ከውይይቱ ምን ይጠበቃል? በሀገሪቱ የተፈጠሩ ተቃውሞና ግጭቶችን ተከትሎ አንጋፋዎቹ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ከገዥው ፓርቲ ጋር የድርድርና ውይይት መድረክ እንዲዘጋጅላቸው በተደጋጋሚ መወትወታቸው አይዘነጋም፡፡ የመጀመሪያው የድርድርና የውይይት መድረክም ባለፈው ሳምንት በፓርላማ ተካሂዷል። አንዳንድ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ውይይቶቹና ድርድሮቹ ለመገናኛ ብዙኃን ፍጆታ የሚውሉና የይስሙላ እንዳይሆኑ ስጋት ቢኖራቸውም አብዛኞቹ በመድረኩ መዘጋጀት ደስተኞች ናቸው። ውይይቱ በታቀደው መሰረት በተከታታይ የሚቀጥል ከሆነ፣ እያንዳንዱ ፓርቲ የውይይት አጀንዳዎቹን ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡ ለመሆኑ ተቃዋሚዎች ከኢህአዴግ/መንግስት ጋር መወያየት ያለባቸው በምን ጉዳዮች ላይ ነው? ሂደቱስ? ከውይይቱ ምን ይጠበቃል? ከተወያዮቹስ? የአዲስ አድማስ ጋዜጠኛ አለማየሁ አንበሴ፣ በዚህ ዙሪያ የጦማሪያንን ሃሳብና አስተያየት … [Read more...] about “ሥር ነቀል ለውጦች ብዙ ዋጋ አስከፍለውናል … ሀገር በድርድር ነው የሚገነባው”
ታሪክን ምርኮኛ የማድረግ ዘመቻ
ከሰሞኑ የፖለቲካችን የስበት ማእከል ታሪክ እና የታሪክ ባለሙያዎች ሆነዋል። ዶ/ር ሃይሌ ላሬቦ የተባሉ የታሪክ ምሁር ከኢሳት ጋር ያደረጉት ቃለ ምልልስ በሶሻል ሚዲያው ከፍተኛ አዋራ ማስነሳቱ ሳያንስ፣ የተዳፈኑ የመሰሉ ጉዳዮችንም በመቀስቀስ ላይ ይገኛል። በመጀመሪያ የዶክተሩን ቃለምልልስ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ በጽሞና ለመከታተል ሞክሬአለሁ። በዚህም ተጠያቂውን ዶ/ር ሃይሌ ላሬቦ ከሙያም ሆነ ስነምግባር አንጻር የበቃ ችሎታቸውን ለመታዘብ ችያለሁ። ውዝግቡ ከተቀሰቀሰም በኋላ የኦሮሞ አክቲቪስት ነን ከሚሉ ሰዎች በተሰነዘረውን ክስ ላይ ተመስርቼ ቃለ-ምልልሱን በሂሳዊ አይን ለማየት ሞክሬአሁ። ህዝብ የተሰደበበት እና ወደ አንድ ሚዛን ያጋደለ አቀራረብ ፈልጌ ማግኘት ተቸግሬአለሁ። እንዳውም ዶ/ር ሃይሌ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ አወዛጋቢ ቦታ ስለሚይዘው ግራኝ አህመድ በጎ የሆነ እይታ … [Read more...] about ታሪክን ምርኮኛ የማድረግ ዘመቻ
“ድር ያደራበት ብዕርዎትን ከሰገባው ባያወጡት ይሻል ነበር!”
“...መሃል ፒያሳ ላይ መርከብ እንዲያንሳፍፍልዎ ነበር እንዴ የፈለጉት? ወይስ አይሮፕላን አኮብኩቦ እንዲያሳርፍልዎ?” አልታዬ የተባሉ ጸሃፊ በቅርቡ “...ለረጅም አመታተ የጣሉትን ብዕር ድር ካደራበት ሰገባው...” መዝዘው “የተቆለፈበት ቁልፍ” በቃላት ቁልፍ ተቆላልፏል!” በሚል ርዕስ አስነብበውናል። ዶ/ር በፍቃዱ በቀለ በ“የተቆለፈበት ቁልፍ” መጽሃፍ ላይ በጻፉት ግምገማ ላይ ተነስተው ትችታቸውን ያስነበቡን አልታዬ፣ ከስነ-ጽሁፋዊ ትችታቸው በፊት ያስቀደሙት፣ ዶ/ር በፍቃዱ፣ በ‘የተቆለፈበት ቁልፍ’ መፅሐፍ ላይ ያቀረቡት ጽሁፍ “...የወዳጅነት ፍቅር፣ አክብሮትና ስሜታቸውን ነው ... ወይስ በእውነት ምክንያታዊ ትችታቸውን?!...” በሚል፣ ምናልባትም “speculation” (ተጨባጭ ማስረጃ የሌለው “ቲዎሪ”) ነው። እንኳንስ አይደለም “ወዳጅ”፤ አባት እና ልጅ ቢሆኑስ አልታዬን … [Read more...] about “ድር ያደራበት ብዕርዎትን ከሰገባው ባያወጡት ይሻል ነበር!”
“አንተስ…?”
ዓይኔን በዓይኔ ያየሁበት፣ በስተእርጅና ያገኘሁት፣ የትናንቱ ማሙዬ፣ ያሳደኩት አዝዬ የንግሊዞችንወረራ ሰምቶ፣ በቴዎድሮስ ሞት ተቆጥቶ፣ ለምን? ለምን ሞተ? ብሎ ሲያለቅስ፣ የዓይኑን ዕንባ ላደርቅ- የልቡን መሰበር ላድስ፣ ጀግኖቻችንን ቆጥሬ- ታሪካችንን ባወድስ፣ ዕንባውን ዋጥ አድርጎ- በአትኩሮት ዓይኔን እያየኝ፣ «አንተስ...?» አንተስ!- ምን ሰርተሀል? በማለት ጠየቀኝ። እድሜ ቢደራረብ ተግባር ሳይላበስ፣ እንደዚህ እንደኔ ያስጠይቃል ለካስ! (ወለላዬ) … [Read more...] about “አንተስ…?”
የድርድር ቅድመ ጸብ “በተቃዋሚዎች” መካከል እና የጠብ-መንጃ “ሰላም” እስከመቼ?
ቅድሚያ "የታሰሩ ይፈቱና አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ይነሳ" የሚለው ኢህአዴግን ሳይሆን “ተቃዋሚዎችን” አላስማምም፤ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች፣ አባላትና ደጋፊዎች "ቅድሚያ ይፈቱ" የማያስማማቸው ተቃዋሚዎችን አንድ የማድረግ ሃሳብም አለ። ይህንን ሃሳብ የሚያራምደው ደግሞ ኢዴፓ ነው። የህብረቱን ጥያቄ በፕሮግራም ደረጃ አርቅቆ በይፋ ጥሪ ያቀረበውን ኢዴፓ ተቃዋሚዎች የሚያቀርቡትን ቅድመ ሁኔታ አይደግፍም። ይህንኑ ተከትሎ ኢዴፓ በኢህአዴግ ይደገፋሉ ተብለው ከሚታሙትና የቤተሰብ ጥርቅም የሆኑትን ካልሆነ በዚህ አቋሙ ያሰበውን ሊያሳካ እንደማይችል አስተያየት እየተሰጠ ነው። ዛሬ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የፖለቲካ አካሄድ እንደተቀየረና ከቀድሞው ይልቅ እየከረረ መሄዱን ሁሉም ወገኖች ይስማሙበታል። በደጋፊና ተከታይ ብዛት ተጽዕኖ ፈጣሪ ወይም ተሰሚነት አላቸው የሚባሉት የብሄር ፓርቲዎች ይህንን የከረረውን … [Read more...] about የድርድር ቅድመ ጸብ “በተቃዋሚዎች” መካከል እና የጠብ-መንጃ “ሰላም” እስከመቼ?
መስጊዳቸው ለተቃጠለባቸው የአይሁድ ቤተመቅደስ ቁልፍ ተሰጣቸው
በቴክሳስ ጠቅላይ ግዛት በቪክቶሪያ ከተማ መሰጊዳቸው ለተቃጠለባቸው ሙስሊሞች በከተማዋ የሚገኘው የአይሁድ ምኩራብ በሩን ከፈተላቸው፡፡ እንደ ሲኤንኤን ዘገባ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ በቪክቶሪ ቴክሳስ የሚገኘው እስላማዊ ማዕከል (መስጊድ) ቃጠሎ ደርሶበት ነበር፡፡ ይህንን የተመለከቱ በከተማው የሚገኘው የአይሁድ ማኅበረሰብ አባላት የአምልኮ ቦታቸውን ለሙስሊም ወገኖቻቸው መሰብሰቢ እንዲጠቀሙበት የምኩራባቸውን ቁልፍ ሰጥተዋቸዋል፡፡ “አሁን ያገኘነውን ዓይነት ዕርዳታና ድጋፍ አናገኝም ብዬ በፍጹም አልተጠራጠርኩም” ያሉት የእስላማዊ ማዕከሉ ፕሬዚዳት ዶ/ር ሻሒድ ሐሽሚ ናቸው፡፡ እንደ እርሳቸው የቀዶ ጥገና ባለሙያና የአይሁድ ቤተመቅደስ አባል የሆኑት ዶ/ር ጌሪ ብራንፍማን ወደ ዶ/ር ሻሒድ ቤት በመሄድ ቁልፉን አስረክበዋቸዋል፡፡ መስጊዱን እንደገና ለመሥራት ከዘጠና … [Read more...] about መስጊዳቸው ለተቃጠለባቸው የአይሁድ ቤተመቅደስ ቁልፍ ተሰጣቸው
ላንዲት መስቲካ ሻጭ ህጻን
በደብተርሽ ምትክ ትንሽ ሱቅ ታቅፈሽ ካልፎሂያጅ እግር ስር፤ እንደ ድንቢጥ ከንፈሽ ጋሼ ግዙኝ ስትይ፤ ኣንጋጠሽ ወደ ላይ ለጉድ ተጎልቸ፤ ምታረጊውን ሳይ ራሴስ ይታመም፤ ምላሴን ምን ነካው ግራዋ ይመስል፤ መረረኝ ማስቲካው:: ኣፈር ጠጠር ለብሶ ፤በዶዘር ተድጦ መስኩ ከነጎርፉ ሰማይ ከነዶፉ ለጌቶች ተሽጦ ኣተር ነው እያሉ፤ ኣፈር ዘግኖ መፍጨት ገነት ነው እያሉ፤ መስክ ላይ መፈንጨት ጠበል ነው እያሉ፤ ተጎርፉ መራጨት ይህንን ማን ሰጦሽ ገና በልጅነት፤ ልጅነት ኣምልጦሽ፡፡ በምቢልታ በዋሽንት፤ በከበሮ ታጥሮ በክራር ተማግሮ በቆመ ከተማ እምባሽ ቅኝት የለው ፤ለሰው ኣይሰማ፡ ጠዋት የፎከረ ፤ቀትር ላይ ሲረታ ዛሬ ዝሎ ሲወድቅ ፤ትናንት የበረታ ኑሮን ያህል ሸክም፤ ያላንቀልባ ሲያዝል፡፡ ምን ጸጋ ለብሶ ነው፤ ትከሻሽ የማይዝል፡፡ (በእውቀቱ … [Read more...] about ላንዲት መስቲካ ሻጭ ህጻን
ፕ/ር ኃይሌ ላሬቦ እና “የቁቤው ትውልድ” ፖለቲካ
ለሰሞኑ ግርግር መንስኤ የሆኑት ፕ/ር ኃይሌ የተጠቀሟቸው ሁለት ቃላት ናቸው ተብሏል። "ጋላ" እና "እረኛ" የሚሉ ቃላት። በኢትዮጵያ የታሪክ መዛግብት ውስጥ እነዚህ ቃላት "ሰፍረዋል" ወይንስ "አልሰፈሩም" የሚለውን ጉዳይ ለግዜው እንተወው። ፕሮፌሰር ኃይሌ ላሬቦ በቃለ-መጠይቁ እነዚህን ቃላት መጠቀማቸው "ስህተት ነው" ወይንም "ስህተት አይደለም" ወደሚለው ትንታኔም አልገባም። እነዚህን ጥያቄዎች ለታሪክ ለተመራማሪዎቹ ልተውላቸው። ፕሮፌሰሩ ከወንድማገኝ ጎሹ ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ እነዚያን ቃላት ባይጠቀሙስ፣ ከስድብ እና ከአድማው ይድኑ ይሆን? የሚለው ጥያቄ ግን ትንሽ ወደ ኋላ እንድዞር አድርጎኛል። "ዳግማዊ ምኒልክና ታሪካዊ ክንውኖቻቸው" በሚል ርዕስ አንጋፋው ጋዜጠኛ ተክሌ የኋላ ከሁለት አመት በፊት ሦስት እንግዶችን በጀርመን ድምጽ ሬዲዮ ጋብዞ አወያይቷቸው ነበር። … [Read more...] about ፕ/ር ኃይሌ ላሬቦ እና “የቁቤው ትውልድ” ፖለቲካ
ጻዕረ ሞትና መስፍን ወልደ ማርያም
አንደኛ፣ ገና በልጅነቴ አሥር ዓመት ግድም ሲሆነኝ አንድ በድቀድቂት ከእንጦጦ ወደታች የሚወርድ ኢጣልያዊና እኔ ተጋጠምን፤ እሱ በዚያ በጥቁር ድንጋይ ኮረት በረበረበበት መንገድ ላይ ሲጓዝ ወደ እንጦጦ የሚወጣ ወታደሮችን የጫነ ከባድ መኪና ቆሞ ነበር፤ በዚያ መኪና ላይ አንድ ዝንጀሮ ነበር፤ የኔ አትኩሮት በዚህ ዝንጀሮ ላይ ነበር! እንደሚመስለኝ ዝንጀሮውን እያየሁ ስሮጥ ከድቅድቂቱ ጋር ተገናኘን፤ እኔ ከስር በተረበረበው የጥቁር ድንጋይ ኮረት ላይ፣ ድቅድቂቱ ደግሞ የእኔን ራስ ጨፍልቆ! ምኒልክ ሀኪም ቤት ከስንት ቀኖች በኋላ የካቶሊክ መነኮሳት አስታማሚዎች ከነመለዮአቸው አልጋዬ አጠገብ ቆመው በትልቅ የበሽተኞች ድንኳን ውስጥ በአንዱ መደዳ ውስጥ ተኝቼ ነቃሁ፤ መድኃኔ ዓለም ማንን ልኮ የእኔን ጭንቅላት ከድንጋዩና ከድቅድቂቱ መክቶ እንዳዳነኝ አላውቅም፡፡ ሁለተኛ ከሶደሬ መውጫ ላይ በመቶ … [Read more...] about ጻዕረ ሞትና መስፍን ወልደ ማርያም
“ኮከብ ባየሁ ቁጥር እበረግጋለሁ” ዘ-ሃበሻ እግዜር ይይልሽ!
ከሶቅራጥስ ዘመን ጀምሮ ሲነገር የኖረውን “እውቀት እና መረጃ ሃይል መሆኑን” መንገር፣ እንዲሁም “...መረጃን መገደብ... የአምባገነኖች እና ህዝብን የሚበዘብዙ እና የሚጨቁኑ ...” ገዢዎች ስራ መሆኑን መጻፍም፣ አንባቢህን አለማወቅ/መናቅ ቢሆንም፣ ክፋት የለውም። “...መረጃዎች እንዳይወጡ ማድረግ የጨቋኞች ባህሪ ነው....”፣ በሚል መንደርደሪያ ተነስቶ፣ ከ“ጨቋኞች” የተጻፈ መሆኑን ለማሳየት/ለማጋለጥ አንድም ሃርግ መዘው ሳያወጡ እና ሳይተቹ፣ ባለፈው የለቀቅሁትን ጽሁፍ “የጨቋኞች ጽሁፍ ... የመንደርተኛ ወሬ ነው...” ማለት አግባብ አይደለም። ጽሁፉ፣ ሙያዊ ግምገማ/ትችት እንኳን ባይመስላቸው “ከጨቋኞች የመጣ ነው” ማለቱ ራሱ፣ የዘሃበሻን ኢዲቶሪያል ቦርድ ትዝብት ላይ ይጥላል። በመሰረቱ ከ“ጨቋኝ” ጋር እየታገልን ነው ማለታቸውም ነው። የዘሃበሻ “ኢዲቶሪያል ቦርድ”፣ ጋዜጠኝነት … [Read more...] about “ኮከብ ባየሁ ቁጥር እበረግጋለሁ” ዘ-ሃበሻ እግዜር ይይልሽ!










