* ትናንት ረፋዱ ላይ በገደምዳሜ "ጉልቻ ቢቀያየር ..." ብለን ያንሹካሾክነው መረጃ ተረጋገጠ! * ለጊዜው ቆንስል ጀኔራሉን ተክተው በጊዜያዊነት ቆንስል መስሪያ ቤቱን ለቀጣይ ሁለት ወራት የሚያስተዳድሩት በቆራጥ አመራራር ብቃታቸው የማይመሰገኑት ቆንስል ሸሪፍ ከይሩ ናቸውም ተብሏል። * ቆንስል ጀኔራል አቶ ዘነበ ከበደ ትናንት ምሽት ጉዳዩን ለማሳወቅ የኢህአዴግ ድርጅት አባላት ስብሰባ ጠርተው እንደነበርና አብዛኛው አለመገኘታቸው ታውቋል። ድርጅት አባላት በተለይም ከጎናቸው የማይጠፉ የነበሩት ተጽዕኖ ፈጣሪ የህወሃት አባላት እንኳ አልተገኙም ተብሏል። አቶ ዘነበ ከበደ በቆንስሉ ዙሪያ የህወሃት አባላትን አምባገነንነትን በማውረድና በማቀዝቀዝ፣ በሙስና፣ በድለላ፣ በማጭበርበር ስራ በቆንስሉ ዙሪያ የነበሩትን በማጥፋት እና በሌብነት አካባቢውን በማጽዳት ይታወቃሉ። ህግ አዋቂ ሆነው … [Read more...] about የጅዳ ቆንስል ሃላፊ ዘነበ ከበደ ከኃላፊነታቸው ተነሱ!
Left Column
ልፋ ያለው በሕልሙ ዳውላ ይሸከማል! ጠርናፊና ተጠርናፊ
ሰሞኑን እንደአዲስ ሆኖ የሚወራው ስለጥርነፋ ነው፤ ጥርነፋ ከዲያብሎስ ፋብሪካ የወጣ የክፋትና የጭቆና መሣሪያ ነው፤ ሰዎችን በመጨቆንና በማሰቃየት፣ ምቾትና እንቅልፍ በማሳጣት፣ ፍርሃትንና ስጋትን በማሰራጨት ሕዝብን ለጥ-ጸጥ አድርጎ ለመግዛት የሚፈልጉ ጠርናፊዎች፣ አምባ-ገነኖች፣ ጨቋኞች፣ አፋኞች፣ ዘራፊዎች፣ ወሮበሎች፣ ምድራዊም ሆነ ሰማያዊ ሕግ የማይገዛቸው፣ አምላካቸው አድርገው የሚያገለግሏቸው ሎሌዎችን በሆዳቸው ገዝተው የሚያሰልፉ ናቸው፤ እንኳን የገጠር ልጆችና አኛም የአዲስ አበባዎቹ መሰንከል ምን እንደሆነ እናውቃለን፤ እንስሳትን (በቅሎዎችንና አህዮችን፣ አንዳንዴ በገግና ፍየልም) የፊት እግር ከኋላ እግር ጋር በአጭር ገመድ እያሰሩ እንደልባቸው እንዳይንቀሳቀሱ ማድረግ ነው፤ ሀብት በመሆናቸው ቢጠፉ ባለቤቶቹ ይጎዳሉ፤ ስለዚህ በየአካባቢያቸው ያለውን እየጋጡ ችለው እንዲኖሩ … [Read more...] about ልፋ ያለው በሕልሙ ዳውላ ይሸከማል! ጠርናፊና ተጠርናፊ
በጅዳ አለም የኢትዮጵያውያን አቀፍ ት/ቤት ከትምህርት ጥራት እስከ ባለሙያው ፈተና
ባሳለፍነው ሃሙስ የወላጅ መምህራን ስብሰባ ላይ ስለጅዳው አለም አቀፍ የኢትዮጵያውያን ትምህርት ቤት አስተዳደር ፍትሃዊነት የቅጥር ሂደት እና በትምህርት ጥራቱ ዙሪያ ላይ አንድ በኢኮኖሚክስ ትምህት በከፍተኛ ማዕረግ የተመረቀ ወጣት የሰላ ሂስ አቀረበ። በቀረበው የወጣቱ የዩኒቨርስቲ መምህር ስደተኛ ስራ ፈላጊ አስተያየት ድጋፍና ተቃውሞ ቤቱን በየተራ ናጠው። በትምህርት ጥራት አለመኖር የሚስማማው ወላጅ በጭብጨባ ድጋፉን ሲገልጽ የትምህርት ጥራቱን አንድ ከኢትዮጵያ ትምህርት ቤት የ12 ኛ ክፍል ተማሪ ጋር በእንግሊዝኛ ትምህርት እውቀታቸው የኤርትራ ኢምባሲ የ7ኛ ክፍል ተማሪ እንደሚልቅ በንጽጽር ማቅረቡ የተከፉ የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ፖርቲ አባላትና ደጋፊዎች ውግዘት አስከተለበት። አንዲት የወላጅ መምህራን ህብረቱ አባል ለትምህርት ጥራቱ ንጽጽር "ኤርትራ" የምትባለውን ሃገር ከአፉ … [Read more...] about በጅዳ አለም የኢትዮጵያውያን አቀፍ ት/ቤት ከትምህርት ጥራት እስከ ባለሙያው ፈተና
በሪያድ የኢትዮጵ ኮሚኒቲ ማህበር ስራ አመራር ማምሻውን ጠርቶት የነበረው ስብሰባ ሳይጀመር በሁከት ተበተነ !
በሳውዲ አረቢያ የሪያድ ኮሚኒቲ ማህበር ስራ እመራር ኮሚቴ በጠራው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በታደሙ አባላት እና የአምባሳደር ዶ/ር መሃመድ ሃሰን የቅርብ ዘመድ እንደሆኑ በሚታወቁት የቀድሞው የኮሚኒቲ ሊቀመንበር ሼክ ሙስጠፋ ሁሴን አሊዬ ደጋፊዎች መሃከል ተነስቶ የነበረው አለመግባባት ወደ ግጭት አምርቶ እንደነበር ምንጮች ከሪያድ ገልጸዋል። የስብሰባውን ታዳሚ ግራ ያጋባው ይህ ግጭት መነሻው የቀድሞው የማህበሩ ሊቀመንበር እንደነበሩ የሚነገርላቸው ሼክ ሙሰጠፋ ሁሴን ለምን ከስልጣኔ ተነሳሁ በሚል በምከትል ሊቀመንበሩ አቶ ቃሲም ላይ ቡጢ መሰንዘራቸውን ተከትሎ መሆኑንን የሚናገሩ ወገኖች ሼክ ሙስጠፋ ከስብሰባው በፊት ሲያስተባብሯቸው የነበሩ ከ 50 የሚበልጡ ደጋፊዎቻቸው ባስነሱት ሁከት የመስብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ከፍተኛ ውጥረት ነግሶ ማምሸቱን ጠቅሰዋል። ይህ ዜና እስከተጠናከረበት ግዜ … [Read more...] about በሪያድ የኢትዮጵ ኮሚኒቲ ማህበር ስራ አመራር ማምሻውን ጠርቶት የነበረው ስብሰባ ሳይጀመር በሁከት ተበተነ !
ግብፅ ሱዳንን ከኢትዮጵያ ለመነጠል ዲፕሎማሲያዊ ዘመቻ ጀመረች
የግብፅ መንግሥት በታላቁ የህዳሴ የኃይል ማመንጫ ግድብ በተመለከተ ሱዳን ለኢትዮጵያ የሰጠችውን ድጋፍ ለማጨናገፍ፣ ሱዳንን ከኢትዮጵያ ለመነጠል ዲፕሎማሲያዊ ዘመቻ መጀመርዋን ዘገባዎች አመለከቱ፡፡ የተለያዩ የግብፅ መገናኛ ብዙኃን ሰሞኑን እንደዘገቡት፣ የግብፅ መንግሥት የተለያዩ የመንግሥት አመራሮችና ፖለቲከኞች ከሱዳን መንግሥት አቻዎቻቸው ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ጀምረዋል፡፡ ለአብነት ከተጠቀሱት መካከል የግብፅ አል ዋፍድ ፓርቲ ሊቀመንበር ሳይድ አል ባዳዊ በካይሮ ከሱዳን አምባሳደር ከማል ሐሰን ዓሊ ጋር በሁለቱ አገሮች ድንበር የፀጥታ ጉዳዮች ላይ በዋነኝነት መክረዋል፡፡ በሁለቱ አገሮች ድንበር የጦር መሣሪያ ዝውውር ለማስቆም የተነጋገሩት ሁለቱ ባለሥልጣናት፣ ኢትዮጵያ እየገነባችው ባለው የታላቁ ህዳሴ የኃይል ማመንጫ ግድብና በሱዳን አቋም ላይ ተነጋግረዋል፡፡ ከውይይታቸው በኋላ … [Read more...] about ግብፅ ሱዳንን ከኢትዮጵያ ለመነጠል ዲፕሎማሲያዊ ዘመቻ ጀመረች
ምሁራኑ ሠልጣኝ፣ ሹመኞች አሰልጣኝ የሆኑበት ዩኒቨርሲቲ ሆኗል – ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ
መጽሔታችን የአገራችን የትምህርት ሁኔታበከፍተኛ ደረጃ ችግር ላይ የወደቀ መሆኑን በመገንዘብ፣ የችግሩን ጥልቀት ለማወቅና የመፍትሄ ሃሳቦችን ለማስቀመጥ በዘርፉ ጥናትና ምርምር ካደረጉ ምሁራን ጋር ተከታታይ ውይይቶችንስታደርግ ቆይታለች፡፡ በዚህ ዕትማችንም ውይይቱን በመቀጠል ከዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ ጋር ስለትምህርት ፍልስፍና፣ ስለዩኒቨርሲቲ ተልዕኮና ስለሌሎቸ ተያያዥ ጉዳዮች ቆይታ አድርገናል፡፡ ዶ/ር ዳኛቸው ለአብዛኛው የመገናኛ ብዙኃን ተከታታይ እንግዳ ስላልሆኑ ማስተዋወቅ ያለብን አይመስለንም፡፡ ውይይቱን እነሆ፡- ዕንቁ፡-ውይይታችን በዩኒቨርሲቲባህሪና ትርጉም እንጀምር፡፡ ለመሆኑ ዩኒቨርሲቲ ምን ማለት ነው? ዶ/ር ዳኛቸው፡-ከሁሉ አስቀድሞ ይኼ ጥያቄ ለአንዴና ለመጨረሻ መልስ የሚሰጠው ሳይሆን በተለያየ ጊዜና በተለያየ የባህልና የአመለካከት አውድ ውስጥ ተፈትሾ ለመግለጽ የሚሞከር ጉዳይ … [Read more...] about ምሁራኑ ሠልጣኝ፣ ሹመኞች አሰልጣኝ የሆኑበት ዩኒቨርሲቲ ሆኗል – ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ
ሌንጮ ለታ – ታሪክ ሊሰሩ ወይንስ ታሪክ ሊጽፉ…?
ኢትዮጵያዊው ቱጃር ለለውጥ ብለው በኮንትራት ታክሲ በመሄድ ላይ ናቸው። እሳቸውን የጫነው ታክሲ መስቀል አደባባይ ላይ ሲደርስ በድንገት ቀጥ ብሎ ቆመ። ሾፌሩ ተደናጋጠ። መኪናውን እንደገና ለማስንሳት ብዙ ሞከረ። ከብዙ ሙከራ በኋላ ጥረቱ ስላልተሳካለት ቱጃሩን ለትብብር ጠየቃቸው። እንዲህ ሲል። "ወጣ ብለው ይግፉ።" ቱጃሩ በመገረም ሾፌሩን አዩት። "ይግዙ" ማለትህ ነው ሲሉም መለሱለት። እኚህ ሰው መኪናውን ከመግፋት ይልቅ አዲስ መኪና መግዛት ይቀላቸዋል። የቤቶች ድራማ ላይ እከ ደከ አስር ጊዜ "እኔን ነው?" የሚለው ወዶ አይደለም። ማመን የሚቸግሩንን ነገሮች ማጣራት ስንፈልግ እንደጋግማለን። በዚያን ሰሞን በኦቦ ሌንጮ ለታ የወጣው ዜና ብዙዎችን አስገርሟል። "ሃገር ቤት ገብተን በመታገል አዲስ ታሪክ እንሰራለን።" የሚል ነበር የዜና እወጃው ርዕስ። ይህን ርዕስ እንዳየሁ አይኔን … [Read more...] about ሌንጮ ለታ – ታሪክ ሊሰሩ ወይንስ ታሪክ ሊጽፉ…?
ዳር ሆነው የሚመለከቱት የጎሳ ፖለቲካ ምሱ “ደም”!!
"ህወሃት" የሚባለው የትግራይ ነጻ አውጪ ትግራይን መቼና ከማን ነጻ እንደሚያወጣ በውል የተቆረጠ ቀን ባይኖርም ህገ መንግስታዊ ዋስትና ግን አለው በሚል እየተተቸ 23 ዓመታትን አስቆጥሯል። አገር እየመራም ነጻ አውጪ፣ በረሃም እያለ ነጻ አውጪ፣ በአህጉርና በዓለም አቀፍ ደረጃ ሲወከልም ነጻ አውጪ!! ይህንን የተለመደና ግራ የሚያጋባ እውነት ያነሳነው ወደን አይደለም። ይህ የህወሃት ግልጽ መለያና ከመለያው የሚነሳው ትንታኔ ለማንም የተወሳሰበ ይሆናል ብለንም አንገምትም። ኢህአዴግ የሚባለው የ"ሎሌዎች" ስብስብ ያበጀውና የሚመራው ህወሃት ከሌሎቹ በተለየ በነጻ አውጪ ስም 23 ዓመት አገር ሲገዛ ሌሎቹ "የነጻ አውጪ" ስም አለመያዛቸው ግን ሁሌም ሊመረመር የሚገባው ጉዳይ ይመስለናል። አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ "ነጻ" መውጣት ያለባቸው ህወሃቶች ሳይሆኑ ሌሎች የአገራችን ህዝቦች፣ የትግራይን … [Read more...] about ዳር ሆነው የሚመለከቱት የጎሳ ፖለቲካ ምሱ “ደም”!!
እስክንድር ነጋ የ2014 የነጻነት ወርቅ ብዕር ተሸላሚ ሆነ
የዓለም የጋዜጦችና ዜና አታሚዎች ማኅበር (WAN-IFRA) የ2014 የነጻነት ወርቅ ብዕር ሽልማቱን ለኢትዮጵያዊው ጋዜጠኛና አሳታሚ እስክንድር ነጋ እንዲሰጥ መወሰኑን ባወጣው መግለጫ አስታውቆዋል:: ህወሃት/ኢህአዴግ "የጸረ ሽብር ሕግ" በማለት ባወጣው አዋጅ ሰበብ እስክንድር ነጋ 18 ዓመት እንዲታሰር የተበየነበት መሆኑን መግለጫው ጨምሮ ገልጾዋል:: መግለጫው እስክንድርን ጨምሮ ሰሎሞን ከበደ፣ ውብሸት ታዬ፣ ርዕዮት ዓለሙ እና ዩሱፍ ጌታቸው ከእስር እንዲፈቱ አሳስቦዋል:: ኢትዮጵያን በቅርቡ የጎበኙት የማኅበሩ ፕሬዚዳንት በአገሪቱ የሚገኙ ጋዜጠኞችና አታሚዎች በፍርሃት የጋዜጠኝነታቸውን ሞያ እንደሚያከናውኑ መታዘባቸውን አስታውቆዋል:: ሽልማቱ በሰኔ ወር በቶሪኖ ጣሊያን በሚደረገው የዓለም የጋዜጦች ኮንግረስ፣ የዓለም አርታኢዎች መድረክ እና የዓለም ማስታወቂያ ሥራ መድረክ ጣምራ … [Read more...] about እስክንድር ነጋ የ2014 የነጻነት ወርቅ ብዕር ተሸላሚ ሆነ
መቼ ነው?
መቼ ነው ይሄ ቀን - ከኛ ቤት ’ሚያልፈው ለመኖር መደፋት - ተረት የሚሆነው? መቼ ነው ወገኔ - መኖር የሚችለው እንደሰው ለመኖር - ሰውን እሚመስለው? መቼ ነው ረሃቡ - ተረታሁ የሚለው እሳቱ እሳት ሁኖ - ኑሮን ’ሚያበስለው? መቼ ነው ይሄ ቀን - ተረት እሚሆነው መኖር አለመኖር - መሆኑ እሚያከትመው? … [Read more...] about መቼ ነው?










