“እና - እንደኔና እንዳንቺው የውበት ዐይኑ የታወረ፣ እግረ ኅሊናው የከረረ፤ ባሕረ ሐሳቡን ያልታደለ፣ የውበት ዐይኑ የሰለለ፣ ሰማይ ጨለማ ነው እንጂ አበባ እኮ አይደለም አለ፡፡ ያልታደለ፤…” (“እሳት ወይ አበባ”) “እና - እንደኔና እንዳንቺው የውበት ዐይኑ የታወረ፣ እግረ ኅሊናው የከረረ፤ ባሕረ ሐሳቡን ያልታደለ፣ የውበት ዐይኑ የሰለለ፣ ሰማይ ጨለማ ነው እንጂ አበባ እኮ አይደለም አለ፡፡ ያልታደለ፤…” (“እሳት ወይ አበባ”) መግቢያ ታኅሣሥ 29 ቀን፣ 2009 ዓ.ም. በዓለ ገና፤ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ዕድገትና ደረጃን በሚመለከት በጋዜጠኝነትና ኮሚዩኒኬሽን ትምህርት ቤት በሚያስተምር ግለሰብ ዋና የመረጃ ሰጪነት፣ ዘጋቢ ፕሮግራም በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ተላልፎ ነበር፤ የፕሮግራሙ አቀራረብም፣ የዩኒቨርሲቲውን ፕሬዝዳንት አድማሱ ጸጋዬን … [Read more...] about አድማሱ “ዛፍ” በቆረጠበት ጊዜ – (የዩኒቨርሲቲው ሥነ ውበታዊ ክስመት)
የካቲት 1929 እና 1966
የየካቲት ወር በሀገራችን ኢትዮጵያ ላቅ ያለ ታሪካዊ ቦታን የያዘ ነው። እራቅ ብለን የካቲት 12 ሺህ 9 መቶ 29 ሲታወስ አካፋና ዶማ፣ ፋስና መጥረቢያ ለሰው ልጅ መጨፍጨፊያ ውለዋል። አዛውንት እናትና አባቶች ሕጻናትን ጨምሮ በመኖሪያቸው በእሳት ጋይተዋል። ዋይታና ጩኸቶች፣ የሰቆቃ ድምጾች እሪታና ጣር እያሰሙ ንጹሐን ዜጎች በየመንገዱ፣ በየጉራንጉሩ፣ በየመንደሩ ተዘርግተዋል። በአዲስ አበባ በትንሹ ወደ 30 ሺህ ኢትዮጵያውያን በግራዚያኒ ተጨፍጭፈዋል። እነሆ የካቲት 12 የሰማዕታት ቀን በየዓመቱ ሲዘከር፣ ሲታወስ 80 ዓመት ሞላው። እኛም “አንድ ሀገር! አንድ ሕዝብ! ኢትዮጵያችን ሕዝባዊ ንቅናቄ” ክብር ለሰማዕታት ወገኖቻችን፣ ኢትዮጵያ በእናንተ ደምና አጥንት ተጠብቃለች እያልን ሰንደቃችንን ዝቅ አድርገን እንዘክራቸዋለን። (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about የካቲት 1929 እና 1966
Ato Nesibu Sebhat Plagiarized the EPRP’s Creative Works
“I want to write so that the reader… can say, ‘You know, that’s the truth. I wasn’t there, and …but that’s the truth.’”, Maya Angelo Critic’s note: this critical analysis contains “competing nouns”. Thus for clarity and specificity, I used a person or a thing name repeatedly instead of a pronoun. The images in this analysis were adapted from Google Images. Reading Ato Nesibu Sebhat’s book titled “ፍጹም ነው እምነቴ” bugged me so much because its stories are incoherent with his situation that he was a … [Read more...] about Ato Nesibu Sebhat Plagiarized the EPRP’s Creative Works
አዲስ እንደ ቬኒስ
ሌላ አደገኛ የጦርነት አዋጅ በወገናችን ላይ ታወጀ!
በማህበረሰባችን መካከል ወልደህ ሳም የሚባል የተለመደ ምርቃን ነበር፤ ከአንደበት የሚወጣ ቃል ደግሞ በረከትን ወይም መርገምን ሊያስከትል እንደሚችል ይገመታል፤ በምድራችን ውስጥ ልጆች በጤና ተወልደው እንዲያድጉ ወላጆች የልጆቻቸውን የጤና ስጋት ለመቀነስ ሲሉ ገና ከእርግዝና በፊት ጀምሮ ገድል ከማሳዘልና እትፍ እትፍ ከሚሉ ሰዎች እስከ የቡና ስኒ ገልባጭ መናፍስት ጠሪዎች ድረስ በልጁ የማደግና የወደፊት የሕይወት እጣፋንታ ላይ ትንቢት መሰል ሟርት እያውጁበት እንዲያድግ ይደረጋል፤ በዚህ ሁሉ ግን ሁላችንም ምንም ዓይነት የጤና ድጋፍ በሌለበትና የመናፍስት ጠሪዎች ቁጥር በርካታ በሆነባት ምድር ውስጥ ተወልደን ማደጋችን ገብቶን በማወቅ ባናከብረውም የፈጣሪ ጥበቃና ምህረት እንደሆነ አምናለሁ። ከዚህ ችግር ስፋትና ጥልቀት የተነሳ በርካታ ልጆች ተወልደው የማደግ እድል ሳያገኙ ከእናታቸው ጋር … [Read more...] about ሌላ አደገኛ የጦርነት አዋጅ በወገናችን ላይ ታወጀ!
በጎንደር ከተማ በተቀሰቀሰው ህዝባዊ አመጽ ንብረታቸዉ ወድሟል የተባሉ የትግራይ ሰዎች ካሳ ሊከፈላቸዉ ነዉ
በ2008ዓ.ም. መገባደጃ ወራት ላይ የወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ አስተባባሪ የኮሚቴ አባላትን የህወሃት/ኢህአዴግ ኃይሎች በጎንደር ከተማ ለማፈን ያደረጉት ሙከራ ከፍተኛ ህዝባዊ ቁጣ ቀስቅሶ የህይወትና የንብረት ዉድመት መድረሱ ይታወሳል። በወቅቱ “ንብረታቸው ወድሟል” የተባለላቸው የትግራይ ተወላጆች የካሣ ክፍ ሊፈጸምላቸው መሆኑ ለጎልጉል የደረሰው መረጃ ያመለክታል። በጎንደር ከተማ በተቀሰቀሰዉ ህዝባዊ ተቃዉሞ “የትግረኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች ንብረት እየተለየ ጥቃት ደርሶበታል” በሚል በህወሃት/ኢህአዴግ (“የፌዴራል መንግሥት”) የበላይ አደራጅነት በኢትዮጵያ ልማት ባንክ በኩል ጎንደር ከተማ ለሚኖሩ ትግራዋያን ነጋዴዎች “የጠፋባቸዉንና የወደመባቸዉን ንብረት” ለኢትዮጵያ ልማት ባንክ በማስመዝገብ የካሳ ክፍያና እንደ አስፈላጊነቱ የረዥም ጊዜ የብድር አገልግሎት ሊመቻችላቸዉ እንደሆነ … [Read more...] about በጎንደር ከተማ በተቀሰቀሰው ህዝባዊ አመጽ ንብረታቸዉ ወድሟል የተባሉ የትግራይ ሰዎች ካሳ ሊከፈላቸዉ ነዉ
የኢህአዴግ ከፍተኛ ሹሞችን ልዩ ልዩ ጥቅማጥቅም የሚያስከብር አዋጅ ጸደቀ
ከሁለት ዓመት በፊት በጭምጭምታ ደረጃ ወሬዉ ወደ አደባባይ የወጣዉ ባለሥልጣናት “ጡረታ” ሲወጡ የሚከበርላቸዉ ጥቅማጥቅም አሁን “ህጋዊ ዕዉቅና” አግኝቷል። ሐሙስ ዕለት በዋለዉ የኢህአዴግ “ፓርላማ” የህወሃት/ኢህአዴግ ከፍተኛ ባለሥልጣናት በልዩ ልዩ ምክንያቶች ከኃለፊነታቸዉ ሲነሱ ጥቅማጥቅማቸዉን የሚያስከብር አዋጅ ተሸሽሎ እንዲጸድቅ ተደርጓል። የተሻሻለዉ አዋጅ ከኃላፊነታቸዉ የሚነሱ የመንግስት ባለሥልጣናት እንደ የኃላፊነት ደረጃቸዉ የመቋቋሚያ አበል፣ የሥራ ስንብት ክፍያ፣መኖሪያ ቤት፣የቤት ሰራተኞች፣ የምግብ አብሳዮች፣ የቀንና የማታ ቤት ጠባቂዎች፣ የተሸከርካሪ አገልግሎት ከነአሽከርካሪዉና ጠባቂ (body guard) እንዲሟላላቸዉ አዋጁ ያብራራል። ቀደም ሲል ለኢህአዴግ ነባር ታጋይ ባለሥልጣናት መኖሪያ ቤት በሚል ከመንግስት ካዝና ያለ ፓርላማዉ ይሁንታ (ምንም እንኳን ልዩነት … [Read more...] about የኢህአዴግ ከፍተኛ ሹሞችን ልዩ ልዩ ጥቅማጥቅም የሚያስከብር አዋጅ ጸደቀ
አማራነቴስ እሺ፤ ጨዋነቴስ?
ከተወለድኩበት እለት ጀምሮ በቅጡ የማውቀው ጎጃሜነቴን ነበር። ከዚያ ልዩ የምጠራበት ስም እንዳለኝ የሰማሁት እያደር ነው። ሌላው ቀርቶ ኢትዮጵያዊ እንደምባል እንኳን የገባኝ ትምህርትቤት ገብቼ ሶስተኛ ወይም አራተኛ ክፍል ግድም ስደርስ ሳይሆን አይቀርም። ከዚያም ሙት ወቃሽ እንዳልሆን ስማቸውን የማላነሳው ግን እጅግ የምወዳቸው ዖሮሞው የህብረት አስተማሪዬ የዛሬን አያድርገውና ኢትዮጵያ 14 ክፍለሀገሮች እንዳሏት ሲነግሩኝ ለካ ከጎጃም ሌላ ሀገር አለ ብዬ ደነቀኝ። በኋላማ አማርኛ የማይናገር ወገን እንዳለኝ ሳስተውል ሆጃሜ ብቻ እንዳልሆንኩ በሚገባ መገንዘብ ጀመርኩ። ልባድርጉልኝ፣ እስካሁን ድረስ (አረ ምን እስከዛ ድረስ ብቻ እስከኋለኛው የስርአት ለውጥ ድረስ) አማራ ነህ ያለኝም፣ እኔም አማራ ነኝ ያልኩበት ጊዜ ትዝ አይለኝም። ብቻ በልጅነቴ አዋቂዎች ሲያወሩ (ያን ጊዜ ከአዋቂ ጋር … [Read more...] about አማራነቴስ እሺ፤ ጨዋነቴስ?
ሁለት ፕሮፌሰሮች፡– ፍቅሬ ቶሎሳና ጌታቸው ኃይሌ
በአንድ ሰኮንድ ውስጥ ስንት ነገሮች ስንት ሁኔታዎች ይታያሉ?፣ ስንት ድርጊቶች፣ ስንት ሥራዎች ይፈጸማሉ? ስንት ሰዎች ይሞታሉ? ስንት ሰዎች ይወለዳሉ? … አንድ ሰኮንድ ባዘለው ጊዜ ውስጥ ብዙ ጥያቄዎች አሉ፤ በአንድ ደቂቃ ውስጥ ባለው ጊዜ ውስጥ ቢያንስ የስድሳ ሰኮንዶችን ያህል ጥያቄዎች ይፈለፈላሉ፤ በአንድ ሰዓት ውስጥ 60*60= 3600 እነዚህ ደግሞ በ24 ሰዓት ሲባዙ 86 400 ይሆናሉ፤ የሚሆኑትንና የሚደረጉትን ነገሮች ሁሉ መዝግቦ፣ የሚነገሩትን ነገሮች ሁሉ አጣርቶ ይዞ ለሚቀጥለው ትውልድ የሚያስተላልፍ አለ ወይ? የትናንትናውን ሃያ አራት ሰዓት በዝርዝር ማስታወስ የሚችል አለ ወይ? ጊዜውና መሣሪያው ያላችሁ የሳምንቱን፣ የወሩን፣ የዓመቱን ሰኮንዶችና ያቀፉትንና ያዘሉትን ጉዳዮች አጣርታችሁ ለማወቅና ‹‹ተረቱንና ታሪኩን›› ለመለየት ሞክሩ፡፡ እንደኔ የጂኦሎጂ ሀሁ የሚያውቅ … [Read more...] about ሁለት ፕሮፌሰሮች፡– ፍቅሬ ቶሎሳና ጌታቸው ኃይሌ
የትግራይ ወፍ ገልብጣ ነፋች
ታሪክ እንደ ፀሃፊው ነው። ትርክትም ዕውነቱና ውሸቱ እንደ ዶናልድ ትራምፕ አገላለጽ ተለዋጭ ሀቅ (alternate fact) የለውም። ነጭና ጥቁር ነው። አንድም ዕውነት አለያም ውሸት። ተለዋጭ ዕውነት ብሎ ነገር የለም። ታሪክና ትርክት ግን ለዘመናት የውሸትና የዕውነት ገጽታ ተላብሰው ሲጓዙ መኖራቸው አይካድም። ሩቅ ሳንሄድ “የኢትዮጵያ ታሪክ የመቶ ዓመት ታሪክ ነው” የሚለውን የወያኔን ክህደት ይጠቅሷል። “ኢትዮጵያ ጀግና ኖሯት አያውቅም። የኢትዮጵያ ህዝብ እንግዳ ተቀባይ ሆኖም አያውቅ...” የመሳሰሉት የስብሃት ነጋ የተስፋ መቁረጥ ምልክቶችን ልብ ይሏል። የዛሬው አነሳሴ እንኳ የስብሃት ነጋን ውሸት ለመዘርዘር አልነበረም። የመምህር ገብረኪዳን ደስታን የእንጨት ሽበት አበቃቀል ለመዳሰስ እንጂ። የወያኔ ሽማግሌ የለውም። ከብዙዎቹ ራስ ላይ የምታዩት ነጭ ፀጉር የዕንጨት ሽበት ነው። … [Read more...] about የትግራይ ወፍ ገልብጣ ነፋች










