ጉብኝቱ “ከHR 128 … ውጪ ሊሆን አይችልም” ኦባንግ የአሜሪካ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት አባል ሴናተር ጀምስ ኢንሆፍ ህወሓት/ኢህአዴግን ለመታደግ በአዲስ አበባ ላይ ከኢህአዴግ ሹሞች ጋር መከሩ። አቶ ኦባንግ ሜቶ ጉብኝቱ “ከHR 128 የተያያዘ ነው፤ ከዚህ ውጪ ሊሆን አይችልም” ይላሉ። በያዝነው የአውሮጳውያን ዓመት (2017) መጀመሪያ አካባቢ ወደ ኢትዮጵያ ሄደው የነበሩት ሴናተር ጀምስ ኢንሆፍ ከከፍተኛ የሕወሓት/ኢህአዴግ ሹሞች ጋር መነጋገራቸው ህወሓት የሚቆጣጠረው የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዘግቧል። የዜና አገልግሎቱ ውይይቱ መቼ እንደተደረገ ባይዘግብም ዜናውን ግን ጥቅምት 2/2010 በማለት ነው ያተተው። በውይይቱ ላይ ሴናተሩ ሌሎች የአሜሪካ እንደራሴዎችንና የሕግ መወሰኛ ምክርቤት አባላትን በመምራት እንደተገኙ ዜናው አስታውቋል። የውይይቱ ትኩረትም “በሠላምና ጸጥታ … [Read more...] about የሴናተር ኢንሆፍ ህወሓትን የመታደግ ዘመቻ ቀጥሏል!
Politics
አባዱላ ወደ ጨፌ ወይስ ወደ ሸቤ?
የሰበር ዜና ልክፍት የተጠናወተው የዘመኑ “ሚዲያ” የአባዱላን ከአፈጉባኤነት መልቀቅ በሰበር ዜናነት ማናፈሱ ቆም ብሎ ላየው ራስን ትዝብት ላይ የሚጥል ነው። የአባዱላ መልቀቂያ ማስገባት “ምስጢር” በቅርቡ የሚለይለት ቢሆንም በህወሓት ተለክቶና ተጠፍጥፎ የተሠራ ድርጅትና ስብዕና ያለው ለዚህ ዓይነት የሞራል ልዕልና ይደርሳል ብሎ መገመት ህወሓትን ካለማወቅ ወይም ራስን ከመሳት የሚመነጭ ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም። በበርካታ የሙስና ተግባራትና ህይወት ማጥፋት አለበት እየተባለ የሚነገርለት አባዱላ ከቀድሞው የኢትዮጵያ ሠራዊት ተማርኮ በሻዕቢያ ፈቃድና በህወሓት ፈጣሪነት አዲስ ስብዕና ተሰጥቶት ኦህዴድ የሚባል የጀመረ መሆኑ የሚዘነጋ አይደለም። ይህ ስብዕናው ህወሓት በህንፍሽፍሽ ልትበታተን ስትል የኦሮሞውን ክንፍ ይዞ መለስን የታደገ በመሆኑ ባለውለታነቱ ለማን እንደሆነ በድጋሚ ያስመሰከረ … [Read more...] about አባዱላ ወደ ጨፌ ወይስ ወደ ሸቤ?
HR 128/SR 168 ጸሐይ እየጠለቀችበት ነው!
ለኢትዮጵውያን ታላቅ ተስፋ ይዞ የተነሳው HR 128/SR 168 በሞት አፋፍ ላይ እንደሚገኘ ተነገረ። የህወሃት/ኢህአዴግን ህልውና በማያፈናፍን አጣብቂኝ ውስጥ እንደሚከት ብዙ የተባለለት ይህ ረቂቅ ሕግ ወደ ሕግ መወሰኛ ምክርቤት ቀርቦ ድምጽ ከማግኘቱ በፊት ጊዜውን ጠብቆ እንዲሞት የማቀዛቀዝ ተግባር እየተፈጸመበት ነው። ኢትዮጵያውያን ተባብረው በመታገል ይህ ዕድል እንዳያመልጣቸው ማድረግ እንዳለባቸው ማሳሰቢያ ተሰጠ። ሐምሌ 20፤ 2009ዓም (7/27/2017) የህወሃት/ኢህአዴግን የሰብዓዊ መብቶች ይዞታና አጠቃላይ አስተዳደርን የሚወቅስ የህግ ረቂቅ በዩናይትድ ስቴትስ የሕግ መምሪያ የውጭ ጉዳዮች ኮሚቴ ፊት ቀርቦ በሙሉ ስምምነት ማለፉ ይታወሳል። ከውሳኔው በላይ የአሜሪካ ወዳጅ በመሆን ሕዝብን ለመከራና ስቃይ ሲዳርግ የኖረው የኢህአዴግ አገዛዝ በአሻባሪነቱ ከሚወገዘው ሒዝቦላ እና ከሰሜን … [Read more...] about HR 128/SR 168 ጸሐይ እየጠለቀችበት ነው!
ሹፌሮችን ያስቆጣ መመሪያ ተሻሻለ ተባለ
የአማራ ክልል መንግስት የመንግስት ተሸከርካሪ አያያዝ፣ አጠቃቀምና የንብረት አስተዳደር መመሪያ ሰሞኑን ማሻሻሉን ይፋ ቢያደርግም የከፍተኛ አመራሮች ሹፌሮች በበኩላቸው የተሻሻለው መመሪያ የኛን ሕልውና የሚፈታተን ነው ሲሉ ቅሬታቸውን ገለጡ። የክልሉ የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ ሰሞኑን ለክልሉ ቢሮዎች በላከው ደብዳቤ ከመስከረም 1 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ወይም የሥራ ኃላፊዎች ለሥራ ጉዳይ ክልሉን ለቀው ወደ አዲስ አበባ ሲሄዱ የሚመሩትን ተቋም ተሸከርካሪ ይዘው እንዳሄዱ እያሳሰበ በተማከለ መንገድ በከተማው በሚዘጋጁ ተሸከርካሪዎች መጠቀም እንደሚችሉ አብራርቷል። በተማከለ መንገድ በሚዘጋጁ ተሸከርካሪዎች መጠቀም የሚችሉ የሥራ ኃላፊዎች ብሎ የተሻሻለው መመሪያ የጠቀሳቸው የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር፣ ም/ርዕሰ መስተዳድርና በዚህ ደረጃ ያሉ ኃላፊዎች፣ የክልሉ … [Read more...] about ሹፌሮችን ያስቆጣ መመሪያ ተሻሻለ ተባለ
የህወሓት ፕሮግራም፤ የመለስ ሌጋሲ – ዜጎችን ማፈናቀል፤ ማጋደል!
ገና ከመነሻው በበረሃ ያወጣው ፕሮግራሙ በግልጽ እንደሚያመለክተው የህወሓት ዋንኛ ዓላማ ኢትዮጵያን አዳክሞና በጎሣ ከፋፍሎ ትግራይን ታላቅ በማድረግ ሪፑብሊክ መመሥረት ነው። ባለፉት 26 ዓመታት ይህንን ለማሳካት በኢትዮጵያ ውስጥ ያልፈነቀለው የጎሳ ድንጋይ የለም፤ ያላጋጨው ሕዝብ፤ ያላጋደለው ወገን የለም፤ ትግራይን ሳይጨምር! ሞት እንደ ቡሽ ክዳን ሳያስበው አስፈነጠረው እንጂ የመለስና ዋናዎቹ የህወሓት መሥራቾች ዕቅድ ይህንኑ ለማሳካት እንደሆነ ሰሞኑን በተከታታይ በምናትመው የአቶ ገብረመድኅን ጽሁፍ በግልጽ የተቀመጠ ሐቅ ነው። የወቅቱ የፍጅት ዓላማ ደግሞ ኦሮሞን ከሶማሊ ወገኖቹ ጋር በማጋጨት የአገዛዝ ዘመኑን ማራዘም፤ ሁለቱን ጎሣዎች በማይረሳ ቂምና ጥላቻ ውስጥ ማስገባት፤ ይህንንም እስካሁን በሌሎቹ ጎሣዎች መካከል ከፈጠረው ጥላቻና ቁርሾ ጋር ተዳምሮ የኢትዮጵያን ኅልውና አጥፍቶ … [Read more...] about የህወሓት ፕሮግራም፤ የመለስ ሌጋሲ – ዜጎችን ማፈናቀል፤ ማጋደል!
ዝሆን ላይ የሚጮህ እብድ ውሻ ብቻ ነው! ህወሓትና ኢትዮጵያን የማፈራረስ ዓላማው!
የአዘጋጆቹ ማስታወሻ፤ ባለፉት ዓመታት ከህወሓት እየኮበለሉ የወጡ የቀድሞ አባላት በርካታ ናቸው። እንዳንዳቸው የሚወጡበት ምክንያት ቢኖራቸውም ህወሃትን በማጋለጥና ማንነቱን ለኢትዮጵያ ሕዝብ በማሳወቅ የአቶ ገብረመድኅን አርአያን ያህል ታላቅ ሥራ የሠራና መስዋዕትነት የከፈለ አለ ለማለት ያስቸግራል። አብዛኛዎቹ የቀድሞው አባላቱ የህወሓትን ምሥጢራዊ አሠራር እና እጅግ አረመኔያዊ ግፍ፤ ኤፈርት በኢትዮጵያ ሐብት ላይ የፈጸመውንና እስካሁንም እየፈጸመ ያለውን የኢኮኖሚ ግፍ፣ ዝርፊያ፣ ሌብነት፣ … የመሳሰሉ ጉዳዮች በአደባባይ ከመናገር ሲቆጠቡ ተስተውለዋል። አንዳንዶቹም በህወሓት ከፍተኛ አመራር ላይ የነበሩ የቀድሞ አባላት ቢሆኑም፤ ኤፈርትም ሲያስተዳድሩ የቆዩ ቢሆኑም ስለጉዳዩ ሲጠየቁ የሚሰጡት ምላሽ አባይ ጸሐዬ ወይም ስብሃት ነጋ ከሚሰጡት ምላሽ ያልተለየ ሆኖ ተገኝቷል። አቶ ገብረመድኅን … [Read more...] about ዝሆን ላይ የሚጮህ እብድ ውሻ ብቻ ነው! ህወሓትና ኢትዮጵያን የማፈራረስ ዓላማው!
የቅማንት ጉዳይ!
ብዙ ወዳጆቼ ስለምንድን ነው የቅማንትን ጉዳይ ዝም ያልከው እያሉ በየቀኑ መልዕክት ይልኩልኛል፡፡ ላም እሳት ወለደች እንዳትልሰው ፈጃት እንዳትተወው ቆጫት ይላሉ አበው ሲተርቱ፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ አንድ ጽንፍ ይዞ መሔዱን አማራጭ አድርጌ አላየሁትም፡፡ መሀል ሰፋሪ ለመሆንም አይደለም፡፡ ግና ዕውነታውን ይዘን ለሁሉም የሚበጀውን መከተል አስፈላጊ ነው ብዬ ስለማምን ነው፡፡ እነኚህ ወዳጆቼ እንደሚሉት ዝም ብዬም አላውቅም፡፡ ነገርን ከሥሩ ውኃንም ከጥሩ እንደሚሉ ከሥር መሠረቱ ጉዳዪን መዘርዘር አስፈላጊ ይመስለኛል፡፡ የቅማንትን ጉዳይ መከታተል የጀመርኩት በ2003/4 ዓም ጀምሮ ነበር፡፡ ይህም የተፈጠረበትን አጋጣሚ ከዚሁ ላይ መግለጹ አስፈላጊ ይመስለኛል፡፡ አይከል ከተማ እሜቴ አይከል የምትባል ዛፍ አለች፤ የሚገባላት ብጻት ብዛት ይኽ ነው አይባልም፡፡ ምርጥ ምርጡን ገብስማ ዶሮ ከጊወን … [Read more...] about የቅማንት ጉዳይ!
ፕሬዚዳንታዊ ምርጫን በፍርድቤት ውድቅ በማድረግ ኬኒያ ከአፍሪካ ቀዳሚ ሆነች!
“ፍርድ ቤቶች በነጻነት እንዲሠሩ ከተለቀቁ ፍትሕ ይበየናል” “ሁለቱም ተወዳዳሪዎች ውሳኔውን በመቀበል ለአገራቸው አኩሪ ተግባር ፈጽመዋል” ኦባንግ ሜቶ “ዛሬ በአፍሪካ ታላቅ ፍትኅ ተፈፀመ” ራይላ ኦዲንጋ በኬኒያ በቅርቡ የተካሄደውን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በርካታ ችግሮች የገጠሙትና በአገሪቱ ሕግጋት መሠረት ያልተካሄደ ነው ሲል የኬኒያ ጠቅላይ ፍርድቤት ውጤቱን ውድቅ አድርጎታል፡፡ ከምርጫው ከመጀመሩ በፊት የኬኒያን ፖለቲካ በቅርቡ የሚከታተሉት ኦባንግ ሜቶ የፍርድ ቤቱን ውሳኔ በማድነቅ “ፍርድ ቤቶች በነጻነት እንዲሠሩ ከተደረጉ በምዕራቡ ዓለም ብቻ ሳይሆን አፍሪካም የሕግ የበላነይትና ፍትህ ይሰፍናል፤ ሁለቱም ተወዳዳሪዎች፤ ራይላ ኦዲንጋ ከአመጽ ይልቅ በሥርዓት ጥቄያቸውን ለፍትሕ አካል በማቅረባቸው፤ ኡሁሩ ኬኛታ ደግሞ ለፍርድ ቤቱ ውሳኔ እገዛለሁን ማለታቸው የሚደነቁ ናቸው፤ … [Read more...] about ፕሬዚዳንታዊ ምርጫን በፍርድቤት ውድቅ በማድረግ ኬኒያ ከአፍሪካ ቀዳሚ ሆነች!
የግፍ ለከት አልባው ህወሓት
የፌዴሬሽን ምክር-ቤት የህገ መንግስት አጣሪ ጉባኤ የሚባለው ኮሚቴ እንደግዴታው "ተርጉሞ" መመለስ የነበረብትን ሠነድ ባለመመለሱ የ3 ወር (ጥቅምት 2010) ተለዋጭ ቀጠሮ ለዶ/ር መረራ ጉዲና ተሰጥቷል - የህወሓት ግፍ ለከት የለውም። ጎልጉል: የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about የግፍ ለከት አልባው ህወሓት
ዋናዎቹ “መዥገሮች” ትንንሾቹን ነቀሉ!
ህወሓት/ኢህአዴግ በራሱ ጉባዔ (ፓርላማ)፣ በራሱ ባለሥልጣናት፣ በራሱ ፈቃድ፣ በራሱ በሚተዳደረው ሚዲያ፣ ፈቅዶም ሆነ ሳይፈቅድ በሚገዛለት ሕዝብ ፊት ይፋ ያደረገው የስኳር ፕሮጀክት ዝርፊያ በራሱ አስፈላጊ ርምጃ ለመውሰድ በቂ ሆኖ ሳለ ሙስናን በመታገል ስም እስካሁን መቆየቱ በራሱ አነጋጋሪ ነው፡፡ ምክንቱም አፈቀላጤ ነገሪ ሌንጮ እንዳለው የኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ እንደመዥገር ተጣብቀው ደሙን የሚጠጡት የበላይ ኃላፊዎች እነማን እንደሆኑ ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ነውና፡፡ ችግሩ ያለው ዋናዎቹን መዥገሮች ማን ይንቀላቸው የሚለው ላይ ነው፡፡ በኢህአዴግ ውስጥ የሚፈጠሩ አደገኛ የፖለቲካ ልዩነቶች ለማስተንፈስና የአመራሩንና አባላቱን አፍ ለማስዘጋት መለስ ዜናዊ ያደርገው እንደነበረው “የሙስና ዘመቻ” ሲጀመር ይህ ያሁኑ የመጀመሪያው አይደለም፡፡ በቅርቡ “ጥልቅ ተሃድሶ” በሚል “ዘመቻ” ሲጀመር … [Read more...] about ዋናዎቹ “መዥገሮች” ትንንሾቹን ነቀሉ!










