ጉዳዩ በህወሓት ዘንድ መጠነኛ መከፋፈል ፈጥሯል “ኃይለማርያም ደሳለኝ የመስዋዕት በግ?” ሲሉ የመረጃው ሰዎች አዲሱን ዜና ይጀምራሉ። የጎልጉል ታማኝ መረጃ አቅራቢዎች በኦሮሚያ ከአሁን በኋላ የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ኃይል - ህወሓት ዕድል ፈንታ እንደሌለው ማመኑን ይጠቁማሉ። የኦሮሞ ጥያቄ የወንበር መሆኑን ህወሃት እንዳመነና ይህንኑ እምነቱን ተግባራዊ ለማድረግ መነሳቱን ለ“ወዳጆቹ”፣ ጌቶቹና አሳዳሪዎቹ ማሳወቁንም ይጠቁማሉ። በሌላ ወገን ደግሞ ይኸው ሁኔታ በህወሓት ውስጥ መጠነኛ መከፋፈልን እንደፈጠረ ይነገራል። እንደዜናው ሰዎች ከሆነ ህወሓት “የወለደውን፣ ያሳደገውንና፣ የሾመውን” ካድሬ ኢትዮጵያን እንዲመራ አጭቶታል። መረጃው ጎልጉል ካነጋገራቸው የተለያዩ ወገኖች በአሉታዊና በአዎንታዊ መልኩ አስተያየት ቢሰጥበትም ለማ መገርሳ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲሆንና የኦሮሞ … [Read more...] about ህወሓት የኦህዴድን የበላይነት በመቀበል ኦሮሞ ጠ/ሚኒስትር ሊሾም ነው
Full Width Top
“ሁሉንም ፈንቅል HR 128ን አምክን” – በሶማሊያ ዕልቂት የህወሓት ሥውር እጅ?
ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ /ህወሓት/ የተነሳበትን ዓላማ ለማሳካት የማይፈነቅለው ድንጋይ የለም የሚለው አስተያየት አሁን አሁን አከራካሪ ሊሆን አይችልም። በብዥታ ውስጥ የነበሩት እንኳን አሁን “ምን እየሆነ ነው” በሚል ራሳቸውን እየጠየቁ ያለአስረጂ ምላሹን እያገኙ ህወሓትን በጥርጣሬ የሚያዩበትን መነጽር አውልቀዋል። ይህ እንግዲህ በውጪውም ዓለም ጭምር እየሆነ ነው። በአስገንጣይነትና በተገንጣይነት ሲርመጠመጥ የነበረው ህወሓት ባላሰበው መልኩ፣ በህልሙም አስቦት የማያውቀውን፤ የአገር መሪነት ያስረከቡት “ቀጣሪዎች” ሳይቀሩ አሁን አሁን ፊት ለፊት “አናምንህም” ባይሉትም፣ ዙሪያውን እየዞሩትና እያዞሩበት ይገኛል። ብዙ ምልክቶች አሉ። አንደበታቸውን የከፈቱና “ዋ” የሚሉም እየተነሱ ነው። ከየአቅጣጫው የሚነሳውን ይህ ከላይ ጨምቀን ያቀረብነውን ጉዳይ የሚያጠናክር መረጃ ጎልጉል … [Read more...] about “ሁሉንም ፈንቅል HR 128ን አምክን” – በሶማሊያ ዕልቂት የህወሓት ሥውር እጅ?
የሴናተር ኢንሆፍ ህወሓትን የመታደግ ዘመቻ ቀጥሏል!
ጉብኝቱ “ከHR 128 … ውጪ ሊሆን አይችልም” ኦባንግ የአሜሪካ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት አባል ሴናተር ጀምስ ኢንሆፍ ህወሓት/ኢህአዴግን ለመታደግ በአዲስ አበባ ላይ ከኢህአዴግ ሹሞች ጋር መከሩ። አቶ ኦባንግ ሜቶ ጉብኝቱ “ከHR 128 የተያያዘ ነው፤ ከዚህ ውጪ ሊሆን አይችልም” ይላሉ። በያዝነው የአውሮጳውያን ዓመት (2017) መጀመሪያ አካባቢ ወደ ኢትዮጵያ ሄደው የነበሩት ሴናተር ጀምስ ኢንሆፍ ከከፍተኛ የሕወሓት/ኢህአዴግ ሹሞች ጋር መነጋገራቸው ህወሓት የሚቆጣጠረው የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዘግቧል። የዜና አገልግሎቱ ውይይቱ መቼ እንደተደረገ ባይዘግብም ዜናውን ግን ጥቅምት 2/2010 በማለት ነው ያተተው። በውይይቱ ላይ ሴናተሩ ሌሎች የአሜሪካ እንደራሴዎችንና የሕግ መወሰኛ ምክርቤት አባላትን በመምራት እንደተገኙ ዜናው አስታውቋል። የውይይቱ ትኩረትም “በሠላምና ጸጥታ … [Read more...] about የሴናተር ኢንሆፍ ህወሓትን የመታደግ ዘመቻ ቀጥሏል!
አባዱላ ወደ ጨፌ ወይስ ወደ ሸቤ?
የሰበር ዜና ልክፍት የተጠናወተው የዘመኑ “ሚዲያ” የአባዱላን ከአፈጉባኤነት መልቀቅ በሰበር ዜናነት ማናፈሱ ቆም ብሎ ላየው ራስን ትዝብት ላይ የሚጥል ነው። የአባዱላ መልቀቂያ ማስገባት “ምስጢር” በቅርቡ የሚለይለት ቢሆንም በህወሓት ተለክቶና ተጠፍጥፎ የተሠራ ድርጅትና ስብዕና ያለው ለዚህ ዓይነት የሞራል ልዕልና ይደርሳል ብሎ መገመት ህወሓትን ካለማወቅ ወይም ራስን ከመሳት የሚመነጭ ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም። በበርካታ የሙስና ተግባራትና ህይወት ማጥፋት አለበት እየተባለ የሚነገርለት አባዱላ ከቀድሞው የኢትዮጵያ ሠራዊት ተማርኮ በሻዕቢያ ፈቃድና በህወሓት ፈጣሪነት አዲስ ስብዕና ተሰጥቶት ኦህዴድ የሚባል የጀመረ መሆኑ የሚዘነጋ አይደለም። ይህ ስብዕናው ህወሓት በህንፍሽፍሽ ልትበታተን ስትል የኦሮሞውን ክንፍ ይዞ መለስን የታደገ በመሆኑ ባለውለታነቱ ለማን እንደሆነ በድጋሚ ያስመሰከረ … [Read more...] about አባዱላ ወደ ጨፌ ወይስ ወደ ሸቤ?
የአባዱላ መጨረሻ
አቶ አባዱላ ገመዳ ከሁለት ሳምንታት በፊት ለዓመታት ከተቀመጡበት የአፈ ጉባኤነት መንበር ላይ ለመልቀቅ መጠየቃቸው ከባለፈው ሳምንት ማብቂያ ጀምሮ ዋነኛ ርዕስ ሆኖ ዘልቋል። ከፓርቲያቸው ኢህአዴግ/ኦህዴድ እንዲሁም ከእራሳቸው አንደበት ዜናውን ለማስተባበል የተሰማ ነገር ስለሌለ ሥልጣን ለመልቀቅ መጠየቃቸው ሃቅ ወደ መሆኑ ያመዘነ በነበረበት ጊዜ ጥያቄ የማቅረባቸውን እውነትነት እራሳቸው አረጋጥጠዋል። ወታደራዊው መንግሥት አባዱላ መስራችና አባል የሆኑበት ኦህዴድ በሚገኝበት ኢህአዴግ ተሸንፎ ከተወገደበት ጊዜ አንስቶ በተለያዩ የወታደራዊና የሲቪል ሃላፊነቶች ላይ ቆይተዋል። አባዱላ ከትግል በኋላ ፓርቲውን የተቀላቀሉ በርካታ አመራሮች ባሉበት ኦህዴድ ውስጥ ተቀባይነት ካላቸው ቀደምት ጥቂት መስራች አባላት ውስጥ ቀዳሚው እንደሆኑ ይነገራል። ለዚህም ይመስላል በርካታ የኦህዴድ አባላትና … [Read more...] about የአባዱላ መጨረሻ
“እስከማውቀው አባዱላ በዚህ መልኩ አይዳፈሩም”፤ አባዱላ እና የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ እዉነት
በኦህዴድ አባላት ዘንድ “ጃርሳው” የሚል መጠሪያ ያላቸው አባዱላ ገመዳ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ከሰለቻቸው ከፍተኛ አመራሮች መካከል በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሱ ናቸው። "ንፍሮ እየበላሁ ከተራው ህዝብ ጋር መኖር ናፈቀኝ፤ ወደ ቤተ ክርስቲያን በነጻነት የምሄድበት ቀን መቼ ነው?" በማለት ለሚቀርቧቸው ሲናገሩ መቆየታቸውን በቅርብ የሚያውቋቸው ምስክርነት ይሰጣሉ። የጦር ሰራዊት መለዮ አውልቀው መከላከያ ሚኒስትር፣ ከዛም የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ሆነው የተሰየሙት አባዱላ፣ በኢህአዴግ አመራሮች የማይደፈሩ ቦታዎች ድረስ ዘልቀው በመግባት ከህዝብ ጋር በተደጋጋሚ የመከሩ፣ ኢህአዴግ ወደ ስልጣን ከመጣ ጀምሮ ኦሮሚያ ላይየተሻለ ተቀባይነት ያገኙ ናቸው። በአቶ ደራራ ሞት እጃቸው አለበት በሚል የሚከሷቸው ያሉትን ያህል፣ በባህሪያቸው ሩህሩህ እንደሆኑ በቅርብ የሚያውቋቸው ይናገራሉ። አርሲና ባሌን … [Read more...] about “እስከማውቀው አባዱላ በዚህ መልኩ አይዳፈሩም”፤ አባዱላ እና የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ እዉነት
HR 128/SR 168 ጸሐይ እየጠለቀችበት ነው!
ለኢትዮጵውያን ታላቅ ተስፋ ይዞ የተነሳው HR 128/SR 168 በሞት አፋፍ ላይ እንደሚገኘ ተነገረ። የህወሃት/ኢህአዴግን ህልውና በማያፈናፍን አጣብቂኝ ውስጥ እንደሚከት ብዙ የተባለለት ይህ ረቂቅ ሕግ ወደ ሕግ መወሰኛ ምክርቤት ቀርቦ ድምጽ ከማግኘቱ በፊት ጊዜውን ጠብቆ እንዲሞት የማቀዛቀዝ ተግባር እየተፈጸመበት ነው። ኢትዮጵያውያን ተባብረው በመታገል ይህ ዕድል እንዳያመልጣቸው ማድረግ እንዳለባቸው ማሳሰቢያ ተሰጠ። ሐምሌ 20፤ 2009ዓም (7/27/2017) የህወሃት/ኢህአዴግን የሰብዓዊ መብቶች ይዞታና አጠቃላይ አስተዳደርን የሚወቅስ የህግ ረቂቅ በዩናይትድ ስቴትስ የሕግ መምሪያ የውጭ ጉዳዮች ኮሚቴ ፊት ቀርቦ በሙሉ ስምምነት ማለፉ ይታወሳል። ከውሳኔው በላይ የአሜሪካ ወዳጅ በመሆን ሕዝብን ለመከራና ስቃይ ሲዳርግ የኖረው የኢህአዴግ አገዛዝ በአሻባሪነቱ ከሚወገዘው ሒዝቦላ እና ከሰሜን … [Read more...] about HR 128/SR 168 ጸሐይ እየጠለቀችበት ነው!
እምቢተኝነት በተግባር!
“ሕዝቡን ካፈንከው እና ከመቃወም ሌላ አማራጭ ካሳጣኸው ይፈነዳል፤ ወጣቱ በሙሉ ዓመጽ ላይ ነው፤ ትውልድ አምጿል”። የኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጠኛ JEFFREY GETTLEMAN በኢትዮጵያ ያለው ወቅታዊ ሁኔታ በተነተነበት ጽሁፍ ላይ ከተናገረው። ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ። ዛሬ በተከበረው የመስቀል በዓል ላይ የህወሓትን ማስፈራሪያና ዛቻ ከምንም ባለመቁጠር የውቅሮ፣ ዓዲግራት፣ መቀሌ፣ ጎንደር፣ ደሴና ሌሎች አካባቢዎች ህዝብ “ባለኮከቡን ባንዲራ አይወክለኝም” በማለት ኮከብ አልባውን ሠንቀድ ዓላማ ይዞ በመውጣት እምቢተኝነቱን አድፍረት አሳይቷል። ሃይለኪሮስ ታፈረ (Hailekiros Tafere) በፌስቡክ ገጹ የዘገበውን አስመልክቶ አምዶን ገብረሥላሴ ይህንን ብሏል፤ “ፖሊስ "ኮከብ የሌለው ባንዴራ ዳሜራ ሸፍናቹሃል" በሚል ሰበብ ዛሬ መስቀል በዓል እያከበረ የነበረው የውቅሮ … [Read more...] about እምቢተኝነት በተግባር!
የህወሃት አጀንዳ + የዘር ፖለቲካ + የሜንጫ ፖለቲካ – መጨረሻው ተያይዞ …
የኢትዮጵያ ህወሓት ሰራሹ “ፌደራሊዝም” ወደ ተፈራው ቀውስ እየተንደረደረ መሆኑንን የሚያሳዩ የዜና ዘገባዎች የተሰሙት ገና ከጅምሩ ነበር። በርካታ ባለሙያዎችና የተቀናቃኝ ፖለቲካ መሪዎች በተደጋጋሚ ስጋታቸውን ቢገልጹም ተቀባይነት ሊያገኙ ባለመቻላቸው የጎሣና የብሄርተኛነት በሽታ እያደር ኢትዮጵያን እየበላት አሁን ያለችበት ደረጃ አድርሷታል። ችግሩ አለመስማትና አለማወቅ ብቻ ሳይሆን ዓላማ ያለው፣ በቅጥረኝነት አገሪቱን የማፈራረስ ተልዕኮ የማሳካት ጉዳይ በመሆኑ የመከሩ፣ የዘከሩ፣ ያስጠነቀቁ፣ ስጋታቸውን አደባባይ ያወጡ ዜጎች ወንድ ሴት ሳይባል ተፈጅተዋል። አገሪቱ ምትክ የሌላቸውን ልጆቿን እንድትከስር ተደርጋለች። ግድያውና አፈናው ብቻ ሳይሆን መላውን የአገሪቱን ህዝብ እርስ በእርስ ጎሣና ጎጥ ለይቶ እንዲናከስ እየተወተወተና እየተገፋ አገሪቱ ቆዳዋ በልጆቿ ደም እንዲለወስ ሆኗል። ዛሬ … [Read more...] about የህወሃት አጀንዳ + የዘር ፖለቲካ + የሜንጫ ፖለቲካ – መጨረሻው ተያይዞ …
የህወሓት ፕሮግራም፤ የመለስ ሌጋሲ – ዜጎችን ማፈናቀል፤ ማጋደል!
ገና ከመነሻው በበረሃ ያወጣው ፕሮግራሙ በግልጽ እንደሚያመለክተው የህወሓት ዋንኛ ዓላማ ኢትዮጵያን አዳክሞና በጎሣ ከፋፍሎ ትግራይን ታላቅ በማድረግ ሪፑብሊክ መመሥረት ነው። ባለፉት 26 ዓመታት ይህንን ለማሳካት በኢትዮጵያ ውስጥ ያልፈነቀለው የጎሳ ድንጋይ የለም፤ ያላጋጨው ሕዝብ፤ ያላጋደለው ወገን የለም፤ ትግራይን ሳይጨምር! ሞት እንደ ቡሽ ክዳን ሳያስበው አስፈነጠረው እንጂ የመለስና ዋናዎቹ የህወሓት መሥራቾች ዕቅድ ይህንኑ ለማሳካት እንደሆነ ሰሞኑን በተከታታይ በምናትመው የአቶ ገብረመድኅን ጽሁፍ በግልጽ የተቀመጠ ሐቅ ነው። የወቅቱ የፍጅት ዓላማ ደግሞ ኦሮሞን ከሶማሊ ወገኖቹ ጋር በማጋጨት የአገዛዝ ዘመኑን ማራዘም፤ ሁለቱን ጎሣዎች በማይረሳ ቂምና ጥላቻ ውስጥ ማስገባት፤ ይህንንም እስካሁን በሌሎቹ ጎሣዎች መካከል ከፈጠረው ጥላቻና ቁርሾ ጋር ተዳምሮ የኢትዮጵያን ኅልውና አጥፍቶ … [Read more...] about የህወሓት ፕሮግራም፤ የመለስ ሌጋሲ – ዜጎችን ማፈናቀል፤ ማጋደል!










