በአጠቃላይ ለ25 ዓመታት ሙሉ ህዝባችንን አፍኖ ሲገዛ የቆየና፣ ለ40 ዓመታት ሰላማዊ ዜጎችን እየረሸኑ አገራችንን እየዘረፉ የቆዩ ባለስልጣኖች ያሉበት ህወሓት/አህአዴግ በተለይ በዚህ ዓመት በኦሮሞና በአማራ ህዝባችን ላይ ጦርነት ከፍቷል። የአገዛዙን የግድያ ወንጀሎች እናወግዛለን፤ የህዝቡን ተቃውሞ እንደግፋለን። ስለዚህ በአገራችን ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲገነባ፣ የህዝባችን አንድነት እንዲጠናከርና የአገራችን ሉኣላዊነት እንዲከበር᎓- 1. ህወሓት/ኢህአዴግ ከስልጣን መወገድ አለበት 2. በኢትዮጵያውያን የፖለቲካ ድርጅቶች፣ ሲቪክ ማህበሮችና ብቃት ባላቸው ግለሰቦች የሽግግር መንግስት መቋቋም አለበት። ከዚህ በላይ የተጠቀሱትን ዓላማዎች ለማሳካት የሚከተለውን ጥሪ እያቀረብን ፣ እኛም ከህዝባችን ጐን ተሰልፈን ለትግሉ መሳካት የአቅማችንን እንደምናበረክት ቃል እንገባለን። 1. ሁሉም … [Read more...] about ከትህወሓት/ኢህአዴግ ከስልጣን ይውረድ የሽግግር መንግስት ይቋቋም
Opinions
ከኢሕብፓ በሃገራችን ወቅታዊ ሁኔታ የተሰጠ መግለጫ
የዘረኛውን ወያኔ አምባገነን የግፍ አገዛዝ ለማስወገድ ጀግናውና ሀገር ወዳድ ወገኖቻችን ለሃገራችሁ የምታደርጉት ታሪካዊ ተጋድሎና በጀግንነት የምትከፍሉት የህይወት መስዋትነት ሁሉንም ወገን የሚያኮራ ተግባር ነው። እኛ የኢትዮጵያ ሕዝብ ብሔራዊ ፓርቲ (ኢሕብፓ) አባሎች ከጎናችሁ ተሰልፈን የትግሉ አጋር ለመሆን አስፈላጊውን ትብብር: አስተዋጽዎና መስዋትነት ለመክፈል ቆርጠን ተነስተናል፡፡ (የመግለጫውን ሙሉ ቃል ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about ከኢሕብፓ በሃገራችን ወቅታዊ ሁኔታ የተሰጠ መግለጫ
ወልቃይት የማን ነው? የማይረባ ጥያቄ!
አንድ በነገረ አስተሳሰብ ወይም በአስተሳሰብ ሕግ (ሎጂክ) ትምህርት ላይ አንድ የማስታውሰው ምሳሌ አለ፤ ‹‹ሚስትህን መደብደብ ትተሃል ወይ?›› የሚል ጥያቄ ነው፤ ጥያቄው የሚነሣው ጠያቂው አውቃለሁ ብሎ ከያዘው እውቀት ወይም እምነት ነው፤ ስለዚህም ጠያቂው የሚፈልገው ጥያቄ ለማስተላለፍና መልስ ለማግኘት አይደለም፤ ጠያቂው የሚፈልገው በጥያቄ መልክ የራሱን ‹‹እውቀት›› ወይም እምነት ለተጠያቂው ለማስተላለፍና ተጠያቂውን የጠያቂው ደቀ መዝሙር ለማድረግ ነው፡፡ ሚስትህን መደብደብ ትተሃል ወይ? መልስ የሌለው ጥያቄ ነው፤ ‹‹አዎ›› የሚል መልስ ሰውዬው ሚስቱን ሲደበድብ እንደነበረ አመነ ማለት ነው፤ ‹‹አልተውሁም›› ከአለ በራሱ ላይ መሰከረ፤ ሁለቱም መልሶች ተጠያቂውን የሚያስወነጅሉ ስለሆኑ መልስ አይደሉም፤ ከዚያም በላይ ጥያቄው ትክክል አይደለም፤ የማይረባ መጥፎ ጥያቄ … [Read more...] about ወልቃይት የማን ነው? የማይረባ ጥያቄ!
ዱቼ ሙሶሊኒ! ቻው ፋሽስት ወያኔ
ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ … [Read more...] about ዱቼ ሙሶሊኒ! ቻው ፋሽስት ወያኔ
ትድረስ በዚህ ዘመን ላላችሁ ካህናት
በምድራችን ላይ የሚደረጉት ነገሮች በጊዜ፤ በሚፈጸምባቸውና በሚፈጽሙት ሰዎች ይለያዩ እንጅ፤ ድግግሞሽ ናቸው። ባህታዊ አምኃ ኢየሱስ በወያኔ መንግሥት በተበደለው በጎንደር ህዝብ መካከል ቆመው ያሰሙን ድምጽ፤ በጣሊያን ወረራ ጊዜ እነመምህር ገብረ ኢየሱስ ላሰሙት ድምጽ ድጋሚ ነው። ወያኔ በወገን በአገር ላይ የሚፈጽመውን ግፍና መከራ በዝምታ በማለፍ ላይ ያላችሁ፤ ከህዝብ ጋራ አለመታየትን የመረጣችሁ ካህናት ሰባክያንና ጳጳሳትም፤ በጣሊያን ጊዜ ጣሊያንን ላለመስቀየም ዝም ያሉትንና ከህዝብ መካከል የተደበቁትን የካህናትን ዝምታ ደገማችሁ። የተደገመ ነው ብልም፤ ወያኔዎች በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የሚፈጽሙት መከራና ግፍ፤ ጣሊያኖች ከፈጸሙት መከራና ስቃይ ጋራ ስናነጻጽረው፤ ወያኔዎች የፈጸሙት ከተመሳሳይነቱ እጅግ የራቀ፤ የባሰና የከፋ እንደሆነ፤ በዚህ ዘመን ዝም ያላችሁትንና፤ ከህዝብ መካከል … [Read more...] about ትድረስ በዚህ ዘመን ላላችሁ ካህናት
ለመፍትሔው መፍትሔ
በሌ/ጄ ፃድቃን ገ/ተንሳይ የመፍትሔ ሀሳቦች ምላሽ ለ፡ ሌ/ጄ ፃድቃን ገ/ተንሳይ “የሃገራችን ፖለቲካ ሁኔታና የመፍትሔ ሀሳቦች” ጽሁፍ እነሆ 17 ዓመት በበረሃ 25 ዓመት በመንግሥት ሥልጣን የተቆናጠጠው ወያኔ ዛሬ የሥልጣን ዘመኑ ማብቂያው የመጨረሻው መጀመሪያ ላይ ደርሷል። በትግሉ ላይ ነበርን ብቻ ሳይሆን በከፍተኛ አመራር እርከን ላይ ነበርን የሚሉ የወያኔ ባለሥልጣን፤ የድርጅታቸውን 17 ዓመት የትግል ጉዞ አብረው ፕሮግራም ሲነድፉ፣ ፖሊሲ ሲያወጡ፣ የትግራይ ነፃ አውጪ ብለው በዘር ሲደራጁ፣ የዐማራ የበላይነት ሰፍኗል ብለው አማራ ላይ ሲያነጣጥሩ፣ የብሔር/ብሔረሰቦች መብት እስከመገንጠል ብለው የዘር ፖለቲካ ሲያራምዱ፣ ኤርትራ በኢትዮጵያ ቅኝ ተይዛለች ብለው ከሻቢያ ጋር ለኤርትራ ነፃነት ሲታገሉና ሲያታግሉ የነበሩ ዋናው የድርጅቱ አመራር ባልደረባ ዛሬ የወያኔ ወንበር እንዳበቃለት … [Read more...] about ለመፍትሔው መፍትሔ
ለኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ጥብቅና!
ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱን በግሌ አላውቀውም፤ ነገር ግን እስከሚበቃኝ ድረስ አውቀዋለሁ። ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ እኔን አያውቀኝም፤ ነገርግን እኔና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ጠበቆቹ እንዳለን ያውቃል። ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ጎንደር ውስጥ አንገረብ እስርቤት ባሁኗሰዓት - ምሽት፣ ረቡዕ ሐምሌ ፳፯ ቀን ፳፻፰ ዓመተ ምህረት - ለጊዜው አለ። እዚያ እንዲቆይ ያደረገው ወገኑ ነው። ሁላችንም እንደምናውቀው፤ በእስርቤት ያለ ግለሰብ፤ በትክክል ይሁን በድፍረት በመታሰሩ ብቻ፤ ጠበቃ ያስፈልገዋል። እናም ጠበቃው ነኝ። (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about ለኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ጥብቅና!
የነፍጠኞች ፖሊቲካ
ነፍጠኛነት ባህላችን ነው፤ ፖሊቲከኛነት አዲስና ባዕድ የትግል ዘዴ ነው፤ ፖሊቲከኛነትና ነፍጠኛነት ተቃራኒ ተግባሮችን ያመለክታሉ፤ ተቃራኒ ተግባሮች አብዛኛውን ጊዜ ተቃራኒ ዘዴዎች ያስፈልጋቸዋል፤ ለምሳሌ መፍጨትና መቡካት ተቃራኒ ተግባሮች ናቸው፤ መፍጨት ሲበታትን፣ ማቡካት ሰብስቦ ያያይዛል፤ የሚፈጭ ሰው ማቡካት ይችላል፤ እንዲሁም ማቡካት የሚችል ሰው መፍጨት ይችላል፤ ፈጪ አቡኪ መሆን የሚችለውን ይህል ወይም አቡኪ ፈጪ መሆን የሚችለውን ያህል ነፍጠኛ ፖሊቲከኛ ወይም ፖሊቲከኛ ነፍጠኛ መሆን ይችላል ወይ? መልሱ ግልጽ ነው፤ አይችልም፤ የነፍጠኛ ትግል በጠመንጃ ነው፤ የፖሊቲከኛው ትግል በቃላት፣ በንግግር ነው፤ በሌላ አነጋገር የነፍጠኛ በዱላ፣ የፖሊቲከኛ ትግሉ በመላ ነው፡፡ የፖሊቲካ ሥልጣንን ነክሶ ይዞ ሕዝብን በሕዝብ በዱላ እያደባደቡ በማሸነፍም ሆነ በመሸነፍ የሥልጣንን ክብር ማግኘት … [Read more...] about የነፍጠኞች ፖሊቲካ
ታሪካዊው የጎንደር ሰልፍ እና እንድምታው
በሰሞነኛው የአዲስ አቤ ቀልድ ልጀምር። ወጣቱ፣ ሱሪ ለመግዛት ወጥቶ አንድ የልብስ ሱቅ ወስጥ ገባ። ባለ ሱቁ ጠየቀው። “የቻይና ይሁንልህ ወይንስ የአውሮፓ ሱሪ?” ወጣቱም መለሰ። “የለም የለም... የጎንደሩን ሱሪ ነው የምፈልገው።” እስረኞችን የማስፈታቱ ሰላማዊ ጥያቄ የእብሪት መልስ ሲያገኝ፤ ጨዋታውም ተቀየረ። “እንዲያውም አናውቅህም። ከህዝብ ጫንቃ ላይ ወረድ” ሲል ነበር የጎንደር ሕዝብ ብረትን ሰብሮ ዙፋኑን የነቀነቀው። “ወንዱን በምርቃና ሴቱን በቃና አደንዝዘን ይዘነዋል!” ያሉት ሕዝብ ከቶውንም እንዳልተዘናጋ አሳየን.... የመናገር እና ሃሳብን ያለፍርሃት የመግለጽ መብትን ህወሃት ሲፈልግ የሚሰጥ ሲያሻው ደግሞ የሚነፍገው የግል ሃብቱ አድርጎ ለ25 አመታት ሰንብቶ ነበር። ይህ መብት በኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ አሸብርቆ ጎንደር ላይ ተከበረ። በባህርዳር፣ በደሴ፣ በኦሮምያ፣ … [Read more...] about ታሪካዊው የጎንደር ሰልፍ እና እንድምታው
ሕዝብን አፍኖና በኃይል ረግጦ መግዛት ያብቃ!
ባለፈው እሁድ ትንሽ ትልቅ፣ ወንድ ሴት፣ ከተሜ ገጠሬ፣ ሳይል የጎንደር ሕዝብ ከዳር እስከ ዳር በነቂስ ወጥቶ ከተማዋን ባጨናነቀ መልኩ የህወሓት አገዛዝ የፈጠረውን የሽብርና የፍርሃት አጥር ሰብሮ በመውጣት የተቃውሞ ድምጹን በሰላማዊ መንገድ አሰምቶ ወደቤቱ ተመልሷል። ምንም እንኳን አገዛዙ የተቃውሞ ሰልፉ እንዳይካሄድ ማናቸውንም እርምጃዎች ቢወስድም፣ ግፍ የበዛበት፣ የቆረጠና የተባበረን ሕዝባዊ ማዕበል የሚመክተው አንዳችም ምድራዊ ኃይል የለምና ከፍተኛ ጨዋነት በተሞላው መልክ ሕዝቡ ተቃውሞውን አሰምቷል። በዕለቱ ካስተጋባቸው መፈክሮች ውስጥ "በኦሮሚያ የሚደረገው የወገኖቻችን ግድያ ይቁም" የሚለው የጎንደር ሕዝብ ምንጊዜም በኢትዮጵያዊነትና በሀገር አንድነት ላይ ያለው የሚታወቀውን ጠንካራ አቋሙን ያሳየበትና የትግል አጋርነቱን በግልጽ ያንጸባረቀበት ነው። ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውስጥ የሕዝብ … [Read more...] about ሕዝብን አፍኖና በኃይል ረግጦ መግዛት ያብቃ!










