ህወሓት/ኢህአዴግ በራሱ ጉባዔ (ፓርላማ)፣ በራሱ ባለሥልጣናት፣ በራሱ ፈቃድ፣ በራሱ በሚተዳደረው ሚዲያ፣ ፈቅዶም ሆነ ሳይፈቅድ በሚገዛለት ሕዝብ ፊት ይፋ ያደረገው የስኳር ፕሮጀክት ዝርፊያ በራሱ አስፈላጊ ርምጃ ለመውሰድ በቂ ሆኖ ሳለ ሙስናን በመታገል ስም እስካሁን መቆየቱ በራሱ አነጋጋሪ ነው፡፡ ምክንቱም አፈቀላጤ ነገሪ ሌንጮ እንዳለው የኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ እንደመዥገር ተጣብቀው ደሙን የሚጠጡት የበላይ ኃላፊዎች እነማን እንደሆኑ ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ነውና፡፡ ችግሩ ያለው ዋናዎቹን መዥገሮች ማን ይንቀላቸው የሚለው ላይ ነው፡፡ በኢህአዴግ ውስጥ የሚፈጠሩ አደገኛ የፖለቲካ ልዩነቶች ለማስተንፈስና የአመራሩንና አባላቱን አፍ ለማስዘጋት መለስ ዜናዊ ያደርገው እንደነበረው “የሙስና ዘመቻ” ሲጀመር ይህ ያሁኑ የመጀመሪያው አይደለም፡፡ በቅርቡ “ጥልቅ ተሃድሶ” በሚል “ዘመቻ” ሲጀመር … [Read more...] about ዋናዎቹ “መዥገሮች” ትንንሾቹን ነቀሉ!
Full Width Top
የህወሃት/ኢህአዴግ ሰብዓዊ መብቶች ረገጣ ከሒዝቦላና ሰሜን ኮሪያ ጉዳይ ጋር በሙሉ ድምጽ ውሳኔ አገኘ
የህወሃት/ኢህአዴግን የሰብዓዊ መብቶች ይዞታና አጠቃላይ አስተዳድርን የሚወቅስ የህግ ረቂቅ ዛሬ በዩናይትድ ስቴትስ የሕግ መምሪያ የውጭ ጉዳዮች ኮሚቴ ፊት ቀርቦ በሙሉ ስምምነት አልፏል። ከውሳኔው በላይ የአሜሪካ ወዳጅ በመሆን ሕዝብን ለመከራና ስቃይ ሲዳርግ የኖረው የኢህአዴግ አገዛዝ በአሻባሪነቱ ከሚወገዘው ሒዝቦላ እና ከሰሜን ኮሪያ የሰብዓዊ መብቶች ጉዳይ ጋር በእኩል ቀርቦ መታየቱ “የአሜሪካና ኢህአዴግ ወዳጅነት ወዴት?” አስብሏል፡፡ በዕለቱ ዘጠን አጀንዳዎች ለውሳኔ የቀረቡ ሲሆን የኢትዮጵያን ጉዳይ ጨምሮ የአውሮጳ ህብረት ሒዝቦላን አሸባሪ ድርጅት በማለት እንዲጠራው፤ የሰሜን ኮሪያን የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት በተመለከተ ከዚህ በፊት የወጣው እንደገና እንዲተገበር፤ ኬኒያ ነጻና ፍትሐዊ ምርጫ እንዳታካሂድ፣ በቬኒዙዌላ ያለውን የሰብዓዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ማኅበራዊ ቀውስ … [Read more...] about የህወሃት/ኢህአዴግ ሰብዓዊ መብቶች ረገጣ ከሒዝቦላና ሰሜን ኮሪያ ጉዳይ ጋር በሙሉ ድምጽ ውሳኔ አገኘ
በጉጂ ዞን ከፍተኛ ውጊያ ተነስቷል
የአማሮ ህዝብ (ኮሬ ጎሳ) እና በጉጂዎች መካከል ከእሁድ (23 ጁላይ) ምሽት ጀምሮ ከባድ በሆነ የድንበር ግጭት መቀስቀሱን ወደ ስፍራው የተጓዙ እማኞች አረጋግጠዋል። ከእሁድ ምሽት ጀምሮ በተነሳው የጎሳዎች ግጭት እስከአሁን ያልበረደ ሲሆን በግጭቱ ሳቢያ በርካታ ቤቶች በመቃጠል ላይ መሆናቸውን ስፍራው ድረስ ስልክ በመደወል ለማረጋገጥ ችለናል። በፎቶው ላይ እንደሚታየው በተነሳው ቃጠሎ አካባቢው በጭስ እየተሸፈነ ይገኛል። የአማሮ መንገድ በግጭቱ ሳቢያ ስለተዘጋ ወደ ዲላ ከተማ መውጣትም ሆነ ወደ ወረዳዋ መግባት እንዳልተቻለ የአይን ምስክሮቹ ገልጸዋል። የጸቡ መንስኤ ምን እንደሆነ እስካሁን በውል ባይታወቅም የሚመመለከተው አካል ጉዳዩን ችላ እንዳለውም ለማወቅ ተችሏል። አንዳንድ ታዛቢዎች ወያኔ አሁን ከገባበት ማጥ ለመውጣት ሲል እንዲህ አይነት ግጭቶችን ሆን ብሎ እንደሚያስነሳ ይናገራሉ። … [Read more...] about በጉጂ ዞን ከፍተኛ ውጊያ ተነስቷል
“በመንግሥታችን ምክንያት አገራችን ተከፋፍላለች” ቴዲ አፍሮ
ቴዲ “የአማራ ሙዚቀኛ በመሆን ቀጥሏል” ዘ ጋርዲያን “ወቅቱ አደገኛ ነው፤ አሁን እኔ ቅድሚያ የምሰጠው ለኢትዮጵያ ነው” ቴዲ የፍቅር፣ የዕርቅና አንድነትን መልዕክት በማንገብ ዘፈን ዘፍኖ ገንዘብ ከመሰብሰብና ታዋቂ ከመሆን በላይ የሚለፋው አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) አዲሱ አልበሙ ከወጣ በኋላ ከእንግሊዙ ጋዜጣ ዘ ጋርዲያን ጋር ባደረገው ቃለምልልስ የኢትዮጵያን ወቅታዊ ቁልጭ አድርጎ ተናግሯል፡፡ “በመንግሥታችን ምክንያት አገራችን ተከፋፍላለች” ያለው ቴዲ “የአፍሪካ ሞዴል ነበርን” በማለትም የቀደመውን የኢትዮጵያን ታላቅነትና ክብር አስታውሷል፡፡ በቅርብ የተለቀቀውን “ኢትዮጵያ” አልበም በተመለከተና ስለ አገሩ እንዲሁም ስለ ራሱ የህይወት ፍልስፍና የዜና ዘገባ ያወጣው ዘ ጋርዲያን ቃለ ምልልሱን ያደረገው በቴዲ የመኖሪያ ቤት በመገኘት ነበር፡፡ ስለ ቴዲ የቀድሞ … [Read more...] about “በመንግሥታችን ምክንያት አገራችን ተከፋፍላለች” ቴዲ አፍሮ
እምዬ ምኒልክ የኢትዮጵያ መሐንዲስ!
አጼ ምኒልክ በሕይወት ዘመናቸው የሰሯቸውን ድንቅ ተግባራት በደማቅ ብእርና ብራና የተከተቡ ናቸው! 1835 ዓ.ም. -------------ወፍጮ (በ1835ዓም ገደማ የሸዋው ንጉሥ ሣህለሥላሴ ነበሩ በውሃ የሚሥራ ወፍጮ ያስተክሉት ሆኖም በደረሰባቸው ተቃውሞ ሳይሳካላቸው ቀረ:: ተቀውሞውን አሸንፈው ምኒልክ በ1893ዓም አዲስ ወፍጮ አስተከሉ) 1882 ዓ.ም. -------------ስልክ 1886 ዓ.ም. ------------ፖስታ 1886 ዓ.ም. ------------ባህር ዛፍ 1886 ዓ.ም. ------------ገንዘብ 1886 ዓ.ም. ----------የውሃ ቧንቧ 1887 ዓ.ም. -----------ጫማ 1887 ዓ.ም. --------------ድር 1887 ዓ.ም. -------------የሙዚቃ ት/ቤት 1887 ዓ.ም. ----------የፅህፈት መኪና 1889 ዓ.ም. … [Read more...] about እምዬ ምኒልክ የኢትዮጵያ መሐንዲስ!
የተማሪዎች ዕውቀት ደረጃ “150 ዓመታት ወደ ኋላ” ቀርቷል!
“የትምህርት ጥራቱ እጅግ አሳፋሪ ደረጃ ላይ ደርሷል” ዶ/ር መስፍን “ከኮሌጅ ተመርቀው 7ኛና 8ኛ ክፍሎችን ለማስተማር ዝግጁ ከሆኑ መምህራን የ12ኛ ክፍል ፈተናን ብቻ ሳይሆን የ8ኛ ክፍል ፈተና ማለፍ አልቻሉም” “የኢትዮጵያ 7ኛና 8ኛ ክፍል ተማሪዎች አስተሳሰብ፣ አሜሪካ፣ ሲንጋፖርና መሰል አገራት የ1ኛ ክፍል ተማሪዎች አስተሳሰብ ጋር እኩል ነው” የግንቦት 20 መርዛማ ፍሬዎችን በተከታታይ ባተምንበት ጊዜ ከፍሬዎቹ መካከል “ትውልድ አምካኝ የትምህርት ፖሊሲ” አንዱ እንደነበር መግለጻችን ይታወሳል፡፡ ሕወሓት ሆን ብሎ በሚከተለውና አዲሱን ትውልድ ከማንኛውም ዓይነት የፖለቲካ አስተሳሰብም ሆነ አመለካከት ለመነጠል በሚያራምደው ፖሊሲ በድንቁር ተገዢ አድርጎ የመግዛቱን ዓላማ በፖሊሲ ደረጃ ሲተገብረው ቆይቷል፡፡ በድንቁርና ጭለማ ውስጥ ያሉትን ሹማምንቱን “ተፈጭና ተመረቅ” … [Read more...] about የተማሪዎች ዕውቀት ደረጃ “150 ዓመታት ወደ ኋላ” ቀርቷል!
“ዘውጌኝነት” እና “ዘውግ-ዘለልነት”…? [ከጉራጌ ምን እንማራለን?]
ለብዙዎቹ ችግሮቻችን ፍቱን መድኃኒት አድርጌ የምወስደው፣ ጉዳዩን በዘመን ቁመት እና በዓለም ሕዝቦች ታሪክ አግድም መመልከት ነው። ዓለም በበቂ ሁኔታ የምንማርባቸው ስኬቶች እና ውድቀቶች አሏት። ዘውጌኝነት፣ ብሔርተኝነት እና ዜግነት የመሳሰሉትም የብቻችን ጉዳዮች አይደሉም። ዓለም በየፈርጁ የዳከረችበት እና እየዳከረችበት ያለ ችግር ነው። ስለዚህ ጥያቄውን በቅጡ ለማበጃጀትም ይሁን፣ አዋጭ መልስ ለመፈለግ ከሰው ልጆች እንደአንድ የሚያደርገንን ታሪክ የምናውቀውን ያክል ማሰስ ያስፈልጋል። ይህን ከጠቆምኩ በኋላ ወደ የበኩሌን ለመሞከር ወደ አጀንዳዬ እዘልቃለሁ። የዘውግ ብሔርተኝነት ምንድን ነው? የዘውግ ብሔርተኝነት (ethnonationalism) የአንድ ዘውግ (ethnic) ቡድን ነጻ አገር እንዲመሠርት ወይም ከመገንጠል ወዲህ ያለውን የራሱን ዕድል በራሱ እንዲወስን ለማስቻል የሚደረግ … [Read more...] about “ዘውጌኝነት” እና “ዘውግ-ዘለልነት”…? [ከጉራጌ ምን እንማራለን?]
ራስ እምሩን በተመለከተ፤
የኢትዮጵያ አርበኞች ቀን ሚያዚያ 27፤2009 የተከበረበትን ዕለት ምክንያት በማድረግ ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በዕለቱ (May 5, 2017) “የኢትዮጵያ አርበኞች ውለታና የባንዳዎች ዕዳ!” በሚል ርዕስ አንድ ጽሁፍ ለኅትመት አቅርቦ ነበር፡፡ የጽሁፉ ዓላማ በዚህ መልኩ ቀርቦ ነበር፤ “በየዓመቱ ሚያዝያ 27 የሚከበረው የድል ቀን በኢትዮጵያ የቀን መቁጣሪያ (ካሌንደር) ላይ ሥራ ተዘግቶ እንዲከበር ቢደረግም ትውልዱ የቀደሙ እናትና አባቶቹን የተጋድሎ ታሪክ እንዲያወቅ የሚያስችል የበዓል አከባበር አይታይም፡፡ ዕለቱም እንደአንድ ተራ የረፍት ቀን ያልፋል፡፡ በአንጻሩ አንዳች አገራዊ ፋይዳ የሌላቸው የህወሃት፣ የብአዴን፣ የኦህዴድ፣ … የምሥረታ ቀን እየተባለ በብዙ ሚሊዮን ገንዘብ የሚወጣባቸው ለወራት በዕቅድ ተይዘው የሚደገሱ በዓላት በድምቀት እንዲከበሩ ይደረጋል፡፡ “አዲስ አበባ አራት … [Read more...] about ራስ እምሩን በተመለከተ፤
የ“ግንቦት 20” ሃያ መርዛማ ፍሬዎች! “ክፋት” – በሁሉም መስክ!!
መርዛማ ፍሬ 11፡ የታሪክ መቃብር! በስሜት በሚነዳ የዘውግ ፖለቲካ ውስጥ ታሪክ ትልቅ ማገዶ ሆኖ ቀርቧል። የኢትዮጵያ ታሪክ አካታችነት ባለው መልኩ በአጎልባች ሚና (ብሔራዊ ተዋፅዖ) መፃፍ እየተገባው ምክንያታዊነትን አስመንኖ የልዩነት ሃረጎችን ብቻ በመምዘዝ በየአቅጣጫው የሚፃፍ መሆኑ ከተካረረ ሙግት ሊፀዳ አልቻለም። መዋቅራዊ ድጋፍ ባለው መልኩ የታሪክ ሙግቱ እየተካረረ በመምጣቱ ብሔራዊ ርዕይ ርቆን የመንደር አጥር እስከመስራት ደርሰናል። ደርግ በየትኛውም ያህል መጠን አምባገነንና ጨፍጫፊ ሆኖ ቢገኝም የኢትዮጵያን ታሪክ ሲንቅና ሲያንቋሽሽ አልተገኘም። ከቶውንም ለብሔራዊ ርዕይ መፍጠሪያነት እንደግብዓት ተጠቅሞበታል። ከመነሻው ጀምሮ ኢትዮጵያዊ ስሜትን (የጋራ ማንነትን) በመካድ ራሱን ብቸኛ የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጭ ግንባር አድርጎ የሰየመው ህወሓት፣ የአገሪቱን የረዥም ጊዜ ታሪክ … [Read more...] about የ“ግንቦት 20” ሃያ መርዛማ ፍሬዎች! “ክፋት” – በሁሉም መስክ!!
የ“ግንቦት 20” ሃያ መርዛማ ፍሬዎች — የአንድ ጎጥ የበላይነትና የመበታተን አደጋ!
ራሳቸውን “የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር” ብሎ በመሰየም የትግራይን ሕዝብ ሽፋን በማድረግ፤ “የምታገለው ለአንተ ነጻነት ነው” በማለት፤ መልሶ እታገልለታለሁ ያለውን ሕዝብ ያስጨፈጨፈው፣ ያስራበው፣ የግፈ ሰለባ ያስደረገው፣ … ራሱን ህወሓት እያለ የሚጠራው የወንበዴዎች ቡድን የኢትዮጵያን የሥልጣን መንበር ከተቆናጠጠ በኋላ የትግራይ ሰዎችን በሌላው ኢትዮጵያዊ ለማስጠላትና “ስም ለማሰጠት” እንዲሁም ለማጠልሸት ባለፉት 26ዓመታት ሲሰራ ቆይቷል። እነዚህ በኮ/ሎ ጎሹ ወልዴ አነጋገር “የሰከረ ርዕዮትዓለም የሚከተሉ፣ በብሄርና በጎሳ ፖለቲካ ላይ የተተከሉ ጠባብ ቡድኖች፣ በስታሊናዊ መርህ የተጠመቁ፣ እንኳንስ 50 ሚሊዮን ህዝብ ያላት አገር ቤተሰብን የመምራትና የማስተዳደር ተሞክሮ የሌላቸው፣ …” የኢትዮጵያን ሃብት እየዘረፉ በትግራይ ኢንቨስት በማድረግ፣ የትግራይ ተወላጆችን የተለያዩ … [Read more...] about የ“ግንቦት 20” ሃያ መርዛማ ፍሬዎች — የአንድ ጎጥ የበላይነትና የመበታተን አደጋ!







![“ዘውጌኝነት” እና “ዘውግ-ዘለልነት”…? [ከጉራጌ ምን እንማራለን?]](https://staging.goolgule.com/wp-content/uploads/2017/07/mc-nat-748174-300x130.jpg)


