የምሁር መሃይም - ተባይ አላዋቂ፤ የመሃይም ኩፍስ - አስመሳይ አዋቂ፤ የጅብ ባለ ጊዜ - ታፋ መራጭ ከሽንጥ፤ ያንበሳ ልክስክስ - ልፋጭ የሚያላምጥ የቁራ ዕርግብ መሳይ - ሠላምን አብሳሪ፤ የፈረስ አዝጋሚ - የግመል ሰጋሪ፤ ንጹህ ሰው ታሳሪ - በፈጠራ ወንጀል፤ ፍርደ ገምድል ዳኛ - ፈራጅ በቂም በቀል፤ የባዕድ ባለቤት - የነባር ባይተዋር፤ ሥልጡን ሥራ ፈቶ - ሞያ ቢስ ሲገብር፤ ልማድ ሆኖ ቀረ - አቀርቅሮ መኖር፤ በተወሇድንባት በጦብያ ምድር :: (ሙሉውን ግጥም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about ጀግና ውለጅ እባክሽ !
Literature
ጽፈኪን
ይድረስ ለእኛ—ከእኛ!
ይድረስ ለእኛ-ከእኛ! - ከላይ ልጀምር ካ’ናቱ፣ በብረት ኃይል ተከቦ - ከተኮፈሰው በከንቱ፣ ይድረስልኝማ ለወያኔ - ለጊዜያዊው ባለጉልበቱ፤ … “ለሕዝባዊነት መጣሁ” ብሎ - ሕዝብን በጥይት መቁላት የለምና፣ አቆልቁለህ እየውማ - የምትሄድበትን ጎዳና! የጭካኔ መጠንህ ጫፍ ደረሰ - የውሸት ቋትህ ሞላ፣ የ’እውቀት‘ ገደብህ አበቃ - ከእንግዲህ ላይኖርህ የቀረ ‘መላ’፣ ከወደቁ ወዲያ መንፈራገጥ.. እንዳይሆን ለመላላጥ፣ ሳሩንም ላለመጋጥ.. መሬቱንም ላለመናጥ…፣ ከአውሬነት ባህል ተላቆ - ሰውነትን ይሻልና፣ ይድረስ! ይድረስ! እልሃለሁ፤ ይድረስ! እንደገና፤ ዛሬ እንኳን እንደማመጥ - ይቅርብህማ ወንድሜ፣ በግፍ ተሞልተህ ጉዞ - ላይሆንህ መልካም ዕድሜ፣ “አበቅቴ ውሉን ሳይስት” - የአመሻሽ ጀንበር ሳትጠልቅብህ፣ ቆም ብለህ ማሰብ ጀምር - እንደ “ጆቤ”ህ፣ እንደ … [Read more...] about ይድረስ ለእኛ—ከእኛ!
አባተ መኩሪያ “ተንቀሳቃሹ ቴአትር ቤት” (1932 – 2008)
‹‹ጥበበኛ በጥበብ እግር ይመላለሳል›› (ጠቢብ የሐውር በእግር ጥበብ) እንዲሉ፣ አባተ መኩሪያ ከግማሽ ምታመት በዘለለ በኢትዮጵያ ቴአትር ሕዋ ውስጥ በጥበብ ለጥበብ ኖሯል፡፡ ለቴአትር እስትንፋሱ ነበርም ይሉታል፡፡ በርሱ ጥበብ ያለፉት ሁሉ፡፡ በጥበብ የባተው አዘጋጅ፣ የውዝዋዜ አሠልጣኝ (ኬሪዮግራፈር)፣ ጸሐፌ ተውኔት፣ የፊልም አዘጋጅ የነበረው አባተ መኩሪያ በአገሪቱ የቴአትር ታሪክ ውስጥ ስማቸው በግዘፍ ከሚነሱትና አሻራቸውን ካሳረፉ በኩሮች አንዱ ነበር፡፡ በተለይ በተውኔት አዘጋጅነት ስመ ጥር ለመሆኑ ዘመን ተሻጋሪ ተውኔቶችን ወጥ እና ትርጉሞች በማዘጋጀቱ ይጠቀሳል፡፡ ከታዋቂ ሥራዎቹ መካከል ሀሁ በስድስት ወር (1966) አቡጊዳ ቀይሶ (1971)፣ መልእክተ ወዛደር (1971)፣ የመንታ እናት (1971)፣ መቅድም (1972)፣ ጋሞ (1973)፣ አሉላ አባነጋ (1979) ይጠቀሳሉ፡፡ … [Read more...] about አባተ መኩሪያ “ተንቀሳቃሹ ቴአትር ቤት” (1932 – 2008)
“ሰው አይደለም ! …” አለኝ
ገና ቁጭ እንዳልኩኝ ቀጥሮኝ እንዳገኘኝ እከሌ ጨርሶ «ሰው አይደለም!» አለኝ ምነው? ምን አ’ረገህ ? «ሰው አይደለም!» ስልህ እኮ! ምን አ’ረገህ? «ሰው አይደለም!» አልኩህ። ቢራችንን አዘን በዝምታ ቆየን እንደገና ደግሞ ሳሉን እየሳለ አንገቱን ነቅንቆ «ሰው አይደለም!» አለ። ሰው ይመስላል አልኩኝ ስሜቱን ልረዳ ፊቱን መረመርኩኝ ባ’ይኑ እየገረፈኝ አይምሰልህ! አለኝ ግንባሩ ታጠፈ ጥርሶቹን ነከሰ ጠረጴዛ መታ፣ ቢራችን ፈሰሰ ልጠራርግ መጥታ - ልጅት እያየችኝ በፊቷ ምልክት ምን ሆኗል? አለችኝ መዳፌን አሳየሁ፣ ከንፈሬን አስረዘምኩ እኔም ልክ እንደሷው በምልክት መለስኩ እሱ ግን ቀጠለ «ሰው አይደለም» ማለት «ሰው አይደለም!» አልኩኝ እኔም ተመቸሁት በቢራ ተራጨን በውስኪ ታጠብን ስሙን እያነሳን «ሰው አይደለም!» አልን። ልጅትም … [Read more...] about “ሰው አይደለም ! …” አለኝ
አባቱን ነገረኝ
በአባቱ ወንበር ላይ ሳሎን ተቀምጦ በባዶ ግድግዳ ተግ ብሎ አፋጦ የፊቱን ሁኔታ እየለዋወጠ ትካዜ ተጭኖት ቃላት እያማጠ ዓይኑን አጨንቁሮ እየመረመረኝ እንደዚህ እያለ አባቱን ነገረኝ አባቴ... አባባ ኤጭ! አለ ፊቱን አጨማዶ ሁሉን ነገር ጠልቷል ውስጡ ሆኗል ባዶ በምሬት ኮምትሯል ... በጥላቻ በግኗል ... አስሬ ኤጭ! ይላል አባባ ኤጭ! አለ እንደገና ደግሞ በሳሎኑ መሀል ተገትሮ ቆሞ እንደገና ደግሞ ቁጭ አለ አንገት ደፋ ካፍጫው አወጣ እምቅ አየር ተፋ ኤጭ! አለ እንደገና ተነሳና ቆመ ሽቅብ አንጋጠጠ ጣሪያው ላይ ቆዘመ የአባባን ንዴት ይቺን አላውቃትም ከወትሮው ተለየች ብዙ አልወደድኳትም አባባ አሳዘነኝ አዝኜም ፈራሁት ምን ሆንክ? አይባልም በንዲህ ያለ ንዴት አባባ ዓይኑ ቀላ ስሩ ተገተረ በአንድ ጊዜ አረጀ ሀያ ዓመት ጨመረ እንደዛ … [Read more...] about አባቱን ነገረኝ
አማኒ ኢብራሂም — “ያልታወቀው” የጥበብ ሰው!
“... ሰው እያለ አጠገባችን፣ ቅንነቱን ማየት ሲያመን ከኛው አብሮ በህይወት ቆሞ፣ መልካም ስሙን መጥራት ሲያንቀን፣ “ሰው ካልሞተ ወይ ካልሄደ አይነሳም” እንላለን። እንዲህ እያልን፣ ስንቱን ጠቢብ እየሸኘን፤ አበባውን ቀጥፈን ጥለን፣ አበባ እናስቀምጣለን!!” መቼም ያለ-ግጥም ፍቅር መኖር የሚሆንልኝ አይመስለኝም። ዛሬ ግን ብዕሬን ያነሳሁት ግጥም ለመጻፍ ባለመሆኑ፣ እነሆ ! የነብይ መኮንን የሆነችውን ይህቺን ግጥም፣ ለተነሳሁለት የጽሁፍ ጭብጥ እንደ መግቢያ ሆና ታግዘኝ ዘንድ ተዋስኩ። ገጣሚ ነብይ መኮንን ይህቺን የቁጭት ስሜት አስተናጋጅ የሆነች ግጥም በመታሰቢያነት ያበረከተው፣ ለእውቁ ሰዓሊና ገጣሚ ገብረክርስቶስ ደስታ ነው። ያ! ድንቅ ኢትዮጵያዊ ሰዓሊና ገጣሚ ደግሞ በመጨረሻው የህይወት ዘመኑ፣ በስደት ባክኖ፣ በሰቀቀን ተጀቡኖ ያለፈው በአሜሪካ—ኦክላሆማ ግዛት ውስጥ … [Read more...] about አማኒ ኢብራሂም — “ያልታወቀው” የጥበብ ሰው!
አስርቱ አምባገነናዊ ትዛዛት!
"እኔ ስላንተ በበረሐ ደሜን አፍስሻለሁና ከእኔና ከአጋሮቼ በቀር ሌላ የፖለቲካ ፖርቲ በቃልህ አትስበክ በልብህም አትመን"፤ "መንግስት የኛ ናትና ወደ መንግስት አትመልከት ስልጣኑንም አትመኝ"፤ "የባለስልጣናትን ጥፋት ... የዜግነት መብቱንም በሶሻል ሚዲያ የተቸ እሱ ወዮለት፤ የባለስልጣን ሚስትም ቅምጥም ሃብትም የማይነኩ፤ የማይደፈሩ "ቅዱስ" ናቸውና ትንፍሽ እንዳትል!! ...." "ከደርግ ጨካኝ አገዛዝ አውጥቼሃለሁና... በፍፁም ልብህ በፍፁም ሃሳብህ ለእኔ ብቻ ተገዛ"፤ "ብሰርቅም፤ ባስርም፤ ብገድልም እንዳለየ እለፍ ... መብራት ቢጠፋ፤ ውሃ ቢቋረጥ ... አርፈህ ተቀመጥ"፤ "እኔ ልማታዊ መንግስትህ በስራዬ ፍፁም የማልሳሳት ነኝና በማስተዳድራት አገር ለሚደርስ ጥፋት ሁሉ የኤርትራን መንግስት ርገም"፤ "ከእኔ አርማ በስተቀር በሰማይ ይሁን በምድር እንዲሁም … [Read more...] about አስርቱ አምባገነናዊ ትዛዛት!
ስለቴክኖሎጂ ሊያነጋግር የከጀለ መጽሀፍ
የዛሬዋ ዓለማችን በደረሰችበት የእድገት ደረጃ ስልጣኔን ወይም ብልጽግናን ከቴክኖሎጂ ለይቶ ማየት ያስቸግራል። የሰለጠነ ህብረተሰብ ማለት ቴክኖሎጂን ያዳበረ ህብረተሰብ ማለት ነው። ባንጻሩም ቴክኖሎጂን ያላዳበረ ህብረተሰብ ማለት ደግሞ ያልበለጸገ ህብረተሰብ ነው። የሰለጠነ ህብረተሰብ ስንል ደግሞ ድኅነት የተረታበት፤ በሽታ የመነመንበት፤ ትምህርት የተስፋፋበት (እውቀት የለመለመበት)፤ ዲሞክራሲ የሰፈነበት፤ የመገናኛና ቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት በስፋት የተንሰራፋበትና ህግ የበላይ የሆነበት ህብረተሰብ ማለታችን ነው። ቴክኖሎጂ እላይ ለተጠቀሱት ለሰው ልጆች አስፈላጊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ አዎንታዊ የሆነ ቀጥተኛ አስተዋጽኦ አለው። ይሄን ሲይደርግ ግን ቴክኖሎጂ ከህብረተሰብ ውጪ ሆኖ በታዓምር ወይም ትእዛዝ በመስጠት ሳይሆን በአንድ ህብረተሰብ ውስጥ የሚኖሩ ዜጎች የሚተገብሩት፤ ሌሎች የህብረተሰብ … [Read more...] about ስለቴክኖሎጂ ሊያነጋግር የከጀለ መጽሀፍ
ልዩ ጥበብ ገንባ
ፍቅር ታሞ ከርሞ አልጋ ላይ እንደሰው ብዙ ዘመን ሆነ ሞቶ ከቀበርነው ይሄ ሆኖ እያለ ሞቱን እያወቅን ለአያሌ ዓመታት ዘፋኞች በዘፈን አሁንም እንዳለ ህይወት እስትንፋሱ ጨርሶ እንዳልሞተ እንዳልወጣች ነፍሱ አድርገው ሲዘፍኑ ሲያቀብሉን ውሸት ነገሩን ዋጥ አድርገን አብረን ጨፈርንበት ከሁሉ ‘ሚገርመው የሚደንቀው ነገር አለ የሚባለው የአሁን ዘመን ፍቅር ገንዘብን ውሃልክ አ’ርጎ ተመስርቶ በዓይናችን እያየን መካካዱ ከፍቶ ዘፋኙ ተነስቶ ሲለን ፍቅር ፍቅር በሆታ በስክስታ የኛ አብሮ ማጫፈር ከ «እማትበላ ወፍ»«እዘበናኝ» ድረስ ሆዴ አንጀቴ እያለ ተሸክሞ እንደ ውርስ ወጣቱም ያንኑ ሲያማስል ሲያቁላላ ስለከረመበት ሳይቀይር በሌላ ያወጣው ሙዚቃ ሳይሰማ ጣፍጦ ዘፈኑ ይሞታል ዘፋኙ ተቀምጦ ይህ ሁሉ ሲሰራ ይህ ሁሉ ሲፈጠር እስከዛሬ ቆየን ምንም … [Read more...] about ልዩ ጥበብ ገንባ
እግርና ጫማ
እግርና ጫማ ተጣብቀው አንድ ላይ በክር ተሳስረው አብረው ውለው ስታይ እውነት አይምሰልህ ያ ሁሉ ፍቅራቸው ሲመሽ ወደማታ ሄደህ ብታያቸው በአንሶላ መካከል እግር ተዘርግቶ ጫማ በራፉ ላይ ወድቋል አፉን ከፍቶ! … [Read more...] about እግርና ጫማ










