ተማሪዎች ያለዕድሜያቸው ጫት፣ ሲጋራና ልቅ ወሲብ ይጀምራሉ ሴት የቢሮ ሠራተኛ ሴቶች በወሲብ ንግድ ኑሮአቸውን ይደጉማሉ ኢትዮጵያ ልጆችዋን እየከሰረች ነው ትግራይ ጫት መቃም ክልክል ነው "በስነምግባር የታነፁ ዜጐችን በማፍራት ረገድ አገሪቱ ፈታኝ ሁኔታ ላይ ናት" በአዲስ አበባ ከአንደኛ ደረጃ እስከ ከፍተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚማሩ ተማሪዎች፤ ለከፍተኛ የስነ ምግባር ጉድለቶች እንደተጋለጡ ጥናቶች አመለከቱ፡፡ ሰሞኑን የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ከባለድርሻ አካላት ጋር “ስነምግባር ለእድገት ሁሉ መሠረት ነው” በሚል ርዕስ ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ በቀረቡት ጥናቶች በተለይ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች፤ በየትምህርት ቤቶቹ አካባቢ ባሉ ህገወጥ የአልኮል፣ የአደንዛዥ እጽ መጠቀሚያ እና የወሲብ ፊልሞች ማሣያ ቤቶች መበራከት የተነሣ ለችግሩ ተጋላጭነታቸው … [Read more...] about 23 ዓመት + አስደንጋጭ + አሳዛኝ = ወዴት እየሄድን ነው?
Left Column
ወገንን በመርዳት ለኢትዮጵያ ያለን ፍቅር ይገለጻል!
የዶክተር ካትሪን ሃምሊን እና የባለቤታቸው በዶ/ር ሬጅ ሃምሊን ግማሽ ክፍለ ዘመን የተጠጋው በጎ ምግባር የሚያሳዩ ድርሳናትን ስፈታትሽ አድሬ አረፋፈድኩበት ። "የፊስቱላ ተጠቂዎች የተስፋ ታሪክ " በሚል በአንድ ወቅት በፊሱትላ በሽታና በዶክተር ካትሪን እና በቤተሰባቸው በስራ ባልደረቦቻቸው ተጋድሎ ዙሪያ የቀረበ በእጀ ነበረ ከሲድኒ አውስትራልያ መስፍን ማሞ ተሰማ ያቀረበልንን ድንቅ በበቂ መረጃ ደጋግሜ አነበብኩት። "ዶ/ር ካትሪን ሀምለን በአሁን ሰአት በአውስትርሊያ ግዛት በአንድ የባህር ዳርቻ በሚገኘው ምቾታማና የናጠጠ መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ ቀሪውን የህይወት ዘመናቸውን እንኳ ለማሳለፍ አልፈለጉም። ዛሬም በዚህ እድሜያቸው ከሃገር ሃገር እየዞሩና እየተንከራተቱ ዕርዳታ በመጠየቅ የፊስቱላን በሽታ ከምድረ ኢትዮጵያ ለማስወገድ እንዲቻል የፋይናንስ፤ የማቴሪያልና የባለሙያ ኃይልን እያደራጁ … [Read more...] about ወገንን በመርዳት ለኢትዮጵያ ያለን ፍቅር ይገለጻል!
“Time to bring back Eritrea from the cold”
Many observers agree that recent unfortunate developments in the Middle East can easily spillover to the Greater Horn of Africa region2. There are groups that are fanning ideologies advanced by the various actors in Middle East’s sectarian conflict. In the light of the new developments in the region, it makes sense for the United States to review its relationship with Eritrea and Ethiopia and rebalance its portfolio. The interesting question for Eritrea and Ethiopia is therefore how to respond … [Read more...] about “Time to bring back Eritrea from the cold”
ዜጋዊ ጥያቄ
የካቶሊክ “ቤተክርስቲያን” በሀገራችን የራሷን ዩኒቨርስቲ ልትከፍት ነው በግንባታ ላይ ይገኛል፡፡ ስለ ጉዳዩ ምን ታስባላቹህ ? ይህ ነገር ከኢትዮጵያዊነትና ከብሔራዊ ጥቅም አንጻር በረከት ነው ወይስ መርገም ? በነገራችን ላይ ዩኒቨርስቲውን በሀገራችን ለምን እንደሚከፍቱት ታውቃላቹህ ? የካቶሊክ “ቤተክርስቲያን” ከመጀመሪያው ጀምሮ በሀገራችንና በሕዝቡ ላይ የነበራትንና ያላትን ጥቅምና ፍላጎት ታውቃላቹህ ? የካቶሊክ “ቤተክርስቲያን” አስቀድሞ በታሪካችን ያደረገችውን ታውቃላቹህ ? የካቶሊክ “ቤተክርስቲያን” አስቀድሞ ከረጅም ጊዜና ከአጭር ጊዜ ዐቅድ አንጻር ጥቅሟን የሚያሳካላት ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር ለሀገራችን ያደረገችው አንድም የመልካም ሥራ ዝጋብ (ሬከርድ) እንደሌለ ታውቃላቹህ ? የካቶሊክ “ቤተክርስቲያን” ፋሺስት ጣሊያን ሀገራችንን በወረረ ጊዜ እጇን በቀጥታ … [Read more...] about ዜጋዊ ጥያቄ
“ወደው አይስቁ”
የጥምቀት በዓልን ተሰባስበን በምናከብርበት አንድ ቤት ውስጥ ካለወትሮው ፓልቶክ ተከፍቷል። በዚያ የበዓል ድባብ፤ የፓልቶክ ንትርክ መከፈቱ ሳይገርመን፣ ርእሱ የሁላችንንም ቀልብ መሳቡ። በእርግጥ አንድም ቁም ነገር በንግግሩ አልሰማንም። አዲሱን ቋንቋ ልዋስና የፓልቶኩ ተናጋሪዎች ሙድ የሚያስይዙ ነበሩ። ሰዎቹ በዚህ ከቀጠሉ የእነ ክበበው ገዳን ገበያ መዝጋት እንደሚችሉ አያጠራጥርም። የድምጽ መነጋገርያውን የያዘው ሰው ጉሮሮውን ጠራርጎ ንግግሩን እንዲህ ሲል ጀመረ። "የምኒሊክ ወንጀል በጡት መቁረጥ ብቻ አያበቃም። ... የወንዶች ብልትም ተቆርጧል።..." በአኖሌ ሃውልት የምትገረሙ ነፍጠኞች ካላችሁ። በዚህ ብዙም አትደነቁ። ገና የወንድ ልጅ ሃፍረተ-ስጋ በሃውልት መልክ በአደባባይ ይቆምላችኋል። "የባሰ አታምጣ!" ነው ነገሩ። ሜንጫዎቹ ሰክረዋል። አእምሮዋቸውም ስቷል። የሚናገሩትን … [Read more...] about “ወደው አይስቁ”
ሶስት ነገር ያጣችው ሳልዋ – አሜሪካ
አሜሪካ የመጣችው ከ27 አመት በፊት ነበር። ሁለት ልጆች የወለደችለት ባለቤትዋ በሞት ሲለያት ታዳጊ ህጻናት ልጆቿን ይዛ በሱዳን በኩል አድርጋ አሜሪካ መጣች። ሳልዋ ትባላለች፤ የጠይም ቆንጆ ናት። በአሜሪካ ዲሲ ከተማ ብዙዎች የሚያውቋት በታታሪ ሰራተኛነቷ፣ በሳቅ ጨዋታዋ፣ እንዲሁም በመልካም ባህርይዋ ነው። ጥሩ ስራና ገቢ የነበራት ሳልዋ በፍቅር ከቀረበችው ሃበሻ ጋር በአብሮነት መኖር ይጀምራሉ። ለረጅም አመት ብዙዎችን የሚያስቀና ፍቅር እንደነበራቸው የሚያውቋቸው ይናገራሉ። በድንገት የሳልዋን ልብ የሚሰብር ሁኔታ ይፈጠራል፤ የምትወደውና ልጅ ያልወለደችለት ፍቅረኛዋ በድንገት በሞት ይለያታል። ሃዘኑን መቋቋም የተሳናት ሳልዋ ይባስ ብሎ ሁለቱ ልጆቿ ጥለዋት ወደ ሌላ ከተማ ሄዱ። ለ17አመታት ገደማ ጠይቀዋት አያውቁም፤ እሷም ልጆቿ የት እንዳሉ አታውቅም። ሶስት ነገር ያጣችው ሳልዋ ጤናዋ … [Read more...] about ሶስት ነገር ያጣችው ሳልዋ – አሜሪካ
ይመቻችሁ ጌቶቼ
ኩርዳዊ ነኝ ከኢራን - ኢማን አባስ እባላለሁ በቋንቋዬ እንዳልቀኝ - እንዳልከትብም ሁኛለሁ፤ የኔ ጌቶች ያሻቸውን - እሆን ዘንዳ ቢያስጨንቁኝ ግዳይ ጣልኩኝ እራሴን - ጭካኔያቸው ቢብሰኝ፤ ያውላችሁ ያሻችሁት - እንዳልሆን እሆን ፍርዳቸሁ አንደበቴን ተቆልፌ - ዐይኖቼን ተለጉሜ ይመቻችሁ እላለሁ - ጆሮቼን አስከርችሜ፤ ብእሬን ወርውሬ - ቀለሙን ደፍቼ ፍረዱኝ እላለሁ - እናንት ወገኖቼ፤ (ለምሥራቅ ኩርድ ባለቅኔው ለኢማን አባስ አመጽ መታሰቢያ) … [Read more...] about ይመቻችሁ ጌቶቼ
ከአምባገነንነት ባሻገር
ማሳሰቢያ፣ የዚህ ጽሁፍ መልዕክት ያለንበትን የተወሳሰበ የዓለም ሁኔታ ለማሳየት ብቻ ነው። የዚህ ጽሁፍ ሌላውና መሰረታዊው ዓላማ የተወሳሰበውን ዓለም ሁኔታ እስካልተረዳን ድረስ ወይም ለመረዳት የማንፈልግ እስከሆነ ድረስ ለነፃነት የሚደረገው ትግል የተሟላ ሊሆን አይችልም። ጽሁፉ ማንንም ለማወናበድ የቀረበ ወይም ደግሞ አንድን ርዕዮተ-ዓለም ለማስፋፋት የታቀደና ወይም በጥላቻ ላይ ተመርኩዞ የቀረበ ሆኖ መወሰድ የለበትም። በማስረጃ የተደገፈ ነው። ሁለተኛ፣ ይህ ዐይነቱ ጽሁፍ የፖለቲካ ሳይንስ ምሁሮችና የኢንቬስቲጋቲቭ ጋዜጠኞች ስራ ነው። ስለሆነም ወደ ፊት የፖለቲካ ሳይንስ ምሁሮች እንደዚህ ዐይነቱንም ሁኔታ እያተቱ ቢያቀርቡ ብዙ ሃሳቦችን ማንሸራሸር ይቻላል። ሶስተኛ፣ ይህ ዐይነቱ አቀራረብ በጣም አድካሚ ስለሆነ ተግባሩን ለፖለቲካ ሳይንስ ምሁሮች አስተላልፋለሁ። ብዙ ነገሮችን … [Read more...] about ከአምባገነንነት ባሻገር
የተመላሾች ጉዳይ …
በርካታ ከሳውዲ ወደ ሃገር ቤት የተመለሱ ዜጎችን በሚመለከት የጀርመንና የአሜሪካ ራዲዮን ጨምሮ በርካታ የመገናኛ ብዙሃን አንድ አይነት የሚመስል መረጃ ግፉአን ተመላሾችን እማኝ እያደረጉ መረጃ አቀብለውናል ። "ራፕለር " በታዝነው ሳምንት ባቀበለን መረጃ ሻንጣቸው ጠፍቷቸው በአንድ የሻንጣ ማጠራቀሚያ ግቢ ሻንጣቸውን ሲፈትሹ የሚያሳየውን ፎቶ አስደግፎ የተመላሾችን አስተያየት አካቶበታል። ዜጎች ወደ ሳውዲ ሲሰደዱ ከቤተሰብ ፣ ከዘመድ አዘመድ አዝማድና ከተለያዩ ቦታወች የወሰዱትን የብድር ገንዘብ ስላልመለሱ ኑሯቸው የሰመረ እንዳልሆነ እየተናገሩ ነው ። ሃገር ቤት ገብተው የስራ ማጣት እና እሳት የሆነው የኑሮ ውድነት ግራ ያጋባቸው በርካቶችም አሁንም መልሰው ለስደት እንደቋመጡ እኛ የምንቀርበው መረጃ ባይስማማ የፈረንጆቹ መገናኛ ብዙሃን የሚያቀርቡት የገሃዱን እውነት አንድምታ … [Read more...] about የተመላሾች ጉዳይ …
አሳዛኙ የትውልድ ህይወት በሳውዲ አረቢያ «ጂዛን» ከተማ!
ጂዛን እየተባለ በሚጠራ የሳውዲ አረቢያ ግዛት ውስጥ ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ የሌለውን ጨምሮ ከ50 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን እንደሚኖሩ ይነገራል። የጂዛን ከተማ ሳውዲ አረቢያን ከየመን የሚያዋስን ከተማ እንደመሆኗ በባህር የሚመጡ ብዛት ያላቸው ኢትዮጵያውያን ወደ ሪያድ እና ጅዳ ከተማ ለማቅናት በመሸጋገሪያነት እንደሚጠቀሙባት ይነገራል። በዚች የድንበር ከተማ አያሌ ኢትዮጵያውያን ጉዳዩ በወል በማይታወቅ ምክንያት ያለ ፍርድ ለ 4 እና 5 አመታት ታስረው የሚሰቃዩባት ከተማ መሆኗን የሚነገሩ ውስጥ አዋቂ ምንጮች ወደ ሃገር ለመመለስ ጥያቄ ያቀርቡ አያሌ ወገኖቻችንም በሪያድ የኢትዮጵያን ኤንባሲ እና ለጅዳ ቆንስላ ጽ/ቤት ያቀረቧቸው ጥያቄዎች እስካሁንም ምላሽ ባለማግኘቱ ህይወታቸው አደጋ ውስጥ መሆኑን ይናገራሉ ። ይህ በዚህ እንዳለ ከሁሉም በላይ እስከፊ አስከፊ በለው የሚገልጹት ምንጮች … [Read more...] about አሳዛኙ የትውልድ ህይወት በሳውዲ አረቢያ «ጂዛን» ከተማ!










