ከመተካካት አልፈው ራሳቸውን "recycle" ያደረጉትን የህወሃት/ኢህአዴግ ሹሞች ያካሄዱትን ውይይትና የሕዝቡን አስተያየት የጀርመን ድምጽ ሬዲዮ ዘግቧል - "የኢህአዴግ ከፍተኛ ባለስልጣናትና የኢትዮጵያ ሁኔታ" በሚል ርዕስ የታተመው ዘገባ እንዲህ ይነበባል:- ኢትዮጵያን የሚመራዉ የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) በቅርቡ ካካሔደው ግምገማ በኋላ በሥራ አስፈጻሚዎቹ ዘንድ ሹም ሽር ሊያካሂድ መሆኑን እየተናገረ ነው። የገዢው ግንባር ሹም ሽርም ይሁን ግምገማ ግን ለውጥ ለማምጣቱ በርካቶች ጥያቄ አላቸው። ከሩብ ምዕተ-ዓመት በላይ በስልጣን ላይ የቆየው የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) ከገባበት አጣብቂኝ ለመውጣት ተሿሚዎቹን ሊገመግም እንደሆነ አስታውቋል። ከጠቅላይ ሚንስትር ሐይለ ማርያም ደሳለኝ አማካሪዎች መካከል አቶ አባይ ፀኃዬ … [Read more...] about “… መብከት፣ መበስበስ ከአንዴ በላይ ይደብራል …” ሕዝብ
News
የቂሊንጦ እስር ቤት ቃጠሎ ለህወሃት ፈተና ተጨማሪ ነዳጅ ሆነ!!
የኢትዮጵያ ፖለቲካ ቀውስ ከቀን ወደቀን እየጋመ ነው። ህወሃት ችግሮችን በሰከነ መንፈስ ከመፍታት ይልቅ ክተት አውጆና ንጹሃንን እየፈጀ ይገኛል። ሥልጣን ከያዙ ጀምሮ የረባ ትዕዛዝ ሰጥተው የማያውቁት ሃይለማርያም “አዝዣለሁ" ሲሉ በወገኖቻቸው ላይ ሞት አውጀው ቀውሱን አግመውታል። አፍቃሪ ህወሃቶችም የ“ቅምጡን ባሪያ ጠቅላይ ሚኒስትር” “ትዕዛዝ” ተከትለው “ትዕግስትም ገደብ አለው” እያሉ በየሚዲያውና በማህበራዊ ገጾች እያሽካኩ ነው። ሕዝብ “መሳሪያ አጣን” እያለ ጥሪ እያቀረበ ነው። ያም ሆኖ ምሬት የገፋቸው ሁሉ አመጹን ገፍተውበታል። በከፋፍለህ ግዛ የፖለቲካ ቁማር ህዝብ እያናከሰ ላለፉት 25 ዓመታት አገር ሲገዛ የኖረው ህወሃት ዛሬ አደረጃጀቱና “አጋሬ” የሚላቸው የተለዩት ይመስላሉ። ኦህዴድ ከተናጋና ከከዳ ሰንብቷል። ብአዴንም መመኪያ ሊሆን የማይችልበት ደረጃ ደርሷል። ለዚህም … [Read more...] about የቂሊንጦ እስር ቤት ቃጠሎ ለህወሃት ፈተና ተጨማሪ ነዳጅ ሆነ!!
“የባንኮች የመተርከክ (hack የመደረግ) ሽብር” አገሪቷን እንዳያናውጥ ተሰግቷል
ህወሃት/ኢህአዴግን በየቦታው እየናጠው ያለው ተቃውሞ በኢትዮጵያ የገንዘብ ቀውስ ሊያስከትል ይችላል የሚል ግምት ተሰጥቶታል፡፡ ችግሩ ባንኮች ላይ የገንዘብ እጥረት እንደሚያስከትልና ባንኮችን ሽብር ውስጥ ሊከታቸው እንደሚችል በስፋት እየተነገረ ነው፤ ደምበኞች ስለገንዘባቸው የሚጠነቀቁበት ጊዜ አሁን ነው፡፡ ህዝባዊ ቁጣ ያሰጋቸው የአገዛዙ ተጠቃሚዎች የውጭ ምንዛሬ እየሰበሰቡ ሲሆን በፍርሃቻ ንብረት በማስያዝ ከባንክ የሚበደሩት ክፍሎች ቁጥርም በርካታ ሆኗል። ከ10 ወራት በላይ ያስቆጠረውና ለተጨማሪ የኢኮኖሚ ማዕቀብ ቀን የቆረጠው የኦሮሞ ህዝባዊ እምቢተኛነት (#OromoProtests) ያስከተለውን መንኮታኮት ህወሃት በይፋ ባያሳውቅም በግብር አሰባሰብ፣ በውጭ ምንዛሬ፣ በጠቅላላ የውጭና የውስጥ ንግድ የገቢ ስርዓቱን እንዳናጋው ከፋይናንስ ተቋማት የተገኙ መረጃዎች ያመለክታሉ። ይህ እንግዲህ … [Read more...] about “የባንኮች የመተርከክ (hack የመደረግ) ሽብር” አገሪቷን እንዳያናውጥ ተሰግቷል
ህወሃት/ኢህአዴግ በአማራው ሕዝብ ላይ የዘር ዕልቂት (genocide) አወጀ
በአማራ ክልል እየተቀጣጠለ የመጣውን ሕዝባዊ እምቢተኝነት (#AmharaResistance) ፖለቲካዊ መፍትሔ ከመፈለግ ይልቅ የመከላከያ ኃይል እርምጃ እንዲወስድ ሃይለማርም ደሳለኝ በኦፊሴል አዟል፡፡ በትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሃት) ሙሉ ቁጥጥር ሥር ያለው የሃይለማርያም የጠቅላይ ሚኒስትርነት ሥልጣን በየቦታው “በቃን፤ አንፈልግም” የተባለውን የህወሃት የበላይነትን እንደገና ለማስፈን የጦርነት አዋጅ አውጇል፡፡ በኦሮሚያ (#OromoProtests) ለ10 ወራት የዘለቀው የኦሮሞን ሕዝብ የመፍጀት ሥልታዊ ጥቃት አሁንም የበርካታዎችን ደም እያፈሰሰ ባለበት ባሁኑ ወቅት በአንድ ክልል ሕዝብ ላይ የተነጣጠረው ይህ በሃይለማርያም ትዕዛዝ የተሰጠው የህወሃት እርምጃ ታሪክ የማይረሳው፣ ሰላም ሊያመጣ የማይችል፣ የዕድሜ ልክ ቁርሾ የሚያስከትል የዘር ማጥፋት (genocide) ወንጀል … [Read more...] about ህወሃት/ኢህአዴግ በአማራው ሕዝብ ላይ የዘር ዕልቂት (genocide) አወጀ
አሜሪካ፡ “ህወሃት አብቅቶለታል”
በኢትዮጵያ የስርዓት ለውጥ እንዲካሄድ የማይፈልጉት የአሜሪካ ባለስልጣናት ህወሃት አገር መምራት የማይችልበት ደረጃ ደርሷል የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሰዋል። የሚያደርጉትን ቢያውቁም ለመፍትሄ በተናጠል ተቀናቃኝ ፓርቲዎችንና የሲቪክ ማህበራትን “ምክር” እየጠየቁ ነው። አሁን ያለው ህዝባዊ ተቃውሞ በዚህ ከቀጠለ ኢትዮጵያን ላለማጣት ድንገተኛ የሚመስል ግን የታቀደ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ሊደረግ እንደሚችልም ፍንጭ እየተሰጠ ነው። የጎልጉል ታማኝ መረጃ ሰዎች እንዳሉት የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሃት) እንዳበቃለት የገመገሙት የአሜሪካ ባለስልጣናት “ከወዲሁ አንድ ነገር ማድረግ አለብን” የሚል አቋም ከያዙ ሰነባብተዋል። ለዚሁም መነሻቸው ህወሃት መልሶ እንዲያገግም ሊረዱት አለመቻላቸውና ለራሳቸው ጥቅም ሲሉ የኢትዮጵያን መክሰር አለመፈለጋቸው ነው። “ህወሃት አገር መምራት … [Read more...] about አሜሪካ፡ “ህወሃት አብቅቶለታል”
ከ25 ዓመት በኋላ!
የዛሬ 25 ዓመት ሟቹ "ባለ ራዕይ እንዳይነሣ አድርገን ቀብረነዋል" ያሉት "ጨርቅና አስተሳሰብ" 25 ዓመት እና ከዚያ በታች በሆኑ እንደገና ተውለብልቧል! ምን ይሆን "ትምክህተኛ" ያደረጋቸው? እውነታው ወይስ የህወሃት ዘረኝነትና ጠባብነት?! … [Read more...] about ከ25 ዓመት በኋላ!
ሕዝባዊ ተቃውሞው ኢኮኖሚውን እየጎዳው ነው!
በኢትዮጵያ የተለያዩ ቦታዎች የተነሳው ሕዝባዊ ተቃውሞ በአገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ እያደረሰ መሆኑ ተሰማ፡፡ የአመጹ ሒደትና ብርታት ያሳሰበው ህወሃት ከመግደል በላይ እንዴት እንደሚያጠብቀው ባያሳውቅም “ጥብቅ እርምጃ” መውሰድ እንደሚጀምር ተናገሯል፡ ህወሃት ለማመን ባይፈልግም ለአስር ወራት የዘለቀው የኦሮሞ ተቃውሞ በክልሉ የንግድና ሌሎች ተቋማት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ አሳድሯል፡፡ ከክልሉ ወደሌሎች የሚደረገው የንግድ፣ የዕቃ፣ የገበያ፣ የሰው ኃይል፣ የገንዘብ፣ … ዝውውር በተቃውሞው ምክንያት በርካታ መስተጓጎሎች ደርሰውበታል፡፡ ከዚህም አልፎ አገሪቱ ለውጭ ንግድ በምታቀርበው ምርትና በምትሰበስበው ግብር ላይ የሚያስከትለውን ጫና ከክልሉ ስፋት አኳያ እጅግ ሰፊ እንደሚሆን ይገመታል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ በአማራው ክልል የተነሳው ተቃውሞ ችግሩን በይበልጥ እያባባሰው እንደሆነ … [Read more...] about ሕዝባዊ ተቃውሞው ኢኮኖሚውን እየጎዳው ነው!
የአገሪቱ ዕዳ “20.6 ቢሊዮን ዶላር” ደርሷል
የውጭ እዳ በፍጥነት እየተከማቸበት የመጣው የኢትዮጵያ መንግስት፣ በ2006 ዓ.ም የብድር እዳ ከነወለዱ 570 ሚ. ዶላር መክፈሉ የሚታወስ ሲሆን፣ ዘንድሮ ክፍያው በእጥፍ ጨምሮበታል። ዘንድሮ እስከ መጋቢት ድረስ፣ 670 ሚ.ዶላር እንደከፈለ ከገንዘብ ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ ገልጿል። ከአራት አመት በፊት፣ የመንግስት ጠቅላላ የውጭ እዳ ወደ 9 ቢሊዮን ገደማ እንደነበረ የገንዘብ ሚኒስቴር ጠቅሶ፣ ዘንድሮ እስከ መጋቢት ወር ድረስ፣ የእዳው ክምችት 20.6 ቢሊዮን ዶላር መድረሱን አስታውቋል። በተለይ፣ በባቡር መስመር ግንባታ፣ በቴሌኮም እና ለአመታት በተጓተቱት የስኳር ፕሮጀክቶች ሳቢያ በፍጥነት እየተከማቸ ከመጣው ብድር ጋር፣ ለእዳና ለወለድ ክፍያ የሚውለው የውጭ ምንዛሬም እየከበደ እንደመጣ የሚኒስቴሩ ሪፖርት ያሳያል። በ2004 እና በ2005 ዓ.ም፣ ለእዳና ለወለድ ክፍያ የሚውለው … [Read more...] about የአገሪቱ ዕዳ “20.6 ቢሊዮን ዶላር” ደርሷል
“ተላላኪና አሸባሪ ነው” ኦህዴድ
* “ወደ ኢትዮጵያ ከተመለስኩ ሊገድሉኝ ይችላሉ” ፋይሣ ሊሊሣ በሪዮ ኦሎምፒክ በማራቶን ሁለተኛ የወጣው ፋይሣ ሊሊሣ “ወደ ኢትዮጵያ ከተመለስኩ ሊገድሉኝ ይችላሉ” በማለት የህወሃትን ጨካኝነት ለዓለም ገለጸ፡፡ የፋይሳ ጉዳይ ያገባናል የሚሉ ሁሉ ሊደርሱለት እንደሚገባ ተነገረ፡፡ አትሌቱን “አሸባሪና ተላላኪ” ሲል ኦህዴድ ኮንኖታል፡፡ የወርቅ ሜዳሊያ ከወሰደው ኬኒያዊ በላቀ ሁኔታ የዓለምአቀፍ ሚዲያን ትኩረት የሳበው ፋይሳ እዚያው ሪዮ ብራዚል በሰጠው ቃለምልልስ የኦሮሞ ተቃውሞ የሚያሳመላክተውን እጁን ከአናቱ በላይ በማጣመር ሳየበትን ምክንያት ገልጾዋል፡፡ “ተቃውሞዬን የገለጽኩት ለሕዝቤ ነው፤ ዘመዶቼ እስር ቤት ናቸው፤ እስር ቤት ሄጄ ከዘመዶቼ ጋር መገናኘት፣ እነርሱን መጠየቅ እፈራለሁ፤ ካወራህ ይገድሉሃል፤ ስለንደዚህ ዓይነት ነገር ማውራት በጣም አደገኛ ነው፤ (እዚያ አገር) ነጻነት … [Read more...] about “ተላላኪና አሸባሪ ነው” ኦህዴድ
ኢህአዴግ ወደ ወታደራዊ አገዛዝ ሊቀየር ይችላል
በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች እየተካሄደ ያለው የሕዝብ እምቢተኛነት ያሰጋው የኢህአዴግ አገዛዝ በይፋ ወታደራዊ አገዛዝ ለማወጅ ዕቅድ እንዳለው እየተሰማ ነው። ህወሃት ወታደራዊ አገዛዝን ለማወጅ አማራጭ መንገድ የያዘው “አጋር” በሚላቸው ድቃይ ድርጅቶቹ ላይ ያለው እምነት እየተሟጠጠና የቀድሞው ታዛዥነታቸው በመመናመኑ ነው። አገርን ለማዳን በሚል ለአሠራር ያልተመቹትን እያስወገደ ለብቻው ይነግሣል ተብሎ ተነግሯል፡፡ የጎልጉል ዜና አቀባዮች የመረጃ ምንጮቻቸውን ጠቀሰው እንደዘገቡት በኢህአዴግ ስም ህወሃት ራሱ ያደራጃቸው “አቻ ድርጅቶች” አሁን የተነሳበትን የከፋ ተቃውሞ እንደተቀላቀሉበት፣ በነዚሁ ታዛዥ ድርጅቶች አማካይነት የተዘረጋው የጥርነፋና የስለላ ሰንሰለት መፈረካከሱና አባላቱ እንደከዱት ከድምዳሜ ላይ ደርሷል። በዚህም የተነሳ ሁኔታዎች ከቁጥጥር ከወጡና ህዝባዊ እምቢተኛነቱ ከሁለቱ … [Read more...] about ኢህአዴግ ወደ ወታደራዊ አገዛዝ ሊቀየር ይችላል










