ጥምል እየዞረ በሰማዩ ማገር በመሬቱ ዙሪያ ዕውነት የሚናገር ጠባሳው ያልጠፋ የታሪክ አሻራ መሬቱ መሰለኝ ጠላት የሚያፈራ። አገር በቀል ይሁን የሰው አገር ባዕዳ ዐይን እየማረከ የሚጋብዝ እንግዳ ከጥንት ጀምሮ እንደ እሚታወቀው ጠላት የሚያፈራ ለምለሙ መሬት ነው። ለምለሙ መሬት ነው ጦርነት አብቅሎ ቤት አልቦ ያስቀረኝ ከቀዬ አፈናቅሎ። ለም መሆኑ ቀዬ አፈረ - መሬቱ ጠላቶቸን ጋብዞ ዛሬም እንደ ጥንቱ ኮሪያው ይሁን ህንዱ ወይ የዐረቢያው ጉምቱ እንዲያፈናቅለኝ ገፍትሮ በሀብቱ ምክኒያት የሆነኝ ጫካውና ዱሩ ጠላቴ ተግሬ ነው መባቀያ አፈሩ። አያበቅሉ አብቅሎ አያፈሩ አፍርቶ የሚያፈናቅለኝ ተጎጆየ አውጥቶ ተግሬ ነው ጠላቴ ተቆምኩበት ምድር ለምለሙ መሬቴ ገዳይ በሰናድር። ማጣት ዕርዛቴን ሞቴን እንዲፈጥር ተፈጥሮው አድርጎት የቆምኩበት ምድር ለምላሜ ለብሶ ሜዳ … [Read more...] about መሬቱ
መሬቱ
የኢሬቻ የጅምላ ጭፍጨፋ ሃውልት እንዲሰራ ሃሳብ ቀረበ
የትግራይ ህዝብ ከማን አገዛዝ ነጻ እንዲወጣ እንደሚፈለግ በውል ባይታወቅም ራሱን “የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር” የሚለው ህወሃት በቢሾፍቱ ሰላማዊ ዜጎች ላይ ያካሄደው የጅምላ ጭፍጨፋ የሚዘክር ሃውልት እንዲቆም ሃሳብ መቀረቡ ተሰማ። የኢሬቻን ክብረ በዓል ለማክበር የተሰባሰቡ የኦሮሞና የሌሎች ቦታዎች ተወላጆች ላይ የተፈጸመውን የጅምላ ጭፍጨፋ ትውልድ ሁሉ በማንና እንዴት እንደተፈጸመ እንዲያውቅ፣ እንዲማርና የተከፈለው ዋጋ ምን ያህል እንደሆነ እንዲረዳ፣ እንዲሁም ምስክር ሊሆን በሚያስችለው መልኩ ሃውልቱ እንደሚታነጽ ለማወቅ ተችሏል። ለመብታቸው የተነሱና በሰላማዊ መንገድ የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባርን “በቃህ፣ ልቀቀን” በማለታቸው የኦሮሞ ተወላጆች ላለፉት አስራ አንድ ወራት ሲገደሉ፣ ሲታሰሩ፣ ሲገረፉና ሲሰቃዩ መቆይታቸው ይታወሳል። ባለፈው ሳምንት ቢሾፍቱ የኢሬቻን ክብረ በዓል … [Read more...] about የኢሬቻ የጅምላ ጭፍጨፋ ሃውልት እንዲሰራ ሃሳብ ቀረበ
አዲስ አበባ ተቆላልፋለች
ወቅታዊ ሪፖርታዥ በሳምንቱ መግቢያ የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ ብሄራዊ እርቅ እና ድርድር እንዲደረግ ጥሪ ማድረጉ ይታወሳል። አምስቱ የሕወሃት ቁንጮዎች ትእቢት የተሞላበት ምላሽ ነው የሰጡት። ከድርድር ይልቅ ከሕዝብ ጋር ጦርነት መግጠምን መርጠዋል። አብዛኛው የፖሊስ እና የሃገር መከላከያ ሰራዊቱ "ሕዝብ ላይ አልተኩስም" ማለታቸው የህወሃት አመራርን ጭንቅ ውስጥ አስገብተውታል። አዲስ አበባ ተቆላልፋለች። በአራቱም አቅጣጫ በኩል የሚገባም የሚወጣም የለም። መንገዶች በሙሉ ተዘጋግተዋል። ስልክ እና ኢንተርኔት ጠፍቷል። በአዲስ አበባ ዙርያ ባሉ ከተሞች ሰኞ መስከረም 23 ቀን የተጀመረውን ሕዝባዊ አመጽ ለማዳፈን በህወሃት የተወሰደው የአፈሳ እርምጃ አመጹን አላቆመውም። ሰኞ ማምሻውን በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ታፍሰው ወዳልታወቀ ስፍራ በመወሰዳቸው ሳብያ አመጹ በዛሬው እለት ተባብሶ … [Read more...] about አዲስ አበባ ተቆላልፋለች
የኢሕአፓ እና የመኢሶን ትንቢትና፤ የኢትዮጵያ ጊዜያዊ ሁኔታ
ሀ. ትንቢት አቶ መስፍን ስዩም "የትግሬ የበላይነት የሚለው ከጀመረ ቆይቷል" ካሉ በዃላ "የአለፉትን ሥርዓቶች አላነሳም፤ በዚያ ሥርዓት ውስጥ በዘውዱ፤ በደርጉ ሁሉም የተናቀ ነው። የአማራ አገዛዝ ተብሎ የሚወሰደው በስሙ ተነገደበት እንጂ ብዙሃኑ ጭቁን የአማራ ሕዝብ ከማንም ሕዝብ በታች ይኖር የነበረ ሕዝብ ነው።" አሉና የሚከተለውን ቀጠሉ፤ "የደርገ ሥርዓት ተገርስሶ ኢህአዴግ አዲስ አበባ የገባ ዕለት ....... ኢህአፓና መኢሶን እርስ በርሳቸው ሲናቆሩ የነበሩት፤ በጋራ ያሰባሰቡት ካናዳ ላይ ተሰብሰበው በሰጡት መግለጫ - ሰነዱን ልታገኙት ትችላላችሁ፤ የትግሬ የበላይነት፤ የቲፒኤልኤፍ ፋሺስታዊ አገዛዝ ከደርግ በላይ ግፈኛ ነው፤ ዘረኛ ነው፤ ይሄ መንግስት የሚመሰርተውን መንግስት አንቀበልም የኢትዮጵያ ሕዝብም እንዳይቀበል፤ ተማጽነዋል። ተፋለሙት ብለው ተንቀሳቅሰዋል።" ምንጭ … [Read more...] about የኢሕአፓ እና የመኢሶን ትንቢትና፤ የኢትዮጵያ ጊዜያዊ ሁኔታ
ለህወሃትና አገልጋዮቹ “አንቱታን” ነፈግን
የኢትዮጵያ ልዩ መጠሪያዎች ከሚባሉት መካከል “ሰው አክባሪነት” አንዱ ነው፡፡ በበርካታው የአገራችን ባህል ሰዎች በዕድሜያቸው የአንቱነትን ማዕረግ ይጎናጸፋሉ፡፡ ሌሎች ደግሞ በሥራቸው፣ በሙያቸው፣ በሕዝብ ዘንድ ባላቸው ከበሬታ ይህ የአንቱነት ማዕረግ ይሰጣቸዋል፡፡ በዕድሜያቸው በጣም ልጆች የሆኑ እንኳን ባላቸው መንፈሣዊ አገልግሎት ወይም ልዕልና በታላላቆቻቸው ሳይቀር አንቱ ይባላሉ፡፡ የመንግሥት ባለሥልጣናትን አንቱ ብሎ መጥራት ለኢትዮጵያዊ የሚነገረው ወይም የሚማረው ግብረገብ አይደለም፡፡ እንደ ህወሃት ዓይነቱን ግን “መንግሥት”፣ “አስተዳደር” ብሎ መጥራት በሕዝብ መቀለድ ነው፡፡ የሕዝብ ይሁንታ የሌለው፤ ሕዝብ አንቅሮ የተፋው፣ በግድ መቶ በመቶ እወደዳለሁ ብሎ ሥልጣን በአፈሙዝ የነጠቀ ወንበዴና የወንበዴዎች ስብስብ “አገዛዝ” መባል ሲበዛበት ነው፡፡ ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ለሕዝብ … [Read more...] about ለህወሃትና አገልጋዮቹ “አንቱታን” ነፈግን
እናቶች፣ “ሶሻል ሚዲያ”ና ህወሃት/ኢህአዴግ
አዲስ አበባ የሰፈር ሴቶችን ሰብስበው መግለጫ ስለ social media አጠቃቀም ስጡ ተብለው የሰጡት መግለጫ እና ከመግለጫው በኋላ ለእናቶች የተደረገ ኢንተርቪው። ዜና FBC ፦ “መንግስት በሶሻል ሚዲያው ላይ ህዝብ የሚቀሰቅሱትን ጸረ-ሰላም ሃይሎች ከሚኖሩበት አገር ጋር በመመካከር ለህግ ማቅረብ አለበት!” ሲሉ ነዋሪነታቸው በቀበሌ 07 ልደታ ክከ የሆነ እናቶች ተናገሩ ... ↩ ከዜናው በኋላ የእናቶች ኢንተርቪው፦ ☞ የመጀመሪያዋ ተጠያቂ እናት (በግምት ከ 60 - 65 አመት እድሜ)፦ ጋዜጠኛ፦ እናት ለቃለ መጠይቅ ፈቃደኛ ስለሆኑ አመሰግናለሁ እናት፦ እኔም አመሰግናለሁ እልልልልል ... ጋዜጠኛ፦ ምነው እናት? እልልታው ምንድነው?? እናት፦ የገደሉት ለህግ ይቅረቡ አይደለም እንዴ ሲባል የነበረው??? ጋዜጠኛ (በድንጋጤ ክው ብሎ)፦ የለም የለም እናቴ ሶሻል ሚዲያ ነው … [Read more...] about እናቶች፣ “ሶሻል ሚዲያ”ና ህወሃት/ኢህአዴግ
Prosopis Juliflora = ወያኔ
አደገኛ አረም ነው። በእንግሊዝኛ “መስኪት”፤ በሳይንሳዊ ስሙ ደግሞ “ፕሮሶፒስ ጁሊፍሎራ” ተብሎ የሚታወቀው ይኸው ጠንቀኛ የዛፍ አረም ስረ መሰረቱ ሰሜንና ሴንትራል አሜሪካ ውስጥ ነው። መስኪት በርካታ ዝርያዎች ያሉት ሲሆን ኢትዮጵያ ዉስጥ የተራባው አንዱ ብቻ ነው። ኢትዮጵያ ዉስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የታየው በአሚባራ አካባቢ የዛሬ ሰላሳ አመት ገደማ ሲሆን ዊልያም ኡል ሱሮ በተባለ እንግሊዛዊ አማካይነት እንደገባም ይነገራል። ይህ የአረም ዛፍ በመካከለኛውና ላይኛው አዋሽ አካባቢ በስፋት የተራባ ሲሆን፤ ሰፋፊ እርሻዎችን እና መስኮችን እየወረረ ይገኛል። ዛፉ የሚራባው እንስሳት የተክሉን ዝንቡጥ ከበሉ በኋላ ከእበት ጋር በሚወጣው ፍሬ አማካይነት ነው። እንሰሳት የተክሉን ዝንቡጥ ከበሉ በኋላ ከእበት ጋር በሚወጣው ፍሬ አማካይነት ካልሆነ በስተቀር እንደ አብዛኛው ተክል ፍሬው ተለቅሞ ቢዘራ … [Read more...] about Prosopis Juliflora = ወያኔ
Did Seyoum Mesfin and Abay Tsehaye Mastermind behind the Stampede?
I am deeply saddened by the death and/or injuries of hundreds of Ireecha festival spectators at Lake Bishoftu, Oromiya on October 2, 2016. So, to the friends and families of the Hora martyrs, I offer my condolences on the passing of their loved one (ones). At ragged cliffs of Lake Bishoftu, I wondered why the TPLF’s/the EPRDF’s police and security forces attempted to disperse a crowd of several hundred thousand by firing tear gas, rubber bullets and live ammunition. I believe that the … [Read more...] about Did Seyoum Mesfin and Abay Tsehaye Mastermind behind the Stampede?
“አሁን ደም ተቃብተናል፤ ዕርቅ የለም፤ ሌላ ሳይከተል ልቀቁልን”፤ “ከህወሃት ጋር ድርድርና እርቅ ብሎ ነገር የለም” የሕዝብ ምላሽ
ኦሮሚያ ብቻ ሳትሆን ድፍን አገርን ማቅ ያለበሰው የጅምላ ጭፍጨፋ እያደር አጥንት የሚያደቅ መረጃ እየወጣበት ነው። ህወሃት የእርቅ መንገዶችን በሙሉ አሟጦ የቀበረበት ይህ “ይቅርታ የሌለው ወንጀል” እስካሁን የ678 ንጹሃንን ህይወት አጥፍቷል። የትዳር ጓደኛውን አስከሬን በግል ተሽከርካሪ ጭኖ እያነባ ወደ ቤተሰቡ የወሰደ አለ። ገንዘብ ተዋጥቶለት የሚስቱን አስከሬን ጭኖ ወደ ሱሉልታ የተጓዘ መኖሩ ተሰምቷል። እናትና ልጅ ባንድነት ቀብራቸው ተከናውኗል። በአንድ ቀን ሁለት ወይም ከዚያ በላይ ወገኖች ከቤተሰባቸው ጎድለዋል። አስከሬን አሁን ድረስ እየተቆፈረ እየወጣ ነው። ሃይቅ ላይ የተንሳፈፉ አስከሬኖች እየተለቀሙ ነው። ህዝብ ቁጣው ገንፍሎ በተለያዩ ስፍራዎች እምቢተኛነቱን እየገለጸ ነው። ህወሃት ግን አሁንም ይዋሻል። በስፍራው የተገኙ ጋዜጠኞች ስፍራውን ለቅቀው እንዲወጡ በታጣቂዎች … [Read more...] about “አሁን ደም ተቃብተናል፤ ዕርቅ የለም፤ ሌላ ሳይከተል ልቀቁልን”፤ “ከህወሃት ጋር ድርድርና እርቅ ብሎ ነገር የለም” የሕዝብ ምላሽ
ምን ስም ይሰጠዋል?
በዓለም ላይ የነበሩና ያሉ ዘረኞች፣ ግፈኞችና አምባገነኖች የተለያዩ ምክንያቶች እየፈለጉ ሕዝብ ገድለዋል፣ አስረዋል፣ አሰቃይተዋል። በዚህም ተግባራቸው፣ « ናዚ፣ ፋሽስት፣ ጨፍጫፊ፣ አረመኔ» ወዘተርፈ ተብለዋል። ከእነዚህ እጅግ በከፋ ሁኔታ የዘረኛው የትግሬ ወያኔ ቡድን በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ በአጠቃላይ፣ በተናጠል ደግሞ በዐማራው፣ በኦሮሞው፣ በአኙዋኩ፣ በኑኤሩ፣ በሶማሊው፣ በአፋሩ፣ በሲዳማው ወዘተርፈ ነገዶች ላይ የሚፈጽመው ሁለንታናዊ ግፍ በምን ቃላት ሊገለጽ እንደሚችል የቋንቋ ሊቃውንት ሊያስቡበት የሚገባ ነው። ከላይ የተገለጹት የጭካኔ እና የአረመኔነት ስያሜዎች በፍፁም የወያኔን ማንነትና ዕውነተኛ ባሕሪ አይገልጹትም። ይገልጹታል ከተባለም ተለምዶአዊ በመሆኑ፣ የቃሎቹ የያዟቸው ጽንሰ ሀሳቦችና ድርጊቶቹ የሚጣጣሙ አይደሉም። በምንም ታምር ከጥንት ጀምሮ ሲወርድ ሲዋረድ የኖረ በዓልን … [Read more...] about ምን ስም ይሰጠዋል?










