ለሞረሽ የዐማራ ድምፅ ሬድዮ ሥርጭት መጀመር የሚያግዘንን ገንዘብ በተከታታይ እርዳታ መጠየቂያ። ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ማስታወቂያና የሕዝብ ግንኙነት … [Read more...] about ለሞረሽ የዐማራ ድምፅ ሬድዮ አገልግሎት የገንዘብ እርዳታ ጥየቃ ማስታወቂያ
Right Column - Primary Sidebar
በመቶዎች የሚቆጠሩ ጋዜጣዊ መግለጫዎች
ገዢው አምባገነን የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት በየዕለቱ በሚያደርገው ፀረ-ኢትዮጵያዊ ተግባር፤ የተለያዩ የፖለቲካ ሕዝባዊ ስብስቦች መግለጫ ያወጣሉ። አዳዲስና ነባር የፖለቲካ ድርጅቶች፤ አለን በማለት ስማቸውን በአንባቢዎች ያስመዘግባሉ። ለመሆኑ ጋዜጣዊ መገለጫዎች ለምንድን ጉዳይ ነው የሚወጡት? ማነው የሚያወጣቸው? መግለጫዎችን ተከትሎ የሚተገበሩት ምንድን ናቸው? አሉስ ወይ? መግለጫ አውጪዎቹና መግለጫ ያላወጡ የፖለቲካ ሕዝባዊ አካሎች መለያቸው ምንድን ነው? መግለጫዎችና አውጪዎቻቸው፤ ሕዝባዊ ናቸው ወይንስ ጠባብ ወገንተኛ? መልዕክት አላቸው ወይንስ አደረግሁ ለማለት የተወረወሩ? አስፈላጊነታቸውስ ምን ያህል ነው? በተደጋጋሚ ጋዜጣዊ መግለጫ በተንጎደጎዱ ወቅት የደረሱኝ እጦማሮች ነበሩ። ሁሉም ወቀሳዎች ናቸው። “ለምን መግለጫ አታወጣም?” “ካሁን በፊትም ዝም ብለሃል!” የሚሉና … [Read more...] about በመቶዎች የሚቆጠሩ ጋዜጣዊ መግለጫዎች
ዓለም አቀፍ ሕብረት ለፍትሕ ለኢትዮጵያውያን የቢሊዮኖች ዶላር ካሣ ይጠይቃል
ጋ ዜ ጣ ዊ መ ግ ለ ጫ መጋቢት 7 ቀን 2008 ዓ/ም Garland, Texas: (ጋርላንድ፤ ቴክሳስ)፡ ዓለም አቀፍ ሕብረት ለፍትሕ - የኢትዮጵያ ጉዳይ፤ መንግሥታዊ ያልሆነ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኢኮኖሚና የማሕበራዊ ጉዳዮች አካል ውስጥ የተመዘገበ ተቋም ነው። በዚህ ሳምንት በኢትዮጵያ እየተከናወነ በሚገኘው የኢጣልያ ፕሬዚዳንትና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጉብኝት አጋጣሚ ጊዜ የድርጅታችን ዓላማ የኢጣልያ መንግሥት እ.አ.አ. በ1928-33 ዓ/ም በኢትዮጵያ ላይ ለፈጸመው የጦር ወንጀልና የሰው እልቂት ተገቢው ፍትሕ እንዲገኝና ከኢትዮጵያ የተዘረፈውን ኢጣልያ፤ የቫቲካን ቤተ መጻሕፍትና ሌሎችም እንዲመልሱና እንዲክሱ ለማድረግ ነው። በ1928-33 ዓ/ም ኢጣልያ በኢትዮጵያ ላይ በፈጸመችው ጦርነት፤ ፋሺሽቶች በአውሮፕላኖች አማካኝነት በነስነሱት የመርዝ ጋዝ ጭምር የብዙ ሰው … [Read more...] about ዓለም አቀፍ ሕብረት ለፍትሕ ለኢትዮጵያውያን የቢሊዮኖች ዶላር ካሣ ይጠይቃል
በርሀብ የሚገድል መንግሥት እንዴት በሥልጣን ላይ ይቆይ?
ታላላቅ ረሀቦች ተብለው በዓለም ታሪክ ከሚዘከሩት ውስጥ የቻይናውያን ረሀብ ኣይዘነጋም። እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከ1958-1961 ድረስ ቻይና ውስጥ ከፍተኛ ረሀብ ተከስቶ ወደ ሰላሳ ሚሊዮን ህዝብ ረግፏል። ብዙ ምሁራን እንደሚሉት ለዚህ አስከፊና ቻይናውያን ሊረሱት ለማይችሉት ረሀብ አንደኛ ተጠያቂ ማዖ ዚዳንግን ነው። የኮሙኒስት ፓርቲ መሪ የነበረው ማዖ ዚዳንግ በሶቪየት ህብረት በነጆሴፍ ስታሊን አብዩት ፍቅር የከነፈ ሲሆን ቻይናን በአምስት ዓመታት ውስጥ ከሁዋላ ቀር ግብርና አውጥቼ ወደ ኢንዱስትሪ እለውጣታለሁ በማለት Great Leap Forward ታላቁ የግስጋሴ ርምጃ የተሰኘ የአምስት ዓመት የትራንስፎርሜሽን እቅድ ነድፎ አመጣ። እቅዱ የግል የመሬት ባለቤትነትን የሚጻረርና የወል እርሻን የሚያራምድ ነበር። በዚሁ እቅድ መሰረት ቻይናውያን በፍጥነት እየተደራጁ የወል እርሻ ሥራን … [Read more...] about በርሀብ የሚገድል መንግሥት እንዴት በሥልጣን ላይ ይቆይ?
ግፍ በገፍ የሞላበት አገር!
ከደቡብ ኦሞ እስከ መተማ፤ ከጅጅጋ እስከ ጋምቤላ፤ ከመቀሌ እስከ ባሌ፤ ከወልቃይት እስከ ኮንሶ! በአንድ ማህበረሰብ ውስጥ ቅድመ-አያቶች፣ አያቶች፣ ወላጆችና ልጆች፤ ሦስትና ከዛም በላይ የሆነ ትውልድ ተመሳሳይ በሆኑ ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች መሃል ተተብትቦ የሚማቅቅ ከሆነ የዛ ማህበረሰብ ጉዞ ጤናማነትና አቅጣጫ ጥያቄ ውስጥ ይወድቃል፡፡ በእንዲህ አይነት ማህበረሰብ ውስጥ መሰረታዊ የሆኑና የጎሉ ለውጦች ብዙም አይስተዋሉም፡፡ አንዳንዶቹም ለውጦች የቁልቁለት ጉዞ ውጤቶች ይሆኑና በራሱ ብቻ ሳይሆን በአያቶቹም ቁስል የሚማቅቅ፣ መቃብር ቆፋሪና ሸክሙ የከበደው ትውልድ ይፈጠራል፡፡ ይህ አይነቱ ትውልድ የተጫነውን ሸክሙን አራግፎ በነገ ህይወቱና ጥቅሞቹ ዙሪያ ላይ በማተኮር ለፈጠራና ለምርምር ሊያውለው የሚችለውን አቅሙንና ጊዜውን ያልኖረበትን ትላንትን እያመነዠከና የወረሰውን … [Read more...] about ግፍ በገፍ የሞላበት አገር!
ከተማርኩት ቁጥር 1
ያሜሪካ ቆይታዬ በጣም አጭር ነው። ሁለት አመት እንኳን አይሞላም። ላገሩ አሁንም ላገሩ ባዳ ለወንዙ እንግዳ ነኝ። ገና ብዙ ያልገባኝ ነገር አለ። ግን በዚህች አጭር ጊዜም ቢሆን ብዙ ጠቃሚ ነገር ተምሬያለሁ ብል “አይ ገና ምኑ ተይዞ” እንደማትሉኝ ተስፋ አደርጋለሁ። ለምን ቢባል ልማር ላለ ሳር ቅጠሉ እውቀት መሆኑን ታውቁታላችሁ ብዬ ነው። ይልቅስ ለመሆኑ ምን ተማርክ ብትሉኝ ወጌን እጀምራለሁ። አዎ! ብዙ ነገር። ከእንግዲህ ምናልባት ሰሚ ካገኘሁ ከተማርኩት እያልኩ በተከታታይ አንዳንድ ነገር ለማካፈል አቅጃለሁ። ታዲያ እኔ ትምህርት አገኘሁበት ያልኩት ነገር ከታወቀ የቆየ ወይም የፊደል ቆጣሪ ግንዛቤ ሆኖ ካገኛችሁት የሞተውን አባባ ይለዋል ወይም የልጅ ነገር ሳትሉ ሃሳብ ስጡበት። እኔ አላማዬ መማር ስለሆነ ከስህተቴ እማራለሁ። ከተማርኩት ቁጥር 1 ወደፍሬ ነገሩ ከመግባቴ በፊት … [Read more...] about ከተማርኩት ቁጥር 1
ኢትዮጵያን የሚወክሉ የተለያዩ ወገኖች፤
የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ መግለጫ መጋቢት 1፤ 2008ዓም፤ ዋሽንግቶን ዲሲ፤ የአፈጻጸም ማጠቃለያ፤ ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) የካቲት 6፤ 2008ዓም (February 14, 2016) በአሜሪካ የሜሪላንድ ጠቅላይ ግዛት ሲልቨር ስፕሪንግ ከተማ ባደረገው ሕዝባዊ ስብሰባ ላይ “የኢትዮጵያ የዕርቅና ርትዓዊ ፍትሕ ምክርቤት” መመሥረቱን ይፋ አድርጓል፡፡ ምክርቤቱ የተመሠረተው ሕዝባዊ ጉባዔው ከመካሄዱ በፊት በነበሩት ሦስት ቀናት ውስጥ ኢትዮጵያን የሚወክሉ ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍል የተውጣጡ ወገኖች ባካሄዱት ስትራቴጂካዊ ውይይት ነበር፡፡ ምክርቤቱ “የእኛ ለኛ” ወይም የሕዝብ ለሕዝብ ንቅናቄ ሲሆን ዕርቅ፣ የጉዳት ፈውስና ርትዓዊ ፍትሕ በኢትዮጵያ እና በኢትዮጵያውያን መካከል ለማምጣት የሚተጋ ይሆናል፡፡ አጀማመር፤ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ገና … [Read more...] about ኢትዮጵያን የሚወክሉ የተለያዩ ወገኖች፤
በዐማራው ነገድ ላይ የደረሰ የዘር ማጥፋትና ማጽዳት ወንጀል ጥናት ውጤት ማጠቃለያ ዘገባ!
ኢትዮጵያ አገራችን እያከተመ ባለው ምዕተ-ዓመት ሁለት የተለያዩ የማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፓለቲካዊ ለውጦችን አስተናግዳለች። የመጀመሪያው በ1966 የፈነዳው አብዮትና ሶሻሊስታዊ እንቅስቃሴ ሲሆን፣ ሁለተኛው በክስተቱም ሆነ በውጤቱ እጅግ የተለየው ደግሞ ከ1983 ጀምሮ የተንሰራፋው የዘመነ መሳፍንት ተምሳሌት ወያኔ መራሹ ፓለቲካ ነው። (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about በዐማራው ነገድ ላይ የደረሰ የዘር ማጥፋትና ማጽዳት ወንጀል ጥናት ውጤት ማጠቃለያ ዘገባ!
ህወሃት ራሱን “ሳያጸዳ” በሌላው ዘምቷል
“የኢህአዴግን መርህ እስከተከተለ ድረስ መሃይምም ቢሆን ሚኒስትር እናደርጋለን” ያሉት መለስ ዙሪያቸውን “የበታች” በሆኑ ሹሞች አስከብበው የቆዩት ያለምክንያት አልነበረም፡፡ “አዋቂ፣ ጠቢብ፣ ባለራዕይ፣ ምንተስኖት፣ …” የሚሉ “ማዕረጎችን” አስገኝተውላቸዋል፡፡ ከዚህ አንጻር የፈለጉትን ሥልጣን ላይ ያስቀምጣሉ፤ ከዚያ በሙስና ያበሰብሳሉ፤ ከዚያም ወደ “ቆሻሻ ቅርጫት” ይጥላሉ፡፡ በሕይወት ለቆዩት “ቅርጫቱ” ትልቅ መድህን ሲሆን ለዚያ ያልታደሉት ግን ትርጉሙ ሌላ ነው፡፡ ይህ የመለስ አሠራር የህወሃት መመሪያ ሆኖ ቆይቷል፤ አሁንም እየተሰራበት ነው፡፡ በኦሮሞ ከተሞች በተነሳው ሕዝባዊ ንቅናቄ የተደናገጠው ህወሃት ከረፈደ “ጽዳት” ጀምሯል፡፡ የችግሩ መንስዔ ራሱ ሆኖ “ልክ መግባት” ሲገባው ለህዝብ “ሥራ ላይ ነን” ለማለት “የኦህዴድን አመራሮች” ማንሳቱ አስታውቋል፡፡ የጎልጉል እማኝ … [Read more...] about ህወሃት ራሱን “ሳያጸዳ” በሌላው ዘምቷል
የኢትዮጵያ ጉዳይ መጽሔት
መጽሔቱን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ። … [Read more...] about የኢትዮጵያ ጉዳይ መጽሔት










