Researches recognized that many change agendas fail not because of resistance to change. It is due to wrong responses to resistances. Many people tend to think that all resistances are one and the same. And hence, they use the same response to all resistances. To give you a quick background, experts in the field agree that there are three major levels of resistances to change. People resist at Level 1 since they don’t understand the change at all. Those who resist at Level 2, they capture the … [Read more...] about My two cents to break the deadlock between the Oromos and Unity Camps
መንፈሳዊ ወኔና ሥልጣን
ባለሥልጣኖቻችን ሚስቶቻቸውንና ልጆቻቸውን በጣም የናቋቸው ይመስላል፤ ሚስቶቻቸውና ልጆቻቸው የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚያውቀውን ሁሉ ያውቃሉ፤ የኢትዮጵያን ቴሌቪዥን ያያሉ፤ የኢትዮጵያን ራድዮ ይሰማሉ፤ ባሎቻቸውና አባቶቻቸው የዛሬ ሳምንት የተናገሩትን ረስተው፣ ወይም ክደው፣ ወይም ዋሽተው ተቃራኒውን ሲናገሩ መሸማቀቃቸው አይቀርም፤ እንዲህ ያለው የንግግር መገለባበጥ የእምነት መገለባበጥን፣ የማሰብ ችግርን፣ የመንፈስ ልልነትን ያሳያል፤ ታዲያ ሚስቶችና ልጆች እየተሸማቀቁ አካላቸውም ነፍሳቸውም ሲያልቅ ለባለሥልጣኖቹ አይታወቃቸውም? ወይስ የቤተሰብ አባሎች ጠባይ እየሆነ ሽታዬ ሽታዬ እየተባባሉ ነው? አንዳንዶች ባለሥልጣኖች ወንበሩ ላይ የወጡት እግዚአብሔርን ሳይይዙ ነው፤ አንዳንዶቹ ደግሞ እግዚአብሔርን ይዘው ወንበሩ ላይ ይወጡና እግዚአብሔርን ከተቆናጠጡ በኋላ እግዚአብሔርን ከውስጣቸው የሚያስወጡት … [Read more...] about መንፈሳዊ ወኔና ሥልጣን
“ሁላችንም አብረን ነጻ ካልወጣን ማንም ብቻውን ነጻ ሊሆን አይችልም!”
ኢትዮጵያ ድንቅ አገር ናት። ይህ ማስደነቋ ደግሞ ከሕዝቧ መደበላለቅ ጋር ውበቷን እጅግ አጉልቶታል። ከዛሬ 40ዓመት በፊት የተጀመረው ጎሣ፣ ዘር፣ … ላይ ትኩረት ያደረገው ገዳዳ የግራ ፖለቲካ ኢትዮጵያ አላት የተባለውን የፖለቲካ ችግር ሲፈታ ሳይሆን ይበልጡኑ ሲያወሳስበውና ሕዝብን ግራ ሲጋባ እዚህ ደርሰናል። በዚያ ርዕዮት የተጠመቁ ሕዝብን ሲያስፈጁ እንጂ ለሕዝብ ጥቅም ሲያመጡ አልታዩም፤ በዚያ የጎሣ ፖለቲካ ጥርሳቸውን የነቀሉም እስካሁን የማይሠራ ነገር በመሞከር በሽታውን ለአዲሱ ትውልድ እንደ ስጦታ አስረክበውታል። ለነጻነት በሚደረገው ትግል የሁሉም ኢትዮጵያ ወገኖች በአንድነት ብሶታቸው፣ ምሬታቸው፣ … ሊሰማ ይገባል እንጂ በተናጠል “ፍትህ ለኦሮሞ፣ ፍትህ ለአማራ፣ ፍትህ ለኦጋዴን፣ …” የሚለው አካሄድ የትም የሚያደርስ አይመስለንም፡፡ የተጨቆንነው ሁላችንም ነን፤ የትግራይ … [Read more...] about “ሁላችንም አብረን ነጻ ካልወጣን ማንም ብቻውን ነጻ ሊሆን አይችልም!”
ኢትዮጵያ ትጠየቅ!
ነገር ቢበዛ በአህያ አይጫንም። ስለዚህ ነገሬን አጠር አድርጌ ላቅርብ። እነሆ! የኢትዮጵያ ማንነት መገለጫው በዋነኛነት ምንድነው? ሕዝቡ ነው። ታዲያ በሕዝቡ ስም (ኢትዮጵያ) ጥላ ስር መሪዎቻችን ሁሉ የማይሰባሰቡት ለምንድነው? የታሪክ እስረኛ ሆነን በር በሌለው ጨለማ እስር ቤት ውስጥ በመታለል ቁጭ ስላልን። ኢትዮጵያን መነሻ ሳናደርግ ኢትዮጵያ መድረሻ እንድትሆንልን ተመኝተን ጉም ስንጨብጥ። ክልላችንን (አጥሩን) አፍርሰን እንዳንያያዝ አጥሩ ጎልያድ ሆኖብን ፍርሀት ስለሞላብን። ሁሉም የሚስማማበት ጉዳይ ምንድነው? የኢትዮጵያ ሕዝብ ሁሉም ብሔረሰብ የጭቆና ሰለባ ሆኗል። የኢትዮጵያ ሕዝብ ሁሉም ብሔረሰብ ደግና ፈሪሃ እግዚአብሔር ያለው ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ ሁሉም ብሔረሰብ የተደባለቀና አብሮ ለዘመናት የኖረ ነው። … [Read more...] about ኢትዮጵያ ትጠየቅ!
የኢሬቻው ጭፍጨፋና ቀጣዩ ትግል
እስካሁን አልበገር ባለውና ከሁሉም በላይ ደግሞ ለህልውናው የተማመነበት የከፋፍለህ ግዛ ፖለቲካው በህዝቦች ወንድማማችነት መንፈስ ከሽፎበት ብርክ በብርክ የሆነው የወያኔ አገዛዝ ከአንድ አመት በላይ በሰላማዊ ህዝብ ላይ ሲያወርድ የቆየውን አመጽ ቀጥሏል፡፡ በያዝነው ሳምንት በሰላም የኢሬቻ ባህላዊ በአላቸውን በሚያከብሩ ኦሮሞዎችና ሌሎች በአሉን ለማክበር በስፍራው በተገኙ ሌሎች ዜጎች ላይ እስካሁን ከታዩት ግፎች ይበልጥ ዘግናኝ የሆነ ጭፍጨፋ አካሂዷል፡፡ በዚህ አሰቃቂ ግፍ በመቶ የሚቆጠሩ ዜጎች ህይወት አልፏል፡፡ በሽ የሚቆጠሩ እናት አባቶች ልጆቻቸውን፣ ጨቅላ ህጻናትና ታዳጊዎች እናት አባቶቻቸውን፣ ወንድም እህቱን እህት ወንድሟን አጥተው ለአስከፊ ሰቆቃ ተዳርገዋል፡፡ ድርጅታችን ይህንን አሰቃቂ ድርጊት በጥብቅ እያወገዘ ለተሰውት ወገኖች ዘመዶችና ወዳጆች መጽናናትን ይመኛል፡፡ ይህ ስርአት … [Read more...] about የኢሬቻው ጭፍጨፋና ቀጣዩ ትግል
እውነትም መክለፍለፍ
ጎልጉል "የዖሮምያ ሰነድ አዲሱ ቃልኪዳን" በሚል ርእስ ባወጣው ፅሁፍ የመክለፍለፍ ፖለቲካ ጎጂ አዝማሚያ በግልፅ መጠቆሙን ሳነብ እኔም "እውነትም መክለፍለፍ" ልል አማረኝ፤ እውነትም መክለፍለፍ። መቼም በኢትዮጵያ የለውጥ ታሪክ ውስጥ ልሂቃን ፖለቲከኞችና ህዝብ ሆድና ጀርባ ከሆኑ ከ40 አመት በላይ ሆኗል። ህዝብ ለሃቀኛ ለውጥ ደሙን ያፈሳል፤ ብልጡ ልሂቅ ስልጣን ይወርሳል። ህዝብ ለጋራ አላማ ይደማል፤ ልሂቅ ለግል ጥቅሙ ይሿሿማል። ህዝብ ለለውጥ ይደማል፤ ብልጣብልጥ ፖለቲከኛ ስልጣን ይቀማል። ህዝብ ላንድነት ይጮሃል፤ ህዝብ እወክላለሁ ባይ ፖለቲከኛ ለልዩነት ይሰራል። ህዝብ ደማችን አንድ ነው በሚል ሰልፉን ሲያደምቅ ለዝቅም የሚማስነው ፖለቲከኛ ለጠብ ይሮጣል። በሰሞኑም የሚታየው ይህንኑ የሚመስል ነው። ሞት አይፈሬዎቹ የህዝብ ልጆች ከጨካኝ ባለክላሾች ጋር በባዶ እጃቸው … [Read more...] about እውነትም መክለፍለፍ
ለመለስ የተፃፈ ደብዳቤና የመለስ መልስ
ከፍቃዱ ጌታቸው ለመለስ እንደምን አለህ ጋሼ እንደምን ነህ መለስ ትመጣለህ ስንል ቀረህ ሳትመለስ እኛማ ይሔውልህ ባንተ ሌጋሲና ባንተ ትልቅ ራዕይ በየአደባባዩ እንላለን ዋይ ዋይ ዛሬም ጀነራልህ ተኩስ ነው ትዕዛዙ ወገን ያጋድማል የግፍ አፈሙዙ ለምንድን ነው ስንል ስምክን አስቀድመው ከክርስቶስ በላይ ምስልህን አትመው ቅዱስ መጽሐፍ ይመስል ባንተ ራዕይና በሌጋሲህ ምለው ቢረፈርፉንም አላለቅንምና ደብዳቤ ላክንልህ ከሞት የተረፍነው! ... የሆነስ ሆነና ግን አንተ ደህና ነህ እኛማ ይኸውልህ ደርሰህ ስትናፍቀን አይሞትም የምትል ሙዚቃ ሞዝቀን መቃብርህን ልንስም አበባ ልናኖር ሥላሴ ብንመጣ ፌደራል ያይሃል እስረኛ ይመስል ሾልከህ እንዳትወጣ መቼም ሥላሴ ውስጥ ባለስም ነውና የሚቀበርበት አንተን አየት አርገን ዞር ስንል … [Read more...] about ለመለስ የተፃፈ ደብዳቤና የመለስ መልስ
“ህወሃት በእስረኞች ላይ አጥንት የሚያመነምን መርዝ ይጠቀማል” እማኝ
በኢትዮጵያ እስረኞች አጥንትን ቀስ በቀስ በሚያፈርስ መርዝ እየተጠቁ መሆኑን ታውቁ ኖሮዋል? ከጥቂት ዓመታት በፊት የግንቦት ሰባት መሪዎች እና አባላት መታሰራቸው ይታወሳል። ብዙዎቹ ቃሊቲ የሚገኘው እስር ቤት ነበሩ። በእስር ቤት እያሉ በደረሰባቸው ያልታወቀ ሕመም ምክኒያት ሕይወታቸውን ያጡ መሪዎችም ነበሩ።ታዲያ አንዴ ከሜክሲኮ ወደ ሃያሁለት በታክሲ ተሳፍሬ ስሔድ በግምት የሃያ ዓመት ዕድሜ ያለው ልጅ ታክሲው ውስጥ ገብቶ አጠገቤ ተቀመጠ። ታክሲው ሞልቶ መሔድ ሲጀምርም ወንድሜ ይቅርታህን የታክሲ ትከፍልልኛለህ ብሎ ጠየቀኝ። ዞር ብዬ ያየሁት ይህን ሲል ነበር። ድንጋጤ እና መሸማቀቅ ይነበብበት ነበር።ልቤ በጣም አዘነለት። ምን ሆነህ ነው? ከዬት ነው የምትሔደው፤ወዴት ነው የምትሔደው ብዬ ጠየኩት። እርሱም ከቃሊቲ እስርቤት ዛሬ መለቀቄ ነው አለ። ለምን ታሰርክ እንዴትስ ተለቀቅህ ስለው … [Read more...] about “ህወሃት በእስረኞች ላይ አጥንት የሚያመነምን መርዝ ይጠቀማል” እማኝ
የኦሮሚያ ሰነድ – አዲሱ ቃል ኪዳን?
ጊዜ ገድቦ መናገር ይከብድ ካልሆነ በቀር በኢትዮጵያ የስርዓት ለውጥ አይቀሬ ስለመሆኑ ክርክር የለም (አንዳንድ የወያኔ አንጋሽ ምዕራባውያን ባለሙያዎች በጥቂት ወራት ይተምኑታል)። ይህ እውነት ቢሆንም አንዳንድ “የፖለቲካ መክለፍለፎች” ሊወድቅ የተቃረበውን አገዛዝ እንዲውተረተር ዕድል ሊሰጠው ይችላል የሚል ስጋት ያላቸው ወገኖች ከያቅጣጫው ብቅ እያሉ ነው። የስጋታቸው መንስኤ ደግሞ በዋናነት የግልጽነት፣ ያለመተማመን፣ የውድድርና “ጊዜን” የመጠቀም ተራ እሽቅድምድም እንደሆነ እነዚሁ ስጋት የገባቸው ክፍሎች ይናገራሉ። ከየአቅጣጫው የሚሰሙት የ“ሽግግር” ዜናዎች፣ ዳር ዳሩን በለሆሳስ ይሰማ የነበረው “የሃሜት በሽታ” ገልጠውታል። በዚሁ መነሻ ይመስላል ለኦሮሚያ የሽግግር ሰነድ እንደሚዘጋጅ ይፋ መሆኑንን ተከትሎ ሰፊና ግልጽ ያለ መልስ ከሚመለከታቸው የእነ በቀለ ገረባ ወኪሎች ህዝብ እየጠበቀ … [Read more...] about የኦሮሚያ ሰነድ – አዲሱ ቃል ኪዳን?
ህወሃት “አስከሬን ልግዛችሁ” አለ!
በሙት መንፈስ አገር እየገዛ ያለው የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሃት) በይስሙላነት ባስቀመጠው ፕሬዚዳንት አማካኝነት ፓርላማ ብሎ በሰየመው የራሱ ስብስብ በኢትዮጵያ ያለ አንዳች ልዩነት ለገደላቸው ወገኖች አስከሬን መግዣ ብር ሰይሜአለሁ ብሏል፡፡ ከዚህ በፊት በኦሮሚያ ላፈሰሰው መድቤአለሁ ያለው 2.4 ቢሊዮን ብር እስካሁን የት እንደገባ አይታወቅም፡፡ የሙት (መለስ ዜናዊን) ፎቶ ከፊት አስቀምጦ አሁንም በአስከሬን አገሪቱን እንደሚመራ በገሃድ ያሳየው ህወሃት ለመለወጥም ሆነ ስለ ለውጥ ለማሰብ ፍላጎት እንደሌለው ነው በጥቅሉ ያመላከተው፡፡ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችን በእስር እያማቀቀ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ውይይት፣ ፓርቲዎች እንዳንቀሳቀሱና ኅልውና እንዳኖራቸው በርካታ መዋዕለ ንዋይ እያፈሰሰ ምርጫ ኮሚሽን ማዋቀር፣ … የሚሉ የጥገናዊ ለውጦች ስሜት እንኳን የሌላቸውን ጉዳዮች … [Read more...] about ህወሃት “አስከሬን ልግዛችሁ” አለ!










