• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“EFFORTን” መውረስ የኢኮኖሚውን ጥገኛ ተውሳክ እንደማስወገድ ነው!

April 26, 2018 07:21 pm by Editor 2 Comments

ትላንት በፌስቡክ ገፄ ላይ የትእምት (EFFORT) ድርጅቶች በመንግስት መወረስ እንዳለባቸው ለመጠቆም ሞክሬ ነበር። ለዚህ ያቀረብኳቸው ምክንያቶችና ማስረጃዎች እንዳሉ ሆነው እነዚህን ድርጅቶች መውረስና ወደ ግል እንዲዛወሩ ማድረግ ምን ፋይዳ አለው? በሀገሪቱ ፖለቲካና ኢኮኖሚ ላይ ምን ዓይነት አሉታዊ ሆነ አዎንታዊ ተፅዕኖ ሊፈጥር ይችላል? እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን በዝርዝር መመልከት ያስፈልጋል። በቅድሚያ ግን ስለ ትእምት (EFFORT) ድርጅቶች አጠቃላይ ባህሪ የተወሰነ ግንዛቤ ሊኖረን ይገባል። ለዚህ ደግሞ ከትእምት (EFFORT) ድርጅቶች የመሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካን እንደ ማሳያ በመውሰድ እንመልከት።

በመቐለ ዩኒቨርሲቲ በቢዝነስ አመራር ሙያ (Business Administration) የሁለተኛ ዲግሪ ትምህርት በምማርበት ወቅት “Operation Management” የሚባለውን ኮርስ ያስተማረኝ አንድ የውቅሮ ተወላጅ የሆነ መምህር ነው። ይህ ስሙን የማልጠቅሰው መምህር የመሰቦ ሲሚንቶ የገበያ ስትራቴጂን እንደ ምሳሌ በመጥቀስ የተናገረው ነገር መቼም ከአዕምሮዬ አይጠፋም።

ነገሩ እንዲህ ነው፤ የመሰቦ ሲሚንቶ በመቐለ ከተማ የሚሸጥበት ዋጋ በአዲስ አበባ ከሚሸጥበት ዋጋ በሁለት ብር ይበልጣል። በዚህ መሰረት የመሰቦ ሲሚንቶ መቐለ ላይ 300 ብር የሚሸጥ ከሆነ ከፋብሪካው 700 ኪ.ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው አዲስ አበባ ደግሞ 298 ብር ይሸጣል። ይህ “dumping” እንደሚባልና ሕገ-ወጥ ተግባር መሆኑን ስናገር መምህሩና የአካባቢው ተወላጅ የሆኑ ተማሪዎች በሙሉ “No” በማለት በአንድ ድምፅ ተቃወሙኝ። ቀጠልኩና “እሺ.. የመቐለ ከተማ ሲሚንቶ ተጠቃሚዎች ያለ አግባብ በድርጅቱ እየተበዘበዙ ነው” ስላቸው አሁንም በአንድ ተቃወሙኝ። በመጨረሻም መምህሩ ያነሳሁትን ጥያቄ ሆነ ሃሳብ በሚያጣጥል መልኩ “ይህ የመሰቦ ሲሚንቶ የገበያ ስልት (Market Strategy) ነው” በማለት በተግሳፅ ተናገረኝ።

በመሰረቱ የሲሚንቶ ፋብሪካ ምርቱን የሚሸጥበት ገበያ ከ300 ከ.ሜትር በላይ የሚርቅ መሆን እንደሌለበት የዘርፉ ምሁራን ይገልፃሉ። ምክንያቱም ሲሚንቶ በባህሪው ከባድ (Bulky) ምርት ስለሆነ ከ300 ኪ.ሜ በላይ በትራንስፖርት አጓጉዞ መሸጥ ለከፍተኛ የትራንስፖርት ወጪ ይዳርጋል። መሰቦ ሲሚንቶ ግን ምርቱን በመኪና 700 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ወደምትገኘው አዲስ አበባ አምጥቶ መቐለ ላይ ከሚሸጥበት ዋጋ የሁለት ቅናሽ አድርጎ ይሸጣል። በዚህ መሰረት፣

አንደኛ፡- መሰቦ ሲሚንቶ ምርቱን አዲስ አበባ ድረስ ወስዶ የትራንስፖርት ወጪውን ሳይጨምር በሁለት ብር ቅናሽ መሸጡ በሕገ-ወጥ ተግባር እንደተሰማራ ያሳያል፣

ሁለተኛ፡- መቐለ ላይ ያለው የመሰቦ ሲሚንቶ መሸጫ ዋጋ ከአዲስ አበባው የመሸጫ ዋጋ በሁለት ብር የሚበልጥ ከሆነ ድርጅቱ የከተማዋን ነዋሪዎች ያለአግባብ እየበዘበዘ መሆኑን ያሳያል።

ከላይ በተጠቀሰው መሰረት፣ መሰቦ ሲሚንቶ የሚከተለው የገበያ ስልት (Market Strategy) ከሕግም ሆነ ከቢዝነስ አንፃር ፍፁም የተሳሳተ ነው። ከሕግ አንፃር የመሰቦ የገበያ ስልት ሌሎች የሲሚንቶ ፋብሪካዎችን ቀስ በቀስ ከገበያ በማስወጣት የምርቱን ገበያ በበላይነት ለመቆጣጠር ያለመ ነው። ከዚህ በተጨማሪ፣ በአካባቢው ማህብረሰብ ላይ ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ በማድረግ ይበዘብዛል። እንዲህ ያለ የገበያ ስልት የድርጅቱን ተወዳዳሪነት ከማሳደግ ይልቅ ለኪሳራ ይዳርገዋል። ይሁን እንጂ ነባር የሲሚንቶ ፋብሪካዎች ከገበያ ከመውጣት ይልቅ ብዛት ያላቸው አዳዲስ ፋብሪካዎች ተከፈቱ። የመሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካም በሚፈለገው ደረጃ ተወዳዳሪ ባይሆንም እንኳን በኪሳራ ምክንያት ከገበያ አልወጣም። ለምን?

አስታውሳለሁ… ደርባ ሲሚንቶ ወደ ገበያ በገባበት ወቅት በሀገራችን ከፍተኛ የሆነ የሲሚንቶ ምርት እጥረት ተከስቶ ነበር። በተመሳሳይ በመቐለ ከተማ ነዋሪዎች የሲሚንቶ ምርት ለመግዛት ለብዙ ቀናት ወረፋ የሚጠብቁበት ወቅት ነበር። በዚህ ወቅት ነው እንግዲህ ደርባ ሲሚንቶ ምርቱን በራሱ ትራንስፖርት ለመቐለ ከተማ ተጠቃሚዎች እንደሚያቀርብ ያስታወቀው። ይህን ተከትሎ አብዛኞቹ ሲሚንቶ ፈላጊዎች ከደርባ ሲሚንቶ ጋር የግዢ ስምምነት ማድረግ የጀመሩት። በዚህ ምክንያት በወረፋና በሰልፍ ሲንያንገላታቸው የነበረውን መሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ ዞር ብሎ የሚያየው ጠፋ።

መሰቦ የትእምት (EFFORT) አባል ድርጅት እንደመሆኑ መጠን ዋና ስራ አስኪያጁ ከፍተኛ የህወሓት ባለስልጣን ነው። ይህ ባለስልጣን ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መቐለ ቅርጫፍ ዋና ስራ አስኪያጅ ቀጭን ትዕዛዝ አስተላለፈ። ትዕዛዙም “በመሰቦ ሲሚንቶ ላይ ፊታቸውን በማዞር ከደርባ ሲሚንቶ የግዢ ውል ለሚገቡ የመቐለ ከተማ ነዋሪዎች የባንክ ሲፒኦ (CPO) እንዳይሰጣቸው” የሚል ነበር። በዚህ መልኩ በህወሓት ከፍተኛ ባለስልጣናት ጣልቃ-ገብነት ምክንያት መሰቦ ሲሚንቶ የተሳሳተና ሕገ ወጥ የሆነ የገበያ ስልቱን ይዞ እንዲቀጥል ያደርጉታል።

ስለዚህ እንደ መሰቦ ሲሚንቶ ያሉ የትእምት (EFFORT) ድርጅቶችን መውረስና ወደ ግል እንዲዘዋወሩ ማድረግ ምን ፋይዳ አለው?

    1ኛ፡- የትእምት (EFFORT) ድርጅቶች የሀገሪቱን ኢኮኖሚ በበላይነት ለመቆጣጠር በሚከተሉት ስልት ምክንያት በተለያዩ የቢዝነስ ዘርፎች የሚያሳድሩትን አሉታዊ ተፅዕኖ ማስወገድ ይቻላል። በዘርፉ የሚታየውን የፖለቲካ ጣልቃ ገብነት ያስቀራል። በመሆኑም በዘርፉ አዳዲስ የቢዝነስ ተቋማት እንዲሰማሩ ያስችላል። እንዲሁም የሀገር ውስጥና የውጪ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ምቹ ሁኔታ ይፈጠራል።

    2ኛ፡- ድርጅቶቹ ወደ ግል ሲዘዋወሩ በምርት ዋጋና ጥራት ተወዳዳሪ የሚያደርጋቸውን የገበያ ስልት ይቀይሳሉ። በመሆኑም ምርቶቻቸውን ለአካባቢው ማህብረሰብ በተመጣጣኝ ዋጋ ያቀርባሉ። ከዚህ በተጨማሪ፣ በገበያው ውስጥ ተወዳዳሪና ትርፋማ ስለሚሆኑ ለአካባቢው ማህብረሰብ ሆነ ለሀገሪቱ አሁን ካለው በተሻለ ሁኔታ ተጨማሪ የሥራ እድል ይፈጥራሉ።

    3ኛ፡- የትእምት (EFFORT) ድርጅቶችን ወደ ግል በማዘዋወር መንግስት ገንዘብ ያገኛል። በዚህ መሰረት፣ በመሰረተ-ልማት ግንባታ አስተዋፅዖ ከማበርከቱ በተጨማሪ ፍትሃዊ የሃብት ክፍፍልን ከማረጋገጥ አንፃር የራሱ የሆነ ሚና ይኖረዋል።

ከላይ በተገለፀው መሰረት፣ መንግስት የትእምት (EFFORT) ድርጅቶችን በመውረስ ወደ ግል ባለሃብቶች ማዘዋወሩ የህወሓት ባለስልጣኖች እያገኙት ያለውን ያልተገባ ጥቅም ያስቀራል። እነዚህ ድርጅቶች ቢወረሱ የሚጎዱት የተወሰኑ የህወሓት አመራሮች እና አባላት ናቸው። ከዚያ በተረፈ ግን እንደ ክልል የትግራይ ሕዝብ ይጠቀማል። እንደ ሀገር ደግሞ ለኢትዮጵያ የተሻለ ነገር ይዞ ይመጣል። ሌላው ቢቀር የህወሓትን አድሏዊ ድጋፍ፥ ማጭበርበርና ኪራይ ሰብሳቢነት ያስቀራል። በአጠቃላይ “EFFORTን” መውረስ ከሀገሪቱ ኢንዱስትሪ ውስጥ ጥገኛ ተውሳክን እንደማስወገድ ነው። እነዚህ ድርጅቶች እስካሁን ባሉበት ሁኔታ በኢኮኖሚው ውስጥ ከጥገኛ ተውሳክ የተለየ ሚና የላቸውም።

 በመጨረሻም፣ አንዳንድ የትግራይ ልሂቃን “የትእምት (EFFORT) ድርጅቶች የሚወረሱት በእኛ መቃብር ላይ ነው” የሚል አቋም የሚያራምዱበትን በተመለከተ ቀደም ሲል የጠቀስኩትን መምህርና ተማሪዎች ማስታወስ ይበቃል። እንኳን የትግራይ ሕዝብን ጥቅምና ተጠቃሚነት የሚማሩትን ሆነ የሚያስተምሩትን ፅንሰ-ሃሳብ መገንዘብ የተሳናቸው ስለመሆናቸው ጥርጥር የለውም።

ስዩም ተሾመ

ምንጭ፤ Ethiopian Think Thank Group by Seyoum Teshome

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Opinions, Politics Tagged With: effort, Full Width Top, Middle Column, tplf

Reader Interactions

Comments

  1. Mulugeta Andargie says

    April 27, 2018 10:02 pm at 10:02 pm

    የማይመስል ወሬ ኣትቅደዱ!!

    Reply
  2. Mulugeta Andargie says

    May 7, 2018 09:57 pm at 9:57 pm

    ሳስበው ግን መምህሩ ደደብ መሆናቸው ገርሞኛል!

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጃዋርና በቀለ መታሠራቸው ተሰማ June 30, 2020 09:17 am
  • አገራዊ መድረክ ውጪ ድብቅ ውይይትን አንቀበልም June 17, 2020 06:57 am
  • ዴክሳሜታሶን! የኮሮና መድሀኒት June 17, 2020 06:49 am
  • የሰኔ 14ቱ ቀለበታዊ የፀሃይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ! June 17, 2020 06:38 am
  • የግብፅ የአባይን ውሃ ብቻዬን ልጠቀም ግትር አቋም ድርድር እንቅፋት ሆኗል June 10, 2020 07:15 am
  • የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!? April 12, 2020 02:48 am
  • በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሚጠቀሙበት የኤርትራ ስደተኛ ካምፕ ሊዘጋ ነው March 18, 2020 08:37 pm
  • እየተፈረካከሰ ያለው አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ March 18, 2020 08:09 pm
  • ኮሮና አዲስ ጉድ መዘዘ – ከቻይና በፊት በአሜሪካ ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎችን ቀጥፏል March 16, 2020 11:41 pm
  • የኮንዶሚኒየም ቤቶች በደላሎችና በመመሪያ ሰጪዎች ኔትዎርክ እየተቸበቸበ ነው! ታከለ የት ናቸው? March 9, 2020 10:18 am
  • ኤርሚያስ ለገሠ ከባለአደራ ተባረረ March 9, 2020 08:09 am
  • ድፍድፍ ሲቀል ይንሳፈፋል፤ ምሁር ሲዘቅት ይመራል፥ March 7, 2020 11:24 pm
  • ኢትዮጵያዊ ምን ይመስላል? በምንስ ይመሰላል? March 7, 2020 10:29 pm
  • WHY I WROTE “MONEY, BLOOD AND CONSCIENCE” March 4, 2020 11:15 pm
  • አድዋ፤ የጥቁር ሕዝብ ድል! March 2, 2020 11:24 am
  • ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ (አባ ጎራው) March 2, 2020 11:12 am
  • የኦነግ ሁለት መልክና ሦስት ግብሮች – ቃርሚያው ኃይል ቅጥር ነፍሰገዳይ ሆኗል February 25, 2020 11:26 pm
  • በቡራዩ “የጃል ማሮ” ፎቶ ጨረታ አፈናከተ፤ “ቡራዩ ሆኖ ከሃዲን ማሞካሸት አይቻልም” ነዋሪዎች February 17, 2020 09:13 pm
  • “ዲቃላ” የፍረጃ ፖለቲካ በኦሮሚያ የኃይል አሰላለፉን እየቀየረ ነው February 13, 2020 11:58 pm
  • “ከዚህ በኋላ ማናቸውንም በወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን” አንታገስም – ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ February 13, 2020 05:07 pm
  • “እኛ ማንም ተሳዳቢ እንዲመጣብን አንፈልግም” የጅማ ነዋሪ February 13, 2020 09:28 am
  • “ወላጆቻችሁ ሰላማዊ ሰልፍ በሕዝቡ ያስደርጉልን” – አጋቾች February 11, 2020 07:53 pm
  • “ወንጀል የፈጸመም ያስፈጸመም ተይዞ ለህግ ይቀርባል፤ ምርመራም ተጀምሯል” February 11, 2020 06:59 pm
  • ጃዋር ወደ መጨረሻው “የትግል” ስልቱ – አማራን ማበጣበጥ! February 10, 2020 11:54 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule