ወልድያ የበቀል ዱላ አትፎባታል። ግድያና አፈናው ለሶስተኛ ቀን ቀጥሎ ውሏል። የወያኔ ቅልብ ጦር የጅምላ ግድያውን የፈጸመው ከዚህ ቀደም በወልድያ ስታድየም የተፈጠረውን ክስተት ለመበቀል መሆኑን ብዙዎች ይስማማሉ። ከልምድ እንዳየነው ህወሃት ሕዝብን መጨፍጨፍ ሲፈልግ - አጋዚ ወታደሮቹን ሕዝብ በሚሰበሰብበት ስፍራ ያሰማራና በመተንኮስ እንዲነሳሱ ያደርጋል። ብሶቱ ከቅጥ ያለፈበት ሕዝብ ድምጹን ማሰማት ሲጀምር ህወሃት የበቀል ስራውን ይሰራል። ከዓመት በፊት የእሬቻ በዓል ላይ የሆነው ይኸው ነበር። በወልድያው ጭፍጨፋም ያየነው ይህንኑ ነው። የቴዲ አፍሮ የባህርዳር ኮንሰርት ላይ አጋዚ ቢኖር ኖሮ እልቂቱ አይቀሬ ነበር። የዘንድሮው እሬቻ በዓል ከአጋዚ ነጻ ቢሆን እንደ አምናው ወገን ይገደል ነበር። እለተ ቅዳሜ፣ ጥር 12 ቀን 2010 ዓ.ም. የጥምቀት በዓልን ለማክበር የታደመ ሕዝብ … [Read more...] about ወልድያ የጦር ቀጠና ሆናለች – ትንቅንቁ ቀጥሏል!
Politics
“ቄሮ አልሸባብ” ነው – ህወሓት!
“ስድስት ሚሊዮን ወጣት በጠላትነት ፈርጀህ ማንን ልታስተዳድር ነው?” ለማ መገርሳ ህወሓት/ኢህአዴግ በኢትዮጵ የተለያዩ ክፍሎች በተለይም በምሥራቅ ሐረርጌ “ቄሮ” በመባል የሚታወቅ ሕገወጥ እንቅስቃሴ እመረምራለሁ፤ ለፍርድ አቀርባለሁ ብሎ ዝቷል። “አመራሩ ብቃት የለውም” በማለት ራሱን የገመገመው ህወሓት/ኢህአዴግ ብቃት አልባነቱን ተገንዝቦ ራሱን ከሥልጣን ማግለል ሲገባው አሁንም የማሰርና የማሰቃየት ግፉን በስፋት ለመቀጠል በዕቅድ ለመቀንቀሳቀስ ማሰቡን ነው በዚህ ዜና የገለጸው። የኢትዮጵያ ወጣቶችን በሥራ በማሰማራት ለአገር እንዲጠቅሙ ከማድረግ ይልቅ “አደገኛ ቦዘኔ” በማለት ሲፈርጅና ሲስር የነበረው ህወሓት አሁን ደግሞ በኦሮሞ ወጣቶች “ቄሮ” ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ለመሰንዘር ጎራዴውን እየሳለ ነው። ግፉ የበዛባቸው ወጣቶች ታላቁ ሩጫ በተካሄደበት ባንድ ወቅት ላይ “አደገኛ ቦዘኔ … [Read more...] about “ቄሮ አልሸባብ” ነው – ህወሓት!
“አመራሩ ከሽፏል” ለማ
ታዲያ ሁላችሁም ለምን ከሥልጣን አትወርዱም? "ለአመጽ የግብረ መልስ የሚሰጥ አመራር እንጂ ለችግሮች ቀድሞ መፍትሄ የሚሰጥ አመራር አይደለም"፤ "አመራሩ ህዝቡ ከሚጠብቀው በታች ነው"፤ "አመራሩ ከሽፏል"፤ የማሸማቀቅና የማስፈራራት ተግባር ነው በፓርቲው ውስጥ ያለው፤ ተመሳሳይ ዓይነት ነገር ወደ ሕዝቡ ሰርጾዋል፤ ወዘተ በማለት "በድፍረት" የተናገረው የኦህዴዱ ለማ መገርሳ እንደዚህ ብቃት የሌለውን አመራር ቢያንስ "ሥልጣኑን መልቀቅ ይገባዋል" ሳይል ወይም ራሱ ሁኔታው የማይስተካከል ከሆነ ሥልጣኑን እንደሚለቅ ምንም ፍንጭ ሳይሰጥ ንግግሩን አብቅቷል። ህወሓት/ኢህ አዴግ እንደ ድርጅት ከሽፏል! ይህ የተመሰከረው ደግሞ በራሱ በአመራሩ ነው። እስካሁን በሥልጣን ለምን እንደቆዩ እና ወደፊትም ለመቆየት ለምን እንዳሰቡ ግልጽ ቢያደርጉ የተሻለ ነው። መለስም "እስከ እንጥላችን ገምተናል" እያለ … [Read more...] about “አመራሩ ከሽፏል” ለማ
ህወሓት/ኢህአዴግ “አሸባሪ” እስረኞችን እፈታለሁ አለ
ላለፉት በርካታ ዓመታት በየአደባባዩ "በኢትዮጵያ ውስጥ አንድም የፖለቲካ እስረኛ የለም" ሲል የነበረው ህወሓት/ኢህአዴግ ዛሬ በኃይለማርያም አማካኝነት "እስረኞችን እፈታለሁ፥ ማዕከላዊን እዘጋለሁ" ብሏል። ባለፉት ዓመታት በግፍ የታሰሩት በሙሉ የተከሰሱት በአሸባሪነት መሆኑ የሚታወቅ ነው። ይህ መግለጫ በራሱ ህወሓት/ኢህአዴግ ሲዋሽ እንደነበር የሚያሳይ ነው ወይም ይቺ ጊዜ መግዣ የህወሓት ጨዋታ ነች። ለሁሉም በመቆየት የሚታይ ነው። የእኛ አቋም ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በፖለቲካ አመለካከቱ መታሰር የለበትም፥ በግፍ የታሰሩት ሁሉም የፖለቲካ እና የኅሊና እሥረኞች ህወሓት/ኢህአዴግ ይቅርታ እየጠየቀ ካሣ ከፍሎ በነጻ ይልቀቃቸው ነው። ጎልጉል! … [Read more...] about ህወሓት/ኢህአዴግ “አሸባሪ” እስረኞችን እፈታለሁ አለ
ኢህአዴግና እነለማ ከ“ምን ይዤ ልመለስ?” እስከ “መግለጫ” ማጽደቅ!
ህወሓት የሚዘውረው ኢህአዴግ ከሁለት ሳምንታት በላይ ስብሰባ አድርጎ “መግለጫ” ያለውን “ቀጭን ትዕዛዝ” በማውጣት ተጠናቋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በለውጥ አራማጅነት ሲጠቀሱ የነበሩት እነለማ መገርሳ “መግለጫውን” አብረው አጽድቀው ወጥተዋል። “የጨለንቆን ፍጅት የፈጸመው ማነው?” የሚለውም ደፋር አጀንዳ አብሮ የሞተ ጉዳይ ሆኗል። “ምን ይዤ (ወደ ሕዝቤ) ልመለስ?” በማለት ወደስብሰባው የገቡት ኦህዴድና ብአዴን “የተቀናጁ ተጨማሪ እርምጃዎች” እወስዳለሁ (መግደሌን እቀጥላለሁ) ለሚለው የህወሓት “መግለጫ” ይሁንታቸውን ሰጥተው ወጥተዋል። የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሓት) ከወር በላይ ስብሰባ በማድረግ የደቆሰውና የፈጨውን በተስፈኞቹ ብአዴንና ኦህዴድ ላይ በመድፋት በድንፋታ ኢህአዴግ የሚለውን የድርጅቱን ሥራ አስፈጻሚ መግለጫ በማውጣት መጠናቀቁ ከራሱ ከአገዛዙ የሚዲያ ተቋማት … [Read more...] about ኢህአዴግና እነለማ ከ“ምን ይዤ ልመለስ?” እስከ “መግለጫ” ማጽደቅ!
“አውሬውን አቁስለነዋል፤ ይህ ግን በቂ አይደለም” ለማ መገርሳ
“አውሬው ቆስሏል*። ቆስሎ ስላልተኛ፣ ማቁሰሉ ብቻ በቂ አይደለም። ተመልሶ እንዳይመጣ እርግጠኞች መሆን አለብን።" የሚለው ቃል የወጣው ከ"ጽንፈኛው ዲያስፖራ" ወይንም ከተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች አይደለም። ከአውሬው ጋር አጋር ሆኖ ከሚሰራ ድርጅት መሪ ነው። ያውም በገዥው ፓርቲ ልሳን። የ26 ዓመቱ ፖለቲካ እየተንከባለለ እዚህ ላይ ደርሷል። አንድ ሰው እውነትን በመናገሩ ጀርባው ተጠንቶ፣ ደሙ ተለክቶ፣ ግንባሩ ተገላልጦ፣ በሽብር በሚፈረጅባት ሃገር ውስጥ፣ ጥቂቶች የእድሜ-ልክ ፈራጅ ሆነው በተሰየሙበት ሃገር ይህ ተከሰት። እነ እስክንድር ነጋ፣ ተመስገን ደሳለኝ፣ አንዷለም አራጌ ከዚህ የባስ ነገር አልተናገሩም። በፍትህ ስም የሚቀለድባቸው እነ ፕ/ር መረራ ጉዲና እና በቀለ ገርባ ይህችን ያህል እንኳን አልተነፈሱም። መቀሌ ላይ በዝግ ስብሰባ፣ አዲስ አበባ ላይ በዝግ ስብሰባ፣ ፓርላማውም በዝግ … [Read more...] about “አውሬውን አቁስለነዋል፤ ይህ ግን በቂ አይደለም” ለማ መገርሳ
የገዱ አንዳርጋቸው ፈተና
በህወሓት ተመልምለውና ለሥልጣን በቅተው ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ “የለውጥ ኃይል” እየተባሉ ከሚወደሱት መካከል አንዱ የሆነው ገዱ አንዳርጋቸው ለምስክርነት መጥሪያ ተቆርጦለታል። ገዱና ሌሎች ህወሓት እንደ ጭቃ ጠፍጥፎ የሠራው ብአዴን አባላት የተጠሩት በነ ንግሥት ይርጋ ክስ በመከላከያ ምስክርነት ነው። ህዝባዊ ዓመጹ የተነሳው “በመልካም አስተዳደር ችግር” ምክንያት እንደነበር እነ ገዱ በተደጋጋሚ በየሚዲያው ሲናገሩ ቆይተዋል። ዓቃቤሕግ ደግሞ ክሱን የመሠረተው ሕዝባዊ ዓመጹን ከ“ሽብር” ጋር በማገናኘት ነው። በ“ለውጥ ኃይልነት” ሲወደስ የነበረው ገዱ አንዳርጋቸው ታማኝነቱ ለማን እንደሆነ በይፋ የሚያሳይበት ፈታኝ ወቅት ላይ የሚገኝ ሲሆን አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች “አንገቱ ላይ ያለውን ገመድ ለማጥበቅ በህወሓት የታቀደ ሤራ ነው” ብለውታል። በተለይ ሃይለማርያም ደሳለኝ እና ደመቀ መኮንን … [Read more...] about የገዱ አንዳርጋቸው ፈተና
“ዶክተሩ” ደብረጽዮን ምላሽ አለው
“… የአመራሩ ድክመት ድርጅቱን ጎድቷል፤ … የበላይ አመራሩ ሥራውን ሲገመግም ብዙ ጉድለት ተገኝቶበታል” በማለት ለፋና ቃለምልልስ የሰጠው አዲሱ የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር የወንበዴዎች ቡድን መሪ ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ነው። በበፊቱ አመራር ውስጥ ምክትል ሊቀመንበር የነበረው ደብረጽዮን፤ 35 ቀናት በፈጀውና ዋናው ችግር አመራሩ መሆኑን በገመገመው ስብሰባ መሠረት መባረር ሲገባው ይልቁንም ሊቀመንበር ሆኗል። Capella University ከተባለው የዲግሪ ወፍጮ ቤት “የዶክትሬት ዲግሪ” ተቀብሏል የሚባልለት ደብረጽዮን እንደ ቀድሞ አመራር “የበላይ አመራሩ ጉድለት ተገኝቶበታል” ካለው ድርጅት ራሱን ማግለል ሲገባው ራሱን በዓለምአቀፍ የአሻባሪነት የመረጃ ቋት ውስጥ የተመዘገበው ህወሓት ሊቀመንበር አድርጎ ራሱን ሾሟል። በከሁለት ቀናት በፊት “በጨለንቆ በተፈፅመው የጅምላ ግድያ … [Read more...] about “ዶክተሩ” ደብረጽዮን ምላሽ አለው
ኦህዴድ በህወሓት ላይ ላወጣው መግለጫ ሃይለማርያም ምላሽ ሠጠ
በጨለንቆ በተፈፅመው የጅምላ ግድያ በስተጀርባ ማን ነው ያለው ? የኢፌዲሪ ህገ-መንግስት አንቀፅ 87 (3) ስር የአገር መከላከያ ሰራዊት የአገርን ሉዓላዊነት ለማሰከበር ነው የተቋቋመው። በዚሁ ንዑስ አንቀፅ 4 እና 5 ስር የአገር መከላከያ ሰራዊት በማንኛውም ጊዜ ለህገመንግስቱ ታዛዥ በመሆን ለፖለቲካ ፓርቲዎች ውግንና ሳያሳይ ነፃ ሆኖ የአገር ደህንነት የመጠበቅ ስራውን እንደሚሰራ ይደነግጋል። ይሄው የመከላከያ ሰራዊቱ ከውጭ የሚመጣውን የአገሪቱን ጠላት ለመከላከል በአገሪቱ ብሄር ብሄረሰቦች የተገነባ ከተቋቋመለት አላማ ውጭ ታሪካዊ ስህተቶችን በህዝቦች ላይ ሲፈፅም ታይቷል። የህገ-መንግስቱ አንቀፅ 8 (1-5) ስር የአገሪቱ ህዝቦች ሉዓላዊነት አስመልክቶ የአገሪቱ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦና ህዝቦች የኢተዮጵያ ሉዓላዊ የስልጣን ባለቤት መሆናቸው ይደነግጋል። ይህ ህገ-መንግስት የአገሪቷ … [Read more...] about ኦህዴድ በህወሓት ላይ ላወጣው መግለጫ ሃይለማርያም ምላሽ ሠጠ
አልሰሙም አልታረሙም
እነሆ ራሳቸው በጠሩዋቸው ጉባዔዎችና ኮንፍረንሶች ላይ ሁሉ በተደጋጋሚ ተነግረዋል አልሰሙም፤ ተመክረዋልም አልታረሙም። እኒህም የኢትዮጵያ ገዢዎች የኢህአዴጋውያን አዛዦች የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር ህወሃታውያን ናቸው። ማስረጃ ቢባል ማርሻል መለስ ከመራው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ጉባዔ ጀምሮ እስከ ቅርብ ጊዜ የዘለቁት መሰል ጉባዔዎች ዋቢዎቻችን ናቸው(1)። እነሆም ህወሃታውያኑ በወጣትነት ዘመናቸው በሽፍትነትና ዘረኝነት እንደታበዩ ገድለው ዘርፈውና አጥፍተው በጎልማሳነታቸው ምኒልክ ቤተመንግሥትን በጠመንጃ ማረኩ። እነሆም በስተርጅና ዘመናቸው ባልገነቡት ቤተመንግሥት እየፏለሉ ከሽፍትነት የድውይ አስተሳሰባቸው፤ ከድኩም ባህሪያቸው፤ ከመሃይምነታቸው፤ ከመሰሪ ተፈጥሯቸው፤ ከናዚስት ዕምነታቸው ይታረሙና ይፀዱ ዘንድ ግን ከቶም አልተቻላቸውም። እነሆም በኢትዮጵያ መንበር ላይ ተኮፍሰው … [Read more...] about አልሰሙም አልታረሙም










