Literature
ጽፈኪን
“አንተስ…?”
ዓይኔን በዓይኔ ያየሁበት፣ በስተእርጅና ያገኘሁት፣ የትናንቱ ማሙዬ፣ ያሳደኩት አዝዬ የንግሊዞችንወረራ ሰምቶ፣ በቴዎድሮስ ሞት ተቆጥቶ፣ ለምን? ለምን ሞተ? ብሎ ሲያለቅስ፣ የዓይኑን ዕንባ ላደርቅ- የልቡን መሰበር ላድስ፣ ጀግኖቻችንን ቆጥሬ- ታሪካችንን ባወድስ፣ ዕንባውን ዋጥ አድርጎ- በአትኩሮት ዓይኔን እያየኝ፣ «አንተስ...?» አንተስ!- ምን ሰርተሀል? በማለት ጠየቀኝ። እድሜ ቢደራረብ ተግባር ሳይላበስ፣ እንደዚህ እንደኔ ያስጠይቃል ለካስ! (ወለላዬ) … [Read more...] about “አንተስ…?”
ላንዲት መስቲካ ሻጭ ህጻን
በደብተርሽ ምትክ ትንሽ ሱቅ ታቅፈሽ ካልፎሂያጅ እግር ስር፤ እንደ ድንቢጥ ከንፈሽ ጋሼ ግዙኝ ስትይ፤ ኣንጋጠሽ ወደ ላይ ለጉድ ተጎልቸ፤ ምታረጊውን ሳይ ራሴስ ይታመም፤ ምላሴን ምን ነካው ግራዋ ይመስል፤ መረረኝ ማስቲካው:: ኣፈር ጠጠር ለብሶ ፤በዶዘር ተድጦ መስኩ ከነጎርፉ ሰማይ ከነዶፉ ለጌቶች ተሽጦ ኣተር ነው እያሉ፤ ኣፈር ዘግኖ መፍጨት ገነት ነው እያሉ፤ መስክ ላይ መፈንጨት ጠበል ነው እያሉ፤ ተጎርፉ መራጨት ይህንን ማን ሰጦሽ ገና በልጅነት፤ ልጅነት ኣምልጦሽ፡፡ በምቢልታ በዋሽንት፤ በከበሮ ታጥሮ በክራር ተማግሮ በቆመ ከተማ እምባሽ ቅኝት የለው ፤ለሰው ኣይሰማ፡ ጠዋት የፎከረ ፤ቀትር ላይ ሲረታ ዛሬ ዝሎ ሲወድቅ ፤ትናንት የበረታ ኑሮን ያህል ሸክም፤ ያላንቀልባ ሲያዝል፡፡ ምን ጸጋ ለብሶ ነው፤ ትከሻሽ የማይዝል፡፡ (በእውቀቱ … [Read more...] about ላንዲት መስቲካ ሻጭ ህጻን
“የተቆለፈበት ቁልፍ” በቃላት ቁልፍ ተቆላልፏል!
ለረጅም አመታተ የጣልኩትን ብዕር ድር ካደራበት ሰገባው እንድመዝ አስገደደኝ - በ ኢትዮ-ሚዲያ (Ethiomedia) እና በጎልጉል (Googlgule) ድህረ-ገፆች ላይ ከወራት በፊት በዶክተር ፍቃዱ በቀለ በተባሉ ግለሰብ በ"የተቆለፈበት ቁልፍ" መፅሐፉ ላይ የቀረበ አንድ ፅሑፍ። "ሃያሲው" በዘመናችን አቻ ያላገኙለት (ወደር የሌለው) መፅሐፉ መሆኑን ነው የገለፁልን። "...የስነ-ጽሁፍም ዋና ዓላማው በአንድ ህብረተሰብ ውስጥ ያሉትን አስቀያሚም ሆነ ቆንጆ ነገሮች ስዕላዊ በሆነ መልክ መግለጽ ሲችሉና አንባቢውን በልዩ ሃሳብ ውስጥ ተመስጦ እንዲዋኝ ማድረግ ሲችሉ ብቻ ነው።..." በማለት ካብራሩ በኃላ ከ`ዚህ አንፃር "የተቆለፈበት ቁልፍ" እንደተዋጣለት መሰክርነታችውን ይሰጣሉ። አንዲህ ሲሉ "....በታሪካችን ውስጥ በመጀመሪያ ጊዜ በልዩ አቀራረብ የተዘጋጀና የተጻፈ ትምህርታዊ መጽሀፍ ነው … [Read more...] about “የተቆለፈበት ቁልፍ” በቃላት ቁልፍ ተቆላልፏል!
“እኩል ደራ ደራ ከነ‘ሜቴ ጋራ!”
ገጣሚና ደራሲ... ከግዑዙ መሬት፣ ከመንደሩ ይልቅ ከዘር ማንዘሩ፣ ሰብዓዊነትን ያልማል ብዕሩ “የሰው ልጅ ልብ...” ነው አገሩና ድንበሩ! ሰብዓዊነት ነው ክብሩ፤ ገጣሚ አገር የለውም፣ “ዩኒቨርሱ”ም አይበቃውም፤ ሰዋዊ ህመም ያመዋል፣ ፈውሱም ይፈውሰዋል፣ ገጣሚ ያ ይበቃዋል! ወርዶ ወርዶ “ቀየ መንደር ውስጥ አይወድቅም” አዎ! ገጣሚ፣ ደራሲ እንዲያውም አገር የለውም፣ የበዓሉ አገሩ ሰው ነው፣ “...ህንጻው ምን ቢረዝም፣ ምን ቢጸዳ ቤቱ፣ መንገዱ ቢሰፋ ቢንጣለል አስፋልቱ፣ ሰው ሰው ካልሸተተ ምንድነው ውበቱ፣ የኔ ውብ ከተማ የኔ ውብ አገር፣ የሰው ልጅ ልብ ነው የሌለው ድንበር...” (ኦሮማይ) ጸጋዬም ጊንጪ ኢምንት ቢሆንበት ጉደር፣ አምቦ፣ ቡራዩ ... ጠ’ቦበት፣ አዲሳ’ባ ኢትዮጵያም ብታንስበት፣ ብዕሩ ፈርዖኦንን ተመኘ፣ ነፈርቲቲ እና አፍሮዳይትን … [Read more...] about “እኩል ደራ ደራ ከነ‘ሜቴ ጋራ!”
የተካደ ትውልድ
የተካደ ትውልድ አይዞህ ባይ የሌለው ታዳጊ የሌለው ወይ ጠባቂ መላክ፤ ወይ አበጀ በለው ደርሶ ከቀንበሩ የማይገላግለው የተካደ ትውልድ፤ አብዝቶ የጾመ፤ ተግቶ የጸለየ ጥቂት መና ሳይሆን፤ ጥይት ሲዘንብ ያየ እድሜ ይፍታህ ተብሎ፤ የተወለደ’ለት አምባሩ ካቴና፤ ማተቡ ሠንሠለት፡፡ ምቾትን የማያውቅ፤ ረፍት የተቀማ አልጋው ያጋም እሾህ፤ ምኝታው የሣማ የተካደ ትውልድ፤ ሞቶ እንኳ ሬሳው፤ አይላላለት ቀንበር በዘብ እጅ ተገድሎ፤ በሹም የሚቀበር ከጡት አስጥል በላይ፤ ኑሮ የመረረው እንዳይሄድ፤ ጎዳናው፤ የተደናገረው ድል ያልሰመረለት ትግል ሳይቸግረው የተካደ ትውልድ በሥጋ በነፍሱ በቀልቡ በገላው ኧረ ምንድን ይሆን ፤ ምንድን ይሆን መላው? (በዕውቀቱ ሥዩም) … [Read more...] about የተካደ ትውልድ
“[ሰዎች] አለሙያቸው ሙያ እየጫንባቸው አበላሽተናቸዋል” ወለላዬ
ሰላም ጎልጉሎች . . . እንኳን ለገና በዓል በሰላም አደረሳችሁ። ከኢትዮጵያ ዛሬ ጋር በግጥሞቼ ሳቢያ ቃለ መጠይቅ አድርጌ ነበር። እናንተም ግጥሞቼን በተገቢው ሁኔታ ያስተናገዳችሁልኝ ስለሆነ እናንተም (ዘንድ) ቢታተም እወዳለሁ። በድጋሚ መልካም በዓል ይሁንላችሁ። ወለላዬ መዝጊያ ትሁንልኝ መቶ ራት ግጥሞችን - ተሸክሜ ይዤ፤ ረብዕ ረቡዕ ስጥል - አንድ አንዷን መዝዤ በዚች ባሁኗ ቀን - በጨበጥናት ሳምንት፤ ወሩን ስደምረው - ሆነኝ ሁለት ዓመት፡፡ ዳግም በአዲስ ዓመት - እስከምንገናኝ፤ የዘንድሮው መዝጊያ - ይቺ ትሁንልኝ፡፡ (ወለላዬ) ወለላዬ በየሳምንቱ ረቡዕ ረቡዕ በኢትዮጵያ ዛሬ ድረ ገጽ ላይ ለሁለት ዓመታት ያህል ሳያቋርጥ 104 ግጥሞች በመጻፍ አስነብቦናል። በነዚህ ግጥሞቹ እኛን ሆኖ ውስጣችን ገብቶ ያልተናገርነውን ተናግሮልናል። ታዝበን ያለፍነውን … [Read more...] about “[ሰዎች] አለሙያቸው ሙያ እየጫንባቸው አበላሽተናቸዋል” ወለላዬ
የዛ ሰውዬ ድምጽ . . .
ፊቱ አሸቦ መስሎ፣ እንደደነገጠ፣ ተጎልጉሎ ወጥቶ፣ ዓይኑ እንደፈጠጠ፣ ባንኮኒው ጋ ሄዶ፣ ቢራውን ጨበጠ። የሆነውን እንጃ! ሁኔታው ያስፈራል፣ እንባው በጉንጩ ላይ፣ አቋርጦ ይፈሳል አልቅሶ ሲበቃው፣ ውጪ እየሰለለ፤ ያየውን በውስጡ፣ እያሰላሰለ፣ ገድለው ሲጥሏቸው፣ በዓይኖቼ አየሁ አለ። ወደ ተናጋሪው፣ አፍጠን እያየን፤ እንደልማዳችን፣ ዝም ተባባልን። ሰውዬው ቀጠለ፣ ገድለው ሲጥሏቸው፣ በዓይኖቼ አየሁ አለ! ዘለው ያልጠገቡ፣ እህል የተራቡ፣ አገር የተቀሙ፣ ፍትሕ የተጠሙ፣ አንድ ፍሬ ናቸው! ገና እንዳገኟቸው፣ ከበው ይዘዋቸው፣ መሣሪያ አስጠግተው፣ ወደ ግንባራቸው፣ ጭንቅላታቸውን ... ፈረካከሷቸው። እያለ ሲናገር፣ ሰውዬው ሲቆጣ፣ ሲያለቅስ ሲያማርር፣ እኔም ልክ እንደሱው፣ በዓይኖቹ ገብቼ፣ አንገቴን አቅፌ፣ በሁለት እጆቼ፣ ጉልበቴ እየራደ፣ ነፍሴ … [Read more...] about የዛ ሰውዬ ድምጽ . . .
ለጀግናው አትሌት ስንብት!
. . . በዚያ ቀውጢ ጊዜ - በዚያ ቀውጢ ዘመን፣ ከአገር በራቀበት - የደስታ ሰመመን፤ ያገር ፍቅር ስሜት - መገለጫ ፈርጦች፣ ብቸኛው አማራጭ - የደስታችን ምንጮች፣ ነበሩን! ነበሩ! “አረንጓዴ ጎርፎች”. . .፤ እንዲህ እንደዛሬው - ሳይዘምን ዘመኑ፣ ያለም መገናኛ - ሳይራቀቅ ኪኑ፣ ዩ ቲዩብ፣ ኢንተርኔት፣ ስማርት ፎን..ሳይኖር፣ ዜና መቀበያው - ራድዮናችን ነበር፤ “. . . ክቡራትና ክቡራን ውድ አድማጮቻችን..”፣ የኦሎምፒክ ውጤት፣ ልክ እንደደረሰን፣ እናስደምጣለን...”፤ በለሆሳስ ሙዚቃ መሳሪያ ቅንብር መሻገሪያ ዜማ፣ ከተራራ ጫፍ ላይ፣ ወይ ከሰማየ-ሰማያት ከሩቅ እሚሰማ፣ “የኛ ነው ድሉ-ድሉ፣ የኛ ነው ድሉ-ድሉ፣ በርቱና ታገሉ..”፤ አገር ትንፋሽ አጥሮት - ጸጥ-ረጭ ብሎ፣ ዐይኖቹን ጎልጉሎ - ራድዮን ላይ … [Read more...] about ለጀግናው አትሌት ስንብት!
የግርማ ይፍራሸዋ ፒያኖ ኮንሰርት በዋሺንግተን ዲሲ
ከ25 ዓመታት በላይ የፒያኖ ድርሰቶችን በመጻፍና በመጫወት የአገራችንን ስም በማስጠራት የቆየው ኢትዮጵያዊው ዜማ ደራሲ እና ፒያኒስት ግርማ ይፍራሸዋ በአሁኑ ቅዳሜ November 26 ምሽት ከ6:30 ጀምሮ በዋሺንግተን ዲሲ እና በአካባቢዋ ለሚገኙት አድናቂዎቹ ግሩም የሆነ የፒያኖ ሙዚቃ ትርኢት Washington Ethical Society አዳራሽ ለማቅረብ ተዘጋጅቷል። ግርማ የሙዚቃ ትምህርቱን የጀመረው በልጅነቱ ክራር በመጫወት ነበር። በመቀጠልም በያሬድ ሙዚቃ ት/ቤት (1975-1978 ዓ.ም)፣ Sofia State Conservatory of Music (1978-1986 ዓ.ም)፣London Royal Academy of Music (1989 ዓ.ም)፣ እናLeipzig Hochschule für Music und Theater (1991 ዓ.ም) ክላሲካል ሙዚቃን በመማር የድርሰትና የትርኢት ችሎታውን ለማዳበር … [Read more...] about የግርማ ይፍራሸዋ ፒያኖ ኮንሰርት በዋሺንግተን ዲሲ







![“[ሰዎች] አለሙያቸው ሙያ እየጫንባቸው አበላሽተናቸዋል” ወለላዬ](https://staging.goolgule.com/wp-content/uploads/2017/01/fake-mask-300x225.jpg)


