• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

እውነትም መክለፍለፍ

October 11, 2016 11:10 pm by Editor Leave a Comment

ጎልጉል “የዖሮምያ ሰነድ አዲሱ ቃልኪዳን” በሚል ርእስ ባወጣው ፅሁፍ የመክለፍለፍ ፖለቲካ ጎጂ አዝማሚያ በግልፅ መጠቆሙን ሳነብ እኔም “እውነትም መክለፍለፍ” ልል አማረኝ፤ እውነትም መክለፍለፍ።

መቼም በኢትዮጵያ የለውጥ ታሪክ ውስጥ ልሂቃን ፖለቲከኞችና ህዝብ ሆድና ጀርባ ከሆኑ ከ40 አመት በላይ ሆኗል። ህዝብ ለሃቀኛ ለውጥ ደሙን ያፈሳል፤ ብልጡ ልሂቅ ስልጣን ይወርሳል። ህዝብ ለጋራ አላማ ይደማል፤ ልሂቅ ለግል ጥቅሙ ይሿሿማል። ህዝብ ለለውጥ ይደማል፤ ብልጣብልጥ ፖለቲከኛ ስልጣን ይቀማል። ህዝብ ላንድነት ይጮሃል፤ ህዝብ እወክላለሁ ባይ ፖለቲከኛ ለልዩነት ይሰራል። ህዝብ ደማችን አንድ ነው በሚል ሰልፉን ሲያደምቅ ለዝቅም የሚማስነው ፖለቲከኛ ለጠብ ይሮጣል።

በሰሞኑም የሚታየው ይህንኑ የሚመስል ነው። ሞት አይፈሬዎቹ የህዝብ ልጆች  ከጨካኝ ባለክላሾች ጋር በባዶ እጃቸው በሚተጋተጉበትና ለፍትህ፣ ዲሞክራሲና አንድነት እየጣሉ በሚወድቁበት ባሁኑ ወቅት የዳያስፖራ ተቃዋሚ ፖለቲከኞች በየስፍራው ቻርተር በማርቀቅና የሽግግር መንግስት በማፅደቅ ስራ ተጠምደዋል ይባላል። ይህን የመሰለ ያገር ጉዳይ በቡድን እንዲወስኑ ከየትኛው ህዝብ እንዴት ያለ ውክልና እንደተቀበሉ የሚያውቁት እነርሱ ብቻ ናቸው። እኛ የምናውቀው ግን ህዝብ የሚለው ሌላ ፖለቲከኛ የሚለው ሌላ መሆኑን ነው።

አንድ ሁሉም ሊያውቀውና ሊጠነቀቅበት  የሚገባ ትልቅ አደጋ አለ። ይሄውም በህዝብ ትግልና መስዋእትነት እየመጣ ያለው ለውጥና የህዝብ አንድነት በተለመደው የፖለቲከኞች የማይረካ የስልጣን ጥም ሩጫ እንዳይኮላሽና ዳግም ኢትዮጵያን ለሞት የሚዳርግ የትውልድ ስህተት እንዳይፈፀም ነው። አሁን የሚበጀው አጋጣሚውን በመጠቀም ለሚያልፍ ስልጣን የማያልፍ የታሪክ ስህተት ለመፈፀም መጣደፍ ሳይሆን ከታሪክ ተምረን የህዝብን እውነተኛ ፍላጎት መሰረት በማድረግ ለሀገሪቱ ህልውናና ለህዝቧም ዘላቂ አንድነት የሚበጅ የጋራ ስልት መቀየስ ነው። -9 ክልል  ህዝብን እንዳላረካ ሁሉ 80 ቻርተር ለህዝብ ጥያቄ መልስ አይሆንም። ጉልጉል ጋዜጣ እንዳለው ለማይረባ የፖለቲካ አጀንዳ ከመክለፍለፍ ላገርና ህዝብ ዘላቂ ጥቅም በህብረት መጣደፍ ይበጃል።

እባካችሁ ለህዝብ ችግር ከቢሮ ተደስኩሮ ለህዝብ የሚወረወር መፍትሄ ሰልችቶናል። ንጉስ ሀይለስላሴ ስለምንወዳችሁ ህገመንግስት ሰጠናችሁ ብለው ከአርባ አመት በላይ ቀጥቅጠው ከገዙብ በኋላ ለጅብ ሰጥተውን ሄዱ። ደርግ ታሪክ አደራ ጣለብኝ አለና የህዝቡን አደራ በልቶ እሱም ህዝቡም በማያውቀው ባእድ ፍልስፍና ሲደናበር ከርሞ ለባሰበት የቀን ጅብ ሰጥቶን ተፈረካከሰ። ተረኛውም የህዝብ አደራ ቀማኛ ፥እናንተ ዝንበሉ እኔ አውቃለሁ መላ፥ አለና ብሄር፣ ብሄረሰብና ህዝብ በተሰኘ የእስታሊን ዘፈን 25 አመት ሲደንስብን ኖሮ አሁን ህልፈቱ እንደቀረበች በማወቅ አርፎ እንዳይሞት መቃብር አፋፍ ላይ ተዘቅዝቆ አስቸኳይ አዋጅ አጣዳፊ አዋጅ እያለ ያንቋርርብናል።

ይኼ ሁሉ የህዝብ መከራ በህዝብ ትግል ሊገፈፍ ተቃረበ በሚል ደስ ደስ ሊለን ሲጀምር ልማደኞቹ ፖለቲከኞች የህዝብ እውነተኛ ፍላጎት የሚነበብበትን ገፅ በመገልበጥ የራሳቸውን የስልጣን ጥም ማረጋገጫ ቻርተር ሊፅፉበት ወንበር ይጎትቱ ገቡ። ደግነቱ ጀግናው የዖሮሞ ህዝብ ባደባባይ ያሳየውን የአንድነትና ፍቅር ፍላጎት አሳምረው የሚያውቁ ፕሮፌሰር ሕዝቅኤል ገቢሳንና ዶ/ር ፀጋዬ ረጋሳን የመሳሰሉ ሃቀኛና በሳል የዖሮሞ ምሁራንን ስላፈራን በብስለት ሳይሆን በስሜት የሚነዱ አላዋቂ ፖለቲከኞች ከምንወደው ህዝባችን ሊለዩን አይችሉም። አረ ቀስ ጎበዝ! እየተስተዋለ እንጂ! የህዝብን ሀቀኛ የዲሞክራሲ ጩኸት ወደፖለቲካ ሸቀጥ ከመቀየር ደዌ ፈውስ የምናገኘው መቼ ነው?

ኢትዮጵያ ሆይ፣ የክፋት መልእክተኞች በሰይፍ የለዩት ህዝብሽ በሰልፍ ዳግም በፍቅር ሊተቃቀፍ እየገሰገሰ ነውና ደስ ይበልሽ! ትንሳኤሽን እናይ ዘንድ ጊዜው ቀርቧል።


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጃዋርና በቀለ መታሠራቸው ተሰማ June 30, 2020 09:17 am
  • አገራዊ መድረክ ውጪ ድብቅ ውይይትን አንቀበልም June 17, 2020 06:57 am
  • ዴክሳሜታሶን! የኮሮና መድሀኒት June 17, 2020 06:49 am
  • የሰኔ 14ቱ ቀለበታዊ የፀሃይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ! June 17, 2020 06:38 am
  • የግብፅ የአባይን ውሃ ብቻዬን ልጠቀም ግትር አቋም ድርድር እንቅፋት ሆኗል June 10, 2020 07:15 am
  • የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!? April 12, 2020 02:48 am
  • በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሚጠቀሙበት የኤርትራ ስደተኛ ካምፕ ሊዘጋ ነው March 18, 2020 08:37 pm
  • እየተፈረካከሰ ያለው አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ March 18, 2020 08:09 pm
  • ኮሮና አዲስ ጉድ መዘዘ – ከቻይና በፊት በአሜሪካ ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎችን ቀጥፏል March 16, 2020 11:41 pm
  • የኮንዶሚኒየም ቤቶች በደላሎችና በመመሪያ ሰጪዎች ኔትዎርክ እየተቸበቸበ ነው! ታከለ የት ናቸው? March 9, 2020 10:18 am
  • ኤርሚያስ ለገሠ ከባለአደራ ተባረረ March 9, 2020 08:09 am
  • ድፍድፍ ሲቀል ይንሳፈፋል፤ ምሁር ሲዘቅት ይመራል፥ March 7, 2020 11:24 pm
  • ኢትዮጵያዊ ምን ይመስላል? በምንስ ይመሰላል? March 7, 2020 10:29 pm
  • WHY I WROTE “MONEY, BLOOD AND CONSCIENCE” March 4, 2020 11:15 pm
  • አድዋ፤ የጥቁር ሕዝብ ድል! March 2, 2020 11:24 am
  • ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ (አባ ጎራው) March 2, 2020 11:12 am
  • የኦነግ ሁለት መልክና ሦስት ግብሮች – ቃርሚያው ኃይል ቅጥር ነፍሰገዳይ ሆኗል February 25, 2020 11:26 pm
  • በቡራዩ “የጃል ማሮ” ፎቶ ጨረታ አፈናከተ፤ “ቡራዩ ሆኖ ከሃዲን ማሞካሸት አይቻልም” ነዋሪዎች February 17, 2020 09:13 pm
  • “ዲቃላ” የፍረጃ ፖለቲካ በኦሮሚያ የኃይል አሰላለፉን እየቀየረ ነው February 13, 2020 11:58 pm
  • “ከዚህ በኋላ ማናቸውንም በወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን” አንታገስም – ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ February 13, 2020 05:07 pm
  • “እኛ ማንም ተሳዳቢ እንዲመጣብን አንፈልግም” የጅማ ነዋሪ February 13, 2020 09:28 am
  • “ወላጆቻችሁ ሰላማዊ ሰልፍ በሕዝቡ ያስደርጉልን” – አጋቾች February 11, 2020 07:53 pm
  • “ወንጀል የፈጸመም ያስፈጸመም ተይዞ ለህግ ይቀርባል፤ ምርመራም ተጀምሯል” February 11, 2020 06:59 pm
  • ጃዋር ወደ መጨረሻው “የትግል” ስልቱ – አማራን ማበጣበጥ! February 10, 2020 11:54 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule