ከዋሽንግተን ዲሲና ከአካባቢው እንዲሁም ከተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች የመጡ ኢትዮጵያውንና ኢትዮጵያውያን አሜሪካውያን በዛሬው እለት በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት፣ በዋይት ሃውስ እና በዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት ደጃፎች የተቃውሞ ሰልፍ አካሄዱ። ሕጻናት የያዙ እናቶችና አዛውንቶች ጭምር የነበሩበት እጅግ የበዛ ቁጥር ያለው ሰላማዊ ሰልፈኛ ከማለዳው አንስቶ ነው “በዚያች አገር እየተካሄደ ነው” ያለውን ግድያ “በአፋጣኝ አስቁሙ!” እና “ለመንግስቱ የምትሰጡትንም እርዳታ አቋረጡ” የሚሉ ጥያቄዎችን ላቀረበላቸው የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ባለሥልጣናትና የምክር ቤት አባላት ሲያሰማ የዋለው። ሳያቋርጥ ቀኑን በዘለቀው ካፊያ ውስጥ ከውጭ ጉዳይ ሚንስቴር መሥሪያ ቤት ወደ በዋይት ሃውስ አልፎ ከምክር ቤት የሚያደርሱትን የከተማይቱን ጎዳናዎች ሞልቶ ሲሰማ የዋለውን … [Read more...] about “እኛ ዝናብ ነው ‘ሚወርድብን ያገሬ ልጆች ግን ደማቸው እየፈሰሰ ነው” የ1 ዓመት ህጻን እናት
News
“ይቺ ሀገር እንደ ሀገር እንድትቀጥል ከተፈለገ እኛ አድማጭ እናንተ ተናጋሪ የምትሆኑበት አካሄድ ማክተም አለበት”
በዩኒቨርሲቲው የቦርድ ሊቀመንበር አቶ ካሳ ተ/ብርሀን አጠቃላይ የውይይት መድረኩ መነሻ አሳብ ትረካ እና የእለቱ የውይይት አጀንዳ በሆነው ያለፉት 25 ዓመታት የትምህርት ጥራትና ተደራሽነት ጉዞ ዙሪያ የሚያጠነጥን ገለፃ በኋላ በምርጦቹ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን የተነሱ አስተያቶች እና የአካሄድ ጥያቄዎች:- 1. የመጀመሪያ ተናጋሪ፡- 1.1 “የዚህ ወይይት አጀንዳ ከጠበኩት በታች ወርዶብኛል በወላይቲኛ አንድ አባባል አለ - ያቺ እንትን'ኮ ወደቀች ቢሏት፤ ቀድሞም አቀማመጧ ለመውደቅ ነው አለች”፡፡ 1.2 “ካሳ! አንተ ሚኒስትር ነህ በዛ ላይ የዩኒቨርሲቲያችን የቦርድ ሊቀመንበር በዚህ ሁሉ ኃላፊነት ውስጥ ሆኖ PhD candidate መሆን አይቻልም ስለዚህ ስራህን ልቀቅ” 1.3 “ጠቅላይ ሚኒሰትሩ ይምጣና ያወየን፣ እናንተ ውረዱና ከእኛ ጋር ተቀመጡ” 2. ሁለተኛ ተናጋሪ … [Read more...] about “ይቺ ሀገር እንደ ሀገር እንድትቀጥል ከተፈለገ እኛ አድማጭ እናንተ ተናጋሪ የምትሆኑበት አካሄድ ማክተም አለበት”
“ህወሃቶች – ምንድነው የሚፈልጉት? ደም አይጠግቡም?”
“ሊገባኝ አልቻለም” ሲሉ ይጀምራሉ። በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለው የጅምላ ጭፍጨፋ ረፍት እንደነሳቸው ያስረዳሉ። አገሪቱ በደም እየታጠበችና በቂም እየነፈረች ጥቅም ህሊናና አእምሯቸውን ስለዘጋባቸው “ዜጎች” ማሰብ ለበሽታ አጋልጧቸዋል፤ ያነባሉ። ግራ በመጋባት “ህወሃቶች - ምንድነው የሚፈልጉት? ደም አይጠግቡም?” በማለት ይጠይቁና አጭሩን መልዕክት “ከርስ እንደዚህ እውር ያደርጋል?” የሚል ጥያቄ ጠይቀው ይሰናበታሉ። “በጥልቅ ስንታደስ የጥፋት ሃይሎች ጊዚያዊ መነቃቃት ይከስማል” ሲል የአዲስ አበባ ኢህአዴግ ጽ/ቤት በህዳሴ ጋዜጣ ላይ ያሰፈረውን አመልክተው፣ “በፍጥነት ወደ ጥልቁ ብትገቡ ለአገሪቱ ዘላለማዊ መነቃቃት ይሆን ነበር” የሚል ርዕስ በመስጠት ከላይ በመግቢያ የተገለጸውን የጠቆሙት የሃዋሳ ነዋሪ መሆናቸውን የጠቆሙ ደንበኛችን ናቸው። ብዙዎች እንደሚስማሙት ራሱን … [Read more...] about “ህወሃቶች – ምንድነው የሚፈልጉት? ደም አይጠግቡም?”
“ሕዝቡ እኔን አይቶ መታረቅ አለበት” ፈይሣ ሌሊሣ
አትሌት ፈይሣ ሌሊሣ ዛሬ በፌሰቡክ ከጋቢና ቪኦኤ ጋር የቀጥታ ውይይት አካሂዷል፡፡ ስላሳ ደቂቃ አካባቢ በፈጀው ቆይታው ከፕሮግራሙ ተከታታዮች ለቀረበለት ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥቷል፡፡ ሕወሃት ደንቁሯል እንጂ ከዚህ በላይ መልዕክት አያስፈልገውም ነበር፡፡ ዜግነቱን ለመቀየር ሃሳብ እንደሌለውና ራሱን ጀግና ብሎ እንደማይቆጥር የተናገረው ፈይሣ ለትግራይ ተወላጆች፣ ትግራዮችን በትግሬነታቸው ለሚጠሉ፣ ለትግራይ ወጣቶች፣ በሥልጣን ለሚገኙት ግፈኛ የህወሃት ባለሥልጣናት፣ ለነ ኃይሌ ገ/ሥላሴና መሰል አንጋፋ አትሌቶች፣ ለኢትዮጵያ ሕዝብ፣ ለወጣቶች፣ … እስኪበቃው ተናግሯል፡፡ የሰላም ታጋይና ዕርቅ ወዳድ የሆነው ፈይሣ ስለ ዕርቅም በሚገባው ሁኔታ አስረድቷል፡፡ በአማርኛ ያደረገውን ሙሉውን ቃለምልልስ እዚህ ላይ መመልከት ይቻላል፡፡ በአፋን ኦሮሞ ያደረገው ቃለምልልስ እዚህ ላይ … [Read more...] about “ሕዝቡ እኔን አይቶ መታረቅ አለበት” ፈይሣ ሌሊሣ
መልዕክት ለመምህራን
እንደሚታወቀው ከቅርብ ቀናት በፊት ከመስከረም 4 ጀምሮ የሚሰጠውን የመምህራን ስልጠና በምን መልኩ ወደ ተቃውሞ መድረክ መቀየር እንደምንችል መምህራኖችን መጠየቃችን ይታወሳል። መምህራኖችም ግልፅ በሆነ ቋንቋ ሀሳባቸውን ገልፀውልናል። ለዚህም ልናመሰግናቸው እንወዳለን። እኛም ሀሳባቸውን ጨምቀን አቅርበናል። ከዛ በፊት ግን ይህንን ስብሰባ መቃወም ለምን እንደሚያስፈልግ መግለፁ ተገቢ ነው። 1) ይህ ስብሰባ መምህራን ሙያቸውን የሚያሻሽሉበት ሳይሆን ገዥው ፖርቲ የራሱን ፕሮፖጋንዳ የሚነዛበት የፖለቲካ መድረክ ነው። ይህንን ደግሞ ከዚህ በፊት ከነበረው ልምድና ለስልጠናው ከተዘጋጁት ማኑዋሎች መረዳት ይቻላል። ስለዚህ ከዚህ ስልጠና ለመማር ማስተማሩ ሂደት የሚጠቅም አንዳች ነገር አይኖርም። 2) ወያኔ የሀገሪቱን የፖለቲካ ቀዉስ በውይይት ሳይሆን በመሳሪያ ለመፍታት ወስኗል። ይህንን ምርጫም … [Read more...] about መልዕክት ለመምህራን
#ተቃውሞ #እምቢተኝነት #ተጋድሎ
እንባ እንባ ይለኛል ይተናነቀኛል እንባ ከየት አባቱ ደርቋል ከረጢቱ: ሳቅ ሳቅም ይለኛል ስቆ ላይስቅ ጥርሴ ስቃ እያለቀሰች መከረኛ ነብሴ:: (በአሉ ግርማ “ኦሮማይ”) ምነው! ፈጣሪ አምላክ! አላለቅስም ያልኩት ... እንባ የፈሪ ነው ብዬ ዋጥ ያ’ረኩት፣ አይቻል ተችሎኝ ይዤው የከረምኩት፣ ገንፍሎ ወጣና እንባዬ ፈሰሰ ጉንጮቼን ሰንጥቆ ፌቴን አዳረሰ በዛ እንባዬ መሀል አንገቴን አቅንቼ ለፈጣሪ ጮኽኩኝ! እጆቼን ዘርግቼ ምነው? ፈጣሪ አምላክ ምነው! ረሳኸን ምነው! ይሄን በደል አላይልን አልከን ምነው? የኛን ጩኸት ሰምተህ ጨከንክብን ብዬ ወተውትኩት አልኩበት እዬዬ አሁንም ይፈሳል አልቆመም እንባዬ ምነው! ፈጣሪ አምላክ! ... ወለላዬ የዛሬ 25 ዓመት ህወሃት የጀመረው በዚህ ነበር - … [Read more...] about #ተቃውሞ #እምቢተኝነት #ተጋድሎ
የአውሮጳ ኅብረት ድጎማ ህወሃት ኮሮጆ አይገባም
ከሕገወጥ ፍልሰት ጋር በተያያዘ የአውሮጳ ኅብረት የአስቸኳይ ጊዜ መተማመኛ ድጎማ (Emergency Trust Fund - ETF) በማለት ለኢትዮጵያ የመደበው ገንዘብ ወደ ህወሃት ኮሮጆ እንደማይገባ ተነገረ፡፡ በኢትዮጵያ እየተባባሰ የመጣው የሰብዓዊ መብቶች ጥሰትን እንደምክንያት በማድረግ ድጎማው እንዲከለስ ወይም እንዲሰረዝ ዩሮአክቲቭ ያቀረበው ጥያቄ ለመረጃው ይፋ መሆን ምክንያት ሆኗል፡፡ አንድ ጊዜ በቃል በሌላ ጊዜ ደግሞ በኢሜይል ከኅብረቱ በኩል የተሰጠው መረጃ የኅብረቱን የድጎማ አከፋፈል በተመለከተ የጠራ አቋም የማያሳይ ድንግዝግዝ መረጃ ሆኗል፡፡ በህገወጥ መንገድ ከአፍሪካ የሚፈልሱት ዜጎች የአውሮጳውያን መንግሥታት ራስምታት ከሆኑ ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የፍልሰት መጠኑ መጨመሩና ከዚያ ጋር ተያይዞ የሚጠፋው የሰው ህይወት አውሮጳውያኑን በስፋት ያነታረከ ነው፡፡ … [Read more...] about የአውሮጳ ኅብረት ድጎማ ህወሃት ኮሮጆ አይገባም
ቂሊንጦ – “የተረሸኑት” እነማን ናቸው?!
“ወይኔ ልጄ፣ እጅ እግሬ ልጄ፣ ወይኔ ልጄ፣ ወዴት ነህ ልጄ፣ የት ላግኝህ ልጄ? እምኑ ጋር ነህ? ልጄ … ልጄ … ልጄ … ልጄ …” ጥቁር ቦርሳቸውን በወገባቸው ተሸክመው፣ ቂሊንጦ እስር ቤት ደጅ የሚያነቡ እናት ለቅሶ!! ሁሉም ያነባሉ። ሁሉም ያለቀሳሉ፣ የሚሰማ ግን የለም። እንደውም “ዘወር በሉ” እየተባሉ ይደገንባቸዋል። “ሊታረሙ በህግ ከለላ ስር ሆነዋል” የተባሉ ወገኖች “ተረሽነዋል” የሚለው አስተሳሰብ እየጠነከረ መጥቷል። ለቤተሰቦቻቸው እንደምን ተቆጥረው ይሁን? ይህ ሁሉ የጭካኔ ግፍ ወዴት ይመራን ይሆን? የብዙዎች ጥያቄና ስጋት ነው። በየሰዓቱ የሚወጡት መረጃዎች ደግሞ ስጋቱን የሚያግሉና ቁጣን የሚቀሰቅሱ ሆነዋል። የህወሃት ሹሞችም “የሆነው ነገር ሁሉ የተከሰተው በዕቅድ አይደለም” ይላሉ፡፡ በአልሞት ባይ ተጋዳነት የሚውተረተረው ህወሃት አሁንም አለሁ ቢልም የቂሊንጦ ጉዳይ … [Read more...] about ቂሊንጦ – “የተረሸኑት” እነማን ናቸው?!
“የገደሉት ልጄ አስከሬን ላይ ቁጭ በይ ብለው ደበደቡኝ” ደምቢ ዶሎ የተገደለ ወጣት እናት
በቄለም ወለጋ ዞን ደምቢዶሎ ከተማ ውስጥ ትናንት ማክሰኞ ማምሻው ላይ ከመንግሥት ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉን የከተማዋ ነዋሪዎች ገለጹ። የአንደኛው ወጣት ወላጅ እናት እኔንም የልጄ አስከሬን ላይ ጥለው ደበደቡኝ ብለዋል። በመንግሥት ታጣቂ ጥይት ህይወታቸው ያለፈው ሁለቱ ሃይሉ ኤፍሬም እና ኢብሳ ሩንዴ የሚባሉ ሲሆኑ የ16 ዓመቱ ወጣት ሃይሉ ኤፍሬም ከተማዋ ውስጥ ተኩስ በመከፈቱ ከሌሎች ጓደኞቹ ጋር ከተኩሱ ለማምለጥ ሲሮጥ መትተው ገደሉት ሲሉ የከተማዋ ነዋሪዎች ገልጸዋል። “ደሞቢ ዶሎ መሃል ከተማ ነበር ተኩስ የተጀመረው። ወደ ቀበሌ ዜሮ አምስት አካባቢም ተኩስ ነበር ። ልጆቹን እያባረሩዋቸው ሲመጡ ወጣት ሃይሉ ኤፍሬም በቅጽል ስሙ ቦጌ ነው የሚባለው ቀበሌ ዜሮ ሰባት በሚገኘው መኖሪያ ቤቱ አቅራቢያ ነው የተገደለው” ብለዋል የአሜሪካ ድምፅ … [Read more...] about “የገደሉት ልጄ አስከሬን ላይ ቁጭ በይ ብለው ደበደቡኝ” ደምቢ ዶሎ የተገደለ ወጣት እናት
የኢኮኖሚ አድማ!
በ#OromoProtests አስተባባሪዎች በተሰጠው ማሳሰቢያ መሠረት በኢኮኖሚ ላይ ያተኮረው የገበያ ማቆም አድማ እየተካሄደ ነው፡፡ በፎቶዎቹ ላይ እንደሚታዩት ከንጋት ጀምሮ የአምቦ አካባቢ ከተማ፣ ሻሸመኔ አዋሾ ክፍለ ከተማ፤ አሳሳ፣ ጉደርና ከተሞች ከነገበያቸው ባዶ ሆነዋል፡፡ ዓድማው በሌሎችም ከተሞች ላይ ሲካህይድ የዋለ ሲሆን በውጤቱም የህወሃትን የገቢ ኮሮጆ በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚጎዳው ይገመታል፡፡ ከአስተባባሪዎቹ የተሰጠውና እስከ መስከረም 2 የሚዘልቀው ማሳሰቢያ እንዲህ ይነበባል፤ ማሳሰቢያ: የገበያ ማቆም አድማ በመላው ኦሮሚያ ነገ ጳግሜን 1 እንደሚጀምር አስቀድመን መግለጻችን ይታወቃል፡፡ ይህ አድማ እስከ መስከረም ሁለት ይቀጥላል። በዚህ አድማ ጊዜ ውስጥ ከሌሎች ክልሎች ለሽያጭ እቃዎችን ወደ አዲስ አበባ እና ሌሎች የኦሮሚያ ከተሞች ማስገባት ክልክል ነው። እቃዎችን ጭነው … [Read more...] about የኢኮኖሚ አድማ!










