የትግራይ ሕዝብ “ነጻ አውጡኝ” ብሎ ሳይሰይማቸው፣ ሳይመርጣቸው፣ ሳይጠይቃቸው፣ ራሳቸውን “የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር” ብለው የሰየሙ ወንበዴዎችና ሽፍቶች የምኒልክ ቤተመንግሥት ከገቡ 26 ዓመታት ተቆጥረዋል። በቂም፣ በበቀል፣ በክፋትና በኢሞራላዊ ተግባራት የተሞሉ፤ ኢትዮጵያዊ መሆናቸው ፈጽሞ የሚያጠራጥር፤ ማንነታቸው ይህ ነው ተብሎ የማይታወቅ፤ በሐሰት ስም ከበረሃ እስከ ቤተመንግሥትና ዓለምአቀፍ መድረክ ላይ የታዩ፤ በሐሰት ፕሮፓጋንዳ የትግራይን ሕዝብ ያስጨፈጨፉ (ሐውዜንን ይጠቅሷል)፤ ሲነሱ አንዳች ገንዘብ ያልነበራቸው መናጢዎች በበረሃ የድሃ ረሃብተኛ እህል ዘርፈው በመሸጥ፤ ሥልጣን ከያዙ በኋላ ደግሞ የኢትዮጵያን ሐብት ሙልጭ አድርገው ዘርፈው ሲያበቁ “የራሳችን ንብረት ነው” በማለት ኤፈርት የሚባል የወንበዴዎች ሃብት ማከማቻ ቋት የፈጠሩ፤ ከበረሃ እስከ መንግሥታዊ ሥልጣን … [Read more...] about የ“ግንቦት 20” ሃያ መርዛማ ፍሬዎች – የመንግሥት ውሸት፣ የሃይማኖት ተቋማት ውድቀት፣ … (ክፍል ሦስት)
Full Width Top
የ“ግንቦት 20” ሃያ መርዛማ ፍሬዎች – የመሬት ነጠቃና ስደት (ክፍል ሁለት)
የዛሬ 26 ዓመት ራሱን የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሓት) ብሎ የሰየመ የወንበዴዎችና የሽፍታዎች ስብስብ በምዕራባውያን አንጋሾቹ ታግዞ የምኒልክን ቤተመንግሥት ከተቆጣጠረ ከጥቂት ጊዜያት በኋላ በዩናይትድ ስቴትስ ሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት ቃላት እንደ እሣት እየተፉ ታሪክ ፈጽሞ ሊረሳው የማይችለውን ንግግር ያደረጉት ድንቅ ኢትዮጵያዊ ነበሩ – ኮ/ሎ ጎሹ ወልዴ!! ስለ ኤርትራ መገንጠል እና ስለ ህወሃት የአስፈጻሚነት ተግባር የቀድሞው የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ኮሎኔል ጎሹ ወልዴ የትንቢት ያህል፤ ሳግ እየተናነቃቸው ይህንን ነበር የተናገሩት፤ “… ሆን ተብሎ በተቀነባበረ እቅድ ህወሃት አዲስ አበባን እንዲቆጣጠር የተወሰነው ውሳኔ አሳዛኝና ከቶውንም ሊታመን የማይችል ነው። የሰከረ ርዕዮትዓለም የሚከተሉ፣ በብሄርና በጎሳ ፖለቲካ ላይ የተተከሉ ጠባብ ቡድኖች፣ በስታሊናዊ መርህ … [Read more...] about የ“ግንቦት 20” ሃያ መርዛማ ፍሬዎች – የመሬት ነጠቃና ስደት (ክፍል ሁለት)
የ“ግንቦት 20” ሃያ መርዛማ ፍሬዎች! (ክፍል 1)
የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሓት) የተባለ የወንበዴዎች ስብስብ በምዕራባውያን አንጋሾቹ ታግዞ የምኒልክን ቤተመንግሥት ከተቆጣጠረ ከጥቂት ጊዜያት በኋላ በዩናይትድ ስቴትስ ሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት ቃላት እንደ እሣት እየተፉ ታሪክ ፈጽሞ ሊረሳው የማይችለውን ንግግር ያደረጉት ድንቅ ኢትዮጵያዊ ነበሩ – ኮ/ሎ ጎሹ ወልዴ!! ስለ ኤርትራ መገንጠል እና ስለ ህወሃት የአስፈጻሚነት ተግባር የቀድሞው የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ኮሎኔል ጎሹ ወልዴ የትንቢት ያህል፤ ሳግ እየተናነቃቸው ይህንን ነበር የተናገሩት፤ “… ሆን ተብሎ በተቀነባበረ እቅድ ህወሃት አዲስ አበባን እንዲቆጣጠር የተወሰነው ውሳኔ አሳዛኝና ከቶውንም ሊታመን የማይችል ነው። የሰከረ ርዕዮትዓለም የሚከተሉ፣ በብሄርና በጎሳ ፖለቲካ ላይ የተተከሉ ጠባብ ቡድኖች፣ በስታሊናዊ መርህ የተጠመቁ፣ እንኳንስ 50 ሚሊዮን ህዝብ … [Read more...] about የ“ግንቦት 20” ሃያ መርዛማ ፍሬዎች! (ክፍል 1)
ፍልሰት፤ ልመናና የጎዳና ህይወት በአዲስ አበባ!
“በመንገዶች አምራ በፎቆች ተውባ” የህወሃት/ኢህአዴግ ኩራት የሆነችው አዲስ አበባ “አገሪቱ አሁን ያለችበት ሂደት በእሳት ላይ ተጥዶ እንደሚንተከተክ ማሰሮ ትመስላለች” አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ሁሉ ነገር ነች፡፡ ከተማዋ ከፖለቲካ ከተማነቷ ባሻገር የኢኮኖሚና የማህበራዊ ዘርፎች ማዕከል መሆኗ የብዙዎችን ትኩረት እንድትስብ አድርጓታል፡፡ በክልሎች የሚታየው የሥራ ዕድል ዕጦት፣ ይህን ተከትሎ የተፈጠረው ሥር የሰደደ ድህነት አዲስ አበባን የከተማ ስደት መከማቻ ማዕከል አድርጓታል፡፡ በርግጥ የከተማ ስደት ስረ-መነሻ ከቀደሙት ጊዜያቶች ጀምሮ የተለያየ መንስኤ አለው፡፡ የኢትዮጵያን የከተማ ስደት ከአገሪቱ ማህበረ-ኢኮኖሚና የፖለቲካ መዋቅር ጋር አስተሳስረው የሚያጠኑ ምሁራን የከተማ ስደትን ከኢትዮጵያ ከተሞች አመሠራረት ጋር አያይዘው የጥናት ውጤታቸውን ያቀርባሉ፡፡ በጥንቱ … [Read more...] about ፍልሰት፤ ልመናና የጎዳና ህይወት በአዲስ አበባ!
ኢትዮጵያ፤ ህወሓትና የትግራይ ወጣት
ኢትዮጵያ ወጣትነትን15-29 ዓመት ባለ የዕድሜ ክልል ከፍላ ትበይነዋለች፡፡ አገሪቱ ውስጥ ካለው የህዝብ ብዛት በአማካይ 60% የሚሆው ወጣት ተብሎ ሊጠቀስ በሚችለው የዕድሜ ክልል ይገኛል፡፡ የተሻለ የትምህርት ጥራት፣ አማራጭ የሥራ ዕድል፣ ምቹ ማህበራዊ አገልግሎት፣ የፖለቲካ ነፃነትና መሰል ወሳኝ ጉዳዮችን አጥብቀው የሚሹት የኢትዮጵያ ወጣቶች ከህወሓት/ኢህአዴግ አፓርታይዳዊ ዘረኛ የፖለቲካ አሰላለፍ ጋር በተደጋጋሚ ሲላተሙ ይስተዋላል፡፡ ለህወሓት/ኢህአዴግ አንድ አይነት ወይንም ተመሳሳይ አጀንዳ የሚያነሳ፣ በዘውጋዊ (በዘረኛ) ማንነት የማይከፋፈል፣ ለአገዛዙ የማያጎበድድ ወጣት “የሥርዓቱ አደጋ” ነው፡፡ በ1997 ታሪካዊ የምርጫ ዘመን የአገዛዙን ዘረኛ የአፓርታይድ አሰላለፍ የማይቀበሉ፣ ከአካባቢያዊ ማንነት ይልቅ የጋራ ማንነትን ያቀነቀኑ ወጣቶችን ከመንግስታዊ ፍጅቱ ጎን ለጎን “አደገኛ … [Read more...] about ኢትዮጵያ፤ ህወሓትና የትግራይ ወጣት
በግብረሰዶማዊያን የተወረረችው አዲስ አበባ!
ግብረ-ሰዶማዊነትን እንደገቢ ምንጭ የሚጠቀሙበት ወንድ አዳሪዎችና (male prostitutes) ደላሎች አሉ! ግብረሰዶማዊያኑ የራሳቸው መገናኛ ቤቶችና ምሽት ክለቦች አሏቸው “ዜጋ” የሚለው ቃል የመግባቢያ ኮድ ሥማቸው ነው! ግብረሰዶማዊያኑ በድብቅ መኖሪያ ቤቶችና በምሽት ክለቦቻቸው “የጋብቻ ሥነሥርዓታቸውን” ይፈጽማሉ! ዳዊት ተሰማ (የባለ ታሪኩ ስም የተቀየረ) በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በድህረ ምረቃ መርሐ-ግብር የህብረተሰብ ጥናት ተመራቂ ተማሪ ነው፡፡ ተማሪው ለዲግሪ ማሟያ ጥናት ለማዘጋጀት ለአማካሪው ካቀረበው የጥናት ሀሳብ አንዱ ግብረሰዶማዊነት በአዲስ አበባ በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ፤ በተለይም ሁኔታውን ከውጪው ዓለም ተጽዕኖ አኳያ በማያያዝ ለማቅረብ ነበር፡፡ የተማሪው የጥናት ሀሳብ በአማካሪው መምህሩ ውድቅ የተደረገ በመሆኑ ሌላ ርዕስ የጥናት ሀሳብ ለመምረጥ … [Read more...] about በግብረሰዶማዊያን የተወረረችው አዲስ አበባ!
ተስፋዬ ገ/አብ “የሚዲያ ያለህ” እያለ ነው!
ለተስፋዬ ዕድል መስጠት ሬዲዮ RTLM መሆን ነው የኢትዮጵያ ስም ሲጠራ፣ ከፍ ከፍ ሲል “የዘር ወባው” የሚነሳበት ተስፋዬ ገ/አብ አሜሪካ ገብቶ የሚያናግረው ሚዲያ በማጣቱ “በሚዲያ ረሃብ” እየተሰቃየ መሆኑ ተሰምቷል፡፡ በክፉም ይሁን በመልካም ከሚዲያ መገለል የማይወደው ተስፋዬ “ሻዕቢያን የሚያጋልጥ መጽሐፍ ጽፌአለሁና አናግሩኝ” እያለ በዳያስፖራ ያሉትን ሚዲያ እየለመነ፣ በራቸውን እያንኳኳ መሆኑ ተነግሯል - በተለይ የተንቀሳቃሽ ምስልና (TV and YouTube) የሬዲዮን፡፡ ዛጎል እንደዘገበው ከሆነ እስካሁን ዕድሉን የሰጠው የለም፡፡ ተስፋዬ ከዚህ በፊት እየጻፈ የሚያወጣቸው መጣጥፎች እንደዱሮው ተነባቢነት ካጡ ሰነባብተዋል፡፡ የኦሮሞም ጽንፈኞችም እንደፈለጉ ሲጠቀሙበትና እሱም በተራው ሲጠቀምባቸው ቆይቶ አሁን ከእርሱ “የተሻሉ” አግኝተው ትተውታል፡፡ በርካታ እርሱን የሚተኩ … [Read more...] about ተስፋዬ ገ/አብ “የሚዲያ ያለህ” እያለ ነው!
የትግራይ ብሄርተኞች ዕብሪትና የጣናው ሞገድ ፈተና በመቀሌ!
“የትምክህት ፈረስ፣ ነፍጠኛ፣ የምኒልክ ርዝራዥ፣ አማራ አህያ፣ ገና መቶ ዓመት እንገዛሃለን፣ …” የመቀሌ ከነማ ደጋፊዎች ጭፈራ “የሌባ አይነ ደረቅ መልሶ ልብ ያደርቅ” የባህርዳር ከነማ ደጋፊዎች የመልስ ጭፈራ የመጨረሻው መጀመሪያ ይሆን? ያስፈራል! በኢትዮጵያ እግር ኳስ ውድድር ከፕሪሚየር ሊጉ ጨዋታዎች ቀጥሎ የከፍተኛ ሊግ ጨዋታዎች የተለየ ትኩረት ይስባሉ። የከፍተኛ ሊግ ጨዋታዎች ወደ ፕሪሚየርሊግ ለማደግ የሚደረጉ ፍልሚያዎች በመሆናቸው የተመልካቾችን ቀልብ ይስባሉ። የከፍተኛ ሊግ ጨዋታዎች ምድብ “ሀ” ላይ የተደለደሉት ክለቦች በወጣላቸው መርሐ-ግብር መሰረት ግንቦት 5 ቀን 2009 ዓም በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ጨዋታቸውን አድርገዋል። የዚህ ውድድር ተሳታፊ የሆኑት መቀሌ ከነማ እና ባህርዳር ከነማ (የጣናው ሞገድ) በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስ ግቢ (FB campus) … [Read more...] about የትግራይ ብሄርተኞች ዕብሪትና የጣናው ሞገድ ፈተና በመቀሌ!
የኮሌራው ምሥጢር! የቴድሮስ “የጥቅምት ዱብ ዕዳ”?
በህወሃት/ኢህአዴግ ከፍተኛ የገንዘብ ድጎማና ድጋፍ ለዓለም የጤና ጥበቃ ድርጅት ዳይሬክተርነት የሚወዳደረው ቴድሮስ አድሃኖም የመመረጡ ጉዳይ አደጋ ገጥሞታል፡፡ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር በነበረበት ወቅት ሦስት የኮሌራ ወረርሽኞች በምሥጢር እንዲያዙ ማድረጉ ለዳይሬክተርነት እንዳይበቃ ያደርገዋል ተብሏል፡፡ እንደ አሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ይህ ጉዳይ የቴድሮስ “የጥቅምት ዱብ ዕዳ” ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል፡፡ ዘ ኒው ዮርክ ታይምስ ሜይ 13፤2017 ዓም “የዓለም ጤና ጥበቃ ድርጅትን ለመምራት የሚወዳደረው እጩ ወረርሽኝ በመደበቅ ተከሰሰ” በሚል ርዕስ ባስነበበው ዜና የቴድሮስን የመመረጥ ተስፋ ስለሚያጨልመው የኮሌራ ወረርሽኝ ምሥጢር በዝርዝር አትቷል፡፡ በያዝነው የግንቦት ወር (ከሜይ 22፣ 2017) ጀምሮ በጄኔቫ በሚካሄደው የአንድ ሳምንት ስብሰባ ድርጅቱን ለመምራት ከሚወዳደሩት ሦስት … [Read more...] about የኮሌራው ምሥጢር! የቴድሮስ “የጥቅምት ዱብ ዕዳ”?
እንባ ካለ አሁን እናልቅስ!! ሊታመን ባይችልም አማኑኤል ሆስፒታል እንዲህ እየሆነ ነው!
“ቅባትና ደረቅ” በአማኑኤል የአዕምሮ ህክምና ሆስፒታል ታካሚዎች እንደ ደረጃ መዳቢ የተሰጠ ስም ነው። ታሪኩ ዘግናኝ፣ ኅሊናን የሚፈትን፣ ወዴት እያመራን እንደሆነ ግራ የሚያጋባ፣ መፈጠርን የሚያስጠላ፣ ሲሰሙት ግራ የሆነ፣ ቃላት ሊገልጹት የማይችል የክሽፈታችን ሁሉ ከሽፈት ነው። አማኑኤል ሆስፒታል ተኝቶ ለመታከም አርባ ሺህ ብር እንደሚከፈል ከመስማት በላይ ዘግናኝ ጉዳይ የለም። ጎልጉል ባሰባሰበው መረጃ ሌሎችም ጉዳዮች አሉ። በአማኑኤል ሆስፒታል ሴት የአዕምሮ ህመምተኞች መደፈራቸውን፣ ሲያረግዙ ጽንስ የሚቋረጥበት ክሊኒክ በውስጥ በተደረገ ስምምነት ይሰጥ እንደነበር ይፋ በተሰማ ጊዜ ጫጫታ ተሰምቶ ነበር። ጉዳዩን በወቅቱ ይፋ ያደረጉት አንድ የሆስፒታሉ ነርስ ነበሩ። ዛሬ ያ ግፍ ተመርምሮ መልስ ሳያገኝ ተጨማሪ ጉድ እየሰማን ነው። የሟቹ መለስ ዜናዊ ባለቤት የበላይ ጠባቂ ሆና ስትመራው … [Read more...] about እንባ ካለ አሁን እናልቅስ!! ሊታመን ባይችልም አማኑኤል ሆስፒታል እንዲህ እየሆነ ነው!










