ወያኔን ከኢትዮጵያ ህዝብ ጫንቃ ላይ አሽቀንጥሮ ለመጣል በመደረግ ላይ ባለው ማንኛዉም አይነት ትግል ውስጥ ተሰማርቶ ለሚገኝ ኢትዮጵያዊ ሁሉ!!! አንዳንድ ግዜ እራሴንም ሆነ የሀገሬን ልጆች ክፉኛ እታዘባለሁ፣ ያለንበትም ዝብርቅርቅ ህይወት እራሳችን የፈጠርነው በመሆኑ በጣም አፍራለሁ። ለዚህም ነበር የስው ልጅ ማንነት መለኪያ ስለሆኑት ሶስቱ ጽንሰ ሃሳቦች እውቀት፣ እምነትና ብልህነት ለመፃፍ የተነሳሳሁት። እኛ የዚህ ዘመን ትውልድ የሆንን ኢትዮጵያውያኖች እምነትና ብልህነት እንደ ቁምጣ ያጥረናል ብል ማጋነን አይሆንብኝም። ምክንያቱም ማንነቱንና የሚሰራውን ጠንቅቆ የሚያውቅ ትውልድ ሁሉ በቀላሉ ወደ ነፈሰበት አብሮ አይነፍስምና። ሰሞኑን ለንደን ላይ የኦሮሞ ልጆች ተሰባስበው ወጥና ሁሉን አቀፍ የሆነ ስምምነት ላይ ለመድረስ ሲመክሩ እንደ ሰነበቱ ሁላችንም የምናውቀው ነው። በዚሁ ስብሰባ … [Read more...] about “ለኦሮሞ ሰላም ኢትዮጵያን እናፍርስ” ያለው ሊበን ዋቆ ፍላቴ ማነው?
Opinions
የኔ ሃሳብ
“ጃዋር፦ ያልተናገረውን በተናገረው ውስጥ መስማት”
“ወያኔ አንድ ታንክ ከመግዛት፣ በ10 ሚሊዩን ዶላር አንድ ከፋፋይ አክቲቪስት መግዛት ትመርጣለች” መስፍን ፈይሳ ሮቢ ጋዜጠኛ ምናላቸው ስማቸው በ“አፈርሳታ” ዝግጅቱ ጃዋርን አቅርቦ አነጋግሮት ነበር። ለጃዋር የቀረበለት አንዱ ጥይቄ “. . . የግንቦት ሰባት እና የኦሮሞ ደሞክራሲያዊ ግንባርን ጥምረት እንዴት አየኸው?” የሚል ነበር። ጃዋር “. . . ቅን አመለካከት ነው ያላቸው. . .ጥሩ ሙከራ እያደረጉ ነው. . . ኢንቴንሽናቸው ቅን ነው. . .” ብሎ በተናገረው ውስጥ “. . . በትክክል የተሰራ ግን አይደለም፣ የፖለቲካ ብስለት ያለበት ግን አይደለም” የሚል እና ያልተናገረውንም ነገር (between the lines) ትሰማለህ። ነገሩ “ከኛ ወዲያ ፉጭት አፍ ሟሞጥሞጥ ነው. . .” ወይም “. . . ፖለቲካ ከኔ ወዲያ ላሳር ነው” የሚል ድምጸት አለው። ጃዋር ሌላም ጥይቄ … [Read more...] about “ጃዋር፦ ያልተናገረውን በተናገረው ውስጥ መስማት”
ለትብብር እንቆቅልሽ መላ
በዚህ ፅሁፍ ስለ አማራጭ ሃይሎች ትብብር አስፈላጊነት የታወቀ ነገር ስለሆነ መናገር አልፈልግም። ማተኮር የምፈልገው እንዴት ትብብሩ እንደሚመጣ መላ ፍለጋ ላይ ነው። ይህም ሲባል ነገሮች ተድበስብሰው አንድ ላይ ተጨፍልቀው ማየት ሳይሆን፥ በየደረጀው ከመነሻው እስከ መድረሻው ጥርት ባለ መልኩ ለማስቀመጥ ነው። ከውጭ ለሚያይ የብሔር ተኮር ሃይሎችና የኢትዮጵያ አንድነት ሃይሎች ተባብለው በሁለት ትልቅ ጎራ ተከፋፍለው በጥርጣሬ መተያየታቸው የአደባባይ ሚስጢር ነው። ባብዛኛው ግን ልባቸው የሚፈልገው ለሁሉም አንድ ነው። ያም ሆኖ አንዳንድ ተስፋ ሰጭ ፍንጭ ከመታየቱ በቀር በሁለቱ ጎራ ዙሪያ ፈቀቅ ያለ ነገር እየተደረገ አይደለም። ስለዚህ አድበስብሰን ለመግባባት እስካሁን የሞከርነው ጠብ ስላላለ አዲስ መንገድ እንከተል። እስቲ ይህንን መንገድ በሶስት ደረጃ ከፍለን እንየው። 1ኛ/ ቅድመ መግባባት … [Read more...] about ለትብብር እንቆቅልሽ መላ
መግባባትን ገንቢ የኢትዮጵያ መድረክ
ለኢትዮጵያ የፓለቲካ ቅራኔ መፍትሄው እርቅና መግባባት መሆኑን ከሚጠቁሙና ከዚያ አልፈው የሽምግልናና የማግባባት ስራ ከሚሰሩ ስብስቦች አንዱ "መግባባትን ገንቢ የኢትዮጵያውያን መድረክ" ነው። ዛሬ ከመድረኩ ሁለት አባላት በፎረም 65 ጋብዘናል። እንግዶቻችን የ"መግባባትን ገንቢ የኢትዮጵያውያን መድረክ" ሰብሳቢ ዶ/ር ብርሃኑ መንግስቱ እና የመድረኩ አባል ዶ/ር ገበየሁ እጂጉ ናቸው። ያዬ አበበ ፎረም 65 አስተባባሪ … [Read more...] about መግባባትን ገንቢ የኢትዮጵያ መድረክ
የ“ጥልቅ ተሃድሶ” ድራማ ተጀምሯል!
በቤተ ሙስና፣ የ"ጥልቅ ተሃድሶ"ው ድራማ ተጀምሯል! የእርስ በርስ እና ራስን በራስ መተካካት ቧልት እና ፌዝ። ከመጋረጃው ጀርባ ስብሃት ነጋ፣ አቦይ ጸሃይ፣ ጌታቸው አሰፋ፣ ደብረጽዮን እና በረከት ስምኦን የሚቆምሩትን ካርታ ሃይለማርያም ደሳለኝ እንደቬጋስ አጫዋች ፊት እያመጣ ይዘረጋዋል። በዲዮጋን ያደረጉት አብዮታዊ እና ልማታዊ "ምሁራን" ፍለጋ ውጤት ነበረው። "የዶክተር ያለህ" ፍለጋ ጥቂት ታማኝ አገልጋዮችና፣ በርካታ ሮቦቶችን አስገኝቷል። "በዲሞክራሲ" በተመረጠው "የህዝብ ምክር ቤት" የሚኒስትሮቹ ስም ይፋ በሆነ ግዜ፤ ለይስሙላ እንኳን ተቃውሞ፣ አልያም ድምጸ-ተአቅቦ ቢያደርግበት ድራማውን ያሳምረው ነበር። በሙሉ ድምጽ ጸደቀ ተባለ። የነዚህ ሮቦቶች ምርጫ የፍልፍሉን ቀልድ ያስታውሷል። የድሃው ልጅ ለሃብታሙ ልጅ፣ "ምን ያንጠባርርሃል? አንተም የምትበላው አንድ እንጀራ፣ እኔም … [Read more...] about የ“ጥልቅ ተሃድሶ” ድራማ ተጀምሯል!
EPRDF: Once again on the wrong side of History
The Ethiopian ruling party, for the first time in its quarter of a century in power, declared a state of Emergency following over a year of protest that claimed thousands of lives and a huge damage of property. Every day people are dying or jailed in connection with the civil disobedience that is going on in different parts of the country. The government, initially, down played the protest as a local issue that can be dealt with local governments. As the protests got momentum, the government … [Read more...] about EPRDF: Once again on the wrong side of History
የተባበረችውን ኢትዮጵያ በጋራ እንገነባለን
በቅርቡ በአንድ የኦሮሞ ወገኖች ስብሰባ ላይ አንድ ሰው ኦሮምያ ሰላም የምታገኘው ኢትዮጵያ ስትፈራርስ ነው ኢትዮጵያ መፍረስ አለባት አለ ተብሎ ሲራገብ እያየን ነው። እኔ በግሌ የዚህን ሰው ተልእኮ ለመረዳት ቅንጣት ጊዜ አልወሰደብኝም። ከራሱ ከወያኔ በቀጥታ መልእክት እየተቀበለ የሚሰራ የወያኔ ተቀጣሪ ነው ወይም እያጃጃሉ በስልት የሚጠቀሙበት ሰው ነው። አለቀ። ይህንን ለማለት ያስቻለኝ ነገር እንደሚታወቀው ይህ መንግስት ገና ሲመሰረት ጀምሮ በስልጣን ላይ ለመቆየት የሚያስችለው መሳሪያ ህዝባዊ ድጋፍ አይደለም። በዚህ ጎጠኛ የፓለቲካ አስተሳሰቡና በሙስና ድር በተፈጠረ ሥርዓት ምን ጊዜም ሰፊ ህዝባዊ ድጋፍ አገኛለሁ ብሎ አያስብም። ይህንን መንግስት በሚገባ ያውቃል። ይህን ስርዓት እድሜ ይቀጥልለታል ተብሎ የሚታሰበው ስልት ቅራኔ ነው። ለዚህም ነው መንግስት ከህገ መንግስቱም በላይ … [Read more...] about የተባበረችውን ኢትዮጵያ በጋራ እንገነባለን
ግልፅ ደብዳቤ ለአቶ ጀዋር መሐመድ
በኢትዮሚዲያ ላይ በለንደን ላይ ያደረጉትን ንግግር ከዚህ በታች የተቀነጨበውን አየውና ይህንን ልፅፍ ተነሳሳሁ። “የኦሮሞ ወጣቶችን ወክዬ ለውጭው ማህረሰብ የማስተላልፈው መልዕክት አለኝ። ካሁን በዋላ በኢትዮጵያ ቢሆን ቢሆን ታግለን መብታችንን አስመልሰን ከሌሎች ጋር አብረን እንኖራለን። ካልሆነ ግን ያችን ሀገር በታትነን ጥለናት እንሄዳለን እንጂ እንደ ትላንቱ የማይረቡት እላያችን ላይ ተጭነው እንዲያስተዳድሩን አንፈቅድም።” ጀዋር መሐመድ፥ ከለንደን ንግግር ከኢትዮሚዲያ የተወሰደ። በመጀመሪያ አሳቤን ይረዱልኝ። በክርክር ለማሸነፍ አሳቡም ምኞቱም የለኝም። እርስዎንም እንደ ጠላት ለመቁጠርና ለመፈረጅ በልቤ ውስጥ ያለው ፍቅር አይፈቅድልኝም። ነገሬ ከአስተሳሰብዎ ጋር ነው። ለማሳመን ብዙ ትንታኔ አልገባም። ቃሌን አጭር በማድረግ ከቃሌ ጀርባ ያለውን ቅን መንፈስ እንዲረዱ ተስፋ ማድረግን … [Read more...] about ግልፅ ደብዳቤ ለአቶ ጀዋር መሐመድ
Ato Emmanuel Abraham (1913-2016)
Ato Emmanuel Abraham who had served his country in a number of important diplomatic and ministerial posts for nearly four decades and half (1931-1974) has died at a great age of 103 on Wednesday. Emmanuel was ambassador to Britain and Italy and cabinet minister and director general at the Ministry of Foreign Affairs and director general of the Ministry of Education and Fine Arts, Minister of Posts, Telegraphs and Telephones; Minister of communications and Transport; and finally, minister of … [Read more...] about Ato Emmanuel Abraham (1913-2016)
ዓለምነህና ጸጋዬ አራርሳ
ዓለምነህ በአዋዜ ፐሮግራሙ ላይ ጸጋዬ አራርሳ ‹‹ኢትዮጵያዊ ማንነት የለም›› ያለውን ይዞ በለዘበ ቋንቋና በለዘበ ድምጽ ደቁሶታል፤ ብዙ ሰዎች የገባቸው አልመሰለኝም፤ በጉዳዩ የተማረውና የተመራመረው ዶር. ጸጋዬ አራርሶም የገባው አይመስለኝም፤ እስቲ እኔ የገባኝን ልንገራችሁ፡፡ በመጀመሪያ በሁለቱ ሰዎች መሀከል ያለውን የትምህርት ደረጃ ልዩነት ዓለምነህ ራሱ እንዳለው እሱ ‹‹በትምህርት እጅግም አልገፋም›› ጸጋዬ ግን የትምህርቱን ደረጃ ጣራው ላይ አድርሶታል ተብሎ በስሙ ላይ ‹‹ዶክተር›› የሚል የትምህርት ማዕርግ እንዲጨምር አድርጓል፡፡ በትምህርት እጅግም ያልገፋው ሰው በትምህርት ጣራ ላይ በደረሰው ሰው አስተያየት ላይ የሰጠው ትችት የትምህርት ደረጃ የሚባለውንም ሆነ የሁለቱን ሰዎች እውቀትና ብስለት የሚለካ ነው፤ የዓለምነህ ትችት ስለቱ ያረፈው ጸጋዬ የሚልዮኖችን እምነት መካዱ ላይ … [Read more...] about ዓለምነህና ጸጋዬ አራርሳ










