ኮሳሳ አገዝፎ፣ ግዙፍ አኮስሶ የሾመውን ሽሮ፣ያሻውን አንግሶ በለወጠው አዲስ ክስተተ ሁኔታ ሀዘንና ደስታ፤ ደስታና ሀዘንን አቀያይሮ ቦታ በራሱ ህግጋት ዘመኑን ዳኝቶ ጊዜ ነው የሚኖር ዓለማችን ገዝቶ። ጥቅምት 2009 አብርሃም በየነ … [Read more...] about ያለም ገዥ
Literature
ጽፈኪን
ይረገም!!
በክፉ ያነሳ ወርቃማውን ስምሽን፣ በሃሜት ያጎደፈ ፀዐዳ ክብርሽን፣ በክፋት ፈረሱ ወዳንቺ የጋለበ፣ በእሾኸም ምላሱ ሊወጋሽ ያሰበ፤ ሰላምሽን የነሳ፣ ባንቺ ላይ ሊሳለቅ፣ ሊቀልድ የቃጣ መልካም ህይወት ትክዳው! ነፍሱ ሰላም ትጣ!! ብርሃንሽን ሊያጠፋ ውበትሽን ሊያከስም፣ መዐዛሽን ሊበክል ህይወትሽን ሊያጨልም፣ በክፋት ያቀደ በሻገተ ህሊናው፣ ብርሃኑ ይደፈን ! ጨለማ ይውረሰው! ስትለመልሚ ስትፈኪ አይቶ፣ በአርኪ ፈገግታሽ በቅናት ተውጦ፣ የቆሸሸ እጁን ባንቺ የዘረጋ፣ ሽባ ይሁን ይስለል! አንደበቱ ይዘጋ! የዘመናት ስምሽን ዝናሽን ሊያጎድፍ፣ ከባዕድ አብሮ ወዲያ ሲያነፈንፍ፣ ህይወቱን በሙሉ ሳይሰራ ቁም-ነገር፣ ገብቶ ሲሽሎኮሎክ ከጢሻ ከቆንጥር...፤ ሊነክስ ያደባ የጠባውን ጡትሽን፣ ሊያጠፋ የቃጣ ሃቀኛውን ልጅሽን፣ የታሪክ መጠሪያ ቅርሳ-ቅርስ … [Read more...] about ይረገም!!
“ትራምፕ – ቢመረጥስ?! …”
… በበረዶ፣ በዝናም፣ በሐሩር፣ በቁሩ . . . መፈክር አንግበን፣ ላንቃችን እስኪታይ - አምባገነኖችን በጩኸት አውግዘን፣ የድምጽ-አልባውን ሕዝብ - የጭቆና ብሶት፣ ላለም ስናሰማ - ለሩብ ምዕተ-ዓመት፤ ጆሮ ዳባ ብለው - የተሳለቁብን፣ ከጨቋኝ ወግነው፣ በዶላር አፋፍተው… ነጻነታችንን በጅ-አዙር ያስቀሙን. . .፤ ቦ! ጊዜ ለኩሉ!... የተፈጥሮ አዙሪት-ህግ - የወር-ተራው እዚያም ደርሶ፣ በታላቋ አሜሪካ - “አምባገነን” ትራምፕ ነግሶ፣ ‘የባቢሎን ግምቡን‘ አጥሮ . . . ነጻነትን ፊጥኝ አስሮ፣ ህገ-መንግስት ተሰውቶ. . . ፍርድ ቤቱም ለርሱ አድልቶ...፣ የአሜሪካ ሃምሳ ስቴቶች - ሰላማዊ ሰልፍ ወጥተው፣ በመፈክር ተጥለቅልቀው - በራብ-አድማ ጠቁረው ከስተው፤ በላያችን የወረደ ፣ መብረቅ... ዝናም ወርዶባቸው፣ የነጻነት ረሃብ፣ ጥሙ - ዘልቆ ገብቶ … [Read more...] about “ትራምፕ – ቢመረጥስ?! …”
“… የጦር ኃይል … እና የብእር ኃይል …” ሃዲስ አለማየሁ
" ... ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ አሁን እስካለንበት ድረስ ታሪኩን መለስ ብለን ብንመለከት በሰው ዘር ላይ ግዛታቸውን ለመዘርጋት፣ ሰውን ባካልም ሆነ በመንፈስ ለመግዛት፣ ሁለት ተቃራኒ ኃይሎች ሲታገሉ እናያለን፡፡ ከነዚህ አንዱ የሀይለኞች፣ ያጥቂዎች፣ የጦር ኃይል፣ ሁለተኛው የደራሲያን የብእር ኃይል ናቸው፡፡ "የጦር ኃይል በየጊዜው፣ በየቦታው የሚነሱ ኃይለኞች ሰራዊት አደራጅተው፣ የጦር መሳሪያ አከማችተው፣ ሰውን እየጨቆኑ ለግል ድሎታቸውና ፍላጎታቸው አገልጋይ የሚያደርጉበት እውር ሀይል ነው፡፡ የብእር ኃይል በየጊዜው በየቦታው የሚነሱ ታላላቅ ደራሲያን ከስው ተለይተው፣ ከብእርና ከወረቀታቸው ጋር በየቤታቸው ተዘግተው፣ ምስጢረ ፍጥረትን እየመረመሩ፣ አዳዲስ ነገር እየፈጠሩ፣ ሰውን ከድንቁርና ሰንሰለት ተፈትቶ፣ ከእንሰሳ ባህርያት ጠርቶ፣ የመንፈስና የአካል ነጻነት አግኝቶ፣ ስርአት ያለው … [Read more...] about “… የጦር ኃይል … እና የብእር ኃይል …” ሃዲስ አለማየሁ
“ምጽአተ ዐማራ” አዲስ መጽሐፍ
ይህ መጽሐፍ ባለ 657 ገፆች ነው። በዘጠኝ ምዕራፎች ተከፋፍሏል። እነርሱም፦ የኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት መከፋፈል፣ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ኃይማኖት ተከታዩና ዐማራው የከፈሉት ዋጋ የኢትዮጵያ አንድነት ትንሣኤ፣ የዐማራው የአንድነትና የፀረ-አንድነት ትግል ውጤት ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ፤ የፍፁማዊ ዘውዳዊ አገዛዝ የአንድነት ግንባታ ሂደት ድምድም እና የኢትዮጵያ ዳግም ብተና ጽንስ የለውጥ ፈላጊው ትውልድ የኃይል አሰላለፍ ዘረኛው የትግሬ-ወያኔ ከ1972 እስከ 2007 ዓም ድረስ በዐማራው ነገድ ላይ ያደረሰው የዘር ማጥፋትና የዘር ማጽዳት ወንጀል ስለ ዐማራና ስለ ኢትዮጵያዊነት ምሑራን ምን ይላሉ? የመላው ዐማራ ሕዝብ ድርጅት (መዐሕድ)፦ ዐማራው ላይ የደረሰው ሰቆቃ የወለደው ነፍስ አድን ድርጅት ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት፦ የአሥራት ዘር ፍሬ … [Read more...] about “ምጽአተ ዐማራ” አዲስ መጽሐፍ
ደንቁሩ በአዋጅ!
እግዚአብሔር ዓይንን ፈጠረና እዩበት አለ፤ እግዚአብሔር ጆሮን ፈጠረና ስሙበት አለ፤ እግዚአብሔር አእምሮን ፈጠረና አስቡበት አለ፤ እግዚአብሔር አንደበትን ፈጠረና ተናገሩበት አለ፤ ወያኔ አይሆንም አለ! በዓይንህ አትይ፤ በጆሮህ አትስማ፤ በአእምሮህ አታስብ፤ በአንደበትህ አትናገር፤ አበሻ ተዋረደ! ዓለም እየሰማ ድንቁርና ታወጀበት! ማን ያሸንፋል? እግዚአብሔር አለ፤ ወይስ ወያኔ አለ? (ምንጭ: Prof. Mesfin Wolde-Mariam Blog) … [Read more...] about ደንቁሩ በአዋጅ!
ላም እሳት ወለደች!
አጉል ዘመን ገጥሟት በረት ብትከሳ፤ ከብቶች በመዥገሮች አዩ ብዙ አበሳ፡፡ ጡቶቿን አቃጣይ የነበልባል ጥጃ ላም እሳት ወለደች፤ ብ’ተው በማይተዋ ዘልለው ባልጠገቡ ወይፈኖች ነደደች፡፡ የከበረው ባህል ባለጌ ረጋግጦት እንደጨው ቀለለ፤ ወፍ ዘራሾች ነግሠው ባጥለቀለቁት ደም ምድር ተበከለ፡፡ አዎ፣ ላም እሳት ወለደች! እንደዮዲት ጉዲት እቶኑ የሚፋጅ፤ ዕረፍት በማያ’ቅ ሠይፍ እንደነደርቡሾች እንደግራኝ አህመድ፤ ጭንቅላትን ገምሶ አንገትን ቆራርጦ ዜጎችን የሚያነድ፡፡ “አጥንትና ደሜ ይሄው የናንተው ነው፤ እኔ ከሌለሁኝ እናተም እንዲያው ነው፤ እርቧችሁ ጠግቤ፣ ብድንም ሞታችሁ፤ ማንም ስለሌለ ከኔ ‘ሚለያችሁ፤ እስከመጨረሻው አጅቡኝ ባካችሁ፡፡ ” እያለ እሳት ጥጃው ሕዝብን ይማጠናል፤ መስሎት የማናውቀው ቁርበት ዘርጉ ይላል፡፡ ክፋትና ተንኮል ተፈጥሮው የሆነ፤ ሕግና … [Read more...] about ላም እሳት ወለደች!
ለመለስ የተፃፈ ደብዳቤና የመለስ መልስ
ከፍቃዱ ጌታቸው ለመለስ እንደምን አለህ ጋሼ እንደምን ነህ መለስ ትመጣለህ ስንል ቀረህ ሳትመለስ እኛማ ይሔውልህ ባንተ ሌጋሲና ባንተ ትልቅ ራዕይ በየአደባባዩ እንላለን ዋይ ዋይ ዛሬም ጀነራልህ ተኩስ ነው ትዕዛዙ ወገን ያጋድማል የግፍ አፈሙዙ ለምንድን ነው ስንል ስምክን አስቀድመው ከክርስቶስ በላይ ምስልህን አትመው ቅዱስ መጽሐፍ ይመስል ባንተ ራዕይና በሌጋሲህ ምለው ቢረፈርፉንም አላለቅንምና ደብዳቤ ላክንልህ ከሞት የተረፍነው! ... የሆነስ ሆነና ግን አንተ ደህና ነህ እኛማ ይኸውልህ ደርሰህ ስትናፍቀን አይሞትም የምትል ሙዚቃ ሞዝቀን መቃብርህን ልንስም አበባ ልናኖር ሥላሴ ብንመጣ ፌደራል ያይሃል እስረኛ ይመስል ሾልከህ እንዳትወጣ መቼም ሥላሴ ውስጥ ባለስም ነውና የሚቀበርበት አንተን አየት አርገን ዞር ስንል … [Read more...] about ለመለስ የተፃፈ ደብዳቤና የመለስ መልስ
መሬቱ
ጥምል እየዞረ በሰማዩ ማገር በመሬቱ ዙሪያ ዕውነት የሚናገር ጠባሳው ያልጠፋ የታሪክ አሻራ መሬቱ መሰለኝ ጠላት የሚያፈራ። አገር በቀል ይሁን የሰው አገር ባዕዳ ዐይን እየማረከ የሚጋብዝ እንግዳ ከጥንት ጀምሮ እንደ እሚታወቀው ጠላት የሚያፈራ ለምለሙ መሬት ነው። ለምለሙ መሬት ነው ጦርነት አብቅሎ ቤት አልቦ ያስቀረኝ ከቀዬ አፈናቅሎ። ለም መሆኑ ቀዬ አፈረ - መሬቱ ጠላቶቸን ጋብዞ ዛሬም እንደ ጥንቱ ኮሪያው ይሁን ህንዱ ወይ የዐረቢያው ጉምቱ እንዲያፈናቅለኝ ገፍትሮ በሀብቱ ምክኒያት የሆነኝ ጫካውና ዱሩ ጠላቴ ተግሬ ነው መባቀያ አፈሩ። አያበቅሉ አብቅሎ አያፈሩ አፍርቶ የሚያፈናቅለኝ ተጎጆየ አውጥቶ ተግሬ ነው ጠላቴ ተቆምኩበት ምድር ለምለሙ መሬቴ ገዳይ በሰናድር። ማጣት ዕርዛቴን ሞቴን እንዲፈጥር ተፈጥሮው አድርጎት የቆምኩበት ምድር ለምላሜ ለብሶ ሜዳ … [Read more...] about መሬቱ
እናቶች፣ “ሶሻል ሚዲያ”ና ህወሃት/ኢህአዴግ
አዲስ አበባ የሰፈር ሴቶችን ሰብስበው መግለጫ ስለ social media አጠቃቀም ስጡ ተብለው የሰጡት መግለጫ እና ከመግለጫው በኋላ ለእናቶች የተደረገ ኢንተርቪው። ዜና FBC ፦ “መንግስት በሶሻል ሚዲያው ላይ ህዝብ የሚቀሰቅሱትን ጸረ-ሰላም ሃይሎች ከሚኖሩበት አገር ጋር በመመካከር ለህግ ማቅረብ አለበት!” ሲሉ ነዋሪነታቸው በቀበሌ 07 ልደታ ክከ የሆነ እናቶች ተናገሩ ... ↩ ከዜናው በኋላ የእናቶች ኢንተርቪው፦ ☞ የመጀመሪያዋ ተጠያቂ እናት (በግምት ከ 60 - 65 አመት እድሜ)፦ ጋዜጠኛ፦ እናት ለቃለ መጠይቅ ፈቃደኛ ስለሆኑ አመሰግናለሁ እናት፦ እኔም አመሰግናለሁ እልልልልል ... ጋዜጠኛ፦ ምነው እናት? እልልታው ምንድነው?? እናት፦ የገደሉት ለህግ ይቅረቡ አይደለም እንዴ ሲባል የነበረው??? ጋዜጠኛ (በድንጋጤ ክው ብሎ)፦ የለም የለም እናቴ ሶሻል ሚዲያ ነው … [Read more...] about እናቶች፣ “ሶሻል ሚዲያ”ና ህወሃት/ኢህአዴግ










