• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“ደብረማርቆስና ባህርዳር ላይ ሰላማዊ ሰልፍ ልታደርጉ ነው የምትሄዱት” ፖሊስ

June 22, 2015 09:19 am by Editor Leave a Comment

• ከአዲስ አበባ ወደ ጎጃም ለሌላ ለቅሶ በመሄድ ላይ የነበሩ ዜጎች ተደብድበው ተመልሰዋል

የሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮችና አባላት ሰኔ 8/2007 ዓ.ም ደብረማርቆስ ከተማ የተገደለው የሳሙኤል አወቀ ለቅሶ እንዳይደርሱ ታገዱ፡፡ አመራሮቹና አባላቱ ሰኔ 13/2007 ዓ.ም በጠዋት ከአዲስ አበባ ተነስተው የሳሙኤል አወቀ ቤተሰቦች ወደሚገኙበት ምስራቅ ጎጃም ዞን ግንደወይን እያቀኑ በነበረበት ወቅት አባይ ድልድይ ላይ በፌደራል ፖሊስ ታፍነው ከቀኑ 8 ሰዓት ጀምሮ ጎሃ ፂዮን ከተማ ውስጥ እስከ ምሽቱ 2 ተኩል ድረስ ታግተው ውለዋል፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላትን ወደ ለቅሶ እንዳይሄዱ ያገዱት ከአዲስ አበባ የሄዱና ከቦታው ተዘጋጅተው ሲጠብቁ የነበሩ የፌደራል ፖሊሶች እንደሆኑ ለማወቅ ተችሏል፡፡

አመራሮቹና አባላቱ ለፖሊስ ቃል ሲሰጡ ከሳሙኤል አወቀ ጋር የነበራቸውን ግንኙነት፣ በፓርቲው ውስጥ ያላቸውን ኃላፊነት፣ ሳሙኤልን ማን እንደገደለው የሚመለከቱ ጥያቄዎች ቀርበውላቸዋል፡፡ ለቅሶ እንዳይደርሱ ከተከለከሉትና ታተው የዋሉት:-

1. ኢ/ር ይልቃል ጌትነት/ የፓርቲው ሊቀመንበር
2. ይድነቃቸው ከበደ/ የፓርቲው የህግ ጉዳይ ኃላፊ
3. ወሮታው ዋሴ /የፓርቲው የፋይናንስ ጉዳይ ኃላፊ
4. ሀብታሙ ደመቀ/ የኦዲትና ኢንስፔክሺን አባል
5. ጌታቸው ሺፈራው/ የነገረ ኢትዮጵያ ዋና አዘጋጅ
6. ጋሻው መርሻ/ የብሄራዊ ምክር ቤት አባል
7. እምላሉ ፍስሃ/ የብሄራዊ ምክር ቤት አባል
8. ሜሮን አለማየሁ/ አባል
9. ጥላሁን አበጀ/ አባል
10. ጠና ይታየው/ አባል
11. እስጢፋኖስ በኩረጽዮን /አባል
12. ኃይለማሪያም ተክለ ጊዮርጊስ/ አባል
13. ጋሻነህ ላቀ/ አባል
14. ግርማ ቢተው አባልና
15. የመኪናው ሾፌር ናቸው

ከምሽቱ 2 ሰዓት ተኩል ከአዲስ አበባ በመንገድ ትራንስፖርት ሰራተኞችና ትራፊክ ፖሊሶች ህጋዊ መሆኑ ተረጋግጦ ያለፈው እንዲሁም ለአራት ቀን ከፓርቲው ጋር ውል የያዘው መኪና እንዳይንቀሳቀስ ተከልክሎ ከፍተኛ አመራሮቹና አባላቱ ከእስር ተለቀዋል፡፡ በተጨማሪም የሰማያዊ ፓርቲ ልዑካን ይዘዋቸው የነበሩ ቁሳቁሶች ለምርመራ በሚል በፖሊስ ተይዘዋል፡፡

በሌላ ዜና ከአዲስ አበባ ተነስተው ምስራቅ ጎጃም ዞን ደብረ ኤልያስ ወደ ሌላ ለቅሶ ሲሄዱ የነበሩ ዜጎች የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት ከታፈኑ በኋላ ደጀን ላይ ተይዘው ከፍተኛ ድብደባ ተፈፅሞባቸው በግዳጅ ወደ አዲስ አበባ እንዲመለሱ ተደርገዋል፡፡ ተመልሰው ወደ ለቅሶው ቢሄዱ እስከ 10 ሺህ ብር ሊቀጡ እንደሚችሉ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል፡፡ እነዚህ ዜጎች በተያዙበት ወቅት ሰማያዊ ፓርቲ ደብረማርቆስና ባህርዳር ላይ ሰላማዊ ሰልፍ ሊያደርግ እንደሆነ እንደተገለጸላቸው እነሱም የሰማያዊ ፓርቲ ሰልፍ ላይ ትገኛላችሁ ተብለው ተጠርጥረው እንደሆነ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ይህ ዜና እየተሰራ ባለበት ወቅት ማረፊያ ክፍል እየፈለጉ የሚገኙት የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት በፌደራል ፖሊስና በደህንነቶች ከፍተኛ ክትትል እየደረሰባቸው መሆኑ ታውቋል፡፡

ተጨማሪ መረጃ

የሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች አሁንም ወደ ሳሙኤል ቤተሰቦች እንዳይሄዱ እንደታገዱ ናቸው

ሰኔ 8/2007 ዓ.ም የተገደለውን የሳሙኤል አወቀን ቤተሰቦች ለማስተዛዘን ከአዲስ አበባ ወደ ግንደወይን በሚሄዱበት ወቅት አባይ ድልድይ ላይ ከአዲስ አበባ በመጡ የፌደራል ፖሊሶችና ደህንነቶች ታፍነው ወደ ግንደወይን እንዳይሄዱ የተከለከሉት የሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮችና አባላት አሁንም እንዳይንቀሳቀሱ እንደታገዱ ናቸው፡፡ ትናንት ከስምንት ሰዓት ጀምሮ ታስረው የዋሉት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ምሽቱ 2 ሰዓት ተኩል ላይ ቢለቀቁም መኪናውን ጨምሮ ቁሳቁሶቻቸው በሰሜን ሸዋ ዞን ወረጃርሶ ወረዳ ፖሊስ ጣቢያ በመያዙ መንቀሳቀስ አልቻሉም፡፡

የፖሊስ ጣቢያው ኃላፊ ኢንስፔክተር ወጋየሁ ጎንፋ መሬ “ወደ ገጠር ወጥቻለሁ” በሚል እንዲሁም ሌሎች አመራሮች ቢሮ ዘግተው በመውጣታቸው ቁሰቁሶቹን መቀበል አልተቻለም፡፡ ይሁንና ኢንስፔክተር ወጋየሁን ጨምሮ ሌሎች አመራሮችም ከተማ ውስጥ እንደሚገኙ ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡

የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ከእስር ሲለቀቁ ደህንነትና ፖሊሶቹ ነጻ እንደሆኑና እንዳጉላሉዋቸው በመግለጽ ይቅርታ ጠይቀው የነበር ቢሆንም ቁሳቁሶቻቸው ግን “ለምርመራ” በሚል ይዘዋቸዋል፡፡ አመራሮቹና አባላቱ “ነጻ ከሆንን ቁሳቁሶቻችንም የሚያዙበት መንገድ መኖር የለበትም፡፡ ቁሳቁሶቻችን ካልሰጣችሁን አንወጣም” ቢሉም ፖሊስ መብራቱን በማጥፋት ከግቢ አስወጥቷቸዋል፡፡ (በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር)

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Politics Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጃዋርና በቀለ መታሠራቸው ተሰማ June 30, 2020 09:17 am
  • አገራዊ መድረክ ውጪ ድብቅ ውይይትን አንቀበልም June 17, 2020 06:57 am
  • ዴክሳሜታሶን! የኮሮና መድሀኒት June 17, 2020 06:49 am
  • የሰኔ 14ቱ ቀለበታዊ የፀሃይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ! June 17, 2020 06:38 am
  • የግብፅ የአባይን ውሃ ብቻዬን ልጠቀም ግትር አቋም ድርድር እንቅፋት ሆኗል June 10, 2020 07:15 am
  • የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!? April 12, 2020 02:48 am
  • በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሚጠቀሙበት የኤርትራ ስደተኛ ካምፕ ሊዘጋ ነው March 18, 2020 08:37 pm
  • እየተፈረካከሰ ያለው አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ March 18, 2020 08:09 pm
  • ኮሮና አዲስ ጉድ መዘዘ – ከቻይና በፊት በአሜሪካ ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎችን ቀጥፏል March 16, 2020 11:41 pm
  • የኮንዶሚኒየም ቤቶች በደላሎችና በመመሪያ ሰጪዎች ኔትዎርክ እየተቸበቸበ ነው! ታከለ የት ናቸው? March 9, 2020 10:18 am
  • ኤርሚያስ ለገሠ ከባለአደራ ተባረረ March 9, 2020 08:09 am
  • ድፍድፍ ሲቀል ይንሳፈፋል፤ ምሁር ሲዘቅት ይመራል፥ March 7, 2020 11:24 pm
  • ኢትዮጵያዊ ምን ይመስላል? በምንስ ይመሰላል? March 7, 2020 10:29 pm
  • WHY I WROTE “MONEY, BLOOD AND CONSCIENCE” March 4, 2020 11:15 pm
  • አድዋ፤ የጥቁር ሕዝብ ድል! March 2, 2020 11:24 am
  • ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ (አባ ጎራው) March 2, 2020 11:12 am
  • የኦነግ ሁለት መልክና ሦስት ግብሮች – ቃርሚያው ኃይል ቅጥር ነፍሰገዳይ ሆኗል February 25, 2020 11:26 pm
  • በቡራዩ “የጃል ማሮ” ፎቶ ጨረታ አፈናከተ፤ “ቡራዩ ሆኖ ከሃዲን ማሞካሸት አይቻልም” ነዋሪዎች February 17, 2020 09:13 pm
  • “ዲቃላ” የፍረጃ ፖለቲካ በኦሮሚያ የኃይል አሰላለፉን እየቀየረ ነው February 13, 2020 11:58 pm
  • “ከዚህ በኋላ ማናቸውንም በወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን” አንታገስም – ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ February 13, 2020 05:07 pm
  • “እኛ ማንም ተሳዳቢ እንዲመጣብን አንፈልግም” የጅማ ነዋሪ February 13, 2020 09:28 am
  • “ወላጆቻችሁ ሰላማዊ ሰልፍ በሕዝቡ ያስደርጉልን” – አጋቾች February 11, 2020 07:53 pm
  • “ወንጀል የፈጸመም ያስፈጸመም ተይዞ ለህግ ይቀርባል፤ ምርመራም ተጀምሯል” February 11, 2020 06:59 pm
  • ጃዋር ወደ መጨረሻው “የትግል” ስልቱ – አማራን ማበጣበጥ! February 10, 2020 11:54 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule