• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“ተላላኪና አሸባሪ ነው” ኦህዴድ

August 21, 2016 10:24 pm by Editor Leave a Comment

* “ወደ ኢትዮጵያ ከተመለስኩ ሊገድሉኝ ይችላሉ” ፋይሣ ሊሊሣ

በሪዮ ኦሎምፒክ በማራቶን ሁለተኛ የወጣው ፋይሣ ሊሊሣ “ወደ ኢትዮጵያ ከተመለስኩ ሊገድሉኝ ይችላሉ” በማለት የህወሃትን ጨካኝነት ለዓለም ገለጸ፡፡ የፋይሳ ጉዳይ ያገባናል የሚሉ ሁሉ ሊደርሱለት እንደሚገባ ተነገረ፡፡ አትሌቱን “አሸባሪና ተላላኪ” ሲል ኦህዴድ ኮንኖታል፡፡

የወርቅ ሜዳሊያ ከወሰደው ኬኒያዊ በላቀ ሁኔታ የዓለምአቀፍ ሚዲያን ትኩረት የሳበው ፋይሳ እዚያው ሪዮ ብራዚል በሰጠው ቃለምልልስ የኦሮሞ ተቃውሞ የሚያሳመላክተውን እጁን ከአናቱ በላይ በማጣመር ሳየበትን ምክንያት ገልጾዋል፡፡ “ተቃውሞዬን የገለጽኩት ለሕዝቤ ነው፤ ዘመዶቼ እስር ቤት ናቸው፤ እስር ቤት ሄጄ ከዘመዶቼ ጋር መገናኘት፣ እነርሱን መጠየቅ እፈራለሁ፤ ካወራህ ይገድሉሃል፤ ስለንደዚህ ዓይነት ነገር ማውራት በጣም አደገኛ ነው፤ (እዚያ አገር) ነጻነት የሚኖርህ መንግሥትን ከደገፍህ ብቻ ነው፤ ይህንን ካላደረግህ መሥራት አትችልም፤ በጣም መጥፎ መንግሥት ነው” ብሏል፡፡ lilesa

በድርጊቱ አምኖበት እንዳደረገ በመግለጽ ሲናገር “የኢትዮጵያ መንግሥት ሕዝቤን እየገደለ ነው፤ እኔ ከኦሮሞ ጎሣ ነኝ፤ ስለዚህ ለሕዝቤ እጄን አንስቻለሁ” በማለት ተናግሯል፡፡ “አሜሪካ፣ እንግሊዝ፣ ፈረንሣይ፣ … ይህንን መንግሥት ይደግፋሉ፤ እነዚህ መንግሥታት በሚሰጡት ዕርዳታ የጦር መሣሪያ እየገዛ ሕዝቡን ይፈጃል” ብሏል፡፡

ፋይሣ እሁድ ማምሻው ላይ ከኢሣት ጋር ባደረገው አጭር ቃለምልልስ “አስቤበት ያደረኩት ነው፤ ብሞትም አይቆጨኝም” ያለ ሲሆን የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግምባር በግፍ ስለሚገዛት ኢትዮጵያና ሕዝቧ “የኢትዮጵያ ሕዝብ በአንድ ላይ ተረባርቦ ይህንን ሥርዓት ሊያስወግደው ይገባል” በማለት መልዕክቱን አሰምቷል፡፡

“(አገር ቤት ብሄድ) ይገድሉኛል፤ ወይም ያስሩኛል፤ ወይም እዚያው አየር ማረፊያ ስደርስ ያግዱኛል” በማለት ፍርሃቱን የተናገረው ፋይሣ ሊሊሣ ወደ ሌላ አገር ለመሄድ እንደሚፈልግ በግልጽ ተናግሯል፡፡

በዓለምአቀፍ የፖለቲካ መድረክ እየከሰረ የመጣው ህወሃት በስፖርቱ መስክ በተለይም አገር ውስጥ በቀጥታ ስርጭት እየተላለፈ በዓለምዙሪያ ፋይሣ ያሳየው ተቃውሞ ዕርቃኑን አውጥቶታል፡፡ ከዚህ አንጻር የሥርዓቱ ደጋፊዎች በማኅበራዊ ገጾች ላይ ፋይሣን ወደ አገርቤት መመለስ ይገባል፤ ሕገመንግሥታዊ መብቱን ነው የተጠቀመው፤ የሚያስፈልገው ርብርብ ተደርጎ የኦሎምፒኩ ጀግና ወደ አገር እንዲመለስ በማለት የህወሃትን ዕርቃን ለመሸፈን ቅስቀሳ ጀምረዋል፡፡ ተመሳሳይ ተቃውሞ ያሳዩ እስከ 1ሺህ የሚጠጉ ኦሮሞዎች በጭካኔ እየገደሉ፤ እነ በቀለ ገርባን በግፍ አስረው እያሰቃዩ ፋይሳን ወደ አገርን ና ማለት የማያስቅ ቀልድ ነው በማለት አስተያየት ሰጪዎች ውድቅ አድርገውታል፡፡ blackpower

የህወሃት ውርደት ያንገበገባቸው በሌላ መልኩ የአትሌቱን ድርጊት በማውገዝ ሜዳሊያው ሊነጠቅ ይገባል ሲሉ ተደምጠዋል፡፡ እኤአ 1968 በአሜሪካ ጥቁሮች ላይ የሚደርሰውን ግፍ በኦሎምፒክ የሚዳሊያ ሥነሥርዓት ላይ ያሳዩትን ቶሚ ስሚዝና ጆን ካርሎስን ሲጠቅሱ ተሰምተዋል፡፡ አትሌቶቹ በ200ሜትር 1ኛ እና 3ና ከወጡ በኋላ ሜዳሊያው በሚሰጥበት ጊዜ “የጥቁር ኃይል” የሚባለውን እጅን በጡጫ መልክ የመጨበት ምልክት፣ የጥቁሮችን ድህነት ለማሳየት ያለጫማ በመሆን እንዲሁም ኢሰብዓዊ በሆነ መንገድ ይገደሉ የነበሩትን ጥቁሮችን ለማመላከት ጨሌ አድገው ታይተዋል፡፡ የአሜሪካ የሕዝብ መዝሙር ሲዘመር አንገታቸውን በማቀርቀር በዝምታ ጨርሰዋል፡፡ በዚህ ድርጊታቸው የአለምዓቀፉ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ሜዳሊያቸውን እንደሚልሱ አድርጓል፡፡ ከዘመናት በኋላ በአሜሪካ ውስጥ ጀግኖች ተብለው በተለያዩ ቦታዎች ሃውልቶች ቆመውላቸዋል፡፡

Lelisa_FeyisaA-World11በሌላ በኩል የፋይሳ የወደፊት ሁኔታ ያሳሰባቸው አሁን ባለበት ቦታ በቶሎ ድጋፍ ሊደረግለት በማለት የድረሱለት ጥያቄ እያቀረቡ ነው፡፡ በውጭ አገር የሚገኙ ኢትዮጵያውን የሕግ ባለሙያዎች፣ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች፣ ያገባናል የሚሉ ሁሉ ፋይሣን እንዲታደጉ፣ ሕጋዊ መብቱ እንዲጠበቅለትና ወደ ሦስተኛ አገር መሄድ የሚችልበትን መንገድ እንዲመቻችለት እንዲረዱት ተማጽኖዎች እየቀረቡ ነው፡፡ በሪዮ የዓለምአቀፉን ኦሎምፒክ ኮሚቴን እንዲወተውቱ፤ ጥገኝነት ሊሰጡ የሚችሉ መንግሥታትን እንዲያማክሩ፣ እርሱም ምን ማድረግ እንደሚገባው አስፈላጊው የምክር አገልግሎት እንዲሰጠው ለጎልጉል አስተያየታቸውን የሰጡ በጥብቅ አሳስበዋል፡፡ በአረመኔው ህወሃት ቁጥጥር በምትገኘው ኢትዮጵያ መመለሱ ለበቀል እንደሚዳርገው ያላቸውን ፍርሃት ጨምረው ገልጸዋል፡፡

እሁድ ማምሻው ላይ ፋይሳን በገንዘብ ለመርዳት ድረገጽ ተከፍቷል፡፡ Go fund me በተባለው በዚህ ድረገጽ ላይ $40ሺህ ዶላር ለመሰብሰብ የታቀደ ሲሆን ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ $28,150 ዶላር ተሰብስቧል፡፡ ለመርዳት የሚፈልጉ ሁሉ ይህንን በመጫን ወደ ድረገጹ መድረስ ይችላሉ፡፡

በፋይሣ የተቃውሞ ድርጊት ያስቆጣው ኦህዴድ ከህወሃት በተሰጠው ትዕዛዝ አትሌቱን ተላላኪና አሸባሪ ሲል ድርጊቱን በማውገዝ በፌስቡክ ገጹ ላይ ኮንኖታል፡፡


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (http://staging.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጃዋርና በቀለ መታሠራቸው ተሰማ June 30, 2020 09:17 am
  • አገራዊ መድረክ ውጪ ድብቅ ውይይትን አንቀበልም June 17, 2020 06:57 am
  • ዴክሳሜታሶን! የኮሮና መድሀኒት June 17, 2020 06:49 am
  • የሰኔ 14ቱ ቀለበታዊ የፀሃይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ! June 17, 2020 06:38 am
  • የግብፅ የአባይን ውሃ ብቻዬን ልጠቀም ግትር አቋም ድርድር እንቅፋት ሆኗል June 10, 2020 07:15 am
  • የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!? April 12, 2020 02:48 am
  • በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሚጠቀሙበት የኤርትራ ስደተኛ ካምፕ ሊዘጋ ነው March 18, 2020 08:37 pm
  • እየተፈረካከሰ ያለው አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ March 18, 2020 08:09 pm
  • ኮሮና አዲስ ጉድ መዘዘ – ከቻይና በፊት በአሜሪካ ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎችን ቀጥፏል March 16, 2020 11:41 pm
  • የኮንዶሚኒየም ቤቶች በደላሎችና በመመሪያ ሰጪዎች ኔትዎርክ እየተቸበቸበ ነው! ታከለ የት ናቸው? March 9, 2020 10:18 am
  • ኤርሚያስ ለገሠ ከባለአደራ ተባረረ March 9, 2020 08:09 am
  • ድፍድፍ ሲቀል ይንሳፈፋል፤ ምሁር ሲዘቅት ይመራል፥ March 7, 2020 11:24 pm
  • ኢትዮጵያዊ ምን ይመስላል? በምንስ ይመሰላል? March 7, 2020 10:29 pm
  • WHY I WROTE “MONEY, BLOOD AND CONSCIENCE” March 4, 2020 11:15 pm
  • አድዋ፤ የጥቁር ሕዝብ ድል! March 2, 2020 11:24 am
  • ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ (አባ ጎራው) March 2, 2020 11:12 am
  • የኦነግ ሁለት መልክና ሦስት ግብሮች – ቃርሚያው ኃይል ቅጥር ነፍሰገዳይ ሆኗል February 25, 2020 11:26 pm
  • በቡራዩ “የጃል ማሮ” ፎቶ ጨረታ አፈናከተ፤ “ቡራዩ ሆኖ ከሃዲን ማሞካሸት አይቻልም” ነዋሪዎች February 17, 2020 09:13 pm
  • “ዲቃላ” የፍረጃ ፖለቲካ በኦሮሚያ የኃይል አሰላለፉን እየቀየረ ነው February 13, 2020 11:58 pm
  • “ከዚህ በኋላ ማናቸውንም በወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን” አንታገስም – ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ February 13, 2020 05:07 pm
  • “እኛ ማንም ተሳዳቢ እንዲመጣብን አንፈልግም” የጅማ ነዋሪ February 13, 2020 09:28 am
  • “ወላጆቻችሁ ሰላማዊ ሰልፍ በሕዝቡ ያስደርጉልን” – አጋቾች February 11, 2020 07:53 pm
  • “ወንጀል የፈጸመም ያስፈጸመም ተይዞ ለህግ ይቀርባል፤ ምርመራም ተጀምሯል” February 11, 2020 06:59 pm
  • ጃዋር ወደ መጨረሻው “የትግል” ስልቱ – አማራን ማበጣበጥ! February 10, 2020 11:54 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule