የሁላችንም ዓይኖች እየዘለሉ እስዋ ላይ ዐረፉ፤ ከሦስታችን አንዱ ስለሴትዮዋ የወሲብ ችሎታ በዝርዝር መናገር ሲጀምር ሁለታችን ተያየንና አፈርን፤ ጨዋታው የጣመለት መስሎት ሲቀጥል የሕግ ባለሙያ የሆነ ጓደኛዬ አቋረጠውና ‹‹ስማ! ይህን ጊዜ እናትህ በአንድ ቦታ ስታልፍ አንዱ እንዳንተ ያለ ስለእርስዋ ችሎታ ያወራ ይሆናል!›› አለው፤ ሊጠጣ ወደአፉ ያስጠጋውን ስኒ ቁጭ አደረገና ተነሥቶ ሄደ፡፡

ሥልጣን ተሰጥቷቸው ሴቶችን ልብስ እያስወለቁ ምርመራ ነው የሚሉ በእናቶቻቸውና በእኅቶቻቸው ላይ ሊደርስ እንደሚችል አይገነዘቡም ይሆናል፤ ደንቆሮ የሚያደርጋቸውም ይኸው ነው፤ የአንዱ እናት አንድ ቦታ ላይ ራቁትዋን ቆማ በሽተኞች ተሰብስበው ሲስቁባት፣ በሌላ ቦታ ደግሞ ጓደኛው የእሱን እናት ወይም እኅት ያንኑ እያደረገ ያስቅባት ይሆናል፤ አንተ በእኔ እናትና በእኔ እኅት አስቅባቸው፤ እኔ ደግሞ በአንተ እናትና በአንተ እኅት አስቅባቸዋለሁ፤ ይህንን እየሠራን ኑሮአችንን እናቃናለን፤ እቤታቸው ሲገቡና ከእናቶቻቸውና ከእኅቶቻቸው ጋር ሲቀመጡና ሲበሉ (?!) ሰው ይመስላሉ፤ እነዚያም ግፉ የተፈጸመባቸው እናቶችና እኅቶች ‹ነውራቸውን› ምሥጢር አድርገው ለሰው ስለማይናገሩ ግፈኞችና የግፍ ሰለባዎች አብረው ይበላሉ!

አሁን ለመጀመሪያ ጊዜ አንዳንድ ሴቶች የደረሰባቸውን ተናገሩ፤ አሁን ያፍራሉ የተባሉት እውነቱን ራቁቱን አወጡትና ከእፍረት ነጻ ወጡ! እውነቱ ሲወጣ የሚያፍረው ማን ነው? ደካማዎቹና የግፍ ሰለባ የነበሩት በጭራሽ አያፍሩም፤ የሚያፍሩት ግፈኞቹ ናቸው፤ የሚያፍሩት የሕዝብን አደራ በማቆሸሻቸው፣ በሥልጣን በመባለጋቸው፣ የሕዝብንና የአገርን ክብር በማዋረዳቸው ያፍራሉ፤ ኅሊናቸው በየቀኑ ነፍሳቸውን አርባ ሲገርፋት እየሳሳች እንቅልፍ ትነሳቸዋለች፡፡

ለመሆኑ በአገሩ ሊቃነ ጳጳሳት፣ ጳጳሳት፣ መነኮሳት፣ ቀሳውስት — ሼሆች፣ ሽማግሌዎች በአገሩ የለንም?

ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም

(ምንጭ: Mesfin Wolde-Mariam Blog)

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Opinions Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. በለው ! says

    May 5, 2015 03:52 am at 3:52 am

    >>>> ለመሆኑ በአገሩ ሊቃነ ጳጳሳት፣ ጳጳሳት፣ መነኮሳት፣ ቀሳውስት — ሼሆች፣ ሽማግሌዎች በአገሩ የለንም? ሊ/ጠበብት መስፍን ወልደ ማርያም..”ዳኛማ ቢኖር!” አሉ እኛ የእኔ አባት…ለመሆኑ ይህ ሁሉ ማዕረጋቸውን የዘረዘሯቸው ከሥም አልፎ በተግባር ቢኖሩን ምንኛ ሀገረ ኢትዮጵያ የተባረከችና የታደለ ህዝብ በሆነ!? እንግዲህ አሁን አውርቶ አደር..አድርባይ..እበላ ባይ…ይህ በደላላ አየር በአየር የተገኘ የትምህርት ወረቀት ጭንቅላታቸውን ያደነዘዘው ምላሳቸው የረዘመ፣ ልባቸው የተደፈነ፣ፈርሃ እግዝሐብሄር የሌላቸው ልማታዊ ወሮ በሎች በበዙበት፣ ክልላዊ ተቧባኞች ዙሪያውን በጥቅማጥቅም (ራዕይ)የተተበተበችና የምትቦጨቅ ሀገር ለመሆኑ በየትኛውን ሕግ፣ ሃይማኖት፣ ባሕልና ወግ ኖረው ለዚህና ለመጪው ትውልድ ይጨነቃሉ…”አሹቅ መብላት ያልፈለገ አንገቱን ለካራ ሰጠ” ይላሉ..፷፪ ሆነው ፬ነጥብ ፱ ሚለየን ብር አዋጥው በሰው ሀገር ከሚገደሉ ለምን ከእኛ ጋር ተጫርተው ከገበያ ውጭ አናደርጋቸውም ነበር” ይላሉ..ሌላው ዓለም ኢትዮጵያውያን ክርስቲያን በሊቢያ በረሃ በጥይትና በሜንጫ ተሰው እያለ ሀዘኑን ሲገልጽ …የኢህአዴግ ቡድን “ማንነታቸው ገና ያልታወቀ ሕገወጥ ስደተኞች፤ “ይህ ለሌላውም ወጣት ጥሩ መማሪያ የሚሆን ነው ብለው ውስጣዊ ደስታቸውን ገልፀዋል!? …ለመታየት በእየአዳራሹ የፀሐይ መነፅር ያደረጉ የአዞ እንባ የሚያነቡ(ዘመነኛ ልማታዊ አገልጋዮች)ጭረሽም ሰማዕታትንና ቤተሰቦቻቸውን ማስታወቂያ መስሪያ አደረጓቸው…የሐዘኑን ድንኳን የምርጫ ካርድ አደሉበት… ለመሆኑ የኋላዊት እመቤት አዜብ ጎላ ልጆቼን በኢትዮጵያ ህዝብ ዕርዳታ እያሳዳግሁ በጋራ ራዕዩን ሳይበረዝና ሳይሸረፍ አስቀጥላለሁ ብለው ለሃጭና ንፍጥ ሲዝረከረክ ታዝበው ለክልላዊ ፎቶ ብቻ ብቅ ሲሉ ለሰማዕታት ለቅሶ ጥቁር ለብሰው ደረት አልደለቁም ጥፍት አሉ።የአዲስ አበባ ሕዝብ ውለታው ይህ ነበር? እንግዲህ አንዳንድ ከጥፋት ተርፈው የተገኙም ሃይማኖታቸውን ጠብቀዋል “ብጹሕ ወቅዱስ አቡነ መቃሪዎስ ለ፳፭ኛ በዓለ ሲመታቸው መታሰቢያነቱ በሊቢያ ለተሰውት እንዲሆን አሳሰቡ!”በሊቢያ የተሰውት ኢትዮጵያውያን ክርስትያኖች “ሰማዕታተ ኢትዮጵያ በምድረ ሊቢያ” በመባል እንዲጠሩና ገድላቸውም በየዓመቱ እንዲዘከር ቅዱስ ሲኖዶስ ወሰነ!!!

    “ማሌሊቶች ሃይማኖተ ቢስ ነን አይሉም! ቃሊቲ እስር ቤት ክርስቶስ በመስኮት ገባ ብለው እያለቀሱ ታምራት ለዓይኔ እንዳያሳዩ “መንግስትና ሃይማኖት የተለያየ ነው” “ሃይማኖታዊ መንግስት የለም!”..የሚሉ ጩልሌዎች ችግሩ ያለው የሃይማኖት ወገንተኝነት/ተጽዕኖ በሌላው ላይ እንዳይኖር ተባለ እንጂ..በነፃ ገበያና በነፃ ሃይማኖት በግብረሰዶም ሀገርና ትውልድ በክሎ አጥፍቶ መጥፋት ሌላ ወንጀል ነው። ግፍ በዝቶ የተረፈበት በከንቱዎች፣ በከሃዲዎችና በእርጉሞች የተወረረች አላግባቡ እየረከሰች ያለች ክብርት ሀገር “አሁን ለመጀመሪያ ጊዜ አንዳንድ ሴቶች የደረሰባቸውን ተናገሩ፤ አሁን ያፍራሉ የተባሉት እውነቱን ራቁቱን አወጡትና ከእፍረት ነጻ ወጡ! እውነቱ ሲወጣ የሚያፍረው ማን ነው? ደካማዎቹና የግፍ ሰለባ የነበሩት በጭራሽ አያፍሩም፤ የሚያፍሩት ግፈኞቹ ናቸው፤ የሚያፍሩት የሕዝብን አደራ በማቆሸሻቸው፣ በሥልጣን በመባለጋቸው፣ የሕዝብንና የአገርን ክብር በማዋረዳቸው ያፍራሉ፤ ኅሊናቸው በየቀኑ ነፍሳቸውን አርባ ሲገርፋት እየሳሳች እንቅልፍ ትነሳቸዋለች፡፡በአርግጥ ለአሁኑ ሆዳቸው ክብራቸው፣ እራቁታቸውን ተወልደው መሬት ላይ ባዶ ቂጣቸውን ተንደባለው ማደጋቸውን እረሱ ከጥጋብ በስተጀርባ እርሃብ፣ ከትምህኪት ጎን ቁርሾ፣ ከበደል ላይ በቀል..ከጭለማውም ባሻገር ብርሃን አለ።ሁሉም ለአምጭው ይከፈላል በለው!

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጃዋርና በቀለ መታሠራቸው ተሰማ June 30, 2020 09:17 am
  • አገራዊ መድረክ ውጪ ድብቅ ውይይትን አንቀበልም June 17, 2020 06:57 am
  • ዴክሳሜታሶን! የኮሮና መድሀኒት June 17, 2020 06:49 am
  • የሰኔ 14ቱ ቀለበታዊ የፀሃይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ! June 17, 2020 06:38 am
  • የግብፅ የአባይን ውሃ ብቻዬን ልጠቀም ግትር አቋም ድርድር እንቅፋት ሆኗል June 10, 2020 07:15 am
  • የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!? April 12, 2020 02:48 am
  • በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሚጠቀሙበት የኤርትራ ስደተኛ ካምፕ ሊዘጋ ነው March 18, 2020 08:37 pm
  • እየተፈረካከሰ ያለው አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ March 18, 2020 08:09 pm
  • ኮሮና አዲስ ጉድ መዘዘ – ከቻይና በፊት በአሜሪካ ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎችን ቀጥፏል March 16, 2020 11:41 pm
  • የኮንዶሚኒየም ቤቶች በደላሎችና በመመሪያ ሰጪዎች ኔትዎርክ እየተቸበቸበ ነው! ታከለ የት ናቸው? March 9, 2020 10:18 am
  • ኤርሚያስ ለገሠ ከባለአደራ ተባረረ March 9, 2020 08:09 am
  • ድፍድፍ ሲቀል ይንሳፈፋል፤ ምሁር ሲዘቅት ይመራል፥ March 7, 2020 11:24 pm
  • ኢትዮጵያዊ ምን ይመስላል? በምንስ ይመሰላል? March 7, 2020 10:29 pm
  • WHY I WROTE “MONEY, BLOOD AND CONSCIENCE” March 4, 2020 11:15 pm
  • አድዋ፤ የጥቁር ሕዝብ ድል! March 2, 2020 11:24 am
  • ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ (አባ ጎራው) March 2, 2020 11:12 am
  • የኦነግ ሁለት መልክና ሦስት ግብሮች – ቃርሚያው ኃይል ቅጥር ነፍሰገዳይ ሆኗል February 25, 2020 11:26 pm
  • በቡራዩ “የጃል ማሮ” ፎቶ ጨረታ አፈናከተ፤ “ቡራዩ ሆኖ ከሃዲን ማሞካሸት አይቻልም” ነዋሪዎች February 17, 2020 09:13 pm
  • “ዲቃላ” የፍረጃ ፖለቲካ በኦሮሚያ የኃይል አሰላለፉን እየቀየረ ነው February 13, 2020 11:58 pm
  • “ከዚህ በኋላ ማናቸውንም በወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን” አንታገስም – ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ February 13, 2020 05:07 pm
  • “እኛ ማንም ተሳዳቢ እንዲመጣብን አንፈልግም” የጅማ ነዋሪ February 13, 2020 09:28 am
  • “ወላጆቻችሁ ሰላማዊ ሰልፍ በሕዝቡ ያስደርጉልን” – አጋቾች February 11, 2020 07:53 pm
  • “ወንጀል የፈጸመም ያስፈጸመም ተይዞ ለህግ ይቀርባል፤ ምርመራም ተጀምሯል” February 11, 2020 06:59 pm
  • ጃዋር ወደ መጨረሻው “የትግል” ስልቱ – አማራን ማበጣበጥ! February 10, 2020 11:54 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule