ህወሃት በግፍ በሚመራት ኢትዮጵያ የማይጠፋ ነገር የለም፡፡ ምናልባት መብራት ብቻ ነው የሚጠፋው ብሎ የሚያስብ የቅርቡን ክስትት ያልተከታተለ ብቻ ሊሆን ይችላል ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ መብራት፣ ውሃ፣ የስልክ ኔትወርክ፣ ወርቅ፣ … ብቻ ሳይሆን ጋዜጠኞች፣ ፖለቲከኞች፣ የሥርዓቱ ተቃዋሚዎች … በሚጠፉባት አገር ከሰማኒያ በላይ ኮንዶሚኒየም ይጠፋል፤ ሰሞኑን ደግሞ በኢትዮጵያ የህወሃት ተጠሪ ኃይለማርያም በነቀምቴ ከተማ አውሮፕላን ማረፊያ ያስቀመጡት የመሠረት ድንጋይ ጠፍቷል ተብሎ የማኅበራዊ ሚዲያውን ሰፈር አድምቆታል፡፡ የነቀምቴው ሳያንስ ደምቢዶሎ ደግሞ ተመረቀ የተባለው የአፈር አየር ማረፊያ ህወሃትን ለከፍተኛ ስላቅና ፌዝ አጋልጦታል፡፡ የሥርዓቱ ደጋፊ የሆኑት ሳይቀሩ "ገንዘቡ ተበልቷል" ያሉበት የዚህ አውሮፕላን ማረፊያ የማኮብኮቢያና የማረፊያ መንገድ ከአፈር መሆኑ ብቻ … [Read more...] about አስፋልቱ “አብስትራክት” የሆነው የደምቢዶሎ ኤርፖርት
News
“ኦጋዴን፤ የኢትዮጵያ [የህወሃት] ድብቅ ኃፍረት”
የኢትዮጵያን ሕዝብ በነጻ አውጪ ስም እስካሁን በግፍ እየገዛ ያለው የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግምባር ሥልጣን በኃይል ከመያዙ በፊት ሲፈጽም የነበረውን የሰብዓዊ መብት ረገጣ፤ ሥልጣን ከያዘም በኋላ ላለፉት 25 ዓመታት ቀጥሎበታል፡፡ ህወሃት ሥልጣን ከያዘ ጀምሮ በኢትዮጵያ ውስጥ ግፍ ያልተፈጸመበት አካባቢ የለም የሚለው አባባል የተጋነነ አይደለም፡፡ “ኦጋዴን፤ የኢትዮጵያ [የህወሃት] ድብቅ ኃፍረት” በሚል ርዕስ ጋዜጠኛ ግራሃም ፔብልስ በኦጋዴን የሚካሄደውን የሚዘገንን ግፍ ሰኔ 15፤ 2008ዓም (June 22, 2016) ዩትዩብ ላይ ለቋል፡፡ (ዘጋቢ ፊልሙ እዚህ ላይ ይገኛል) “በዛፍ ላይ ለተወሰኑ ደቂቃዎች ሰቅለውኝ ነበር፤ በርካታ ደቂቃዎች ካለፉ በኋላ አወረዱኝ፤ … ከዚያም ካሁን በኋላ የምንልሽን ታደርጊያለሽ አለበለዚያ እንገድልሻለን አሉኝ” የግፍ ዶፍ የወረደባት አናብ … [Read more...] about “ኦጋዴን፤ የኢትዮጵያ [የህወሃት] ድብቅ ኃፍረት”
ህወሃት “አምባሳደሮችን” በታማኞቹ ሊተካ ነው!
በተለያዩ አገራት የሚገኙ አምባሳደሮች በወሳኝ የህወሃት ሰዎች ሊተኩ እንደሆነ ተነገረ፡፡ በህወሃት ውስጥ ያለው ፍርሃቻና አለመረጋጋት ለሁኔታው አስገዳጅነት ምክንያት ሆኖ ቀርቧል፡፡ ህወሃት ለዓመታት ያገለገሉትን ሎሌዎች የማያምናቸው ከሆነ እነርሱም “አለመታመናቸውን” ማሳየት ይገባቸዋል፡፡ በአሜሪካ፤ በአውሮጳ፤ በአውስትራሊያና በኢትዮጵያ አጎራባች በሆኑ አገራት የሚገኙ አምባሳደሮች በቅርቡ ወሳኝ በሆኑ የህወሃት ሰዎች ሊተኩ መታሰቡን ማንነታቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ የጎልጉል መረጃ አቀባይ አስታውቀዋል፡፡ ለመረጃው ቅርብ እንደሆኑና የአገራቱም ዝርዝር እንዳላቸው የተናገሩት መረጃ አቀባይ የሹምሽሩ ምክንያት ይህ ነው ተብሎ በውል ባይታወቅም ህወሃት ከውስጥና ጫና ተጠቃሽ እንደሆነ ይጠቁማሉ፡፡ በኢህአዴግ ተለጣፊና ድቃይ ድርጅቶች ታቅፈው የሥርዓቱ ሎሌ የሆኑት አምባሳደሮች በመጪዎቹ … [Read more...] about ህወሃት “አምባሳደሮችን” በታማኞቹ ሊተካ ነው!
“‘ጭካኔ የተሞላበት አፈና’ – የግድያ እና የእስራት ምላሽ፤ ለኢትዮጵያ የኦሮሞ ተቃውሞ”
ከሰብዓዊ መብቶች ጋር በምንም ዓይነት መልኩ የማይተዋወቀው፤ መተዋወቅና መግባባትም የማይችለው ህወሃት ሰሞኑን “የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን” ብሎ ባቋቋመው ጽ/ቤቱ አማካኝነት “በኦሮምያ ክልል የተቃውሞ እንቅስቃሴ ወቅት በፀጥታ ኃይሎች የተወሰደው እርምጃ አስፈላጊና ተመጣጣኝ ነበር” በማለት ዘገባ ካወጣ ጥቂት ቀናት በኋላ ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብት ጥበቃ ድርጅት ማምሻውን የህወሃትን ቅጥፈት ርቃኑን የሚያወጣ ዳጎስ ያለ ዘገባ ይፋ አድርጓል፡፡ ከዘገባው ጋር በማያያዝ የተወጣው መግለጫ ከዚህ በታች ይገኛል፡፡ (ናይሮቢ፤ ሰኔ 9 ቀን 2008 ዓ.ም) – ከህዳር ወር 2008 ዓ.ም. ጀምሮ በኦሮሚያ ክልል በተካሄዱ የተቃውሞ ሰልፎች የኢትዮጵያ መንግስት የጸጥታ ሀይሎች ከ400 በላይ የሚሆኑ ሰልፈኞችን የገደሉ ሲሆን ከአስር ሺህ በላይ የሚቆጠሩትን ደግሞ ማሰራቸውን ሂዩማን ራይት ወች ዛሬ ይፋ … [Read more...] about “‘ጭካኔ የተሞላበት አፈና’ – የግድያ እና የእስራት ምላሽ፤ ለኢትዮጵያ የኦሮሞ ተቃውሞ”
ከ300 በላይ ዜጋ መገደሉ “አስፈላጊና ተመጣጣኝ ነው” የህወሃት ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን
በኦሮምያ ክልል የተቃውሞ እንቅስቃሴ ወቅት በፀጥታ ኃይሎች የተወሰደው እርምጃ አስፈላጊና ተመጣጣኝ ነበር ሲል የኢትዮጵያ (ህወሃት/ኢህአዴግ) ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አስታውቋል፡፡ ዓለም በሙሉ በሚያውቀው በየትኛውም ሚዛን እርምጃው ተመጣጣኝም፣ አስፈላጊም አልነበረም ሲሉ የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና ተናግረዋል፡፡ አያይዘውም “የኢትዮጵያ መንግሥት እንኳን ያላለውን ኮሚሽኑ ደፍሮ ‘ተመጣጣኝ ነው’ ማለቱ አስቂኝም አስገራሚም ነው”ብለዋል። ከቅማንት የማንነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ ለተፈጠረው ግጭት የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ሕዝቡን ይቅርታ መጠየቅ እንዳለበት ሪፖርቱ ሃሣብ ያቀረበ ሲሆን የክልሉ መስተዳድር ቀደም ብሎ ይቅርታ መጠየቁን አስታውቋል፡፡ ዝርዝሩን ከዚህ በታች ይገኛል ተጭነው ያድምጡ:: (ምንጭ: የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ - VOA) … [Read more...] about ከ300 በላይ ዜጋ መገደሉ “አስፈላጊና ተመጣጣኝ ነው” የህወሃት ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን
ህወሃት ጉሮሮውን ሳይታነቅ የበላውን በ30 ቀን “እተፋለሁ” አለ
ህወሃት በቦንድ ስም ህግ ጥሶ ሲሰበስብ የነበረውን ገንዘብ ክስ ተመስርቶበት ጉሮሮው ሳይታነቅ ወዶ ለመትፋት መስማማቱ ታወቀ። ድርጊቱ ኢትዮጵያን መሳቂያ፣ የምትተዳደረው በህገ አራዊት መሆኑን የሚያረጋግጥ መሆኑንና የህወሃትን የወሮበላነት ባህሪ እርቃን ያወጣ ነው ተባለ። ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው እንደሚሉት ከውጭ ምንዛሬ ገበያ ጋር በተያያዘ ተጨማሪ ምርመራ ሊካሄድ የሚችልባቸው በርካታ አግባቦች እንደሚኖሩ ነው። ራሱን “የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ” የሚለው አገዛዝ ከቦንድ ሽያጭ ጋር በተያያዘ ሰሞኑንን ይፋ የሆነበት ዜና “ነጻ አውጪው ሃይል” አሁንም ከጫካ አስተሳሰብ አለመላቀቁን የሚያመለክት እንደሆነ ተጠቆመ። በፍርድቤት ተከስሶ እና ጉሮሮውን ታንቆ ከውርደት ጋር በርካታ የገንዘብ ክፍያ ውስጥ ከመግባቱ በፊት “ጥፋተኛ ነኝ፤ ፍርድቤት አትውሰዱኝ፤ ያላችሁኝን አደርጋለሁ” በማለት … [Read more...] about ህወሃት ጉሮሮውን ሳይታነቅ የበላውን በ30 ቀን “እተፋለሁ” አለ
የመለስ “ሌጋሲ” የመጨረሻው ዙር የመጀመሪያ ክፍል?
ሰሞኑን የተሰማው ዜና በህወሃት መንደር የሥርዓት መናጋትና የፖለቲካው ችግር ነጸብራቅ እንደሆነ ብዙዎች ይስማማሉ። “ይህ ችግር እንደ ተስቦ ይዛመታል፤ ሲዛመት መቆሚያ አይኖረውም” የሚሉም አሉ። ሲያክሉም “ተስቦው ወደ መበላላት ሊያመራ ይችላል። ይህ ሊሆን ግድ ካለ ደግሞ እሽቅድድም ይጀመራል። እሽቅድድም ሲኖር ላለመቀደም የፈሪ ዱላ አይነት ጨዋታ ይነሳል። የፈሪ ዱላ ክፉ ነው” በሌላ በኩል ደግሞ ሁሉንም ወገኖች አስተሳሰብ የሚያጣጥሉ አልታጡም። ይህ አስተያየት የተሰጠው ከሁለት ሳምንት በፊት አብረዋቸው ከሚሰሩት ባለቤታቸው ጋር ከሃላፊነታቸው ተነሱ የተባሉት የመረጃና የደህንነት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ኢሳያስ ወልደጊዮርጊስ ዜና ተከትሎ ነው። አቶ ኢሳያስ የደህንነቱ “መለስ” በሚል ስያሜ ይጠሩ ስለነበር ዜናው በህወሃትም ሆነ ህወሃት “መንግስት” የመሆን አጋጣሚ ሲመቻችለት ባቋቋመው … [Read more...] about የመለስ “ሌጋሲ” የመጨረሻው ዙር የመጀመሪያ ክፍል?
የጀርመን ኤምባሲ ትግርኛን ቅድመ መስፈርት ያደረገ የስራ ማስታወቂያ አወጣ
ተቀማጭነቱ አዲስ አበባ የሆነው የጀርመን ኤምባሲ የትግርኛ ቋንቋን ቁልፍ ቅድመ መስፍርት የሚያደርግ ክፍት የስራ ማስታወቂያ አዲስ አበባ ለሚገኘው ጽህፈት ቤቱ አወጣ። ትግርኛ ዋና መስፈርት የሆነበት ምክንያት ይፋ አለመደረጉ ጥያቄ አስነስቷል። ጉዳዩን የሚከታተሉ ወገኖች የኤምባሲው ተግባር የኢትዮጵያውያንን እኩልነትን ከህወሃት በላይ ያንቋሸሸ ነው ብለውታል፡፡ ኤምባሲው ማብራሪያ እንዲሰጥ ይጠበቃል። ኢምባሲው በድረገጹ ሜይ 4 ቀን 2016 ያወጣው ማስታወቂያ የሚፈልገው ባለሙያ የቪዛ ማመልከቻ ስራን የሚያመቻች፣ የሚያረጋግጥ፣ ቪዛ ነክ ጉዳዮችን አስመልክቶ የቃልና የጸሁፍ መረጃዎችን የሚሰጥ፣ የቪዛ ክፍያን የሚፈጽምና የመዝግብ አያያዝ ስራን የሚያከናውን እንደሆነ ያረጋግጣል። የስራው ቦታ ከአዲስ አበባ ውጪ ስለመሆኑ የሚለው ነገር የለም። ማስታወቂያውን የተመለከቱ ወገኖችን ያነጋገረውም … [Read more...] about የጀርመን ኤምባሲ ትግርኛን ቅድመ መስፈርት ያደረገ የስራ ማስታወቂያ አወጣ
ኦባንግ አባ “ቃኘው” የደቡብ ኮሪያ ዳግም ዘማች!
የመን ትነድዳለች ኢትዮጵያውያን ግን ወደዚያው ያቀናሉ። ሶማሊያ ዋስትና ቢርቃትም ወገኖች ሊረማመዱባት አሁን ድረስ ምርጫቸው ናት። በሲና በረሃ ሰው በቁሙ ይበለታል። ለእኛ ኢትዮጵያውያኖች ግን አሁንም አማራጭ መንገድ ነው። ሲኦል መሆኑ እየታወቀ እህትና ወንድሞች ወደ አረብ አገር ይተምማሉ። ኬንያን፣ ታንዛኒያን፣ ዛምቢያን፣ … አቆራርጠው ወደ ደቡብ አፍሪካ የሚጓዙ ቁጥራቸው ሲቀንስ አይታይም። በደቡብ አፍሪካ ወገኖች በእሳት ሲቃጠሉና በገጀራ ሲጨፈጨፉ ማየት ወደዚያ የሚደረገውን ጉዞ አልቀነሰውም። ለምን? በቀይ ባህርና በሜዲትራንያን የሰመጡ ወገኖች መርዶ ሳያሰልስ ሌሎች መሰመጥ የመጨረሻ አማራጭ መሆኑን እያወቁ ይገቡበታል። ሊቢያ የታረዱትን ወገኖች እያዩ ሌሎች ወደ ሊቢያ ለማቅናት አያቀማሙም። ለምን? በኩባ ቪዛ ተነስተው መከራቸውን ለወራት በበረሃ የሚያሳልፉ ወገኖች ቁጥር ... ስንቱ … [Read more...] about ኦባንግ አባ “ቃኘው” የደቡብ ኮሪያ ዳግም ዘማች!
ጋምቤላ ከውስጥም ከውጭም የምትለበለብ ለም ምድር!!
ጋምቤላ ውብ ምድር፣ ጋምቤላ የተፈጥሮ ባለጸጋ፣ ጋምቤላ ድንግል መሬት፤ ጋምቤላ ያላትን የማትበላ፣ የተረገሙ የሚመሯት፣ የደም መሬት፣ የዕንባ ምድር፤ ጋምቤላ የምትዘረፍ ምድር፣ ግፍ የተትረፈረፈባት የግዞት መሬት፣ የደም አውድ፣ ከውስጥም ከውጭም የምትለበለብ “አካላችን”፤ ጋምቤላ ያላቸውን የማይበሉ ህዝቦች፣ ባላቸው ሃብት የተነሳ የግፍ መከራ የሚጋቱ ምስኪን ወገኖች የሰፈሩባት ገነተ ሲኦል፤ ተቆርቋሪ አልባ “ኢትዮጵያኖች” ፍትህን ስትናፍቁ ከሁልጊዜውም በላይ በከፋ ሃዘን ተመታችሁ!! አዎ፣ የጎልጉል ዝግጅት ክፍልን ጨምሮ ዜጎችን ያቃጠለው ዜና ባልተለመደ መልኩ የተበሰረው በህወሃት ንብረት ራዲዮ ፋና አማካይነት ነው። ባለፈው አርብ የተሰማው ክፉ ዜና እነዚያ ለቱሪዝም ማስታወቂያነት ብቻ የሚፈለጉት ወገኖቻችን በድንገት ስለመጨፍጨፋቸው ነው። ከ240 በላይ እናቶችና ህጻናት በጅምላ … [Read more...] about ጋምቤላ ከውስጥም ከውጭም የምትለበለብ ለም ምድር!!


![“ኦጋዴን፤ የኢትዮጵያ [የህወሃት] ድብቅ ኃፍረት”](https://staging.goolgule.com/wp-content/uploads/2016/06/Slide4-e1466824461975-300x148.jpg)







