የሚወለድበትን መሬት ማንም ሰው አይመርጥም፤ የዘመኑ ቅንጦት ኢትዮጵያ አርግዞ አሜሪካ መውለድ ቢሆንም፣ ልጁ ምርጫው ውስጥ የለበትም፤ አንኳን ልጁ አባትዬውም ምርጫው ውስጥ የሚገባ አይመስለኝም፤ በእንደዚህ ያለው ኢትዮጵያን አስጠልቶ-ሌላ-እንዲሆን በተፈጠረ ቅንጦት የሚወለድ ኢትዮጵያዊ ምን እንደሚሆን መተንበይ ያዳግታል፤ ልጁ ወይም ልጅቱ በራሳቸው ዝንባሌ፣ ፍላጎትና ጥረት ከኢትዮጵያ ጋር ያላቸው ግንኙነት በእልህ ከአልተለወጠ እናቶቻቸው የተለሙላቸው ማንነት ከኢትዮጵያዊነት ይገነጥላቸዋል፤ ነገር ግን የኢትዮጵያዊነት ስሜት እንዲህ በቀላሉ ተቀርፎ የሚወድቅ አይደለም፤ ሲደንቀኝ የቆየ ነገር ልናገር፤ አንድ ጊዜ በኢሰመጉ ተልእኮ ካናዳ ሄጄ አንድ ስብሰባ ላይ አንድ አርመን ወጣት ነበረ፤ ይህ ሰው ለኢትዮጵያ ያለው ስሜት በጣም የጋለ ነበር፤ በሌላ ዘመን ደግሞ ፋጡማ ሮባ በአትላንታ ማራቶን … [Read more...] about የሚወለዱበት፣ የሚሞቱለትና የሚሞቱበት መሬት
Opinions
ይድረስ ለተገፋው ወገኔ !. . .
ይድረስ ትናንተም ሆነ ዛሬ ግፍ በነገሰባት ምድር ኑሮን በመከራ ለምትገፋው ወገኔ ! ይድረስ መልካም አስተዳደር ጠፍቶ በደል ለተጫነብህ ፣ ፍትህ ርትዕ ተዛብቶ የአስተዳደር ሚዛኑ ኑሮህን ላጨለመው ወገኔ ! ይድረስ ከዲስኩር ባላለፈ "የእድገት ስልጣኔ መንገድ እየተጓዝክ ነው " ለሚሉህ ፣ ይድረስ ግልጽነት በጎደለው "መልካም አስተዳደር" ለምትረገጠው ታጋሽ ወገን፣ ይድረስ ትናንትም ሆነ ዛሬ ከአብራክህ ወጥተው አንተን ያልሆኑ ፣ ህመምህ የማያማቸው፣ በደልህ በማይገባቸው የመንግስት ምስለኔ ልጆችህ እየተሰቃየህ ላለህው ! ይድረስ የግፍ በደል ቀንበር ከትከሻህ ላልወረደልህ፣ ስቃይ መከራው ላላባራልህ ይድረስ ለከልታማው ወገኔ! ይድረስ የአንድ ጎልማሳ እድሜን በጭቆና መግፋቱ እያመመህም ቢሆን ለቻለከው፣ በቁጣ አመጻን ከመግለጽ ተገትተህ ጎስቋላ ኑሮን በዝምታ፣ በይሁንታ እየገፋህ ላለህው … [Read more...] about ይድረስ ለተገፋው ወገኔ !. . .
በሕዝቡ ያልተመራ አመፅ፤ ሰላማዊ ቢሆንም ውጤቱ ሕዝባዊ አይሆንም
ሰላማዊ ፓርቲ የመጀመሪያውን ጥሩ አቅጣጫ አመልካች ሰላማዊ ሰልፍ ግንቦት ፳ ፭ ቀን ፳ ፻ ፭ ዓመተ ምህረት በአዲስ አበባ በማድረግ፤ የሕዝቡን የነፃነት ፍላጎት ባደባባይ አሳዬ። ይህ ታሪካዊ ነው። ተደጋጋሚ ሰላማዊ ሰልፎች መጪ መሆናቸውንና አይቀሬነታቸውን አረጋገጠ። ካሁን በፊት ታጋዮች፤ በተደጋጋሚ፣ በየቦታው፣ ሰላማዊና የትጥቅ አመፅ በማድረግ ግባቸውን ለመምታት ጥረት አድርገዋል። በሕዝቡ ላይ በደል እስካለ ድረስ፤ አመፅ በተለያዬ መልክና በተለያዩ ቦታዎች መቀጠሉ፤ የሕልውና ግዴታ ነው። ለዚህ ምስክር አያሻም። ሕዝባዊ ግቡ አንድ በሆነበት ወቅት ደግሞ፤ ለሕዝባዊ ግቡ የትግሉ አንድ መሆን፤ ግዴታ ነው። ማሳየት የፈለግሁት፤ ሰማያዊ ፓርቲ በጀመረው ሰላማዊ ሰልፍ ተነሳስትን፤ አሁንም የተለያዬ ሰላማዊ ሰልፍና የተነጣጠለ ትግል እያካሄድን፤ ሕዝባዊ ድል ለማግኘት ማሰብ የትም እንደማያደርሰን … [Read more...] about በሕዝቡ ያልተመራ አመፅ፤ ሰላማዊ ቢሆንም ውጤቱ ሕዝባዊ አይሆንም
Proving them wrong – the Ethiopian way.
They say all kinds of bad stuff about us. It is said so many times and so often sometimes some of us start to believe the lie. That is always the problem with being lied to. I am sure by now Woyanes are drunk with their own silly propaganda. The situation with us is that they used to own the means of communication and we were their potted plants waiting to be told, lectured and abused to no end. I have so many instances of this situation I just don’t know where to start. I believe 2005 is day … [Read more...] about Proving them wrong – the Ethiopian way.
ዜጎች ከስራ አጥነትና ከድህነትን ለማምለጥ ይሰደዳሉ
መብት አስከባሪ አላቸው ለማለት ግን አልደፍርም "በሽታውን ላልተናገረ መድሃኒቱ አይገኝም!" አልጀዚራ ቴሌቪዥን በኢትዮጵያ ለስደት ስለሚዳረጉ ዜጎች ዙሪያ ያሰራጨው መረጃ ቀልቤን ቢስብው በማለዳ ወጌ ልተነፍስ ብዕሬን አነሳሁ ። የአልጀዚራ ቴሌቪዥን Escaping Ethiopia's unemployment "በኢትዮጵያ ስራ አጥንትን ለመሸሸ " ያለው ዘገባ ስለ ስደቱ ከስደተኞች አንደበት፣ ለቀጣዩ ስደት እየተዘጋጁ ስላሉት ፣ ሰለ ህገ ወጥ አሸጋጋሪዎችና ስደቱን ለመገደብ መንግስት እየወሰደ ስላለው ጥረት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን እማኝ አድርጎ በዘገባው አሳይቶናል ። በዚሁ ዘገባ ላይ በቀረበው መረጃ ስደትን ለማስቆምና የአዘዋዋሪዎችን ወሽመጥ ለመቁረጥ የተጠና ስራ ላቀረቡ ወጣቶች ስደትን ለመገደብ በመንግስት የተቋቋመው ግብረ ሃይል ወደ 27 ሽህ ዶላር ያበድራል ተብሎ … [Read more...] about ዜጎች ከስራ አጥነትና ከድህነትን ለማምለጥ ይሰደዳሉ
የሮመዳን ዋዜማ እና ሮመዳን በሳውዲ
እንኳንስ ለኔ ቢጤ አፍላ የጎልማሳነት እድሜውን በሳውዲ እየገፋ ላለ ላንድ ሰሞን ጉብኝት ሳውዲን የመጎብኘት እድልን ላገኘ የሮመዳን ወር የጾምና የጸሎት ወር ልዩና የማይረሳ ትዝታ ይቋጠርበታል፡፡ በሮመዳን ዋዜማ የገበያ ጥድፊያ የተለመደ ነው፡፡ ጾሙን ለመያዝ የሚያስችሉ የምግብ ፍጆታና ቁሳቁሶችን ዋዜማ መገለጫ ሆኖ ከአመት አመት የሚስተናገድ ቀልብን ሳቢ ትዕይንት ነውና በዛሬው የማለዳ ወጋወጌ ስለ ሮመዳን ዋዜማ ከማውቀው ጥቂቱን ላካፍላችሁ ወድጃለሁ ! የፈቀዳችሁ ተከተሉኝ. . . . . . ጾም ሲፈታ ለሚቀርበው የጾም መፍቻ ተምርና ጣፋጭ መጠጦች ጨምሮ የምግብ ማዕዱን ለማድመቅ ታላቅ ቅናሽን በሚያደርጉት ትላልቅ የገበያ አዳራሾች የሚደረገው ግብይት ደምቆ የሚስተዋለው በሮመዳን ዋዜማ ባሉት ጥቂት ቀናት ውስጥ ነው፡፡ ለአረቦች ነዳጅ ለሰጠ ፈጣሪ ምስጋና ይግባውና የዘመኑ ቴክኖሎጂ … [Read more...] about የሮመዳን ዋዜማ እና ሮመዳን በሳውዲ
Reexamining Structural Adjustment Programs!
Introduction It is now almost 30 years that the structural adjustment programs (SAPs) were introduced, and implemented as a new approach to deal with the economic crises of many Sub-Saharan African countries. Especially after the second oil crisis in 1979, many African countries were severely affected by balance payments of deficits, increasing external debts, and internal economic crises as a result of huge trade deficits. Because of decreasing raw material prices on the world market, many … [Read more...] about Reexamining Structural Adjustment Programs!
የቆሎ ተማሪና ኢትዮጵያዊነት
በኢትዮጵያዊ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ካህናትርእዮት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መሰረታውያን የሆኑትን ዓበይት ነገሮችን ፩ኛ ዘመን ያስቆጠሩትን ሶስቱ እምነቶች ፪ኛ የሚወራረሱባቸውን ጥቂት ነገሮች ፫ኛ ያሉበትን የጨለማ ዘመን ፬ኛ የእሳትን አስፈላጊነት ለማሳየት በቆሎ ታማሪነት ርእዮት ለማቅረብ እሞክራለሁ። የቆሎ ተማሪ ኢትዮጵያዊነትን እንዴት ያየዋል? (ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about የቆሎ ተማሪና ኢትዮጵያዊነት
Special Issue on the Ethiopian Economy
Announcement Re: Ee-JRIF Vol.5, no.1 : Special Issue on the Ethiopian Economy is finally out now! It is with great pleasure that the editors announce the publication of this important special issue on the Ethiopian economy after a review process that took two years! Below please access the link http://www.nesglobal.org/eejrif4/eejrif-v-5-1-13.php We hope all the stakeholders involved directly or indirectly with the Ethiopian economy will read the papers and the book … [Read more...] about Special Issue on the Ethiopian Economy
የኢትዮጵያዊያን ትግል
ክፍል አንድ የመድረክ የአደባባይ ውይይትን በመንተራስ የአንድነት ፓርቲ ግምገማዉንና የመድረክ አመራር መልሱን በአደባባይ ማቅረባቸው ታላቅ በር ከፋች ጥረት ነው። አንድነት መድረክን ብቻ ሳይሆን፤ የራሱን አመራር አካላትም ገምግሞ ለኢትዮጵያዊያን ማሳየቱ፤ ብስለቱንና ጥንካሬውን አመልካች ነው። ከመድረክ በኩል የተሠጠውም መልስ፤ በድብቅ ሳይሆን በአደባባይ መውጣቱ የሚያኮራ ነው። እዚህ ላይ አንዱም ሆነ ሁለቱ ትክክል ናቸው ወይንም ስህተተኞች ናቸው ማለቴ አይደለም። ጥረታቸው የሚያኮራ መሆኑን ለመጠቆም ነው። በዴሞክራሲያዊ ማዕከልነት ስምና በፓርቲ አባልነት ግዴታ ማነቆ ልሳናቸው ሳይዘጋ የተጻጻፉበት ምልልስ፤ ትልቅ ትምህርት ለሁላችን ሠጥቷል። እስከዛሬ ያልተለመደው ግልፅነት በሩ ተከፈተለት። ራሳችንን መገምገም ራሳችንን ዝቅ እንደማድረግ ስለሚወሰድና ይኼን ማድረግ እንደተቸናፊነት … [Read more...] about የኢትዮጵያዊያን ትግል










