A. Introduction The Amharic version of the Voice of America (journalist Solomon Abate serving as moderator) entertained a discussion on corruption which was broadcast on May 17 and 18, 2013. Participants included Messrs. Mulugeta Aragawi of Addis Ababa University, Abebe Gutta (attorney at law in Addis Ababa), Berhanu Assefa (Ethical Education and Communication Affairs Director of the Federal Ethics and Anti Corruption Commission-FEACC) and I. The first two gentlemen who really knew the … [Read more...] about The Humanitarian Aid-Corruption Nexus in Ethiopia
Opinions
የአባይ ግድብ ዲፕሎማሲ አጀንዳ!
በአለም አቀፍ ደረጃ እንደ አባይ ግድብ አወዛጋቢ የሆኑ ጉዳዮች ተፈጻሚነት የሚያገኙት አለም አቀፍ የዲፕሎማሲ ትግል በማድረግ አለም አቀፍ ደጋፊ ማብዛት ሲቻል ነው። የዲፕሎማሲ ትግል ደግሞ ሰላማዊ ትግል ትግል በመሆኑ ብስለት እንጂ ክፉ ቃል አይሻም። ቀረርቶ ደጋፊን አስበርግጎ እንደሚያርቅ እና ለባላንጣ የማጥቂያ ቀዳዳ እንደሚከፍት ግልጽ ነው። የሆነው ሆኖ ይኽን ጽሁፍ እንድጽፍ ያነሳሳኝ የህውሃት ውጭ ጉዳይ ቴዎድሮስ እና አቻው የግብጹ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሰኔ 11 ግድም ዲፕሎማሲያዊ ውይይት አደረጉ ከተባለ በኋላ ቴዎድሮስ “አብረን እንዋኛለን ወይንም እንሰምጣለን” ማለቱን ካነበብኩ በኋላ በዚህ ጉዳይ ላይ ከኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ኃይሎች ጋር ውይይት መክፈት ያስፈልጋል የሚል እምነት ስላደረብኝ ነው። “አብረን እንዋኛለን ወይንም እንሰምጣለን” የሚለው የቴዎድሮስ አባባል “ግብጽ እና … [Read more...] about የአባይ ግድብ ዲፕሎማሲ አጀንዳ!
የአባይ ጉዳይ የዛፍ ላይ እንቅልፍ የሆነባት ግብጽ እና ለስልጣን ጸብ ጫሪው ህውሃት!
የአባይ ጉዳይ ለግብጽ የዛፍ ላይ እንቅልፍ ነው። ዛፍ ላይ ሆነህ እንቅልፍ ይወስድሃል? ሸለብ እንኳን ያደርግሻል ዛፍ ላይ ሆነሽ? እነደዚያ ነው የአባይ ጉዳይ ለግብጽ። ይኽ እንቅልፍ ማጣት እና ስጋት ዛሬ የጀመረ አይደለም። ባጭሩ ልተርክ። ሪቻርድ ፓንክረስት በግብጽ የተገኙ መረጃዎችን መሰረት በማድረግ ክርስቶስ ከመወለዱ ከ3 ሺ አመቶች በፊት ጀመሮ የግብጽ ነጋዴዎች በእግራቸው የአባይን ወንዝ ዳርቻ ተከትለው እንዲሁም በቀይ ባህር በነፋስ በሚገፉ ጀልባዎች ዛሬ ኢትዮጵያ (ያኔ የፐንት ግዛት) በሚባለው ግዛት ውስጥ ከሚኖረው ህዝብ ጋር የንግድ ልውውጥ ማድረጋቸውን እና ግዛቱን ምድረ ታ-ኔትጄሩ (Land Ta-Netjeru) ማለትም “ምድረ አማልዕክት” እንደሚሉት እና “የመጀመሪያ አገራችን ነው” ይሉም እንደነበር የኢትዮጵያውያን ድንበር-መሬቶች (The Ethiopian Borderlands) … [Read more...] about የአባይ ጉዳይ የዛፍ ላይ እንቅልፍ የሆነባት ግብጽ እና ለስልጣን ጸብ ጫሪው ህውሃት!
ከአረብ ሃገራት ሰማይ እስከ ሚሊንየም አዳራሽ!
እኔን ያሰፈራኝ ጎርበጥባጣው መንገድ . . . ኢትዮጵያውያን በግብጽ . . . ሰሞነኛ የማለዳ ወጌን ወደ እናንተ ላደርስ አንዱን አንስቼ አንዱን ስጥል አንድ ወዳጀ ስልክ ደውሎ በግብጵ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የአባይን ግድብ ውዝግብ ተከትሎ አደጋ ላይ መሆናቸውን መረጃ ቢጤ አቀበለኝ ። በማስከተልም ከጥቆማ መረጃው ጋር በቀጣዩ ቀን ነዋሪዎች በነቂስ ሰላማዊ ስልፍ ለማደረግ እንዳቀዱ በመግለጽ እንዳነጋግራቸው መከረኝ ። መረጃ ለመሰብሰብ የሚረዱኝን ወንድሞች አድራሻ የሰጠኝን ወንድም አመስግኜ ወደ ሃገረ ግብጽ ካይሮ ደጋግሜ ደወልኩ። ከብዙ ጥረት በኋላ ግን የፈለግኩትን መረጃ ሙሉ በሙሉ ባላገኝም ያገኘሁትን ሰባስቤ ለተጨማሪ መረጃ የሚረዱኝን ተጨማሪ ስልክ ቁጥሮች ሰባሰብኩ። ያሰባሰብኳቸው መረጃዎች ግን ለኢትዮጵያ መጻኤ ህይወት እንድሰጋ እንድፈራ አድርገውኛልና ፈራሁ! ልቤ እንቢ እያለኝ … [Read more...] about ከአረብ ሃገራት ሰማይ እስከ ሚሊንየም አዳራሽ!
አባ ማትያስ “እንዲህ ያለ ፓትርያርክ አይተን አናውቅም”
". . . እንዲህ ያለ ሰው አይተን አናውቅም የሚለው ንግግር አንዱን ከሌላው ጋራ በተመሳሳይ መስፈርት አነጻጽሮ ልቆ የተገኘውን ከፍ አርጎ ለማቅረብ ነው። ይህን ቃል ካፋቸው አውጥተው የተናገሩት አባ ማትያስ ናቸው። የተናገሩትም ለብጹዕ አባታችን ፓትርያርክ ተክለ ሃይማኖት ነው። ምን ጊዜና እንዴት ተናገሩት? አቅራቢውስ ይህን ምስክረነት ለመግለጽ ያስቻለው በዚህ ወቅት የት ነበር? የሚሉ ጥያቄዎች ባንባቢ ህሊና ላይ መፈጠራቸው አይቀርም። "ለምስክርነት ያበቃኝን ዝርዝር በዚህች ጦማር ለማቅረብ ሰአት ወስኖኛል። አስፈላጊ ከሆነ ዝርዝር ሀተታውን ከዚህች ጦማር ቀጥየ ማቅረብ እችላለሁ። . . ." (ሙሉውን ጥናታዊ ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about አባ ማትያስ “እንዲህ ያለ ፓትርያርክ አይተን አናውቅም”
ኢሕአፓ በአዲስ አበባ በርካታ ቦታዎች በህቡዕ ወረቀት በተነ
በስውር የሚንቀሳቀሱ የኢትዮጵያ ህዝብ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ)አባላት በአዲስ አበባ በርካታ ቦታዎች ረቡዕ ሌሊት ሰኔ 5/2005 ዓ.ም. /June 12, 2013/ "ተነሥ" በሚል ርዕስ የተዘጋጁ ቀስቃሽ ፅሑፎችን የበተኑ ሲሆን በዋናነት በቦሌ፣በካዛንቺስ፣በአራት ኪሎ፣በሽሮ ሜዳ፣በቄራ፣በፈረንሳይ ለጋሲዪን፣በሜክሲኮ፣በፒያሳ፣በመገናኛ፣በኮልፌ፣በመርካቶ፣በጎፋ እና በመሳሰሉት ዋና ዋና የከተማዋ ክፍል በሚገኙ የማስታወቂ ቦርዶች ላይ ተለጥፈው የታዩ ሲሆን በተለይ ሐሙስ ሰኔ 6/2005 ዓ.ም. በርካታ ነዋሪዎች ጽሑፉን ማንበብ ችለዋል።ይሁን እንጂ ይህ ዜና የደረሳቸው የገዢው ፓርቲ አመራሮች ወዲያው የፌደራል ፖሊሶችን እና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አባላትን በማሰማራት በዋና ዋና ቦታዎች ላይ የሚገኙትን ያነሱ ሲሆን በአንዳንድ አካባቢ ግን ጽሑፎቹ እስከ ቀትር ሳይነሱ በበርካታ ሰዎች መነበብ … [Read more...] about ኢሕአፓ በአዲስ አበባ በርካታ ቦታዎች በህቡዕ ወረቀት በተነ
አስቸጋሪው ነገር አገርን መገንባት ነው!!
ወያኔን ማስወገድ አይደለም የሚያስቸግረው፤ አስቸጋሪው ነገር አገርን መገንባት ነው !! "We are just leaving barbarism and are still entirely at the beginning. The French, however have already gone a piece of the way and have a century`s lead in every respect.” Friedrich the Great II to Wilhelm of Prussia መግቢያ የወያኔን አገዛዝ ነፍስ ለመዝራት፣ ወይንም የአገዛዙን ዕድሜ ለማራዘም የሚደረገውን በአንዳንድ ምሁሮች የሚነዛውን የማያስፈልግ አጻጻፍ ትተን፣ እስከዛሬ ድረስ በተለይም ብዙዎቻችንን ያሰጨነቀንና የሚያስጨንቀን፣ የቀድሞዎቹ አገዛዝም ሆነ ወያኔ ያተራመሰውን አገር እንዴት መገንባት አለብን ? የሚለው ሳይሆን፣ እሱን አስወግዶ እንዴት ስልጣን መያዝ … [Read more...] about አስቸጋሪው ነገር አገርን መገንባት ነው!!
የአባይ ኢትዮ-ግብጽ ጦርነት ወይንስ የነፃነት ትግላችን!
አምባገነኖች ስልጣናቸውን ለማጠባበቅ አጋጣሚውን ሁሉ ይጠቀማሉ። ሰሞኑን የአባይን ግድብ አስታከው አምባገነኖቹ ህውሃት/ኢህአዴግ እና የግብጽ መንግስት መምታት የጀመሩት የጦርነት ከበሮም ከዚህ የተለየ አይደለም። የህዝባቸውን ብሄራዊ ክብር ስሜት ተቆጣጥረው የዲሞክራሲ ኃይሎችን ለማዳከም እና ስልጣናቸውን ለመጠጋገን የሚያደርጉት ድራማ ነው። ኢትዮ-ግብጽ ጦርነት አይቀሬ አይደለም። የግብጽ ዴሞክራሲ ኃይሎች ወደ ጦርነት አይሄዱም። የኢትዮጵያ ሰላማዊ ትግል ወታደር አይኑን ከነፃነት ትግሉ መንቀል የለበትም። የአባይ ወንዝ የሚጓዝበትን ሽምጥ ሸለቋማ ክፍል የአዲሱ ግድብ አካል ቢደረግ ግድቡ ሰፊ ቦታ እንዳይዝ፣ ውሃው ለጸሐይ ብዙ ተጋልጦ እንዳይተን እና መጠኑ እንዳይቀንስ ይረዳል። የግድብ ግንባታ ወጪም ይቀንሳል። ይኽን ተፈጻሚ ለማድረግ ደግሞ የአባይን ወንዝ ለጊዜው አቅጣጫውን ማስቀየር … [Read more...] about የአባይ ኢትዮ-ግብጽ ጦርነት ወይንስ የነፃነት ትግላችን!
አባይ የኢህአዴግ ኤአርቲ!
Nile River, Arabic Baḥr Al-Nīl or Nahr Al-Nīl river, the father of African rivers and the longest river in the world. It rises south of the Equator and flows northward through northeastern Africa to drain into the Mediterranean Sea. Encyclopedia Britannica. በዓለማችን በግዙፍነታቸው ከሚወደሱትና አንቱ ከተባለላቸው ወንዞች መሃል የአባይ ወንዝ /Blue Nile/ግንባር ቀደሙ ነው።ከ6ሺ ኪሎሜትር በላይ ርዝማኔ ያለው የኣለማችን ግዙፉ ወንዝ በርካታ አገሮችን እያቋረጠ የሜዲትሪያንያን ባህርን ይቀላቀላል። አባይ የሚያቋርጥባቸው አገሮች ደም ስር ሆኖ በማገልገልም ላይ ይገኛል።ምንም እንኳን የአባይ ወንዝ ምንጭና የ80 በመቶ ባለድርሻ … [Read more...] about አባይ የኢህአዴግ ኤአርቲ!
ታላቅ ሕዝባዊ የስብሰባ ጥሪ
ኢትዮጵያን እናድን አንድነት ማህበር በእስራኤል በአገራችን ኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ለመምከር ቅዳሜ ጁን 22 ቀን 2013 ሕዝባዊ ስብሰባ አዘጋጅቷል። በዕለቱም የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ በክብር እንግድነት ይገኛሉ። ስለሆነም በተጠቀሰው ቀን ከምሽቱ 8:00 ጀምሮ በኢየሩሳሌም ከተማ በያፎ 97 ብንያን ክላል ሕንጻ እንዲገኙና የበኩልዎን ተሳትፎ እንዲያደርጉ አስተባባሪ ኮሚቴው ጥሪውን ያቀርባል። ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 054-2950990 ወይም 052-4062853 ይደውሉልን አስፈላጊውን መረጃ ልንሰጥዎ ዝግጁ ነን። አስተባባሪ ኮሚቴው … [Read more...] about ታላቅ ሕዝባዊ የስብሰባ ጥሪ










