ከዚህ በታች የተጻፈውን ፕሬዚደንት ትራምፕ አለ ተብሎ ፌስቡክ ላይ ያገኘሁት ነው፤ “ነፃነታችሁን ካገኛችሁ ከ50 ዓመታችሁ በኋላ ለሕዝቦቻችሁ አስፈላጊውን የመገናኛ ዘዴ ካልሠራችሁላቸው እናንተ ሰው ናችሁ? እናንተ በወርቅ ላይ፣ በዕንቁ ላይ፣ በዘይት ላይ፣ በማንጋኒዝ ላይ፣ በዩራኒየም ላይ ተቀምጣችሁ ሕዝቦቻችሁ የሚበሉት ሳይኖራቸው ሲቀር እናንተ ሰው ናችሁ? እናንተ በሥልጣን ላይ ሆናችሁ የጦር መሣሪያ ከባዕዳን ለመግዛትና ዜጎቻችሁን ለመግደል የማታመነቱ ከሆነ እናንተ ሰው ናችሁ? የናንተ ማኅበረሰባዊ ዓላማ ሕይወታችሁን በሙሉ በሥልጣን መንበር ላይ መቆየት ከሆነ እናንተ ሰው ናችሁ? እንደሚታደን አውሬ ዜጎቻችሁን የምትገድሏቸው ከሆነ ማን ያከብራቸዋል? ” (ባለቤት ያቀለለውን አሞሌ ባለዕዳ አይቀበለውም!) እነዚህ ሁሉ እውነቶች የሚያጠራጥሩ አይመስለኝም። … [Read more...] about “እናንተ ሰው ናችሁ?” ትራምፕ ለአፍሪካ መሪዎች
mesfin
ወልቃይት የማን ነው? የማይረባ ጥያቄ!
አንድ በነገረ አስተሳሰብ ወይም በአስተሳሰብ ሕግ (ሎጂክ) ትምህርት ላይ አንድ የማስታውሰው ምሳሌ አለ፤ ‹‹ሚስትህን መደብደብ ትተሃል ወይ?›› የሚል ጥያቄ ነው፤ ጥያቄው የሚነሣው ጠያቂው አውቃለሁ ብሎ ከያዘው እውቀት ወይም እምነት ነው፤ ስለዚህም ጠያቂው የሚፈልገው ጥያቄ ለማስተላለፍና መልስ ለማግኘት አይደለም፤ ጠያቂው የሚፈልገው በጥያቄ መልክ የራሱን ‹‹እውቀት›› ወይም እምነት ለተጠያቂው ለማስተላለፍና ተጠያቂውን የጠያቂው ደቀ መዝሙር ለማድረግ ነው፡፡ ሚስትህን መደብደብ ትተሃል ወይ? መልስ የሌለው ጥያቄ ነው፤ ‹‹አዎ›› የሚል መልስ ሰውዬው ሚስቱን ሲደበድብ እንደነበረ አመነ ማለት ነው፤ ‹‹አልተውሁም›› ከአለ በራሱ ላይ መሰከረ፤ ሁለቱም መልሶች ተጠያቂውን የሚያስወነጅሉ ስለሆኑ መልስ አይደሉም፤ ከዚያም በላይ ጥያቄው ትክክል አይደለም፤ የማይረባ መጥፎ ጥያቄ … [Read more...] about ወልቃይት የማን ነው? የማይረባ ጥያቄ!
የማፍረስ አባዜ
በአለፉት ሃያ አንድ ዓመታት፣ በተለይም ከ1997 ዓ.ም. ወዲህ፣ የወያኔ/ኢሕአዴግ አገዛዝ ልዩ መታወቂያው ያደረገው እያፈረሱ መገንባትን ነው፤ ማፍረስ ቀላል ሥራ ነው፤ ጭንቅላትም፣ ማሰብም አይጠይቅም፤ ልብም፣ ስሜትም አይጠይቅም፤ የሚጠይቀው የዝሆን አካልና ጉልበት ብቻ ነው፤ አንድ ቤተሰብ ስንት ዓመት በዚያ ቤት ውስጥ ኖረ? ጎረቤቶች ምን ዓይነት ትስስር አላቸው? በማኅበር፣ በእድር፣ በዝምድና በቤተ ክርስቲያን ወይም በቤተ መስጊድ፣ በመቃብር፣ በሥራ፣ በአጠቃላይ የእያንዳንዱ ሰው ኑሮ ከልደት ጀምሮ የተፈተለበትና የተደራበት ውስብስብ የኅብረተሰብ አካል መኖሪያ ነው፤ ይህንን አካል ለማፍረስ ትንሽ ጭንቅላትና ግዙፍ ጡንቻ ያለው አይቸግረውም፡፡ መኖሪያ ቤቶችን ማፍረስ፣ መቃብሮችን ማፍረስ፣ የንግድ ድርጅቶችን ማፍረስ፣ ትምህርት ቤቶችን ማፍረስ፣ … ማፍረስ… ማፍረስ… ማፍረስ! ሳያለቅሱ … [Read more...] about የማፍረስ አባዜ
ያስፈራል፤ ግን ኢትዮጵያ አትፈርስም!
ይቺ ኢትዮጵያ የምትባል አገር ስንት የመከራ ወንዞችን ተሻግራለች! ገና ስንት ትሻገራለች! ስንት የግፍ ተራራዎችን አቋርጣለች! ገና ስንት ታቋርጣለች! ስንት የበደል ሰይፎችንና ጦሮችን አምክናለች! ገና ስንት ታመክናለች! ስንት የውጭ ኃይሎችን አሳፍራለች! ገና ስንቱን ታሳፍራለች! ስንት አምባገ- ነኖችን እያለቀሰች ቀብራለች! ገና ስንቱን ትቀብራለች! ጭቆና ከኢትዮጵያውያን ደም ሙልጭ ብሎ ወጥቶ በነፃነት፣ በእኩልነት፣ በዳኝነት በጠራ ደም እስቲተካ ድረስ “ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ዘርግታ” ትጸልያለች! እግዚአብሔርም ቃል ኪዳን አለበት ይሰማታል! የኃያላን ኃያል ኢትዮጵያ እንድትፈርስ አይፈቅድም! የኢትዮጵያን መፈራረስ የሚመኙ ግለሰቦችም መንግሥቶችም ሞልተዋል፤ ኢትዮጵያ እንድትፈራርስ የሚመኙ ጭንጋፍ ልጆችም አሏት፤ ማኅጸንዋ እየደማ እየረገማቸው ሰላምና እንቅልፍ አጥተው … [Read more...] about ያስፈራል፤ ግን ኢትዮጵያ አትፈርስም!




