የመጨረሻውን በማያውቁት ያዘቀዘቀ ጨለማ መንገድ እየተውዘረዘጉ፤ መሪዉን በማስተካከል ከማያውቁት መጨረሻ ለመድረስ የሚጣድፉ መሪዎች፤ የድንቁርና ኒሻን ይገባቸዋል። በፈጠሩት የራሳቸው የመኖሪያ የገዢነት መኮፈሻ “ሀቅ” ተጀንነው በመቀመጥ፤ ፈንጠር ብሎ ርቆ ሌላውን ማየት ባለመቻላቸው፤ የተከተላቸውን ሳይውቁት እጃቸውን ሠጥተዋል። የተለዬ የመሰለ የራስ “ሀቅ” የብዥታ ጭጋግ፤ ሩቅ ማየትን ነፈጋቸው። ማስተዋልን ከአእምሮ መዝገባቸው ሰወረው። መደናበርን አነገሠባቸው። ካይናቸው ፊት በተገተረው የእብሪታቸው መነፅር፤ ዓለምን ግቢ ውጪ እያሉ በማስገደድ፤ ያለው የሌለ ሆኖ፣ ከተጨባጩ ይልቅ በምኞታቸው ዓለም ሲዳክሩ፤ የቆሙበት መሬት ከዳቸው። ከሕዝቡ መሆናቸው ቀርቶ ሕዝቡ የነሱ አገልጋይ ሎሌ ሆነና፤ የነሱ መኖሪያና የሕዝቡ መኖሪያ በአጥር ተለያዬ። መኖሪያቸው ዓለማቸው ሆነና ከሕዝቡ ዓለም ወጡ። ረጋ … [Read more...] about የገዢዎቻችን መጨረሻና የተከተላቸው ሀቅ
Left Column
የሻምበል ፍቅረሥላሴ ወግደረስ አሳሳች መረጃዎችና የተምታታ አስተያየት
በመሠረቱ ሻምበል ፍቅረሥላሴ ወግደረስ ስለ አብዮቱ “ እኛና አብዮቱ “ የሚል መጸሐፍ ጻፉ የሚል ዜና ስሰማ ፣ መጸሐፋቸው እንደ ሌ/ኮ መንግሥቱ ኃይለማርያም መጸሐፍ በቅጥፈት የተሞላ አይሆንም ብዬ ተስፋ አድርጌ ነበር ፡፡ ግን ሳይሆን ቀረ፡፡ በነገራችን ላይ የሻምበሉን መጸሐፍ ገና አላገኘሁትም፣ ነገር ግን አንድ ወዳጄ ከምዕራፍ 13–16 ያሉትን ገጾች ፎቶ ኮፒ አድርጎ ስለሠጠኝ አየተገረምኩኝ አነበብኳቸው፡፡ ሻምበሉን ምን ነካቸው ብዬም እራሴን ጠየኩኝ፡፡ ደራሲው በትምህርታቸው እንዳልገፉ ይገባኛል ፡፡ ሆኖም ግን በትምህርት ያለመግፋት ትንታኔ ላይ ችግር ይፈጥር እንደሆን እንጂ ፤ “ በእጅ የገባን መረጃ ” አሳስቶ ማቅረብ ከምን ሊመነጭ እንደሚችል ፈጽሞ ሊገባኝ አይችልም፡፡ ፍቅረሥላሴ መረጃው በእጃቸው ከሌላቸው አርፈው መቀመጥ አለባቸው እንጂ ባልሆነ ማስረጃ አንባቢን ማሳሳት … [Read more...] about የሻምበል ፍቅረሥላሴ ወግደረስ አሳሳች መረጃዎችና የተምታታ አስተያየት
በኢንቨስትመንት ስም አፍሪካ ውስጥ የሚደረገውን የመሬት ቅርምት አስመልክቶ
Coalition for Equitable Land Acquisitions and Development in Africa በምህጻረ ቃል CELADA በመባል የሚታወቀው በካናዳ ኦታዋ ውስጥ የተቋቋመ ድርጅት በአፍሪካ እየተኪያሄደ ያለውን የመሬት ቅርምት አስመልክቶ በርካታ የፓርላማ አባላት፣ የተራድኦ ድርጅት ሃላፊዎች የዩኒቨርሲቲ መምህራን በተገኙበት በአፍሪካ በኢንቨስትመንት ስም የሚደረገውን የመሬት ቅርምትና ካናዳ ልትይዘው የሚገባትን ፖሊሲ በተመለከተ በኦታዋ ፌብሩዋሪ 25 ቀን 2014 ዓም የተሳካ ስብሰባ አድርገዋል። በሚሊየን የሚቆጠሩ በእርሻ የሚተዳደሩ ማህበረሰቦችን አግባብ በሌለው ሁኔታ የማፈናቀሉ ሥራ እጅጉን ተጧጡፎ ያለው በተለይ በአፍሪካ በመሆኑ CELADA የተሰኘው ድርጅት ይህ ጉዳይ አለም አቀፍ ትኩረት ያገኝ ዘንድ የበኩሉን ለማድረግ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል። ይህ ድርጅት በተለያየ … [Read more...] about በኢንቨስትመንት ስም አፍሪካ ውስጥ የሚደረገውን የመሬት ቅርምት አስመልክቶ
አድዋ ለኔ
እኔ የምኖረው በአሜሪካ ነው። በአሜሪካ ሆኜ የአድዋን በዓል አከበርኩ። የኢትዮጵያዊያን ድረገፆችን እየተመላለስኩ ቃኘኋቸው። ሬዲዮኖችን አዳመጥኳቸው። የስልከ ልውውጦችንና የእንግዶችን ሃሳቦች ተከታተልኩ። ስደሰት፣ ሳዝን፣ በጣም ስደሰትና በጣም ሳዝን ዋልኩ። ሲመሽና የምኝታ ሰዓቴ ቀርቦ ባልጋዬ ላይ ስጋደም፤ እንቅልፍ ቶሎ አልወስድህ አለኝ። መገለባበጡ ለውጥ አላመጣ ሲል በሃሳብ መዋተቱን ተያያዝኩት። አድዋ ለኔ ምንድን ነው? የሚለው ጥያቄ ከዕለቱ ወደላይና ወደታች መዋዠቅ ጋር ተዛምዶ አፋጠጠኝ። እውነት አድዋ ለኔ ምንድን ነው? አድዋ ከመቶ ዓመት በፊት የተከሰተ ጉዳይ ነው። በዚያ ጊዜ የተካፈሉትና የነበሩት አሁን የሉም። አድዋ በአንድ የሀገራችን አካባቢ የተፈፀመ ጉዳይ ነው። ታዲያ ለኔ ከአንድ መቶ ዓመት በኋላ ላለሁት ምኔ ነው? በዚህ ጉዳይ ላይ ስመላለስበት እኩለ ሌሊት ሆነ። ለካስ … [Read more...] about አድዋ ለኔ
ሕወሃትና የኢትዮጵያዊነት ገጽታው
ባለፈው የካቲት 11 2006 የህወሃት ምስረታ በአል ሲከበር ጠ/ሚንስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ ያደረጉትን ንግግር ሲጀምሩ የትግራይ ሀዝብ ከአስከፊው ብሄራዊ ጭቆናና ፋሽስታዊ ስርአት ጋር ተናንቀው … ብለው ነበር እናም በርግጥ የህወሀት የትግል መስመር እና አለማ ምን ነበር? አሁን እንደሚባለው ኢትዮጵያን ከአስከፊው የደርግ ስርዐት ለመታደግ ወይስ በአንድ ወቅት መለስ ዜናዊ እነደተናገሩት “የድህነት ጠበቃ የነበረውን ደርግ” አሸንፎ ብልጽግና ለማምጣት? ሕወሐት የተመሰረተበትን አላማ የሚገልጽ የህወሀት ማኒፌስቶ (በ 1968 የታተመ መጸሔት) ለዚህ ጥሩ መልስ አለው ሰነዱ ላይ በግልጽ እንደተቀመጠው አጠቃላይ የህወሀት አላማ እና መድረሻ “የጨቋኟ አማራ ብኄርን” ጭቆና ለማስወገድ እና የትግራይ ሪፓብሊክ ማቋቋም ነው፡፡ ስለኢትዮጵያ እድገትም ሆነ የወደፊት አላማ ያስቀመጠው የልማት እቅድ … [Read more...] about ሕወሃትና የኢትዮጵያዊነት ገጽታው
የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና …
"የኢትዮጵያ ሃየር መንግድ ለአፍሪካ ኩራት ነው" ሲባል ከቃላት መፈክርነት ባለፈ የአውነትም ኩራት ስለመሆኑ ጥርጣሪ የሚያድርባቸው ዜጎች እንደሚኖሮ እገምታለው፡፡ ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ አየር መንግድ በረዥም ታሪኩ ውስጥ ከሌሎች የአፍሪካ አገሮች በአንፃራዊነት በተቋሙ ውስጥ ስማቸው እጅግ የገነነ ብቁ አብራሪዎች፣ የቴክኒክ ባለሙያዎች (ግራውንድ ቴክኒሻን) እና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች በአብዛኛው በኢትዮጵያዊያን የተሞላ ነው፡፡ ለዚህም ነው የአፍሪካ ኩራት ለመባል የበቃው፡፡ ይህ ኩራት እና አድናቆት ከታላቁ አፍሪካዊ የነፃነት ታጋይ ኔልሰን ማንዴላ ጀምሮ ጥቂት በማይባሉ አፍሪካዊያን ዘንድ ተቀባይነት ያገኘ ነው፡፡ በተጨማሪም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሎሜ፣ማላዊ እና ቶጎ በመሳሰሉ የአፍሪካ አገሮች ከፍተኛ አክሲዮን ሼር በመግዛት እያስተዳደረ እና እያንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡ እንዲሁም የተለያዩ … [Read more...] about የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና …
ለስምህ ስም ሁነው
ከሚለጥፍብህ ከአፉ እንደመጣ ሚሻለውን መርጠህ ለራስህ ስም አውጣ ሺ ጨዋ ብትሆን ሚልዮን ጥንቁቅ ሰው ሰው በሰውነትህ የሚልህ ስላለው በችሎታህ መጠን ኪሎህን መዝነህ ጭማሪ መጠሪያ ስም ስጠው ለራስህ ሚጠራህ ከጠፋ አንተ ባወጣኸው በተግባር ታይና ለስምህ ስም ሁነው። … [Read more...] about ለስምህ ስም ሁነው
ቦይንግ 767 – እገታ እና እንድምታው
አንድ የኢህአዴግ ካድሬ፣ ቤት ለመከራየት ወደ አንዲት ወይዘሮ መኖርያ ይሄዳል። ስፍራው እንደደረሰ ሌላ ተከራይም ከወይዘሮዋ ቤት ብቅ እንዳለ አስተዋለ። ሌላኛው ተከራይ ሰይጣን ነበር። ሁለቱ ተከራዮች ሰርቪስ ቤቱን ለመያዝ እንደ ጨረታ ብጤ ጀመሩ። ሰይጣኑ 400 ሲጠራ፣ ካድሬው ግን 500 ሊሰጥ ተስማማ። በመጨረሻ፣ ወይዘሮዋ ቤቱን ለሰይጣኑ በትንሽ ዋጋ ማከራየቱን መረጡ። የወይዘሮዋ ውሳኔ እንግዳ ነገር ነበር። ለሰይጣን፣ ለዚያውም በትንሽ ዋጋ ቤታቸውን ለመስጠት የወሰኑበትን ምክንያት ሲጠየቁ፤ "ሰይጣኑ አልወጣ እንኳን ቢል በጸበል ይለቃል። ካድሬው ገብቶ ቤቴን አልለቅም ቢለኝ ምን ላደርግ ነው?" ነበር ያሉት ወይዘሮዋ። ከፍ ባለ ገንዘብ ለኢህአዴጉ ሰርቪስ ቤታቸውን ቢያከራዩት ኖሮ ባጭር ጊዜ ዋናውን ቤታቸውን ለቀው የመውጣት ክፉ እድል ይገጥማቸው ነበር። ዶ/ር መረራ ጉዲና ባለፈው … [Read more...] about ቦይንግ 767 – እገታ እና እንድምታው
የሌላቸው ባለቤቶች (ከበድሉ ዋቅጅራ ሳላስፈቅድ የተዋስሁት)
በድሉ ዋቅጅራ ‹የሌላቸው ባለቤቶች› የሚል ቅራኔ ውስጥ የገባው ከተጨባጭ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሁኔታ ተነሥቶ ነው፤ አንዳንዴ ሁኔታዎች እያስገደዱን ቅራኔዎችን እንቀበላለን፤ አንድ ጌታ አሽከራቸውን ይጠሩና ባላገር ወደሚኖሩ እናታቸው ዘንድ ይልኩታል፤ ነገር ግን ‹ሞተው ከሆነ እንዳትነግረኝ› ብለው አስጠንቅቀውት ይሄዳል፤ ሴትዮዋ ሞተው ይደርሳል፤ ምን እንደሚያደርግ ግራ ገባው፤ ሲያንሰላስል ብዙ ቀናት ከቆየ በኋላ ጎፈሬውን ለሁለት ከፍሎ ግማሹን ይላጭና ግማሹን ብን አድርጎ ያበጥርና ጌታው ዘንድ ይቀርባል፤ አንዴ ጎፈሬውን እየነካካ፣ አንዴ የተላጨውን እየዳበሰ ጥያቄዎቻቸውን ሲመልስ፣ ጌታው ተቆጡና ‹ምንድን ነው የምታድበሰብሰው አርፈው እንደሁ በወጉ አትነግረኝም!› ብለው ሲጮሁበት ‹አዬ ጌታዬ አርስዎ መቼ በወጉ ላኩኝና!› ብሎ መለሰላቸው። የበድሉ ‹የሌላቸው› በግማሽ እንደተላጨው ጸጉር ነው፤ … [Read more...] about የሌላቸው ባለቤቶች (ከበድሉ ዋቅጅራ ሳላስፈቅድ የተዋስሁት)
ግብጽ ከሩሲያ ጋር የ2 ቢሊዮን ዶላር የጦር መሣሪያ ውል ተደራደረች
በመጪው ምርጫ የግብጽ ፕሬዚዳንት ይሆናሉ የሚባሉት የግብጽ ጦር ዋና አዛዥ ፊልድ ማርሻል አብደል ፋታህ አል-ሲሲ ከሩሲያ ጋር የ2ቢሊዮን ዶላር የጦር መሣሪያ ውል ድርድር ላይ መሆናቸው በዓለምአቀፍ ሚዲያዎች ተዘግቧል፡፡ ረቡዕ ሞስኮ የገቡት አል-ሲሲ ከሩሲያ አቻዎቻቸው ጋር የመሣሪ ውሉን በተመለከተ የሁለት ለሁለት ውይይት እያደረጉ ናቸው፡፡ ከግብጽና ከሩሲያ በኩል የውጭ ጉዳይ እና የመከላከያ ሚኒስትሮች የድርድር ውሉ ዋና አካላት ናቸው፡፡ “ጉብኝታችን በግብጽና ሩሲያ መካከል የወታደራዊና የቴክኖሎጂ ልማት ስምምነት በማድረግ አዲስ ምዕራፍ መክፈት ይሆናል” ያሉት አል-ሲሲ ትብብሩን ለማፋጠን ተስፋ እንዳለቸው ጠቁመዋል፡፡ ይጸድቃል የተባለው ይህ ስምምነት ከሩሲያ በኩል ድጋፍ እንዳለው ፕሬዚዳንት ፑቲን አል-ሲሲን ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት ጠቁመዋል፡፡ “የግብጽ ፕሬዚዳንት ለመሆን … [Read more...] about ግብጽ ከሩሲያ ጋር የ2 ቢሊዮን ዶላር የጦር መሣሪያ ውል ተደራደረች










