ከአራት ቀናት በፊት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አህመድ ለ“ካቢኔያቸው” ወደ ሁለት ሰዓት የሚፈጅ ሥልጠና ሰጥተዋል። ይህ በሥነአመራር ጥበብ ላይ ያተኮረው የጠ/ሚ/ሩ ገለጻ በኮሌጅ ደረጃ የሚሰጥ ትምህርት ተጨምቆ የቀረበበት ነው። በካቢኔ አባልነት የተቀመጡት ግለሰቦች አንዳንዶቹ በመደነቅ፣ ሌሎቹ በመገረም፣ አፋቸውን በመያዝ አንዳንዶች በመናደድ ሌሎች ደግሞ አልገባ ብሏቸው ግራ በመጋባት ሲያደምጡ ተስተውለዋል። በርካታዎቹ ከየ“ዲግሪ ወፍጮ ቤቱ” የከፍተኛ ትምህርት ምሩቃን ተብለው ከሚችሉት በላይ ዲግሪ ተሸክመው የሚንገዳገዱ በመሆናቸው የጠቅላዩ ንግግር አቅማቸውን የማይመጥን ሆኖ እንዳገኙት ከፊታቸው ላይ የሚታይ ነበር። ምክንያቱም እነርሱን ወደዚህ ዓይነት ማዕረግ እንዲመጡ ያደረጋቸው ራሱ ከዲግሪ ወፍጮ ቤቶቹ በአንዱ በፖሰታ ቤት ዲግሪውን የተቀበለው መለስ ዜናዊ ነበር። መለስ አካባቢውን … [Read more...] about ጠ/ሚ/ሩና ውቅር የማይገባው “የዲግሪ ወፍጮ” ምሩቃን ካቢኔ
Politics
ጠ/ሚ/ር ዓቢይ እና ህወሓቶች፡ ለይቶ ማሰር ወይስ አብሮ መሥራት?
ኢህአዴግ ውስጥ ስለተደረገው አመራር ለውጥና ለውጡ የተካሄደበትን ሁኔታ አስመልክቶ የተለያዩ ሃሳቦችና አስተያየቶች ይሰጣሉ፡፡ አንዳንድ ተቃዋሚዎች ኢህአዴግ የአመራር ለውጥ ያደረገው በሀገሪቱ እየታየ ያለውን ህዝባዊ አመፅና ተቃውሞ ለመግታት እንደሆነ ሲገልፁ ይሰማል፡፡ በሌላ በከል አንዳንድ የህወሓት/ኢህአዴግ ደጋፊዎች የአመራር ለውጡ የተካሄደው በተለመደው የፓርቲው ደንብና ስርዓት እንደሆነና የአዲሱ ሊቀመንበር ምርጫ በአባል ድርጅቶች የጋራ መግባባት የተመሠረተ እንደሆነ ሲገልፁ ይሰማል፡፡ ነገር ግን፣ ሁለቱም አመለካከቶች በተሳሳተ ግንዛቤ ላይ የተመሠረቱ ናቸው፡፡ ምክንያቱም እንዲህ ያሉ አስተያየቶች፤ አንደኛ፦ የለውጡን መነሻ ምክንያት በጥልቀት ካለመረዳት፣ ሁለተኛ፦ የአመራር ለውጡ የተካሄደበትን ሁኔታ በግልፅ ካለመገንዘብ የመነጩ ናቸው፡፡ ኢህአዴግ የአመራር ለውጥ እንዲያደርግ … [Read more...] about ጠ/ሚ/ር ዓቢይ እና ህወሓቶች፡ ለይቶ ማሰር ወይስ አብሮ መሥራት?
ለገደንቢ “የእርም” መሬት!
የራሱ የሆነ ገንዘብ ሳይኖረው “ልማት አከናውናለሁ” በማለት መሬት ሲወስድ፣ አጥር አጥሮ ለዓመታት ባዶ መሬት ከጥቅም ውጪ ሲያደርግ፣ በወሰዳቸውና ፋብሪካ ከፈትኩባቸው በሚላቸው ድርጅቶች አለአግባብ ከመበልጸግ አልፎ ተገቢውን ግብር ባለመክፈል፣ እንዲከፍል ሲገደድ ደግሞ የህወሓት ወንበዴ ሹመኛዎችን በመደለል፣ ኪሳቸውን በማደለብ፣ የሕዝብ ተቀባይነትን ለማግኘት ታዋቂ በሆኑ ግለሰቦችና ጉዳዮች ላይ ከኢትዮጵያ ከሰበሰበው ሃብት ፍርፋሪውን በመጣል “የሕዝብ ልጅ” በመባል፣ በአጠቃላይ የኢትዮጵያን ሐብት በጨበጣ ኪሱ ያስገባው አላሙዲ በለገደንቢ የወርቅ ምርት እንደ ስንዴ በመሰብሰብ የአገርና የሕዝብ ሃብት ሲዘርፍ በወገን ላይ ያስከተለው ጉዳት ትውልድና ዘመን ተሻጋሪ ነው። የአላሙዲ ሚድሮክ ጎልድ የለገደንቢን ምድር ከረገጠ ጊዜ ጀምሮ አካባቢውን የዕርግማን ምድር፤ ቦታውን “የእርም” መሬት … [Read more...] about ለገደንቢ “የእርም” መሬት!
የህወሓት ዕቅድ፥ የእስር ማዘዣው እና የብአዴን ጆከር!
በእርግጥ ፖለቲካ ማለት ልክ "Bicycle" ነው። ሁልግዜም በማያቋርጥ ለውጥና መሻሻል መሽከርከር አለበት። ለውጥና መሻሻል ከቆመ ልክ እንደ "Bicycle" ፖለቲካዊ ስርዓቱም ተንጋሎ ይወድቃል። ህወሓት የማይለወጥ የፖለቲካ ቡድን ከመሆኑም በላይ ሌሎች እንዳይለወጡ የሚያደርግ ፀረ-ለውጥ ቡድን ነው። ስለዚህ ይህ ቆሞ-ቀር ቡድን የሌሎችን የለውጥ እንቅስቃሴ ለማደናቀፍ ያለመታከት ጥረት ያደርጋል። በሀገሪቱ ፖለቲካ ውስጥ ለውጥና መሻሻል ጠፍቶ መንግስታዊ ስርዓቱ ለመውደቅ እየተንገዳገደ ባለበት ወቅት እንኳን ህወሓት በኦህዴድ መሪነት የተጀመረውን የለውጥ እንቅስቃሴ ለማስተጓጎል ላይ-ታች ሲል ነበር። አዲሱ የኦህዴድ አመራር ወደ ስልጣን እንደመጣ የወሰደው የለውጥ እርምጃ ፀረ-ለውጥ አቋም ከሚያራምደው የህወሓት ቡድን ራሱን ማላቀቅ ነው። በዚህ ረገድ የክልሉ ፕሬዚዳንት ኦቦ ለማ መገርሳ … [Read more...] about የህወሓት ዕቅድ፥ የእስር ማዘዣው እና የብአዴን ጆከር!
ከሁሉም የፖለቲካ ሃይሎች ጋር ግልጽ ውይይትና ድርድር ሊደረግ ይገባል!
ዶ/ር አብይ የኦህዴድ ጽ/ቤት አላፊ በነበሩበት ወቅት ኦህዴድ ሁሉንም ሰላም ወዳድ ዜጋን ያስደሰተ ጥሪ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጪ ላሉ ተቃዋሚዎች አቅርቦ ነበር። ይህ ጥሪ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ የቀረበ በመሆኑ አንዳንድ በኦሮሞ ስም የሚታገሉ በውጪም በውስጥም ያሉ ተቃዋሚዎች በደስታ የተቀበሉት ነበር። ነገር ግን ይህ የኦህዴድ ጥሪ ምንም ያህል ለሀገሪቱ ሰላም ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያለው ቢሆንም ያለ ኢህአዴግ አሺታ ሊሳካ እንደማይችል የገመቱ ነበሩ። ዶ/ር አብይ ወደ ስልጣን በመጡ የመጀመሪያዋ ቀን በፓርላማው ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ኦህዴድ ለተቃዋሚዎች ካቀረበው ጥሪ ጋር ተመሳሳይነት ያለውን ሃሳብ ተናግረው ነበር። ጠቅላይ ሚንስተሩ በኢትዮጵያ ጉዳይ “በተለያየ መልኩ” ከሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ሀይሎች ጋር አብሮ ለመስራት እንደሚፈልጉ ጠቅሰው ነበር። የዲስፖራው ፖለቲካ ብዙውን … [Read more...] about ከሁሉም የፖለቲካ ሃይሎች ጋር ግልጽ ውይይትና ድርድር ሊደረግ ይገባል!
“EFFORTን” መውረስ የኢኮኖሚውን ጥገኛ ተውሳክ እንደማስወገድ ነው!
ትላንት በፌስቡክ ገፄ ላይ የትእምት (EFFORT) ድርጅቶች በመንግስት መወረስ እንዳለባቸው ለመጠቆም ሞክሬ ነበር። ለዚህ ያቀረብኳቸው ምክንያቶችና ማስረጃዎች እንዳሉ ሆነው እነዚህን ድርጅቶች መውረስና ወደ ግል እንዲዛወሩ ማድረግ ምን ፋይዳ አለው? በሀገሪቱ ፖለቲካና ኢኮኖሚ ላይ ምን ዓይነት አሉታዊ ሆነ አዎንታዊ ተፅዕኖ ሊፈጥር ይችላል? እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን በዝርዝር መመልከት ያስፈልጋል። በቅድሚያ ግን ስለ ትእምት (EFFORT) ድርጅቶች አጠቃላይ ባህሪ የተወሰነ ግንዛቤ ሊኖረን ይገባል። ለዚህ ደግሞ ከትእምት (EFFORT) ድርጅቶች የመሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካን እንደ ማሳያ በመውሰድ እንመልከት። በመቐለ ዩኒቨርሲቲ በቢዝነስ አመራር ሙያ (Business Administration) የሁለተኛ ዲግሪ ትምህርት በምማርበት ወቅት “Operation Management” የሚባለውን ኮርስ … [Read more...] about “EFFORTን” መውረስ የኢኮኖሚውን ጥገኛ ተውሳክ እንደማስወገድ ነው!
EFFORTን መውረስ ለዶ/ር አብይ ቀዳሚ ተግባር ነው!!!
ዶ/ር አብይ ጠ/ሚኒስትር ሆነው የተመረጡ ዕለት ባደረጉት ንግግር የሀገሪቱን ኢኮኖሚ እድገት እና ፍትሃዊ የሃብት ክፍፍል ለማረጋገጥ፣ በተለይ አዳዲስ ባለሃብቶችን እንዲፈጠሩ ቅድሚያ ሰጥተው እንደሚሰሩ ገልፀዋል። ይህን እውን ለማድረግ የጠ/ሚኒስትሩ የመጀመሪያ ተግባር መሆን ያለበት #EFFORTን በመውረስ ወደ ግል ባለሃብቶች ማዘዋወር (privatize) ነው። ምክንያቱም፣ 1ኛ) ለሀገሪቱ የኢንዱስትሪ ልማትና እድገት፣ በተለይ አዳዲስ ባለሃብቶችን በመፍጠሩ ረገድ ዋና እንቅፋት መሆናቸው በዚህ ጥናታዊ ፅሁፍ በዝርዝር ተገልጿል። 2ኛ) #በአርከበ_ዕቁባይ መሪነት ተግባራዊ የተደረገው የሀገሪቱ ኢንዱስትሪ ፖሊስ የEFFORT ድርጅቶችን ተጠቃሚ በማድረግና የግል ቢዝነስ ተቋማትን እድገት በማቀጨጭ ላይ የተመሠረተ ስለመሆኑ ይህን ፅሁፍ ያንብቡ። 3ኛ፦ የEFFORT መነሻ ካፒታል 100ሚሊዮን … [Read more...] about EFFORTን መውረስ ለዶ/ር አብይ ቀዳሚ ተግባር ነው!!!
ቋንቋን በቋንቋ
ስለ ቋንቋ የተለያዩ እይታዎች መኖራቸው አዲስ አይደለም። የሚገርመው ይልቅ፣ ብዙዎች እንደ ሹምና አቡን ትእዛዝ ሲሰጣጡ ማየት ነው። ትእዛዙን ማን፣ እንዴት ይፈጽም? እይታዎችን ማቀራረብና መተግበርስ ይቻላል? መቸ በምን ቅደም ተከተል? ወዘተ። ይህን ያሰቡበት ቢኖሩ ድምጻቸው አልተሰማም። የራስን አጉልቶ፣ የሌላኛውን ማድበስበስ የተለመደ በመሆኑ፣ የጽሑፌ ይዘት ለያንዳንዱ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ፣ የተዘነጉ ጥቃቅን አሳቦችን ማነጋገር ይሆናል። ቋንቋ ቢያንስ ሀ/ ድንበር ተሻጋሪ መሆን ይኖርበታል፤ አማርኛ ተናጋሪ፣ እርስ በርሱ ብቻ ከሆነ፣ ከኬላው ውጭ በምን ይግባባል? ለ/ ድንበር ተሻግረን እንግሊዝኛ፣ አማርኛ፣ ወዘተ፣ የቆነጠርን ቢያንስ አኗኗራችንን ለማሻሻል እንደ ሆነ አንርሳ ሐ/ ቋንቋ ተሻጋሪ እንዲሆን፣ ድልድይ የሚሆን ቋንቋ ይሻል። አማርኛ ድልድይ ነው። እርግጥ፣ ሁሉን ቋንቋ ማወቅ … [Read more...] about ቋንቋን በቋንቋ
ጠ/ሚ/ር አብይ “የወልቃይት ኮሚቴ አባላቱን ከወንበር ተነስቶ ይቅርታ ጠይቋል”
“እኛ ትግሬ አንጠላም፣ እነሱ ግን አሁም ያሳድዱናል። ለምን ያሳድዱናል?” የወልቃይት አማራ ማንነት ኮሚቴ በመቀሌ ንግግር ከፍተኛ አቧራ ያስነሳውን የወልቃይትን ጉዳይ ጠቅላይ ሚንስትር አቢይ አህመድ ከኮሚቴው አባላት ጋር በመነጋገር መቁዋጫ አድርጎለታል። በቅድሚያ ጎንደር ላይ ባደረገው ንግር ይህንን ብሎ ነበር፤ "የወልቃይትን ጉዳይ በተመለከተ በህግ አግባብ ሊፈታ እንደሚችል ህዝቡ ማመን አለበት። ህገ መንግስቱ ይህን ጉዳይ ሊፈታ ይችላል። በቀጣይም ከወልቃይት ኮሚቴዎች ጋር ውይይት አደርጋለሁ ብለዋል፤ጠቅላይ ሚኒስትሩ። በመወያየት ያሉ ጥያቄዎች መመለስ እንችላለን። ዋናው ነገር በዚህ ሂደት ውስጥ ሀይል የተቀላቀለበት እና ወደ ቁርሾ በሚያስገባ መንገድ መሆን እንደሌለበት ህዝቡ ሊያውቅ ይገባል”። ከማህበራዊ ድረገጽ በተገኘ መረጃ ደገሞ ከወልቃይት ኮሚቴ አባላት ጋር … [Read more...] about ጠ/ሚ/ር አብይ “የወልቃይት ኮሚቴ አባላቱን ከወንበር ተነስቶ ይቅርታ ጠይቋል”
አብይ አህመድ፤ ለክፉ ቀን የታሰበ የኦሮሞ ወጣቶች ብሶት ማስታገሻ?
የዶ/ር አብይ መሾም “ይህንን ክፉ ቀን የኦሮሞ ወጣቶችን አስታግሶ ለማለፍ” ይሆን? የዶ/ር መረራ ጥያቄ ለአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ ቃለምልልስ የሰጡት የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና በአዲሱ ጠ/ሚ/ር ሹመትና የወደፊት የኢትዮጵያ ፖለቲካ አካሄድ ከኢህአዴግ ድርጅታዊ አሠራር አንጻር ትንታኔ ሰጥተዋል። “ኢህአዴግ ለምን ተዘጋጅቷል?” የሚሉት መረራ ቀለል ያሉ መሠረታዊ ጥያቄዎችን ያስከትላሉ፤ “ለነጻና ፍትሃዊ ምርጫ፤ ለሃቀኛ የፖለቲካ ውድድር (ኢህአዴግ) ተዘጋጅቷል ወይ?” በማለት ይጠይቃሉ። ራሳቸው ሲመልሱትም “ይህንን ካሁኑ ለመገመት ያስቸግራል” ይላሉ። የጠ/ሚ/ሩ ተስፋ የተሞላበትን ንግግሮች ሁሉ መልካም መሆናቸውን ቢገልጹም እርሳቸው እንደ ዜጋ እና ድርጅታቸውም እንደ አንድ የፖለቲካ ፓርቲ የአብይ አህመድን ንግግሮችና የወደፊቱን ሁኔታ “ጥንቃቄ የተሞላበት … [Read more...] about አብይ አህመድ፤ ለክፉ ቀን የታሰበ የኦሮሞ ወጣቶች ብሶት ማስታገሻ?










