እጅግ መረን በለቀቀ ሁኔታ የኢትዮጵያን የመንግሥት ሥልጣን ተቆጣጥሮ የነበረው የተገንጣይ ወንበዴዎች ቡድን እና በዚሁ የተገንጣይ ቡድን ስም አገር ሲገዛ የኖረው ትህነግ/ህወሓት በአሁኑ ወቅት በሚኒስትሮች ም/ቤት ያለው ኅልውና ሊከሰም ጥቂት ነው የቀረው። የጠ/ሚ/ር፣ የውጭ ጉዳይ፣ የመከላከያ (ኤታ ማዦር ሹም)፣ የማስታወቂያ (በኋላ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን የተባለው) ወዘተ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶችን በብቸኝነትና በማንአለብኝነት ለበርካታ ዓመታት ሲቆጣጠር የነበረውን የተገንጣይ ቡድን በሚኒስትሮች ም/ቤት ትወክለው ነበረችው ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሔር ከሥልጣኗ ተወግዳለች። የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የላከውን መረጃ የኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ አማርኛ ልሳን በፌስቡክ አረጋግጧል። የህወሓት የፖሊትቢሮ አባልና የደብረጽዮን ምክትል የሆነችው ፈትለወርቅ (ሳሞራ የኑስ ባወጣላት የበረሃ ስሟ … [Read more...] about በኢትዮጵያ የሚኒስትሮች ም/ቤት የህወሓት ኅልውና እየከሰመ ነው
Right Column
ዜግነትን መቀየር በተመለከተ አንዳንድ ነጥቦች
ባይሳ ዋቅ-ወያ ከጥቂት ወራት በፊት ስለ አንዳንድ የውጭ አገር ዜግነት ከነበራቸውና በዶ/ር ዓቢይ ጥሪ መሠረት ወደ ኢትዮጵያ ከተመለሱ በኋላ የኢትዮጵያ ዜጋ ባለመሆናቸው ያጋጠማቸውን አስመልክቼ አንድ ጽሁፍ በተለያዩ ሚዲያዎች አሳትሜ ነበር፡፡ ዛሬም ጥያቄው ወቅታዊ የሆነና ከሕግ አንጻር ትንታኔና ገለጻ እንደሚያስፈልገው ስለተረዳሁ በፊተኛው ጽሁፌ ላይ ተመርኩዤ ይህንን ጽሁፍ ለማቅረብ ወሰንኩ፡፡ ዓላማዬም ዜግነትን የመሰለ ለማንኛውም ሰብዓዊ መብት ቁልፍ የሆነውን ጉዳይ በቀላሉ እንዳናይና ይህንን በሕይወታችን ወሳኝ የሆነውን “ዜግነትን የመቀየር” እርምጃ ከመውሰዳችን በፊት ከሕግ አንጻር ማድረግ ያለብንና መከተል ያለብንን ሂደት ችግሩ ላጋጠማቸውና ለወደፊትም ተመሳሳይ እርምጃ ለመውሰድ ለሚፈልጉ ትውልደ ኢትዮጵያውያን አስፈላጊውን ሕጋዊ ምክር ለመስጠት ነው፡፡ ወደ ኢትዮጵያ … [Read more...] about ዜግነትን መቀየር በተመለከተ አንዳንድ ነጥቦች
እየተስተዋለ – ለኢትዮ 360 ተንታኞች!
አምስተርዳም (በቪቫ ምኒልክ) ለዛሬው ጽሁፌ መነሻ የሆነኝ በኢትዮ 360 በሰሞኑ የኢትዮጵያን መከላከያና ደህንነት ክፍል አስመልክቶ የቀረበው ውይይት እጅግ ስለ አስደነገጠኝ ነው። ከውይይት ጭብጥ እንደተረዳሁትም ከመከላከያና የደህንነት መስሪያቤት ከፍተኛ አመራሮች በደረሰን መረጃ መሰረት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አገራችንን ለአረቦች አሳልፎ በመስጠት የእስልምና ሐገራት አባል ለማድረግ እየሰራ ነው የሚልና የምእራብ እዝን ወደ ወለጋ ያዛወረው የኦሮሞን ልዩ ሃይል ለማደራጀት እንዲመቸው ነዉ የሚል በጥላቻ ላይ ብቻ የተመሰረተው ክሳችሁን መሉ ለሙሉ የምቃውምበትን ነጥብ ከዚህ በታች በአጭሩ ዘርዝር አድርጌ ለማስተላለፍ እሞክራለሁ። የውይይት ሃሳባችሁ መነሻ ያደረጋችሁት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ ከሰይፉ ጋር ያደረጉት ዉይይት ላይ ስለ አረብ አገራት ለኢትዮጵያ በሚሰጡት የገንዘብ … [Read more...] about እየተስተዋለ – ለኢትዮ 360 ተንታኞች!
የወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ለጃዋር
ሕግን በማስከበር ስመጥር የሆኑትና ለዚህም የቀድሞው ታሪካቸው የሚመሰክርላቸው የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ለጃዋር መሃመድ የማስጠንቀቂና የማብራሪያ ደብዳቤ ሊልኩ መሆኑን ታወቀ። ጃዋር ለደብዳቤው በቂ ምላሽ ካልሰጠ ከምርጫ ጋር በተያያዘ የሚያደርጋቸው የፖለቲካ ተግባራት በሙሉ ሊታገዱ እንደሚችሉ አብሮ ለመረዳት ተችሏል። የጎልጉል የአዲስ አበባ ዘጋቢ በላከው መረጃ መሠረት ምርጫ ቦርድ ለጃዋር ለመላክ ያረቀቀው ደብዳቤ ጃዋር በየትኛው የሕግ አግባብ ኢትዮጵያዊ ዜግነት ሳይኖረው በኢትዮጵያ የምርጫ ሒደትና የፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ ሊገባ እንደቻለ ማስረጃና ማብራሪያ በቀነ ገደብ እንዲሰጥ የሚጠይቅ ነው። በምርጫ ቦርድ ውስጥ የሚገኙ የጃዋር ሰዎች ደብዳቤው ሊላክለት መሆኑን ያስታወቁት ሲሆን ጃዋርም ደብዳቤው ወጪ ከመደረጉ በፊት የቦርዱ ሰብሳቢዋን … [Read more...] about የወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ለጃዋር




