• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“ሃፍታም ምሆነው ሕወሃት ሲለቅቀኝ ነው!” አዜብ መስፍን

November 28, 2017 11:52 am by Editor Leave a Comment

  • የህወሃት ሽኩቻ አላባራም!

“ሃፍታም የምትሆነው ህወሃት ወይንም ኤፈርት ሲለቅቀኝ ብቻ ነው!” ብላ ከነገረችን ገና መንፈቅ እንኳ አልሞላም። ከጥልቅ ተሃድሶ እና ከመተካካት ቀጥሎ የተመሰከረለት የአዜብ ጎላ መሪ ቃል ነበረች። የመልቀቁን ጨዋታ ለኛ ተየት አድርጊያትና መሪርዋን ጽዋ ተጎንጪ ሲሉ እነሆ መርዶውን ነግረዋታል። ሂስዋን አልውጥም ብላ ከመቀሌ እንደፈረጠጠች በዚያው ቀርታለች። መቼም “መለስ የሞተው አሁን ነው!” ሳትል አትቀርም በልብዋ። የዛሚዋ ደላሊት እድል አትሰጣትም እንጂ፣ ይህንኑ የልብዋን ሃሳብ “ለሚወዳት ሕዝብ” ትተነፍሰው ነበር። ግን ምን ያደርጋል? የወደቀ ፈላጊ አይኖረውም። ቀልደኛይቱ የጎላ ልጅ፣ “ድሮስ ቢሆን ድሃን ማን ይወደዋል” ማለትዋ በፌዝ ቡክ ላይ አነበብን።

አዎ! አዜብ መስፍን ከታሰረችበት የህወሃት ጎራ አሁን ተለቅቃለች። ቃል እንደገባችውም የድህነትን በሽታ ከራስዋ ላይ የምታባርርበት ግዜ አሁን ነው። ጉልት ቁጭ ብላ ቸርችራ ሃብታም እንደምትሆን ታሳየናለች። ይህንን ስታደርግ ታዲያ የባለ ራዕዩን “ታላቁ መሪ” ፎቶ ከአጠገብዋ ማራቅዋን እንዳትዘነጋ። አንዲት ድሃ እናት ጉልት ተቀምጣ ውላ ልጆችዋን እንዴት እንደምታሳድግ በቃል ሳይሆን በተግባር ስታሳየን – ያኔ እናምናታለን። እርግጥ የፖለቲካ ሀ-ሁ በውል ሳይገባትና  ከአመራር እውቀት ነጻ ሆና እስካሁን መርታለች። የመኖርዋ ትርጉም የተቋጨው የመለስ ሚስት በመሆንዋ ብቻ ባገኘችው በዚሁ እድል ፈንታዋ ነበር። የአርባ ቀን እድልዋን በዜሮ እስካባዙባት እስከዛሬዋ ሰዓት በርግጥም ቀልዳብን ነበር።   

ወ/ሮ አዜብ መስፍን ከህወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ መባረርዋ የባንክ ሂሳቧ ላይ አንዳች ሃሳብ አያመጣባትም። ከህወሃት የገንዘብ ክምችት ከሆነው ኤፈርት ያስወገድዋት ቀን ግን የተመኘችው ጉልትዋ ተቀምጣ ስትቸረችር እናያት ይሆናል። ለዚያም እድል ከሰጥዋት! ሰዎቹ ወገብዋ ላይ መቆማቸው እርግጥ መሆኑ የታወቀው የአድዋው ጸረ-ሙስና ቡድን የአዜብ ፋይሎችን አዋራ እያራገፈ መሆኑ ሲሰማ ነው። በነገራችን ላይ ከ 16 ዓመት በፊት መለስ ዜናዊ፣ ስብሰባ ረግጠው በወጡት በእነ አቶ ገብሩ አስራት፣ አረጋሽ አዳነ፣ ስዬ አብርሃ፣ ጀነራል ፃድቃን ገ/ተንሳኤ ላይ የወሰደው እርምጃ ነው አሁን በአዜብ ላይ የደረሰው። እነ ስዬ በወቅቱ አብዛኛ ድምጽ ቢኖራቸውም እንደወጡ በዚያው ቀሩ። ከጸረ-ሙስናው በትርም ሊያመልጡ አልትቻላቸውም ነበር። የሚገርመው፣ ያ ታሪክ መደገሙ ሳይሆን የቅጣት ዱላው በቀጭዋ አዜብ ላይ መዞሩ ነው።

ጎናቸው እየተመታ ያለው እነ ሳሞራ የኑስ አውቆ እንደተኛ ዝም ብለው አድፍጠዋል። እንደ መርዘኛ እባብ ራሱን ቀብሮ የመቀሌውን ድራማ መጨረሻ የሚጠብቀው ቡድን ዝምታም የአድዋውን ቡድን ስጋት ውስጥ መጣሉ ግልጽ ነው።

“የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ /ህወሓት/ ማዕከላዊ ኮሚቴ በድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች ላይ የእርምት እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ።” የሚለውን ዜና ሲያሰሙን ትልቅ ለውጥ የመጣ መስሎን ነበር። በሕዝብ ጫንቃ ላይ ለ27 አመታት ሸክም የሆኑት ታሰሩ የሚል ዝርዝር ስንጠብቅ ይልቁንም ስለ አዜብ እና ስለ ቦታ መቀያየር ይነግሩናል።

አድዋዎች ከመቀሌ፣ መቀሌዎች ከአዲግራት፣ አዲግራቶች ከኤርትራዎች… የሚያደርጉት የፍትጊያ ድራማ አሁንም መስመር አልያዘም። የድራማው ዦንራ ኮሜዲም ትራጀዲም ነው። በታንክ እና መትረየስ መታጀቡ ደግሞ ጦርነትም አስመስሎታል። በሴራ፤ ሽብር እና ብቀላ ዙርያ ባጠነጠነው በዚህ ማራቶን የአድዋዎቹ ጡንቻ ለግዜውም ቢሆን ፈርጥሞ፣ ሌሎቹን ሲያብጠለጥል፣ ያሻውን ሲያወርድና ያሻውን ደግሞ ሲሰቅል ከርሟል። የተነካው ወገንም የተኛ መስሎ ሹክሹክታውን  እያደመጠ ነው። ምን ይታወቃል የስብሃት ቡድን ገና የአሸናፊነት ድሉን ሳያጣጥም ሃዘን ይቀመጥ ይሆናል።

ሰሞናዊው የመቀሌ ፉክቻ፤ በሰባዎቹ የነበረውን የኡጋንዳ ድራማ ያስታውሰናል። ሚልተን ኦቦቴ እና ኢድ አሚን ዳዳ፤  ተባብረው፣ ተሰባብረው፣ በለስም ቀንቷቸው የስልጣን ማማ ላይ ጉብ እንዳሉ፣ ከበድ ያለ የኮንትሮባንድ ንግድ ላይ ነበር የተሰማሩ። የሃገሪቷን ወርቅና የዝሆን ጥርስ ሁለት ሆነው ጋጡት። ዘረፋው ላይ ምንም ጸብ አልነበረም። ችግሩ የመጣው  የሃብት ክፍፍሉ ላይ እንደደረሱ ነው። ከዚያ በኋላ አብረው መብላት አልቻሉምና ተለያዩ። ብሄራዊውን ጉዳይ ረሱትና። ግዜያቸውን የሚያጠፉት አንዱ ሌላውን ማጥፋት ላይ ሆነ። የታሪክ መዛግብት እንደሚለን ሁለቱ የሰው ጅቦች በመፈንቅለ መንግስት እየተገለባበጡ ሃገሪቱን በፈረቃ መግዛትን ያዙ። መተካካት!

“የኢትዮጵያን ችግር ሊፈቱ” መቀሌ ላይ የተሰበሰቡት ዱዶች ነገር እንደ አዲስ ማስገረሙ አልቀረም። የሚዘርፉት እነሱ፣ የሚገድሉት እነሱ፣ የሚተካኩት እነሱ፣ የሚታደሱት እነሱ፣ የሚገመግሙት እነሱ፣ የሚገመገሙትም እነሱ! ስለሆኑ  የኢትዮጵያ ጉዳይ የትግራይ ብሄረተኞች ጉዳይ ብቻ ነው ብለው ከደመደሙ ሰነባበቱ። የመቀሌውን ክስተት መተካካት እንበለው ወይንም መከካካት ግና ሃገሪቱ ለገባችበት ቀውስ ምንም ፋይዳ የለውም። የህወሀት ሊቀመንበርና የትግራይ ክልል ኘሬዝደንት የሆኑትን አቶ አባይ ወልዱን ከዚያ አንስቶ እዚያ ማስቀመጥ ለውጥ አይደለም። የኤፈርት ምክትል ሥራ አስፈፃሚ አቶ በየነ ምክሩ፣ ከፓርቲው ሥራ አስፈፃሚነት ወደ ማዕከላዊ ኮሚቴነት አባልነት ማዛወር እርምጃ ሊሆን አይችልም። ባልዋ በህይወት እያለ የቀለደችባቸው አዜብን መገፍተርም እንዲያው ከአህዮች እርግጫ አያልፍም። አህያ ለአህያ ቢራገጥ ደግሞ ጥርስ አይዋለቅም።

በዚህ ሁሉ መሃል ግን ቀረብ ብሎ የሚታይ ነገር አለ። መፍትሄ ያልተገኘለት ችግር፣ የማይታረቅ ቅራኔ፣ የማያባራ ሽኩቻ። …. (በፎቶው የሚታዩት አዜብ መስፍን፣ አባይ ወልዱና በየነ ምክሩ ናቸው – ፎቶው በጸሃፊው የተላከ ነው)

ክንፉ አሰፋ


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው።

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጃዋርና በቀለ መታሠራቸው ተሰማ June 30, 2020 09:17 am
  • አገራዊ መድረክ ውጪ ድብቅ ውይይትን አንቀበልም June 17, 2020 06:57 am
  • ዴክሳሜታሶን! የኮሮና መድሀኒት June 17, 2020 06:49 am
  • የሰኔ 14ቱ ቀለበታዊ የፀሃይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ! June 17, 2020 06:38 am
  • የግብፅ የአባይን ውሃ ብቻዬን ልጠቀም ግትር አቋም ድርድር እንቅፋት ሆኗል June 10, 2020 07:15 am
  • የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!? April 12, 2020 02:48 am
  • በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሚጠቀሙበት የኤርትራ ስደተኛ ካምፕ ሊዘጋ ነው March 18, 2020 08:37 pm
  • እየተፈረካከሰ ያለው አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ March 18, 2020 08:09 pm
  • ኮሮና አዲስ ጉድ መዘዘ – ከቻይና በፊት በአሜሪካ ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎችን ቀጥፏል March 16, 2020 11:41 pm
  • የኮንዶሚኒየም ቤቶች በደላሎችና በመመሪያ ሰጪዎች ኔትዎርክ እየተቸበቸበ ነው! ታከለ የት ናቸው? March 9, 2020 10:18 am
  • ኤርሚያስ ለገሠ ከባለአደራ ተባረረ March 9, 2020 08:09 am
  • ድፍድፍ ሲቀል ይንሳፈፋል፤ ምሁር ሲዘቅት ይመራል፥ March 7, 2020 11:24 pm
  • ኢትዮጵያዊ ምን ይመስላል? በምንስ ይመሰላል? March 7, 2020 10:29 pm
  • WHY I WROTE “MONEY, BLOOD AND CONSCIENCE” March 4, 2020 11:15 pm
  • አድዋ፤ የጥቁር ሕዝብ ድል! March 2, 2020 11:24 am
  • ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ (አባ ጎራው) March 2, 2020 11:12 am
  • የኦነግ ሁለት መልክና ሦስት ግብሮች – ቃርሚያው ኃይል ቅጥር ነፍሰገዳይ ሆኗል February 25, 2020 11:26 pm
  • በቡራዩ “የጃል ማሮ” ፎቶ ጨረታ አፈናከተ፤ “ቡራዩ ሆኖ ከሃዲን ማሞካሸት አይቻልም” ነዋሪዎች February 17, 2020 09:13 pm
  • “ዲቃላ” የፍረጃ ፖለቲካ በኦሮሚያ የኃይል አሰላለፉን እየቀየረ ነው February 13, 2020 11:58 pm
  • “ከዚህ በኋላ ማናቸውንም በወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን” አንታገስም – ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ February 13, 2020 05:07 pm
  • “እኛ ማንም ተሳዳቢ እንዲመጣብን አንፈልግም” የጅማ ነዋሪ February 13, 2020 09:28 am
  • “ወላጆቻችሁ ሰላማዊ ሰልፍ በሕዝቡ ያስደርጉልን” – አጋቾች February 11, 2020 07:53 pm
  • “ወንጀል የፈጸመም ያስፈጸመም ተይዞ ለህግ ይቀርባል፤ ምርመራም ተጀምሯል” February 11, 2020 06:59 pm
  • ጃዋር ወደ መጨረሻው “የትግል” ስልቱ – አማራን ማበጣበጥ! February 10, 2020 11:54 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule