በሕዝብ ተጋርደን ባ’ገር ተከልለን ለካስ እኔና አንቺ ብዙም ዕውቀት የለን። እኔን ስመረምር አንቺን እዚህ ሳይሽ እኔም ያን አይደለሁ አንቺም ያቺ አይደለሽ። እንዲህ ካደረገን ስደት አሸንፎ ጭራሽ ከሚለየን ኑሮአችንን ገፎ ሠርግ ባንደግስም ባይረጭ አበባ በአዲስ ትውውቅ ድጋሚ እንጋባ። ****************** እኔና አንቺ … ፩ - ፖለቲካና ስደት እኔና አንቺ…፪ - ሀገርና ክህደት … [Read more...] about እኔና አንቺ… ፫
Right Column - Primary Sidebar
የአድዋ ድልና ትሩፋት ፈተናዎቹ
በእርግጠኝነት ኢትዮጵያዊ ልብ ላለው ሰው ሁሉ ስለ አድዋ ድል ሲሰማና ሲያወራ ልቡ በኩራት ይሞላል መንፈሱ ይነቃቃል፡፡ ኢትዮጵያዊ ብቻም አይደለም በየትኛውም ዓለም ያለ በቅኝ ግዛት ቀንበር ፍዳ ያየ የትኛውም የሰው ዘር ጭምርም እንጅ፡፡ ይህን አንጸባራቂ ድል መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ በአንድነት ተሰልፎ ካስመዘገበ እነሆ ነገ የካቲት 23 ቀን 2006ዓ.ም 118 ዓመቱን ይይዛል፡፡ ይህንን ድል ለመቀዳጀት ፈተና የነበሩት ነገሮች ምን ምን ናቸው? ለመሆኑ ይህ ድል እንዴት ተገኘ ? የዚህ ታላቅ ድል ትሩፋቶችስ ምን ምን ናቸው? የዚህ ድል ጠላቶች እነማን ናቸው? ይህ ድል እንዴት ይጠበቃል? ብዙ ቢባልለት ከማይበቃው ከአድዋ ድል እነዚህን ነጥቦች ብቻ ነጥለን ለማየት እንሞክራለን፡፡ ዐፄ ምኒልክ ምታ ነጋሪት ክተት ሠራዊት ብለው ፋሽስት ጣሊያን በዘመነ ዐፄ ዮሐንስ 4ኛ ከነበረበት አልፎ … [Read more...] about የአድዋ ድልና ትሩፋት ፈተናዎቹ
ጀግናውና ከሀዲው ረዳት አብራሪ ኃይለ መድኅን አበራ
ረዳት አብራሪ ኃይለ መድኅን አበራ በረዳትነት የሚያበረውን ቦይንግ 767 አውሮፕላን አቅጣጫ ቀይሮ ስዊዘርላንድ የፖለቲካ ጥገኝነት በመጠየቅ ካሳረፈ ወዲህ የዓለም አቀፍ የብዙኃን መገናኛውን ትኩረት ይዞ ቆይቷል፡፡ ከዚህ ድርጊት በኋላም በሁለቱም ጎራ ያሉ አካላት ረዳት አብራሪ ኃይለ መድኅን አበራን በተመለከተ የተለያየ መላምት ትችትና ነቀፋ ሲሰነዝሩበትና ሲሰናዘሩበት ሰንብተዋል፡፡ የሕዝብ ወገን የሆነው ረዳት አብራሪ ኃይለ መድኅን አበራን ጀግና ነው አርበኛ ነው ሲለው “መንግሥት” እና ደጋፊዎቹ ደግሞ ከሀዲ ነው ብለውታል፡፡ እነኝህ ሁለቱም አካላት ረዳት አብራሪ ኃይለ መድኅን አበራን በየበኩላቸው ያሉትን ለመሆኑ የየራሳቸውን ማስረጃ የሚሏቸውን ነገሮች በመግለጽ ላይ ናቸው፡፡ የሕዝብ ወገን የሆነው ክፍል ረዳት አብራሪ ኃይለ መድኅን ጀግና ነው የሚሉበትን ምክንያት ሲጠቅሱ በአገዛዙ ተማሮ … [Read more...] about ጀግናውና ከሀዲው ረዳት አብራሪ ኃይለ መድኅን አበራ
ትዝታ በ60/በስድሳ
ወደ ኋላ ሄዶ አበባ ሲፈካ፣ ጊዜ ሲተካካ፣ ልጅ ስልጣኔ መጥቶ በራችን ሲያንኳዋካ፤ ከባህል ጥል ገጥሞ ለመኖር ለብቻው፣ ማየት ማስተዋል ነው፣ ኧረ የሰላም ያለህ ተው አይሆንም ሲለው ባህል ሲማጠነው ደባል እንዲሆነው፤ (ቀሪውን ግጥም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about ትዝታ በ60/በስድሳ
የእርስ በእርስ ግጭት ነገሶበት የከረመው በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማህበር ጠቅላላ ጉባኤ በሰላም ተጠናቀቀ
በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚቴ ማህበር ስራ አመራር አባላት እና በቀድሞው የማህበሩ ሊቀመንበር ደጋፊዎች መሃከል በተፈጠረው የስልጣን ሽኩቻ በአባላቱ ላይ አጥልቶ የነበረው የእርስ በእስር ግጨት መቀልበሱን ምንጮች ከሪያድ አስታወቁ። ፌብረዋሪ 21 2014 ምሸት ሲጠበቅ የነበረው በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት ማህበር ጠቅላላ ጉባኤ በሰላም መጠናቀቁን ተከትሎ በሪያድ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ደስታቸውን በመግለጽ ፈጣሪያቸውን አመስግነዋል ብለዋል፡፤ በጉባኤው ላይ ከኤንባሲው የተወከሉ ዲፕሎማቶች በታዛቢነት መገኘታቸውን የጠቀሱት አንድ የጉባኤው ተሳታፊ በስራ አመራሩ እና በሼክ መስጠፋ ሁሴን መሃከል ተከስቶ የነበረው ልዩነት በዲፕሎማቱ ብለሃት ከወዲሁ መቀልበሱን ጠቅሰው ስብሰባው ያለምንም ችገር እና ስጋት በሰላም መካሄዱን አረጋግጠዋል። አስተያየት ሰጪው አያይዘው ሲገልጹ ጥቂቶች በብዙሃኑ ደም ዎኝተው … [Read more...] about የእርስ በእርስ ግጭት ነገሶበት የከረመው በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማህበር ጠቅላላ ጉባኤ በሰላም ተጠናቀቀ
በጭካኔ እየተገዳደልን፣ ወዴት እየሔድን ነው?
ከሳምንት በፊት እዚህ ጅዳ ሻረ ሄራ በሚባል አካባቢ የሃበሻን ዘር ያሳዘነ የግድያ ድርጊት መፈጸሙን ሰማሁ። ትውውቅ ባይኖረንም በአይን የማውቀው ወንድም አብዱ ሁሴን ይማም በጭካኔ መገደሉን የሰማሁት ድርጊቱ በተፈጸመ ከሰአታት በኋላ ከአንድ ወዳጀ በኩል በደረሰኝ የስልክ መልዕክት ነበር። በቀጣይ ቀናት ወጣቱ አብዱ የተቀጠፈበትን የጭካኔ ድርጊት የሚያወግዙ በርካታ መልዕክቶች ማስተናገድ ጀመርኩ። በመካከላችን ባሉ ጥቂት የሰው አውሬዎች እየሆነ ያለው እና ስማችን የመክፋቱ ነገር ያሳሰባቸው በርካታ ወገኖች በግድያው ማዘናቸውን በመግለጽ በርካታ መልዕክቶችን ልከውልኛል። በጭካኔ ተፈጸመ የተባለው ድርጊት ዘልቆ ነፍሱን አስጨንቆ ያሳዘነው አንድ ወንድም የላከልኝ መልዕክት እንዲህ ይላል .... "ጩኸት ሰሚ ሲያጣ እንዴት ያናዳል ... ሀበሻ የድሮዎቹ የሉም ... ውድ የሆነውን የሰውን ደም … [Read more...] about በጭካኔ እየተገዳደልን፣ ወዴት እየሔድን ነው?
ጥላ መጽሔት 9ኛ ዕትም
ጀርመን አገር የምትታተመው ጥላ መጽሔት 9ኛ እትም ለንባብ በቅታለች። ለወቅታዊው ሁኔታም ልዩ ትኩረት ሰጥታለች። (ሙሉውን መጽሔት ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about ጥላ መጽሔት 9ኛ ዕትም
የኢትዮጵያ የድህነት አዙሪት መንስኤና መፍትሄዎች “በጥቂቱ”
አርእስቴን በጥቂቱ ያልኩበት ምክንያት የተነሳሁበት ርእስ ምን ያህል ሰፊ እንደሆነ ስለማውቅ ነገር ግን ልንወያይበት እንደሚገባ በመረዳቴ ለውይይት መክፈቻ ይሆን ዘንድ እንጂ እኔ ባለኝ እውቀት ብቻ ሙሉ በሙሉ ልተነትነው እንደማልችል በማመኔ ነው። ይህም ቢሆን እንደዜግነቴ ሃገሬን ለዘመናት ለተቆራኛት የድህነት ችግር መንስኤና መፍትሄ ሊሆኑ ይችላሉ ብዬ ያሰብኳቸውን ዋና ዋና ነጥቦች በመጠኑ ለመተንተን ለመሞከር ነው። በአንድ ሃገር ወይም አካባቢ የሚኖር ማህበረሰብ ለግላዊም ሆነ ማህበራዊ ፍላጎቶቹ በበቂ ሁኔታ መሟላት አጣጥሞና አስማምቶ በእኩልነት ሊያኖረው የሚችል ህግና ስርዓት በብዙሃኑ ፍላጎትና ስምምነት ላይ ተመስርቶ መቀረፅ አለበት። የሰውን ልጅ ከእንሰሳት የሚለየውና የተሻለ ያደረገውም አንዱ ሌላውን በእኩልነት ማየቱ እንዲሁም ሰው በጉልበቱ የበላይ መሆን የማይችልበት ሁናቴ መፈጠሩ … [Read more...] about የኢትዮጵያ የድህነት አዙሪት መንስኤና መፍትሄዎች “በጥቂቱ”
የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ሊቀመንበር አቶ ኦባንግ ሜቶ የ3 ቀን ቆይታ በኖርዌ
ተወዳጁ የሰብአዊ መብት ተከራካሪና የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ሊቀመንበር አቶ ኦባንግ ሜቶ በ8-2-2014 በኖርዌ ኦስሎ በመገኘት ከኢትዮጵያዉያን የስደተኞች ማሕበር ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ጋር በኖርዌ ስለሚገኘው ጥገኝነት ጠያቂ ኢትዮዽያዊ የሰብዓዊ መብት አያያዝ ሁኔታ እና ይህ ጥገኝነት ጠያቂ በኖርዌ ምን ያህል ተቀባይነት አለው በሚለው ላይ ሰፋ ያለ ውይይት አድርገዋል። በተጨማሪም አቶ ኦባንግ በ9-2-2014 በሳውድ አረቢያ የተጎዱ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችንን ለመርዳት በተዘጋጀው የገንዘብ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ላይ እኛ ስንሰቃይ አሜሪካ ዝም ብላ ይሆናል፣ እኛ ስንሰቃይ የአውሮፓ ሕብረት ምንም አላለ ይሆናል የኢትዮጵያ አምላክ ግን ከኛ ጋር ነው በሚል ልብ የሚንካ ነገር ተናግረዋል። በተጨማሪም አቶ ኦባንግ በ10-2-2014 በኖርዌ ጥገኝነት በጠየቁ ኢትዮዽያዊ ወገኖቻቸው ላይ … [Read more...] about የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ሊቀመንበር አቶ ኦባንግ ሜቶ የ3 ቀን ቆይታ በኖርዌ
Foreign regimes use spyware against journalists, even in U.S.
Mesay Mekonnen was at his desk, at a news service based in Northern Virginia, when gibberish suddenly exploded across his computer screen one day in December. A sophisticated cyberattack was underway. But this wasn’t the Chinese army or the Russia mafia at work. Instead, a nonprofit research lab has fingered government hackers in a much less technically advanced nation, Ethiopia, as the likely culprits, saying they apparently bought commercial spyware, essentially off the shelf. This … [Read more...] about Foreign regimes use spyware against journalists, even in U.S.










