ፕሬዚዳንት ኦባማ የአፍሪካ ጉብኝታቸውን ከመጀመራቸው በፊት የብሔራዊ ጸጥታ አማካሪ የሆኑት ሱዛን ራይስ ወደ ኬኒያ እና ኢትዮጵያ ስለሚደረገው ጉብኝት መግለጫና ከጋዜጠኞች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሸ ሰጥተው ነበር፡፡ የጉብኝት ዝርዝር መርሃ ግብር በማስረዳት ንግግር የጀመሩት ራይስ ፕሬዚዳንቱ በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከኢህአዴ ሹማምንትና ከአፍሪካ ኅብረት ኃላፊዎች እንዲሁም ከአህጉሪቱ መሪዎች ጋር እንደሚነጋገሩ አስረድተዋል፡፡ ከጠያቂ ጋዜጠኞች መካከል ተራው የደረሰው አይዛክ አምባሳደር ራይስን ስለ ጉዞው የጸጽታና ደኅንነት ጉዳይ ከጠየቀ በኋላ ከዚህ በፊት ሌላኛዋ ጋዜጠኛ (ክሪስቲ) ያነሳችውን ሃሳብ በማጠናከር “ፕሬዚዳንት (ኦባማ) የኢትዮጵያና የኬኒያ መሪዎች በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጡ አድርገው ይቆጥሯቸዋል?” በማለት ጠየቀ፡፡ ሱዛን ራይስ ማስረዳት ጀመሩ የጸጥታውና የደኅንነቱ … [Read more...] about የሱዛን ሳቅ
Left Column
ዝዋይ እስር ቤት
ሐምሌ 16/2007 ዓ.ም. ለአሥር ወራት በእስር ላይ የቆየውን ጋዜጠኛ፣ ተመስገን ደሳለኝን (ከኃይለ ማርያም ደሳለኝ ጋር ዝምድና የለውም፤) ለመጠየቅ ወደዝዋይ ወህኔ ቤት ሄጄ ነበር፤ የወሕኒ ቤቱ ባለቤቶች ማረሚያ ቤት ይሉታል፤ ማረሚያ ቤት ማለት ሀሳቡን በነጻነት የሚገልጽና በሀሳቡም ከወያኔ ጋር በሎሌነት ለመተዳደር የማያመች ሲሆን የቀናውን በጉልበት የሚያጎብጡበት ማለታቸው ነው፤ ማረም ማለት ቀጥታውን ማጉበጥ ነው፤ እንዴት እንደሚያጎብጡት ላሳያችሁ፤-- 1. የኛን እንተወውና በተባበሩት መንግሥታት ውሳኔ እስረኞች ሰዎች በመሆናቸው ሰብአዊ ደኅንነታቸውና ክብራቸው ሁልጊዜም እንዲጠበቅላቸው ያስፈልጋል፡፡ 2. የኛን እንተወውና በተባበሩት መንግሥታት ውሳኔ እስረኞች ሁሉ ከመሰቃየትና ከመጉላላት በጸዳ አያያዝ እንዲጠበቁ ይደነግጋል፤ 3. የኛን እንተወውና በተባበሩት መንግሥታት ውሳኔ … [Read more...] about ዝዋይ እስር ቤት
ኳስ አፍቃሪ ሆንኩኝ
ለረጅም አመታት፣ ለብዙ ዘመናት፣ ፓርቲ ሲጠልዘኝ፣ መንግስት ሲረግጠኝ፣ ፖሊስ ሲነርተኝ፣ ሕጉ ሳይደግፈኝ፣ ዳኛው ቢፈርድብኝ፣ በቡድን ተካፍለው፣ በስም ተሸንሽነው፣ የሚጠልዟት ኳስ፣ የሚነርቷት ኳስ፣ ምትለጋዋ ኳስ፣ እኔ ራሴን መስላኝ፣ ኳስ አፍቃሪ ሆንኩኝ። … [Read more...] about ኳስ አፍቃሪ ሆንኩኝ
“ሙቅ በገንፎ ሲደገፍ”
በአገሪቱ የኤሌክትሪክ ኃይል መሥሪያ ቤት ላይ ኅብረተሰቡ የሚያሰማው እሮሮ ኤሌክትሪኩ መጥፋቱ ብቻ አይደለም፡፡ መብራቱ ሄዶ ሲመጣ የሚያደርሰው ጥፋት የትየለሌ ነው፡፡ የኤሌክትሪኩ ኃይል መጠን ከመደበኛው ውጭ ከፍና ዝቅ ሲል የሚያደርሰው ጥፋት ቤት ይቁጠረው፡፡ ማቀዝቀዣው፣ ቴሌቪዥኑ፣ አምፖሉ፣ ልዩ ልዩ "ቻርጀሮች" የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ ውጤቶች ተቃጠሉብን የሚል የሕዝብ እሮሮ በየጊዜው ይሰማል፡፡ የሚመለከተው መሥሪያ ቤት ፈጣን ምላሽ ከመስጠት ይልቅ አገልግሎት የማይሰጠውን "905" ላይ ደውላችሁ አስመዝግቡ ከማለት ያለፈ መልስ የለውም፡፡ "የኤሌክትሪክ ምሰሶው ሊወድቅብን ነው፣ ዘሟል፣ ኧረ ድረሱልን" እያሉ ለሚወተውቱም ፈጣን ምላሽ መስጠት እንዳልተቻለም ማስረጃ ከሚሆኑ ትዕይንቶች (በፎቶዎቹ የሚታዩት) መካከል በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 እንደራሴ አካባቢ ያሉ የኤሌክትሪክ ምሰሶዎች … [Read more...] about “ሙቅ በገንፎ ሲደገፍ”
ቴዲ በድጋሚ ፓስፖርቱን ተቀምቶ ነበር
ባለፈው ሳምንት ወደ ከአዲስ አበባ ናይሮቢ-ኬንያ ይጓዝ የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራውን ከጀመረ በኋላ እንዲመለስ መደረጉን የአየር መንገዱ ምንጮች አስታወቁ። በዚህም ምክንያት አየር መንገዱ የሁለት መቶ ሺህ ዶላር ኪሳራ እንደደረሰበት ምንጮቹ ጠቁመዋል። በተሳፋሪዎች ላይም ከፍተኛ መጉላላት ደርስዋል። አውሮፕላኑ ካኮበኮበ በኋላ እንዲመለስ የተደረገበት ምክንያት ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ ከባለቤቱ ከአለምሰት ሙጬ ጋር በአውሮፕላኑ በመሳፈሩ ምክንያት መሆኑ ተረጋግጧል። ይህ አስደንጋጭ ክስተት የተፈጸመው አለምሰት ሙጬ በደረሰባት ድንገተኛ ህመም ለህክምና ወደ ኬንያ እየተጓዘች ባለችበት አውሮፕላን ነው። አውሮፕላኑ ዞሮ ከተመለሰ በኋላም ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ በደህንነቶች ተይዞ ከአውሮፕላኑ እንዲወጣ ተደርጓል። የህወሃት የደህንነት አባላት የቴዲ አፍሮን ፓስፖርት ቀምተው አሰናብተውት … [Read more...] about ቴዲ በድጋሚ ፓስፖርቱን ተቀምቶ ነበር
ኢህአዴግ በኢንተርኔት ስለላ ተከሰሰ
የኢትዮጵያ መንግሥት ኮምፕዩተሬ ላይ “የስለላ ማልዌር ልኮብኝ ሲሰልለኝ ቆይቷል” ሲሉ ኪዳኔ ተብለው የተጠሩ አሜሪካዊ ዋሺንግተን ዲሲ በሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ ወረዳ ፍርድ ቤት ክሥ መሥርተው ጉዳዩ ትናንት ዳኛ ፊት ቀርቧል፡፡ የከሣሽና የተከሣሽ ጠበቆች ረዥም ክርክር አድርገዋል፡፡ የግለሰቦችን የግል ሕይወት ወይም ገመና መዳፈር፣ የስልክ ንግግሮቻቸውን ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ መጥለፍ፣ ኢሜሎቻቸውን ማንበብ ከአግባብ ውጭ፤ እንዲያውም ሕገወጥ የሆነ አድራጎት ነው ተብሎ ይበየንልን ሲሉ የኪዳኔ ጠበቃ ኔት ካርዶዞ ጠይቀዋል፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት ጠበቃ አድራጎቱን ፈፅሟል የተባለው የውጭ ሉዓላዊ መንግሥት በመሆኑ የዩናይትድ ስቴትስ ፍርድ ቤት ክሡን የማየት ሥልጣን የለውም ስለዚህም ችሎቱ ውድቅ ሊያደርገው ይገባል ብለዋል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ሃኪንግቲም የሚባለው ጣልያን የሚገኝ የስለላ … [Read more...] about ኢህአዴግ በኢንተርኔት ስለላ ተከሰሰ
“የክስ መቋረጥ” ወይስ የኦባማ ጉብኝት?
"ክሴን አቋርጫለሁ" ከማለት ባለፈ ምክንያቱን ከመናገር ተቆጥቧል ከአንድ ዓመት በፊት ሚያዝያ 26 እና 27 ቀን 2006 ዓ.ም. በድንገት ተይዘው ከታሰሩ በኋላ፣ በፌዴራል ዓቃቤ ሕግ ክስ ተመሥርቶባቸውና የሰነድና የሰው ማስረጃ ቀርቦባቸው፣ ለብይን የተቀጠሩበትን ቀን እየተጠባበቁ ከነበሩት አሥር ተከሳሾች መካከል አምስቱ በድንገት ሐምሌ 1 እና 2 ቀን 2007 ዓ.ም. መፈታታቸው እያነገጋገረ ነው፡፡ ለተከሳሾቹም ሆነ ወክለዋቸው ለሚከራከሩላቸው ጠበቆቻቸው ምንም ዓይነት መረጃ ሳይደርሳቸው በድንገት፣ ‹‹ዓቃቤ ሕግ ክሱን አቋርጣል፡፡ በመሆኑም ከዛሬ ጀምሮ ከእስር ተለቃችኋል፤›› የተባሉት ተከሳሾች ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ፣ አስማማው ኃይለ ጊዮርጊስ፣ ኤዶም ካሳዬና ጦማሪያን ዘለዓለም ክብረትና ማህሌት ፋንታሁን ናቸው፡፡ ክሱ እንደተቋረጠ በማረሚያ ቤት ኃላፊዎች ከማወቃቸው … [Read more...] about “የክስ መቋረጥ” ወይስ የኦባማ ጉብኝት?
የኢህአዴግ ዉሸት – እስካሁን ደህና ነኝ ማለት
እሙሩ ብሪታንያዊ የምርመራ ጋዜጠኛ ኒኮላስ (ኒክ) ዴቪስ የብዕሩ ሞገስ ይደርጅለትና ዕውነት እንዳንናገር፣ ሀቅ እንዳንዘረዝር የሚያደርጉን ሠለስቱ ቀታሊያን ሥህተቶች፣ ሦስቱ ገዳይ ድክመቶች:- "1) የምንመርጣቸው ርዕሰ ጉዳዮች ዕውነታውን በመሠረታዊ መንገድ የሚያፋልሱት እንዲሆኑ በማድረግ ዋናውን ጭብጥ ማሳት፣ "2) በተደጋጋሚ የምንጠቀምባቸውን ኢተአማኒ፣ አንዳንዴም ፈጽሞ ውሸት፣ የሆኑ ጭብጦች ደጋግመን በመጠቀም ዕውነተኛ ማስረጃዎች እንዲመስሉ ማድረግ፣ "3) ከአካባቢው ህብረተሰብ መካከል ኃይለኛ ጉልበት ያላቸውን ወገኖች የሚያደምቁ ዕሴቶችን የማያቋርጥ አሻራ እንዲኖራቸው ፖለቲካዊና ሞራላዊ ውትወታን ማብዛት፣ ናቸው" ሲል የጣፈው ቀልብ የሚማርክና ለአብነት የሚጠቀስ መንደርደሪያ ሆኖ አግኝቼዋለሁ። ማለፊያ አስተዉሎት ነው መቼም። ታድያ ይህን የኒኮላስ ዴቪስን ሓቲት ባስታወስኩ … [Read more...] about የኢህአዴግ ዉሸት – እስካሁን ደህና ነኝ ማለት
ያልተፈቱት “አሸባሪዎች”
1 - ተመስገን ደሳለኝ 2- እስክንድር ነጋ 3- ናትናኤል መኮንን 4- አንዳለም አራጌ 5- ውብሽት ታዬ 6- አበበ ቀስቶ 7- ሃብታሙ አያሌው 8- ድልንኤል ሺበሺ 9- አብርሃ ደስታ 10- የሽዋስ አሰፋ 11- ዘላለም ወርቅአገኘሁ 12- አቤል ዋበላ 13- ናትናኤል ፈለቀ 14- በፍቃዱ ሃይሉ 15- አጥናፍ ብርሃኔ 16- ፍቅረማርያም አስማማው 17- እየሩሳሌም ተስፋው 18- ብርሃኑ ተክለያሬድ 19- ኦልባና ለሌሳ 20- ቴድሮስ አስፋው 21- ማትያስ መኩርያ 22- ብሌን መስፍን 23- ተዋቸው ደምሴ 24- ንግስት ወንዳፈራሁ 25- ሜሮን አለማየሁ 26- ደሴ ካህሳይ 27- ናትናኤል ያለምዘውድ 28- ሰንታየሁ ቸኮል 29- ማስተዋል ፈለቀ 30- ንግስት ወንድይፍራው 31- ሂሩት ክፍሌ 32- እማዋይሽ አለሙ 33- ሰለሞን ከበደ 34- የሱፍ … [Read more...] about ያልተፈቱት “አሸባሪዎች”
በኤርትራ ላይ ምርመራው እንዲቀጥል ተወሰነ
በኤርትራ ላይ የሚካሄደው የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ምርመራ የሚጠረጠረውን በሰብዕና የሚፈፀም ወንጀል እንዲያካትት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ትናንት ወስኗል፡፡ ኤርትራ ውስጥ ያለውን የሰብዓዊ መብቶች አያያዝ እንዲመረምር የተቋቋመው ልዩ አጣሪ ኮሚሽን ሥራውን በአንድ ዓመት እንዲያራዝም የተስማማው አርባ ሰባት አባላት ያሉት የመንግሥታቱ ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች አያያዝ ክትትል አካል ነው፡፡ ምርመራው ሙሉ ተጠያቂነት ባለበት ሁኔታ እንዲካሄድ የምክር ቤቱ ውሣኔ አክሎ አሳስቧል፡፡ ኤርትራ ውስጥ ይፈፀማል የተባለውን ጅምላ የሰብዓዊ መብቶች ረገጣ የምክር ቤቱ የውሣኔ ሃሣብ ረቂቅ በአጀንዳነት እንዲያዝ ጥያቄ ያቀረቡት ጅቡቲና ሶማሊያ እንደሚያወግዙ አስታውቀዋል፡፡ የአውሮፓ ኅብረት የምርመራውን ጊዜ መራዘም “ኤርትራ ውስጥ እየተፈፀሙ ያሉ” ያላቸው የሰብዓዊ … [Read more...] about በኤርትራ ላይ ምርመራው እንዲቀጥል ተወሰነ










