“To deny people their human rights is to challenge their very humanity.” Nelson Mandela Today, 10 December, as we celebrate international Human Rights Day, we remember all prisoners that are victims of grave human rights violations in Ethiopia. On this day, AHRE is sharing a very striking personal story of a family that has fallen victim of the Ethiopia’s government’s repression. The story is symbolic in that it signifies the broader, much bigger fracture in Ethiopia’s political climate. It … [Read more...] about On Human Rights Day: Victims of grave human rights violations in Ethiopia
Opinions
የኔ ሃሳብ
“ነን ሶቤ (ዋሸሁ እንዴ?)” ይላል የአምቦው ፈርጥ ሃጫሉ
"ዋሸሁ እንዴ?" (ነን ሶቤ) ሲል ይጠይቃል፣ ድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ። ይህንን ጥያቄ የሚያቀርበው ለታዳሚው ሕዝብ አይደለም። በአስር ሺዎች የታደሙበት የኮንሰርት አዳራሽ ውስጥ ከታዳሚው ፊት-ለፊት ለተቀመጡት ለእነ አባዱላ ገመዳ፣ ወይንም ደግሞ ለእነ ለማ መገርሳ ይመስላል። ከፍ ሲል ደግሞ ኮንሰርቱን በቀጥታ ስርጭት እየተከታተሉ ላሉት የአድዋ ባለ ግዜዎች የቀረበ ጥያቄ ነው። ይህ ድምጸ-መረዋ ወጣት በምርጥ ቅላፄው ያንጎራጎረው ፉከራ እና ዜማ እጅግ ያስደምማል። ማስደመሙ እውነትን በመድረክ ላይ መዘርገፉ አይደለም። ከራሱ ደህንነት ይልቅ የወገኑን ስቃይ እና ሰቆቃ በማስቀደሙ ነው። እንዲህ አይነቱ እውነትን አደባባይ ወጥቶ በድፍረት የመናገር "ገት" የነበረው ቴዲ አፍሮ ነበር። ይህንን በማድረጉም በአንባገነኖቹ ጥርስ ውስጥ ገብቶ ብዙ ቢያስከፍለውም፣ ከህዝብ ልብ ውስጥ ሊወጣ … [Read more...] about “ነን ሶቤ (ዋሸሁ እንዴ?)” ይላል የአምቦው ፈርጥ ሃጫሉ
የአማራና ኦሮሞ ሕብረት ለዘላቂ ለውጥ!
የመቀሌው ስብሰባ ማራቶን ሹምና ሽረቱ የመግለጫ ጋጋታው የጥልቅ ተሃድሶው ውጤት ከግር ጥፍሩ እስከ ዶቃ ማሰሪያው በንጹሀን ደም ለጨቀየው የሌባና የሰው በላ የወያኔ ቡድን ለዳግም ግፍ ለበለጠ አፈና በሚያመቸው መልኩ የጭካኔ ጠበብቶቹን መሪ አድርጎ ሊዘምትብን መዘጋጀቱን አውጇል። የሕዝብ ለህዝብ መተላለቅን የሚሰብኩ ጀሌዎቹን አሰልፎ በሕዝባችን ላይ ከነመርገሙ ሊጫንብን አፈር ልሶ ተነስቷል። የህወሃት ትዕቢት ጨለምተኝነቱና ለህዝብ ያለው ንቀት ድንበር የለሽ በመሆኑ አማራና ኦሮሞን በእሳትና ጭድ መስሎ በአደባባይ የተናገረውን ስቅላት ይገባው የነበረን ጸረ ሕዝብ ግለሰብ ከፍ ላለ ወንበር መሾም ነደው እንዲጠፋ በተመኘላቸው ሕዝቦች ላይ ሌላ ዙር የከፋ ዘመቻ አቅዶ ለመነሳቱ አመላካች መሆኑ የሚያጠራጥር አይደለም። የትግሬ ነጻ አውጪውን ወያኔን በተንኮሉ አይነት በጭካኔው ደረጃ በክፋቱ ልቀት … [Read more...] about የአማራና ኦሮሞ ሕብረት ለዘላቂ ለውጥ!
Modern Slavery in Libya and the Plight of Ethiopians.
The Honorable Fayez Seraj, Prime Minister, Libya's Government of National Accord (GNA) Tripoli, Libya. Via email ambassador@embassyoflibyadc.com Re: Modern Slavery in Libya and the Plight of Ethiopians. Honorable Prime Minister, The Consortium of Ethiopian Civic Society Organizations (TIBIBIR) is a coalition of 27 major Ethiopian civil society groups within and outside Ethiopia that have consolidated their efforts to defend and advance human rights, justice and the rule of law, national … [Read more...] about Modern Slavery in Libya and the Plight of Ethiopians.
ደጋፊ ያጣው ጎልማሳ ለአረብ ሀገር ስደተኛ
"ስደት ይብቃ!" የስደትን አስከፊነትና በወገኖቻችን እየደረሰ ያለቀውን ሰቆቃ እንደ አዲስ እናየው ዘንድ በአረባዊቷ አፍሪካ ሀገረ በሊቢያ የሚፈጸመውን ግፍ እያየን ነው በታላቅ ክብርና ሞገስ የሚታወቀው ወገኔ ዛሬ ክብሩ ቀርቶ ለሽያጭ በደረሰ የግፍ ቀንበር ተጭኖበታል ... ውርደት አንገታችን አስደፍቶናል፣ ከሰው ተራ አውጥቶናል! በቀረው የባህረ ሰላጤ ሀገራት ስደት በአረብ ሀገሩ ስደት በሚሊዮን የምንቆጠር የአብዛኞቻችን ኑሮ እየከፋ ለመምጣቱ የተሻለ የሚባለውን የሳውዲ ስደት እየኖርኩበት ነውና ዛሬም እውነቱን እነግራችኋለሁ! ሳውዲዎች "ህገ ወጦች ከሀገሬ ይውጡ" ብለው በጀመሩት የምህረት አዋጅ የማስወጣት ዘመቻ 228 ሽህ የሚጠጉ ዜጎችን ማስወጣታቸውን በቅርቡ ነግረውናል። በሳውዲ ቅጣቱን የፈራው ሩብ ሚሊዮን ኢትዮጵያዊ በወጣ ማግስት በውጡው ዘመቻ የወጡት ተመልሰው ስለመ ምጣታቸው … [Read more...] about ደጋፊ ያጣው ጎልማሳ ለአረብ ሀገር ስደተኛ
የኢትዮጵያ ጉዳይ መጽሔት
ሕዳር 2010 ዓ.ም አራተኛ ዓመት ቁጥር ፩ ዕትም ኢትዮጵያን ከውድቀት መታደግ የዜግነት ግዴታ ነው የዘር ፖለቲካ ያስከተለው ሰብዓዊ ቀውስ ኢትዮጵያ ከወያኔያዊ ዘመነ መሣፍንት የሚታደጋት ቴዎድሮሥ ሣልሣዊ ትሻለች በጎሣ ፌዴራሊዝም ኢትዮጵያዊነት አይደበዝዝም የወያኔ የዘር ፖለቲካ እና ዩኒቨርስቲዎቻችን በዘመነ ወያኔ አዲሱ ህፃናትን የመሸጫ መንገድ “የግድ አንዱን ምረጥ ብባል ነፍሴ ወደ ትያትሩ የምታዘነብል ይመስለኛል” ወዘተ ርዕሰጉዳዮችን በአማርኛና በእንግሊዝኛ በማካተት ታትሟል፤ መጽሔቱን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ። “ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት … [Read more...] about የኢትዮጵያ ጉዳይ መጽሔት
“ሃፍታም ምሆነው ሕወሃት ሲለቅቀኝ ነው!” አዜብ መስፍን
የህወሃት ሽኩቻ አላባራም! "ሃፍታም የምትሆነው ህወሃት ወይንም ኤፈርት ሲለቅቀኝ ብቻ ነው!" ብላ ከነገረችን ገና መንፈቅ እንኳ አልሞላም። ከጥልቅ ተሃድሶ እና ከመተካካት ቀጥሎ የተመሰከረለት የአዜብ ጎላ መሪ ቃል ነበረች። የመልቀቁን ጨዋታ ለኛ ተየት አድርጊያትና መሪርዋን ጽዋ ተጎንጪ ሲሉ እነሆ መርዶውን ነግረዋታል። ሂስዋን አልውጥም ብላ ከመቀሌ እንደፈረጠጠች በዚያው ቀርታለች። መቼም "መለስ የሞተው አሁን ነው!" ሳትል አትቀርም በልብዋ። የዛሚዋ ደላሊት እድል አትሰጣትም እንጂ፣ ይህንኑ የልብዋን ሃሳብ "ለሚወዳት ሕዝብ" ትተነፍሰው ነበር። ግን ምን ያደርጋል? የወደቀ ፈላጊ አይኖረውም። ቀልደኛይቱ የጎላ ልጅ፣ "ድሮስ ቢሆን ድሃን ማን ይወደዋል" ማለትዋ በፌዝ ቡክ ላይ አነበብን። አዎ! አዜብ መስፍን ከታሰረችበት የህወሃት ጎራ አሁን ተለቅቃለች። ቃል እንደገባችውም የድህነትን … [Read more...] about “ሃፍታም ምሆነው ሕወሃት ሲለቅቀኝ ነው!” አዜብ መስፍን
“ኢትዮጵያ ወዴት፤ የተረጋጋ ሽግግርና የዴሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ”
የኢትዮጵያውያን ፎረም በአውሮፓ፣ ሁለተኛውን ዓለማቀፍ ኮንፈረንስ December 2, 2017 በብሪስልስ ከተማ ያዘጋጀ መሆኑንበደስታ ይገልጻል። ዘንድሮም “ኢትዮጵያ ወዴት፤ የተረጋጋ ሽግግርና የዴሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ” በሚል ርዕስ ባዘጋጀው የአንድ ቀን ሴሚናር ላይ አራት ታውቂ ባለሙያዎች ጥናታዊ ስራዎቻቸውን እንዲያቀርቡጋብዟል። የኮንፈረንሱን ዝርዝር መረጃ የያዘውን ፖስተር እዚህ ላይ በመጫን ያገኙታል። ዕርስዎም የዝግጅታችንን መርሀ ግብር ላይ እንዲገኙልን እና ጥሪያችንንም ለሌሎች ኢትዮጵያውያን እንዲያስተላልፉልን በትህትና እንጠይቃለን። ከማክበር ሰላምታ ጋር ኮሚቴው “ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች … [Read more...] about “ኢትዮጵያ ወዴት፤ የተረጋጋ ሽግግርና የዴሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ”
“አንተ ሌባ – አንቺ ሌባ” – የመቀሌው ሽኩቻና የህወሃት የውድቀት አፋፍ
መቀሌ ወሩን ሙሉ ውጥረት ውስጥ ከርማለች። ከተማዋ ላይ እየወረደ ያለው ዶፍ የሚያባራ አይመስልም። የህወሃቶቹ የዘንድሮ መሰባሰብ ለጤና እንዳልነበረ ግልጽ ነው። ሰዎቹ እንደወትሮው “በሃገር ጉዳይ ላይ” ለመዶለት ወደ መቀሌ አልተጓዙም። ቀደም ሲል ጠላታችን ድህነት ነው ሲሉን ነበር። አሁን ግን ለሁለት ተቧድነው አንዱ ሌላውን ጠላት ሲል ይሰማል። በግል ጸብ ለሁለት መሰንጠቃቸው የአደባባይ ምስጢር ይሁን እንጂ፤ እርቅ እና ሰላም በአጀንዳቸው ውስጥ አልተካተተም። ሃገሪቱ የገባችበትን ችግር ወደጎን ትተው፣ “አንተ ሌባ – አንቺ ሌባ” ሲባባሉ እንደከረሙ ነው እየተሰማ ያለው። ይህንን የማይታረቅ ቅራኔ ይዘው አብረው ስለማይዘልቁ የአንዱ ቡድን ማሸነፍ ግድ ይላል። በዚህ ‘ታሪካዊ’ ስብሰባ የሙስና እና የሌብነት ፋይሎች ተጠርዘው ቀርበዋል። ህወሃቶች አፍ አውጥተው “በስብሰናል”ም ብለዋል። … [Read more...] about “አንተ ሌባ – አንቺ ሌባ” – የመቀሌው ሽኩቻና የህወሃት የውድቀት አፋፍ
ፎቶና ታሪኩ
በወያኔ ዘመን በህወሃት ቀንበር ያሳለፍነው ህይወት የጠጣነው አረር እንዴት እንደሆነ እንዴት እንደነበር ጠበቃ ከማቆም እማኝ ከመደርደር ይኸው የኛ ፎቶ ታሪኩን ይናገር። *የተከበርክ አንባቢ ሆይ! ቀጣዮቹን ፎቶዎች በፅሞና እና በማስተዋል ተመልከታቸው፤ መልዕክቶቹንም ረጋ ብለህ ወደ ነፍስህም ቀርበህ አንብብ። ምናልባት ለመፍትሄውም ሆነ ለችግሩ አንተ ትቀርብ ይሆናልና። በጎንደር ከተማ የሚታየው ዘግናኝ የቁልቁለት ‘እድገት’። በህወሃት በይፋ ጠላትነት ተፈርጆ የቁም ስቅሉን እያየ በሚገኘው የአማራ ህዝብ ላይ ሆን ተብሎ በመካሄድ ላይ ያለው የኢኮኖሚ ተዐቅቦ ያስከተለው መከራና ድህነት እጅግ ዘግናኝ ሲሆን በቅርቡ በወጣ ጥናታዊ ዘገባም የአማራ ህፃናት ከዚህ በፊት ታይቶ በማያውቅ ሁኔታ (በርግጠኝነትም በሌሎች ክልሎች በዚህ ስፋትና መልክ ያልተከሰተ) ያለ ዕድሜያቸው … [Read more...] about ፎቶና ታሪኩ










