… ቋንጣ ዜና አመጣሽ አትበሉኝና፤ ሰሞኑን ከፌስቡክ ጠፍቼ በከረምኩበት ወቅት የአራት አመት ከስድስት ወር ልጅ የደፈረው ዋልጌ በአራት ወር "ሲቀጣ"፣ ምስር ወጥ የሰረቀው ሰው ደግሞ አመት ከአራት ወር እስር ተፈርዶበታል ሲባል ሰምቼ በንዴት ስንተከተክ ከርምኩ፡፡ ከዚያ ደግሞ እነ አብርሃ ደስታ ሲፈቱ በደስታ ተፍነከነኩ፡፡ …ልጅ ሆኜ እናቴ ሰው ቤት ይዛኝ ሄዳ ለየኔ ቢጤ ምግብ ለመስጠት የሚሰስት ሰው ስታይ፤ "አበስኩ ገበርኩ…!ደግሞ ለሞተ…ለበሰለ ምግብ መስቆንቆን ምንድነው!" ትል ነበር፡፡ እነሆ ፍትሃችን፣ "የበሰለ" እና "የሞተ" ምግብ ለሰረቀው ሰውዬ ፣ አመት ከአራት ወር! "ያልበሰለች" እና "ታዳጊ" ልጅ ለደፈረው ሰውዬ፣ አራት ወር ሆኗል፡፡ እነሆ ፍትሃችን፣ እንዲህ እንዲህ የሌሎችን መብት ግጥም አደርጎ የሚጥስን ማበረታቻ በሚመስል የአራት ወር "ቅጣት" … [Read more...] about እነሆ ፍትሃችን
Left Column
በአፋር በየቀኑ እስከ 100 የሚደርሱ ከብቶች ይሞታሉ
* እንደተለመደው ኢህአዴግ የድርቅ አደጋና የምግብ እጥረት ስጋት የለም እያለ ነው ባለፉት ሁለት ወራት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የተከሰተው የዝናብ እጥረት የድርቅ አደጋ እንዳይከሰት ስጋት የፈጠረ ሲሆን ግብርና ሚኒስቴር በበኩሉ፤ የዝናብ እጥረት ቢኖርም የድርቅ አደጋና የምግብ እጥረት ስጋት የለም ብሏል፡፡ በአፋር ክልል ግን ሁኔታው ተባብሷል፡፡ በየቀኑ እስከ 100 የሚደርሱ ከብቶች በመኖና በውሃ እጥረት እየሞቱ መሆኑን ምንጮቻችን ጠቁመዋል፡፡ የአፋር ክልልን አቋርጠው ወደ ጅቡቲ ወደብ ከሚጓዙ ሹፌሮች አንዱ ለአዲስ አድማስ እንደገለፀው፤ በመንገድ ዳርና ዳር በርካታ በጎችና ፍየሎች ሞተው ይታያሉ፡፡ በክልሉ ካለፈው ዓመት ሰኔ ወር ጀምሮ እስካሁን ድረስ ዝናብ የጣለባቸው ቀናት በጣት የሚቆጠሩ መሆናቸውን የጠቆሙት ምንጮች፤ የድርቁ ሁኔታ እየተባባሰ ቢሆንም በመንግስት … [Read more...] about በአፋር በየቀኑ እስከ 100 የሚደርሱ ከብቶች ይሞታሉ
ለአሚራና ቤተሰቦቿ የጎደለው ፍትህ…!
* የ4 ዓመት ከ6 ወር ህጻን የደፋረን በ4 ወር እስር መቅጣት ምን ይሉታል? * ወላጆቿ "ወላጅ ይፍረደን፣ ህዝብና ሀገር ይፍረደን!"ይላሉ የኢፌዴሪ ህገ መንግሥት ሴቶች ልክ እንደ ወንዶች በሕገ-መንግሥቱ እኩል መብትና ጥበቃ እንዲሰጣቸው ይደነግጋል። ትግበራውን መከታተልና ማስፈጸም ያለባቸው ህግ እውጭና አስፈጻሚ አካላት የሴቶችን መደፈር ለመከላከል የከበደ ኃላፊነት እንዳለባቸው ይህው የፈረደበት ህገ መንግስት ያስረዳል! ዳሩ ግና አልፎ አልፎ የሚሰማ የሚታየው የነገር ጭብጥ ውጤት ህግ አውጭና የሚያወጡት ህግ ደንብና መመሪያ ከወንጀል ፈጻሚው ባልተናነሰ በህግ አስከባሪና አስፈጻሚዎች ህጉ ይጣሳል። ህግ ተጥሶ የዜጎች ሰብአዊ መብት መዳጡ በአደባባይ እየተሰማና እየታየ ህግ አውጭ አካላት የሚወስዱት እርምት እርምጃ አያስደስትም። የሴት ጠለፋ በተለይም በህጻናትና ታዳጊዎች ላይ የሚፈጸም … [Read more...] about ለአሚራና ቤተሰቦቿ የጎደለው ፍትህ…!
በሪያድ ከተማ በሙስሊም ኢትዮጵያውያን የፀረ ህወሃት/ኢህአዴግ ተቃውሞ ተደረገ
ሰሞኑን ህወሃት/ኢህአዴግ በሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ላይ የወሰደውን ኢፍተሃዊ ውሳኔ በመቃወም ሪያድ ከተማ ውስጥ አርብ ኦገስት 7 2015 ምሸት ኢትዮጵያዊው ህዝበ ሙስሊም አንድነቱን ጠብቆ ተቃውሞውን አሰምቷል። ቁጥሩ ከፍተኛ እንደሆነ ህዝብ የተገኘበት ይህ ታላቅ ተቃውሞ የአካባቢውን ድባብ ለውጦት እንደ ነበር ለማወቅ ተችሏል። የተከሰተው ነገር በራሳችን እንደደረሰ ተሰምቶን በሶስት ቀን ውስጥ በተጠራ የተቃውሞ ጥሪ ይህን ያህል ህዝብ አንድነቱን ጥብቆ ለተቃውሞ በነቂስ መውጣቱ የትግሉ አንድነት ጥንካሬ መገለጫ መሆኑን የገለጹት ሼክ ሲዒድ አህመድ ህዝበ ሙስሊሙ በአገዛዙ ከባድ ፈተና እንደ ተጋረጠበት አውስተዋል፡፡ ሲቀጥሉም ይህ ፈተና አዲስ ሆኖብን ሳንደናገጥ ትግሉን በበሰለና በሰለጠነ መንገድ በማጠናከር እስከ ድል መቀጠል እንደሚገባ በቁጣ የወጣውን ህዝብ ሙስሊም … [Read more...] about በሪያድ ከተማ በሙስሊም ኢትዮጵያውያን የፀረ ህወሃት/ኢህአዴግ ተቃውሞ ተደረገ
የሰላም ትግሉ ያቸንፋል
የሰላማዊ ትግል ተግባራዊነትና ስኬት መለኪያው ምንድን ነው? በዚህ ልጀምር ጽሑፌን። በርግጥ መጀመር ያለበት፤ ሰላማዊ ትግል ምንድን ነው? የት ተተገበረ? እንዴት ተተገበረ? ከትጥቅ አመጹ በምን ተሽሎ ይገኛል? እዚህ ሰላማዊ ትግል፤ እዚያ ግን የትጥቅ ትግል የሚባለው እንዴት ነው? በሚሉት ነበር። ነገር ግን፤ አንባቢዬ በትክክል እንደሚረዱት፤ አሁን የያዝነው፤ በተጨባጩ በሀገራችን ባለው የፖለቲካ ሀቅ፤ ምን ላይ ነው ያለነው? ምን ማድረጉ ለትክክለኛው ሕዝባዊ ድል አመርቂ ውጤት ያስገኝልናል? ከሚለው በመነሳት ነው። እንግዲህ መሠረታዊው መነሻ፤ አሁን ያለንበት የሀገራችን የፖለቲካ ሀቅ ነው፤ ማለት ነው። እዚህ ላይ ነው እኔ፤ ሽንጤን ገትሬ፤ “ሰላማዊ ትግሉ ያቸንፋል!” በማለት የቆምኩት። እናም ላስረዳ! ገዥው ወገንተኛ አምባገነን የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት፣ ከሕዝቡ ተነጥሎ … [Read more...] about የሰላም ትግሉ ያቸንፋል
ከሳሽ ሲከሰስ
(ኢትዮጵያ ውስጥ ፍትሕ ቢኖር እኛ ኢትዮጵያን ሙስሊሞች እንዲህ ብለን እንከስ ነበር!) የፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001 የተመለከተውን በመተላለፍ የተከፈተ ክስ የቀ/ቁ/001/2006 የወ/መ/ቁ. 01/0001/06 ለኢትዮጵያ ህዝብ በሙሉ በመላው ዓለም ከሳሽ ….. ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች (የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ) ተከሳሾች… 1/ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ መንግስት የሽብር ቡድኑ አጠቃላይ አስፈጻሚ 2/ የህውኃት/ኢህአዴግ ማዕከላዊ ኮሚቴ የሽብር ቡድኑ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ 3/ የቀድሞው ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ (በሌሉበት) የሽብር ቡድኑ የቀድሞ አመራር 4/ ጠ/ሚኒስትር ኃ/ማርያም ደሳለኝ የሽብር ቡድኑ አመራር 5/ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የሽብር ቡድኑ ወታደራዊ ክንፍ 6/ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት ቢሮ የሽብር ቡድኑ መረጃ ክፍል 7/ … [Read more...] about ከሳሽ ሲከሰስ
አዱሊስ/Adulis
ባለ 21 ገጽ የአዱሊስን ልዩ ዕትም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ:: … [Read more...] about አዱሊስ/Adulis
የፌዝ ችሎት
በኢትዮጵያ የሙስሊሙ ማህበረሰብ ችግሮች መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት የታሰሩበትን ፖለቲካዊ ጉዳይ ህጋዊ ለማስመሰል የተሰየመው የፊዝ ችሎት ለአመታት የከረመበትን ተውኔት ከ 7 አመት እስከ 22 አመት እስር በመፍረድ አጠናቋል፡፡ የፍርዱን ዜና ተከትሎ የሚሰማው የሚነበበው ስሜት ከዚህ በተቃራኒ ፍትሀዊ የሆነ ፍርድ የጠበቁ ሰዎች እንደነበሩ የሚያመለክት ነው፡፡ ከወያኔ የፌዝ ችሎት ይህን ማሰብ ወያኔን አለማወቅ ወይንም ትናንትን መርሳት ይመስለኛል፡፡ ይህ ደግሞ ትግሉ በሚጠይቀው ጽናትና ቁርጠኝት እንዳይካሄድ የሚያደርግ ነው፡፡ ወያኔ በፍትህ ሲያላግጥ በህግ ሽፋን ወንጀል ሲፈጽም እውነትን በጠመንጃው ሲረግጥ ወዘተ ይህ የመጀመሪያው አይደለም፡፡ በሀሰት ወንጅሎ፣ በትእዛዝ የሚፈርዱ ዳኞች ሰይሞ፣ የፌዝ ችሎት አቋቁሞ፣ ኣቃቤ ህግ ሳይሆን አቃቤ ወያኔ አቁሞ ፣ በፍትህ ላይ ትያትር ሲሰራ እኛ … [Read more...] about የፌዝ ችሎት
ለህወሃት/ኢህአዴግና መሰል የአፍሪካ አምባገነኖች የባራክ ኦባማ መልዕክት
በቅድሚያ ለህወሃት/ኢህአዴግ “የአንድን አገር (ኅልውና በማስጠበቅ) አንድ አድርጎ ማቆየት የሚችለው መሪው (ወይም በኢህአዴግኛ ፓርቲው ወይም ግምባሩ) እርሱ ብቻ እንደሆነ የሚናገር ከሆነ ያ መሪ (ፓርቲ ወይም ግምባር) አገሩን ከመገንባት ከሽፏል ማለት ነው … ማንም ሰው (ፓርቲ/ግምባር) ዕድሜልኩን መሪ/ፕሬዚዳንት መሆን የለበትም፤ አዲስ ሃሳብና ትኩስ ኃይል ወደ ሥልጣን ሲመጣ ያቺ አገር ከቀድሞው እየተሻለች ትሄዳለች፡፡” ቀጠሉ - “ሰዎች ለረጅም ጊዜ በሥልጣን ለምን መቆየት እንደሚፈልጉ እኔ አይገባኝም፤ በተለይ ብዙ ገንዘብ እያላቸው …” ልማታዊ አምባገነኖቹን የሚመለከት ነበር፡፡ ለሕገመንግሥት ቀያሪዎችና ሕግ አሻሻዮች “አንድ መሪ በሥልጣን ለመቆየት በጨዋታው መሃል ሕግ ለመቀየር ሲሞክር (በዚያች አገር) ያለመረጋጋትና የነውጥ አደጋ ያስከትላል፡፡” ራሳቸውን ከአፍሪካ “ዘላለማዊና … [Read more...] about ለህወሃት/ኢህአዴግና መሰል የአፍሪካ አምባገነኖች የባራክ ኦባማ መልዕክት
Democracy at Work: Making it Happen in Diaspora
There needs to be a paradigm shift as to how to go about forming a more united front. The usual practice is for one or couple of organizations making the call for unity in one form or shape. We have seen several meetings like this that couldn’t bring all to the table. How can the diaspora model a life of democracy by coming together to create an environment for a dialogue that brings consensus towards One Voice for Ethiopia? We do that by choosing a path we didn’t choose before. The Road Less … [Read more...] about Democracy at Work: Making it Happen in Diaspora









