• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

በአፋር በየቀኑ እስከ 100 የሚደርሱ ከብቶች ይሞታሉ

August 12, 2015 05:38 am by Editor Leave a Comment

* እንደተለመደው ኢህአዴግ የድርቅ አደጋና የምግብ እጥረት ስጋት የለም እያለ ነው

ባለፉት ሁለት ወራት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የተከሰተው የዝናብ እጥረት የድርቅ አደጋ እንዳይከሰት ስጋት የፈጠረ ሲሆን ግብርና ሚኒስቴር በበኩሉ፤ የዝናብ እጥረት ቢኖርም የድርቅ አደጋና የምግብ እጥረት ስጋት የለም ብሏል፡፡

በአፋር ክልል ግን ሁኔታው ተባብሷል፡፡ በየቀኑ እስከ 100 የሚደርሱ ከብቶች በመኖና በውሃ እጥረት እየሞቱ መሆኑን ምንጮቻችን ጠቁመዋል፡፡

የአፋር ክልልን አቋርጠው ወደ ጅቡቲ ወደብ ከሚጓዙ ሹፌሮች አንዱ ለአዲስ አድማስ እንደገለፀው፤ በመንገድ ዳርና ዳር በርካታ በጎችና ፍየሎች ሞተው ይታያሉ፡፡

በክልሉ ካለፈው ዓመት ሰኔ ወር ጀምሮ እስካሁን ድረስ ዝናብ የጣለባቸው ቀናት በጣት የሚቆጠሩ መሆናቸውን የጠቆሙት ምንጮች፤ የድርቁ ሁኔታ እየተባባሰ ቢሆንም በመንግስት በኩል ፈጣን እርምጃ አልተወሰደም ሲሉ ቅሬታቸውን ገልጸዋል። የግብርና ሚኒስቴር ግን በዚህ አይስማማም። የዝናብ እጥረቱ የፈጠረው ድርቅ በእንሰሳቱ ላይ የከፋ ጉዳት እንዳያደርስ ከክልሉ መንግስት ጋር በመቀናጀት የመጠጥ ውሃና መኖ በማቅረብ ላይ መሆኑን ጠቁሞ ከብቶች እየሞቱ ነው ስለሚባለው ግን መረጃው እንደሌለው ገልጿል፡፡

በክልሉ የተከሰተው ድርቅ የሚያደርሰውን ጉዳት ለመከላከል አስፈላጊው ሁሉ እየተደረገ ነው ያሉት የሚኒስትሩ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ም/ኃላፊ አቶ ወንድሙ ፍላቴ፤ “ሀገሪቱ በቂና አስተማማኝ የአደጋ መከላከል ዝግጁነት አላት” ብለዋል፡፡

ምንጮቻችን እንደሚሉት፤ በተለይ በአማራ ክልል በወሎ እንዲሁም በሐረር አካባቢ በተከሰተው የዝናብ እጥረት የድርቅ ስጋት አንዣቧል፡፡

ዘንድሮ በአገሪቱ የሰሜንና ምስራቅ እንዲሁም መካከለኛ ክፍሎች በአየር ፀባይ ለውጥ (ኤሊኖ) የተነሳ የዝናብ እጥረት መፈጠሩን የጠቆመው ግብርና ሚኒስቴር፤ በሰኔና በሐምሌ ይጠበቅ የነበረው ዝናብ መቆራረጥ ቀድሞ የተዘሩ ሰብሎች እንዳይበቅሉ ቢያደርግም ከነሐሴ ጀምሮ መዝነብ መጀመሩንና ቀጣይነት እንደሚኖረውም ገልጿል፡፡

“ገበሬዎች ዝናብ ሲዘንብ ጠብቀው ውሃውን በማቆር ለሰብሎቻቸው እንዲጠቀሙ እየተደረገ ነው፤ የግብርና ልማት ጣቢያ ሰራተኞችም የወትሮው የግብርና ስራ እንዳይስተጓጎል ያልተቋረጠ ድጋፍ እያደረጉ ነው” ብለዋል ም/ኃላፊው፡፡

በአሁኑ ወቅት ግብርና ሚኒስቴር የዝናብ እጥረቱን መቋቋም የሚችሉ የድንች፣ ስንዴ፣ ማሽላ፣ ጤፍና የመሳሰሉ ሰብሎችን ምርጥ ዘር በማቅረብ ችግሩን ለመከላከል ጥረት እያደረገ መሆኑንም ኃላፊው ጠቁመዋል፡፡  በተለይ የሰብል አምራች በሆኑ አካባቢዎች የተከሰተው የዝናብ እጥረት በቀጣይ ዓመት የሃገሪቱ የምርት አቅም ይቀንሳል፣ ረሃብም ሊፈጠር ይችላል የሚል ስጋት እንዳላቸው ምንጮቻችን የገለፁ ሲሆን ግብርና ሚኒስቴር በበኩሉ፤ የተፈጥሮ ክስተቱ ፈታኝ ቢሆንም ሃገሪቱ በቂ የአደጋ መከላከል ዝግጁነት እንዳላት ጠቁሞ፣ በቂ ምርት ማግኘት እንደሚቻልና የምግብ እጥረት ስጋት እንደማይኖር አስታውቋል፡፡ (ምንጭ: አዲስ አድማስ)

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: News Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጃዋርና በቀለ መታሠራቸው ተሰማ June 30, 2020 09:17 am
  • አገራዊ መድረክ ውጪ ድብቅ ውይይትን አንቀበልም June 17, 2020 06:57 am
  • ዴክሳሜታሶን! የኮሮና መድሀኒት June 17, 2020 06:49 am
  • የሰኔ 14ቱ ቀለበታዊ የፀሃይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ! June 17, 2020 06:38 am
  • የግብፅ የአባይን ውሃ ብቻዬን ልጠቀም ግትር አቋም ድርድር እንቅፋት ሆኗል June 10, 2020 07:15 am
  • የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!? April 12, 2020 02:48 am
  • በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሚጠቀሙበት የኤርትራ ስደተኛ ካምፕ ሊዘጋ ነው March 18, 2020 08:37 pm
  • እየተፈረካከሰ ያለው አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ March 18, 2020 08:09 pm
  • ኮሮና አዲስ ጉድ መዘዘ – ከቻይና በፊት በአሜሪካ ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎችን ቀጥፏል March 16, 2020 11:41 pm
  • የኮንዶሚኒየም ቤቶች በደላሎችና በመመሪያ ሰጪዎች ኔትዎርክ እየተቸበቸበ ነው! ታከለ የት ናቸው? March 9, 2020 10:18 am
  • ኤርሚያስ ለገሠ ከባለአደራ ተባረረ March 9, 2020 08:09 am
  • ድፍድፍ ሲቀል ይንሳፈፋል፤ ምሁር ሲዘቅት ይመራል፥ March 7, 2020 11:24 pm
  • ኢትዮጵያዊ ምን ይመስላል? በምንስ ይመሰላል? March 7, 2020 10:29 pm
  • WHY I WROTE “MONEY, BLOOD AND CONSCIENCE” March 4, 2020 11:15 pm
  • አድዋ፤ የጥቁር ሕዝብ ድል! March 2, 2020 11:24 am
  • ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ (አባ ጎራው) March 2, 2020 11:12 am
  • የኦነግ ሁለት መልክና ሦስት ግብሮች – ቃርሚያው ኃይል ቅጥር ነፍሰገዳይ ሆኗል February 25, 2020 11:26 pm
  • በቡራዩ “የጃል ማሮ” ፎቶ ጨረታ አፈናከተ፤ “ቡራዩ ሆኖ ከሃዲን ማሞካሸት አይቻልም” ነዋሪዎች February 17, 2020 09:13 pm
  • “ዲቃላ” የፍረጃ ፖለቲካ በኦሮሚያ የኃይል አሰላለፉን እየቀየረ ነው February 13, 2020 11:58 pm
  • “ከዚህ በኋላ ማናቸውንም በወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን” አንታገስም – ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ February 13, 2020 05:07 pm
  • “እኛ ማንም ተሳዳቢ እንዲመጣብን አንፈልግም” የጅማ ነዋሪ February 13, 2020 09:28 am
  • “ወላጆቻችሁ ሰላማዊ ሰልፍ በሕዝቡ ያስደርጉልን” – አጋቾች February 11, 2020 07:53 pm
  • “ወንጀል የፈጸመም ያስፈጸመም ተይዞ ለህግ ይቀርባል፤ ምርመራም ተጀምሯል” February 11, 2020 06:59 pm
  • ጃዋር ወደ መጨረሻው “የትግል” ስልቱ – አማራን ማበጣበጥ! February 10, 2020 11:54 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule