ቅማንት እና ዐማራ የተባሉት ነገዶች ለዘመናት አብረው ኖረዋል። አብረው በመኖራቸው ብዛትም በረጅሙ የአገራችን የመዋሐድ እና የመቀላቀል ሂደት አንድ ሆነዋል። ስለዚህ እኒህ ሁለት ነገዶች በጊዜ ሂደት የጋራ ኃይማኖቶች ተከታዮች፤ አንድ መግባቢያ የአማርኛ ቋንቋ፣ አንድ የጋራ አገር እና መልከዐምድራዊ መለያ፣ ከዚህም በላይ አንድ የነፃነት ታሪክ ባለቤት ለመሆን በቅተዋል። በመሆኑም የወል የሆነ ማኅበራዊ ሥነልቦና መስርተዋል። በዛሬው ዘመን የነገዶቹን ተወላጆች ሁለንተናዊ ማንነትን መነሻ አድርጎ ለመለያየት መሞከር፣ ውኃ እና ወተት ከቀላቀሉ በኋላ እንደገና ለመለየት እንደመሞከር ይቆጠራል፥ ውሕድ አካል ሆነዋልና። ሆኖም የትግሬ-ወያኔ ኢትዮጵያን፣ ኢትዮጵያዊነትን እና ዐማራን ለማጥፋት ላለው ረጅም ዕቅድ ብቸኛ ማሳኪያ መንገድ አድርጎ የወሰደው የ«ከፋፍለህ ግዛው» ሥልትን ነው። የዚህ ሥልት … [Read more...] about “ቅማንት ዐማራ፣ ዐማራም ቅማንት ነው”
Left Column
ማፈናቀል እንደገንዘብ
ከ1966 ዓ.ም. በፊት መሬት አገር ነበር፤ ከዚያ በኋላ እስከ 1983 መሬት የጋራ ሀብት ሆነ፤ ከ1983 ወዲህ መሬት ገንዘብ ሆነ፤ ጡንቻ ገንዘብ ሆነ፤ መሬት ጡንቻና ገንዘብ ሆነ፤ አገር የት ደረሰ? በጡንቻ ሀብታም መሆን ይቻላል፤ በጡንቻ ገበያውን መቆጣጠር ይቻላል፤ በጡንቻ ሻጩን መቆጣጠር ይቻላል፤ በጡንቻ ገዢውን መቆጣጠር ይቻላል፤ ገበያውን፣ ገዢውንና ሻጩን መቆጣጠር ከተቻለ ዋጋውን መቆጣጠር ይቻላል፤ እዚህ ደረጃ ላይ ከተደረሰ ምሥጢሩ ግልጽ ይሆናል፤ ምሥጢሩ ምንድን ነው? ዋናው ነገር ጡንቻ ነው፤ ጡንቻ የሀብት ምንጭ ነው፡፡ ጡንቻ ካለ ተማሪ ቤት ወይም ሀኪም ቤት፣ ወይም አንድ መሥሪያ ቤት ለመሥራት በሚል ሰበብ አንድ መቶ ቤተሰቦችን ከኑሮአቸው ማፈናቀል ሕጋዊ ያሆናል፤ አንድ መቶ ቤተሰቦች ሰፍረውበት የነበረው በአማካይ በነፍስ ወከፍ 100 ሜ.ካ. መሬት ነው እንበል፤ አንድ … [Read more...] about ማፈናቀል እንደገንዘብ
ለፍትሕና ለነጻነት የሚደረገው ትግል ኢትዮጵያዊ መልክ ይያዝ!
“Injustice anywhere is a threat to justice everywhere” Martin Luther King Jr. ላለፉት ሦስት ሳምንታት አወዛጋቢውን የአዲሰ አበባ ማስተር ፕላን እቅድና የትግበራ ዝግጅት በመቃወም በአገራችን የተለያዩ የኦሮሚያ ክልል ከተሞች ውስጥ የተቀሰቀሰው የተማሪዎች ተቃውሞ እያደር ወደ ሕዝባዊ ቁጣና አመጽ እየተቀይረ መምጣቱን በግልጽ እየተመለከትን ነው፡፡ አድሮ ጥሬ የሆነው የወያኔ አገዛዝ ሥርዓትምየተነሱትን ጥያቄዎች በወቅቱና ስልጡን በሆነ መልኩ ከመፍታት ይልቅ ላለፉት 24 አመታት እንደሚያደርገው ሁሉ ዛሬም የኃይል እርምጃ በመውሰድበአስሮች የሚቆጠሩ ሰዎችን ሕይወት አጥፍቷል፣ በርካቶችን ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት አድርሶባቸዋል፣ ቀላል ግምት የማይሰጠው የህዝብ ንብረትም እየወደመ ይገኛል፡፡ የህዝባዊ ተቃውሞው መንስዔ ተማሪዎቹ ያነሱትና በተቀረው … [Read more...] about ለፍትሕና ለነጻነት የሚደረገው ትግል ኢትዮጵያዊ መልክ ይያዝ!
ድርቅ እና የተማሪዎች ተቃውሞ የአለመግባባት አደጋ መገለጫዎች ናቸው
አለመግባባት ለአገራችን ህልውና የሚፈጥራቸው አደጋዎች በየጊዜው እየጨመሩና እየተስፋፉ መምጣቱ በእጅጉ አስጊ ደረጃ ላይ ደርሷል። መንግስት ዋና ዋና ችግሮች ላይ አገራዊ መፍትሄን ለማግኘት ከህዝብ፣ ከህጋዊ ተቃዋሚዎችና ከዲያስፓራው ማህበረሰብ ጋር መግባባት ላይ ካልደረሰ አለመግባባት ወደ ቀውስና ግጭት ማደጉ አሳሳቢ ነው። መንግስት ለድርቅ አደጋ የተዳረጉ አስራ አመስት ሚሊዮን ዜጎችን አስፈላጊውን እርዳታና ድጋፍ እንዲያገኙ ሁሉንም ያሳተፈ፡ ግልጽና አፋጣኝ መፍትሄ ካልፈጠረ፤ እንዲሁም የኦሮሚያ ተማሪዎች በአዲስ አበባ ከተማ ፕላን ላይ የሚያሰሙትን ተቃውሞ በማግባባት መፍትሄ ከመፍጠር ይልቅ ተማሪዎችን በመግደልና በማሰር ብቻ አላማውን የማስፈጸም አሰራሩ ከቀጠለ ለአገራችን ሰላምና መረጋጋት ከፍተኛ አደጋ ነው። (ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about ድርቅ እና የተማሪዎች ተቃውሞ የአለመግባባት አደጋ መገለጫዎች ናቸው
በወገኖቻችን ላይ የሚካሄደው አፈናና ጭፍጨፋ ባስቸኳይ ይቁም
የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ በወቅቱ ጉዳይ ላይ ያወጣው መግለጫ ከዚህ በታች ይገኛል፡፡ … [Read more...] about በወገኖቻችን ላይ የሚካሄደው አፈናና ጭፍጨፋ ባስቸኳይ ይቁም
“ሕዝብ ከሸፈተ ሠራዊት አያቆመውም” መለስ ዜናዊ
የሩስያ ኮሚኒስት አምባገነኖች ሕዝቡን ሰንገው በሚገዙበት ዘመን፤ አንድ ስመጥር ፈረንሳዊ ደራሲ ወደ ሞስኮ ጎራ ይላል፡፡ በጊዜው የመንግሥት ታጣቂዎች ተቃዋሚዎችን በማፈንና በመግደል ተጠምደው በማየቱ አዝኖ ቅሬታውን ላንድ ካድሬ ገለጸ፡፡ ካድሬው ቅሬታውን ከሰማ በኋላ “እንቁላል ፍርፍር ለመሥራት ከፈለግህ እንቁላሉን መስበር አለብህ” ብሎ ተፈላሰፈ፡፡ ደራሲው የዋዛ ስላልነበረ እንዲህ ብሎ መለሰት፤ “እዚህም እዚያም የእንቁላል ስብርባሪ ይታየኛል፡፡ ግን ፍርፍሩ የታል?” እስከቅርብ ጊዜ ስንሰማው የነበረው፤ “ዲሞክራሲን ቸል ያልነው ቅድሚያ ሕዝቡን ዳቦ ለመመገብ ነው” የሚለው መከራከርያ ውሃ በልቶታል፡፡ ዳቦውም ሆነ ዲሞክራሲውም ገደል ገብቷል፡፡ የምለው አንድ ነገር ብቻ ነው፡፡ በሀገሪቱ በየቦታው እየተፈጸመ ያለውን ግድያ በጊዜ አቁሙ! ገባሩ ህዝብ የሚላችሁን ስሙ፡፡ ስለ “ዘለቄታዊ … [Read more...] about “ሕዝብ ከሸፈተ ሠራዊት አያቆመውም” መለስ ዜናዊ
የሞረሽ የአቋም መግለጫ
እኛ የሞረሽ ወገኔ ዐማራ ድርጅት ማዕከላዊ ምክር ቤት አባላት እሑድ ኅዳር ፳፮ ቀን ፪ሺህ፰ ዓ.ም. (Sunday December 6, 2015) ባደረግነው የማዕከላዊ ምክር ቤቱ ሰባተኛ መደበኛ ስብሰባ ፣ በማዕከላዊ ምክር ቤቱ ስድስተኛ መደበኛ ስብሰባ በጸደቁት የ፮(ስድስት) ወራት የሥራ ዕቅዶች አፈጻጸም ምዘና ሪፖርት፣ በድርጅቱ የቁጥጥርና ፍተሻ የአካላትና የአባላት የሥራ እንቅስቃሴና የገንዘብ አሰባሰብና አጠቃቀም ሪፖርት በአንክሮ አዳምጠን አስፈላጊውን ውይይት በማድረግ ሪፖርቶቹ ከምክር ቤቱ አባሎች የቀረቡትን ገንቢ ሀሳቦችን አካትቶ የድርጅቱ ቋሚ ሰነድ እንዲሆን በሙሉ ድምፅ ወስነናል። ከሁሉም በላይ በዚህ መደበኛ ስብሰባ ምክር ቤቱ አጽንዖት ሰጥቶ ሠፊ ጊዜ ወስዶ የተወያየበት «የድርጅቱን ዓላማና ተልዕኮ በተሻለ መንገድ እንዴት ማከናወን ይቻላል?» ለሚለው ጥያቄ ተገቢና ሁነኛ መልስ … [Read more...] about የሞረሽ የአቋም መግለጫ
ጋምቤላ: የፌደራሊዝሙ ክሽፈት ማሳያ?
ሐሙስ 20 – 01 – 2003፣ ጋምቤላ ከተማ፡ የጋምቤላ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አዲሱን የስራ ዘመኑን የመጀመሪያውን የእድገትና የትራንስፎርሜሽን እቅድ በማጽደቅ ያጠናቀቀ ሲሆን፤ በመዝጊያው ስነ ስርዓት ላይ በጊዜው የክልሉ ፕሬዝደንት የነበሩት ኡሞት ኡባንግ ባደረጉት ንግግር፡ ‹‹ጋምቤላን ወደ ቀድሞው ክብሯ እንመልሳታለን፡፡ ያችን አኙዋዎች፣ ኑዌሮች፣ መዠንገሮች፣ ኦፖዎች፣ ኮሞዎችና ደገኞች አንድ ላይ በሕብረት የሚኖሩባትን - ጋምቤላ፡፡ ሁላችንም አፍሪካዊያኖች ነን፡፡ ጥላቻና ልዩነት ለማናችንም አይበጁንም…›› በማለት የሁሉንም ተሰብሳቢዎች ልብ የሚነካ ሃሳብ አቀረቡ፡፡ 156 መቀመጫዎች ያሉት የክልሉ ምክር ቤትም በጭብጨባ ተናጋ፡፡ ኡሞት ይሄን ታሪካዊ ንግግር ሲያደርጉ ከኡሞት ጎን የተቀመጡት የክልሉ ምክር ቤት አፈጉባኤ እንዲሁም የፌደሬሽን ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ አሽኔ … [Read more...] about ጋምቤላ: የፌደራሊዝሙ ክሽፈት ማሳያ?
“ትግራይ ወረዳ ውስጥ ያለ የመንግሥት አሰራር በኦሮሚያ ውስጥ … ይገኛል”
* "የአዲስ አበባ መሬት በማለቁ ወደ ኦሮሚያ መሬት እጃቸውን መዘርጋት ጀመሩ" * "ማስተር ፕላኑ መሰሪ ነው" በቀለ ገርባ የአዲስ አበባና የፊንፊኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ማስተር ፕላንን በተመለከተ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ያለውን ዝርዝር አቋም በተመለከተ የፓርቲው ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባን አዲስ አድማስ ጋዜጠኛ አለማየሁ አንበሴ በፅ/ቤታቸው ተገኝቶ አነጋግሯቸዋል፡፡ መንግሥት ማስተር ፕላኑ ከተሞችን በመሰረተ ልማት በማስተሳሰር እድገትን ለማምጣት ከፍተኛ ጥቅም አለው ይላል፡፡ ፓርቲያችሁ ደግሞ ማስተር ፕላኑን አልቀበልም ብሏል፡፡ በምን ምክንያት ነው የማትቀበሉት? እኛ ማስተር ፕላኑን የማንቀበለው በትክክል የህዝቡን የልማት ጥያቄ ለመመለስ የተዘጋጀ ነው የሚል እምነት ስለሌለን ነው፡፡ መንግሥት በዚህ አሳቦ ወደ ኦሮሚያ አጎራባች ከተሞች ዘልቆ እየገባ … [Read more...] about “ትግራይ ወረዳ ውስጥ ያለ የመንግሥት አሰራር በኦሮሚያ ውስጥ … ይገኛል”
የመለስ ሬሣ በህይወት ያሉትን ዜጎች እያፈናቀለ ነው
የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባርን በራሳቸው ልክ አሰፍተው፤ ተቃዋሚዎቻቸውን አስገድለው፤ ሌሎችን ደግሞ እንዲሰደዱ አድርገው አገር በነጻ አውጪ ስም ለዓመታት የገዙት መለስ ሞተውም ሬሳቸውን እና በሕዝብ ደም የጨቀየውን “ሌጋሲያቸውን” ለመጠበቅ ዜጎች ከመኖሪያቸው ይፈናቀላሉ፤ እምቢ ያሉ ደግሞ ህይወታቸውን ያጣሉ፡፡ ለመለስ መዘከሪያ ቦታ ለማስቀቅ የተፈቀደበት ደብዳቤ ለዝግጅት ክፍላችን በፌስቡክ በኩል በሰነድነት ደርሶናል፡፡ ደብዳቤው እንደሚያስዳው ሬሣ ለማክበር ሕያዋን እንዲገደሉ፤ እንዲፈናቀሉ ይደረጋል፡፡ ሬሣ ሕያዋንን ለሞት ሲዳርግ! ህወሃት በኃይል በሚገዛት ኢትዮጵያ የማይሰማ ጉድ የለም፡፡ (ጎልጉል) … [Read more...] about የመለስ ሬሣ በህይወት ያሉትን ዜጎች እያፈናቀለ ነው









